የሼጋ ግጥሞችናጥቅሶች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby አኒታ » Sun Jan 29, 2006 3:10 am

ከሳይት ላይ መውሰድ ይቻላል የሌለኝ አክሮ ፖሊስ ብቻ ነው እንጂ ሁሉም አልበሞቹ አሉኝ.. በጣም ከምወደው ከምሰማው አንዱ ነው.. እና የ ጃፓኖች ክላሲካል ስሙ Secret Garden የሚል በጣም ነው የምወዳቸው.. ብዙዎች አሉ.. ግን ማንም እንደ ያኒ የለም ... ልዩ ነው የርሱ.. በይብልጥ.. ብቻህን ሆነህ ስታነብ.. ወይም ለብቻ መቀመጥ ስትፈልግ የሚሰጠው ሰላም አለ... አይንኳኳብህም አይረብሽህም..ለማንኛውም አሁን አልጋዬን ላቅፋት ልጓዝ ነው.. ትንሽ እንቅልፍ እጦት አለብኝ እና .. እስኪ እንዲወስደኝ ጸልይ! :(
አክባሪህ.. እንቅልፍ ዝርር ያላለባት
አኒታ
ቺርስ.. በእንቅልፍ :lol:
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Postby ሳምቻው » Sun Jan 29, 2006 3:42 am

ዋውውውው ! What a coincidences ! ታንክዩ ሶ ማች For being yanni’s fan group . አንድ አሪፍ ልጅ ተገኘ ማለት ነው .... ደግሞ ...

እኔ ያለሱ መስራት አልችልም :: I feel like am in heaven አኒታ ቦኒታ ልዩ ነው :: ሪፍሌክሽንስ ኦፍ ፓሽን ላይ ያለውን "" ትሩ ኔቸር "" የሚለውን ኮንሰርት ላይ ሆነው ሲሰሙት ከፊት ለፊት ያሉት ሰዎች ሲያለቅሱ አይተሽ ታውቂያለሽ ? ኢን-ሴላብሬሽን ኦፍ ላይፍ የሚለውን በየኮሌክሽኑ ሁሉ እንዳስገባሁት ነው የኔ ነገር የኢትዮጵያ የታሪክ መጻህፍት እና ያኒ ከእጄ አይለይም :: ድሮ ኳስ እና ደበተር ነበር :: This man is the greatest event of my life . አንድ ቀን ከ አንዲት ኢታሊያን ጋር ኦን ላይን ቼስ ስንጫወት ሁለታችንም ባጋጣሚ ያኒን እየሰማነው ነበር እና ኢፍ አይ ኩድ ቴል ዩ ከሚለው አልበሙ ሚድ-ናይት ሀ'ሚን የሚለውን እንደምተወደው እየነገርችኝ ( ከቦይ ፍሬንዷ ጋር ቀለበት ያሰሩት በዚህ ትራክ ሳውንድ ነው ምናምን .. ) እና እኔም "" ሳንቶሪኒ "" ""የሚለውን ሙዚቃ እንደምወደው ከነገርኳት በኃላ , ሳንቶሪኒ ማለት ግሪክ ውስጥ ያለች ደሴት መሆኗን ነገረችኝ :: ሳንቶሪኒን ብወደውም ትርጉምን ግን ከዚያ በፊት አላውቀውም ነበር :: እንዲህ እያለች ንግስቴን በላቻት :: እውነቴን ነው የማጫውትሽ :: ለሳኖቶሪኒ ያልሆነች ንግስት ምንትሰራለች እያልኩ ...ሁለተኛውንም ጫወታ ተሽነፍኩ !!

ከ አልበሞቹ መሀከል የሌለሽ የትኛውን ነው :: ከዚህ ውስጥ :.

ኤትኒሲቲ ሌተስቱ ነው , ኦኬ እንደሱ እያልሽ ውረጂ :: ሪፍሌክሽንስ ኦፍ ፓሽን ከሌለሽ ገደልኩሽ ::

Ethnicity
If I could tell you
Tribute
Acropolis
In my time
Dare to dream
In Celebration of life
Reflections of passion
Nika nana
Cameleon
Out of silence
Imagination
Optimistic
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby ሳምቻው » Sun Jan 29, 2006 4:12 am

ልትተኚ ስትይ ደግሞ ቅር አለኝ :: ለማንኛውም ብትተኚ ይሻላል :: ይሄ ሁሉ ሰአት ዋርካ ስር .....

ግን ለምንድነው እንቅልፍ የማይዝሽ ? እንዴ ምናልባት ዋርካ ውስጥ ፍቅ.........

ከዌብ -ሳይት ላይ ማውረድ ትችያለሽ ግን ለዚያ የሚሆን ፕሮግራም ያስፈልግሻል :: እንዲህ ማድረግ ኢሌጋል ነው :: ኮፒ ራይት የባለቤቱ ብቻ ነው እንደምታውቂው :: ለንግድ ስራ በብዛት ባይሆንም ለራስሽ ማውረድ የምትችይበትን ፕሮግራም እሰጥሻለሁ :: በፕራይቬት ጻፊልኝ :: ፕሮግራሙ ሌተስት ሲሆን ኮድ ሰብሮ እየሰረቀ ነው የሚያወርደው :: አዲስ ገበያ ላይ የዋለ ፊልም ጭምር ያወርዳል :: በጣም አክሳሪ የሆነ ጉደኛ ፕሮግራም ነው :: ኤድዋርድ ዘ ትዊስት የሚለውን ሙቪ አስቢው ገና ገበያ ላይ በ ድቪዲ ሳይውል ( አሁን ፊልም ቤት ብቻ ነው የሚታየው ) አጅሬው ግን ያወርደዋል :: ያኒ በ pmp3 ስለሆነ ያለው ኔት ላይ በርከት ያለውን ወደ ሲዲ መገለበጥ ትቺያለሽ ::

Acroplis የለሽም :: የሚገርመው ሳንቶሪኒ ያለው እዚህ አልበም ላይ ነው :: አሁን በዚህ ሙመንት ላይ ራሱ እመሰማው እሱን ነው :: እንዴት አይነት ሰላም የሆነ ሪትም መሰለሽ የቀረብሽ !! ለሁሉም ሳንቶሪኒን ብቻ ለግዜው በ ኢሜይል አታች አደግልሻለሁ ነገ :: WINAMP ይኖርሻል አይደል ?

ህልም እዪልኝ !

ሳም
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby አኒታ » Sun Jan 29, 2006 4:26 am

እንዲህ እያለች ንግስቴን በላቻት :: እውነቴን ነው የማጫውትሽ :: ለሳኖቶሪኒ ያልሆነች ንግስት ምንትሰራለች እያልኩ ...ሁለተኛውንም ጫወታ ተሽነፍኩ !!
:lol: :lol: :lol: አሳዘንከኝ ከምር.. እኔ ከነ ስብናው ነው ምወደው.. እጅግ የተለየ ሰው ነው.. በስራዎቹ..Tribute ኮንሰርቱ አለኝ live show የቀዳሁት እናም እዛ ላይ ሰዎች በተመስጦ እንዴት እንደሚሆኑ አይተሀል? ደግሞ ሚመርጣቸው የድሮ ቅርስ የሆኑት Taj mahal.. chinies tower.. እና የግሪክ የትውልድ ቦታው ድንቅ ስፍራዎች ጋር ያቀረባቸውን? ደግሞም ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ተስፋም አለኝ.. መቼም የኛ ሀገር ሰው እሱን እንደ ኦፕራ እንደማይሸኝ ነው በፊት እሷም የመጣች ሰአት ማለትም ሀገሯ ሄዳ ሳትወቅሰን በፊት.. ጋርድቿን ነበር ያስቀደሙት ሂልተን.. እናም እሷን ከኋላ.. አሁን እውቅ መሆኗን ሲያዩ በ ኦርኬስትራ .. በጭፈራ ተቀበሏት.. እኔ ምፈራው ያኒም እኛ ሀገር መጥቶ ለስራው እኔ ብቻ እንዳልቀበለው ነው.. እንጃ በጣም ጥቂት ሚባሉ ሰዎች ናቸው የርሱን ስራዎች ሲያደንቁ የሰማሁት.. እናም በአብዛኛው የራሴ ቦታ ላይ እንጂ ሌላ ቦታ ስሰማው .. ብዙ ሰዎች ይሄን የሚያለቅስ ነገር አጥፊልን ሲሉህ ይስተዋላሉ.. ለመሳሪያ ቅንብር.. Instrumenta ያላቸው አመለካከት ከ አስረሽ ምቺው ጋር የሄደ መሰለኝ ግን እዚህ ያኒ ውስጥ ያለውን ሰላም ግን የትኛውም ቦታ ውስጥ አላገኘውም.. ሌላ ከማደንቃትና ከማዘወትራት ዘፋኝ Celion dion በጣም ነው ምወዳት.. ከምግባሯና ስራዎቿ ጋር እጅግ ስሰማቸው የማልረበሽባቸው ነች. K.G.Phille colins and Tracy Chapman በፊት አዘውትሬ ከምሰማቸው ናቸው.. ስራቸው ልስላሴው ያስደስተኛል ድሮ ት/ቤት ሳለሁ ከጥናት መልስ ምሰማቸው ካሴቶች ነበሩና ሁሌ የሚናፍቀኝን ትምርት ያስታውሱኛል.. ከያኒ ከሌሉኝ አልበሞቹ መሀል Acropolis,Dare to dream የሉኝም እኔንጃ ለምን እንደሆነ እስካሁን እጄ ሊገባ አልቻለም...አንዴም እንዲሁ እንደ ጦር ማስቲካ ጸሀይ ላይ ሰትረው ሚሸጡ አሉ እዚህ ኦሪጅናል ሳይሆን ቅጂ እናም ሲዲውን ገዝቼ ... እቤቴ ስሰማው.. 1ዱን 12 ጊዜ እየደጋገመ.. ያጫውታል ምን አደርገዋለሁ ያንን ብቻ ሰምቼ.. ፎቶውን ብቻ ቀሪ አረኩት.. ብቻ ድንቅ ሰው ነው ያኒ..ለ እርሱ አልበምና ለመጽሀፍ ማወጣው ብር አይቆጨኝም ከንግግሩ.. ከገጽታው እራሱ የሆነ እረፍት አለው ትልቅ ተሰጦ አለው የሰውን አይምሮ የሚያዝናና ስራዎች!.. እንኳን ስራዎቹ.. የርሱን ህይወት አድናቂው ነኝ.. አጋር አድናቂው በማግኘቴ ደስ ብሎኛል
ይቅርታ.. አማርኛና እንግሊዘኛ መደባለቅ ማልወደው ነገር ነው.እንደ still እስካሁን አይነት :lol: እንደሀገሬ ሰዎች እንደሚያስገቧት እዳታስመስልብኝ.. በ አንዱ መጭረስ አሊያም አለማነካካት..ብሏል አንዱ ጓዴም ለአዝማቾቹ ምንም አይነት የ አማርኛ መግለጫ ስላጣሁለት ነው.. እናም መሀል መሀል ጣል ጣል ሰላረኳት እንግሊዘኛዎች መራቀቅ እንዳይመስልህ አደራ እሺ! :wink:
Nika nana sesa
Nika nana comoya
Nika nana sesa
Nika nana we'r one! :wink:
ሰላም እደር..
አክባሪህ
አኒታ
ቺርስ በቅራሪ..!
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Postby ሳምቻው » Sun Jan 29, 2006 8:28 pm

እሺ አኒታ ቦኒታ

አንቺ ልጅ ምርጫዬን ሁሉ እኮ ነው የቀማሽኝ :: የፊል ኮሊንስ ትሩ ከለር የልጅነት ትዝታዬ ነው :: ሳቆማቸው አብረሽኝ ማቆምሽም ገርሞኛል :: የ ትሬሲን be someone ! የሚለውን ዘፈኗን ግን እስካሁን እሰማዋለሁ :: አንቺስ ስቲል እስካሁን አትወጂውም ... ? ቅቅቅቅቅቅ :: ላስቅሽ ብዬ ነው :: ዋናው መግባባቱ ነው :: እንጂ እሱማ እስካሁን እስቲል ነበር መባል የነበረበት ::

እኔ`ምልሽ yanni አዲሳባ የሚመጣ እንኳን አይመስለኝም :: በ 2006 ላይ ከተያዘው ቱር ላይ ኢትዮጵያ የለችበትም :: እንኳን ስፖንሰር ሊገኝ ማንነቱን የሚያውቅ አንድ አዳራሽ ኣይሞላም :: ደግሞም ህዝቡ አንድ አዳራሽ ከሞላ በቅንጅትነት ሊጠረጠርም ይችላል :: ቅንጅት ካልሆነ እንዴት አንድ ሰው አንድ አዳራሽ ሙሉ ሰው ሊሰበስብ ይችላል ?? ይሄ ትሪዝን ነው በራሱ !!

እሱ ሲመጣ ቡቶቶ ቡቲክሽን ግን ማን ሊጠብቅልሽ ነው ? ወይስ ልትዘጊው ነው :: ጆን ቡቲክ ሊገዛው ነው የሚባል ወሬ አለ እንዴት ነው !?

ሁለቱን የሌሉሽን የ yanniን አልበሞች ፒያሳ ዙቤር ሚዩዚክ ሾፕ ጠይቂ አሺ የኔ አኒታ ቦኒታ ከፒያሳ ስትመጪ በብሪትሽ ካውንስል መንገድ ሞዝቮልድ አካባቢ ድልድዩን ሳትሻገሪ መድሀኒት ቤቱ ጎን ላይ ነው ያለው :: እራሱ ዙቤር ወይ እህቱ ናቸው የሚሰሩት :: ምንአልባት ነው አሁን ግን እኔንጃ :: ባይኖረው እንኳ ኦሪጅናሉን ከየትም ብሎ ያመጣልሻል :: ምናልባት ሲማ ብትጠይቂ እዛም ሊኖር ይችላል :: ወይም ክርዲት ካርድ ካለሽ Yahoo shoping ላይ ኦርደር አድርጊው :: ሳንቶሪኒ`ን ግን ቃል እንደገባሁት አታች አደርግልሻለሁ :: በኢመርጀንሲ ኬዝ ተመዝግቧል :: እሺ ምን ያህል idea እንደሰጠሁሽ ግን ኣላውቅም :: ሶ ፋር ሶ ጉድ !! እስቲል እስካሁን ጉድ ቅቅቅቅቅቅ

ዛሬ አላመሽም ዕሺ :: ኮሎን ነው ያለሁት ኮሎኒያ! ከፍራንክፈርት ርቄ !! ትመጪያለሽ......?

take care
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

የ አምድ ዝውውር!

Postby አኒታ » Sun Jan 29, 2006 9:21 pm

መጀመሪያ .. ትልቅ ይቅርታን ለ ሼጋው ልገልጽ እወዳለሁ... እኔ እንደምጠላው የመልእክት ሳጥን አስመሰልኩት አምድህን... ይቅርታ..ሳምቻው እኔና አንተን የምናደንቀውን ሁሉ በዚህ አምድ ማድረግ ነውር ነበር.. እናም ይቅርታን ልንጠይቅ ይገባል ለማንኛውም ይህን የኔና ያንተን ንግግሮች በአዲስ ርእስ ሌሎችም እንዲሳተፉበት አድርጌ ቦታውን እቀይራለሁ ከምንወደው ልማበሚል ርእስ ላይ እገልጽልሀለሁ.. ለማንኛውም እንደ እኔ ታላቅ ይቅርታ ይድረስህ ሼግዬ.. ግጥሞችህን ላማንበብ እጂ.. እንዲህ ለማድረግ አስቤ አልመጣሁምና.. ካስከፋሁ ይቅርታ..!!
አክባሪህ እህትህ
አኒታ
ቺርስ በቅራሪ!
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Re: የ አምድ ዝውውር!

Postby ሳምቻው » Mon Jan 30, 2006 1:16 pm

ሼጋ

ሆስቴልህን በሰላም ለቅቄልህ ሄጃለሁ :: ፒትሽን......!!

አኒ

እንዴት ነሽ :: በጣም እኮ ነው ፕብሊኩ ፊት ሀርድ የሰጠሽኝ :: በኅላ ግን ያው ገባኝ ሼጋ በፕራይቬት ጽፎ ሩሙን ፖላይትሊ ልቀቅልኝ ሲለኝ አንቺንም እንደሱ እንዳለሽ ገባኝ :: የዋርካ ተለጣፊ ቤቶች ስንል ከንክኖታል ማለት ነው :: እስቲ ሌላ የተከፈተ ቤት ፈልጊና ጥሪኝ :: ያው ባለቤቱ እስኪመጣ :: ቤተ-ሰሪ ደም ስለሌለው አዲስ ቤት መገንባቱ ምን በወጣሽ :: በተወደደ ኑሮ ...

ምንምን እንዳትሆኚብኝ


ማለቴ ቤት ስትሰሪ

ሳም
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby አኒታ » Mon Jan 30, 2006 10:22 pm

ሰላም ሳምቻው.. እረ ሰውዬው ሳይቆጣ አዲሱ ድንኳን ግባ.. መልሴን አስፍሬያለሁ... ሰውዬው ሸንጎ ሳያቆምህ እዛ ብቅ በል መልሶቼ ሁሉም አሉ.. በዛው አወራሀለሁ
የቤቱ አቅጣጫ Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር .. ""በ ከምንወደው ልማድ "" ርእስ ስር ይገኛል.. ብቅ በል
አክባሪ እህትህ
አኒታ
ቺርስ በቅራሪ!!
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests