Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by manche » Wed Dec 14, 2005 4:45 am
እስቲ ሁላችንም ሰለዚህ መጽሀፍ ያለንን አስተያየት እናስፍር::
-
manche
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 98
- Joined: Tue Nov 04, 2003 4:52 pm
by ይሁኔ » Sat Dec 17, 2005 5:25 pm
የማንበብ ፍላጎትን የሚያዳብር የሚስብና ቆንጆ የፈጠራ ጽሁፍ ነው
-
ይሁኔ
- ኮትኳች

-
- Posts: 144
- Joined: Sat Sep 17, 2005 5:45 pm
- Location: india
by Getsh » Mon Dec 19, 2005 11:19 pm
ሌላ አዲስ መጽሀፍ ካልሆነና በብእር ስም የዛሬ 10 አመት ገደማ የወጣውን መጽሀፍ ከሆነ : ከእውነት የራቀ ፈጠራ በመሆኑ ያን ያህል አላስደሰተኝም :
-
Getsh
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 64
- Joined: Sat Aug 09, 2003 1:14 pm
by ቀብራራው » Mon Dec 19, 2005 11:54 pm
የሆነ ቦታ ላይ የሱ አለመሆኑን መሆኑን የገለጸ ይመስለኛል::
Getsh wrote:ሌላ አዲስ መጽሀፍ ካልሆነና በብእር ስም የዛሬ 10 አመት ገደማ የወጣውን መጽሀፍ ከሆነ : ከእውነት የራቀ ፈጠራ በመሆኑ ያን ያህል አላስደሰተኝም :
peace for all
-
ቀብራራው
- ኮትኳች

-
- Posts: 397
- Joined: Sun Dec 05, 2004 10:00 am
by እንሰት » Sat Jan 14, 2006 12:42 am
ቀብራራው wrote:የሆነ ቦታ ላይ የሱ አለመሆኑን መሆኑን የገለጸ ይመስለኛል::
Getsh wrote:ሌላ አዲስ መጽሀፍ ካልሆነና በብእር ስም የዛሬ 10 አመት ገደማ የወጣውን መጽሀፍ ከሆነ : ከእውነት የራቀ ፈጠራ በመሆኑ ያን ያህል አላስደሰተኝም :
ከዚህ በፊት ስለዚህ መጽሀፍ ተነስቶ ሀሳብ ሰንዝሬ ነበር:: አሁንም ማለት የምፈልገው ምናልባት በአማርኛ ስነጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ተወዳዳሪ የሌለው መሆኑን ነው:: በቅርቡ ደግሞ የቃየን መስዋእትን አበርክቶልናል:: ፈጠራ ቢሆንም በጥናት የተመሰረተ ታሪክ ነው::
አካባሪያችሁ
-
እንሰት
- ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1213
- Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
- Location: united states
by Debzi » Sat Jan 14, 2006 3:27 am
እኔም ይህን መጽሀፍ ወደ 1997 አካባቢ አንብቤዋለሁ በጣም መስጦኝ ነበር::
Ke akbrot selamta gar!!
-
Debzi
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1918
- Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
- Location: Los Angeles, CA
by ቡባ » Mon Jan 16, 2006 11:12 pm
እንደ ""ቆንጆዎቹ"" ባደረገውና "አፍሪካችን" አንድ ሆና ባየናት!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
በጣም ያደነኩተ መጽሀፍ ነው:: እንደውም ደግሜ አንብቤዋልሁ::
eee
-
ቡባ
- አዲስ

-
- Posts: 19
- Joined: Mon Dec 26, 2005 10:05 pm
- Location: Italy
-
by ቀስት1 » Tue Jan 17, 2006 11:34 pm
አቀራረቡ ባህላዊ አይደለም:: እንደውም የተተረጎመ ፊልም ነው የሚመስለው:: ዛሬ ችግራችን መጽሐፎች ሁሉ ትርጉም ብቻ ናቸው:: አንድም የሀገር ውስጥ ስራ በቅርቡ አልታየም ለዚህም የባህል ወረራ ተደርጎብናል::
-
ቀስት1
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 82
- Joined: Thu Jan 12, 2006 8:21 am
by እንሰት » Tue Jan 17, 2006 11:41 pm
ቀስት1 wrote:አቀራረቡ ባህላዊ አይደለም:: እንደውም የተተረጎመ ፊልም ነው የሚመስለው:: ዛሬ ችግራችን መጽሐፎች ሁሉ ትርጉም ብቻ ናቸው:: አንድም የሀገር ውስጥ ስራ በቅርቡ አልታየም ለዚህም የባህል ወረራ ተደርጎብናል::
ሰላም በመጀመሪያ::
1. አቀራረቡ ባህላዊ አይደለም ስትል ምን ለማለት እንደፈለክ ግልጽ አይደለም::መቸም እንደፍቅር እስከመቃብር ይሁን እንደማትል ነው:: ከበአሉ ግርማስ ጽሁፎች ለምሳሌ ከአድማሥ ባሻገር በምን ይለያል? ስለባህል ስላነሳህ ነው::
2. የተተረጎመ ፊልም ነው የሚመስለው አልክ? ይህ በአድናቆት ከታየ ደራሲው የመግለጽ ብቃቱ ከፍተኛ በመሆኑ ፊልም ነው እንድትል አድርጎሀል ማለት ነው::ሊሸለም ይገባዋል አትልም ታዲያ::
3. መቶ በመቶ የማረጋግጥልህ ትርጉም አይደለም::ፈጠራና ወጥ ስራ ነው::
-
እንሰት
- ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1213
- Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
- Location: united states
by ቀስት1 » Wed Jan 18, 2006 12:56 am
ለአብነት የሲሳይ ንጉሱን ሰመመንን ተመልከት:: ዘመናዊ ነው ደሞም የህብረተሰቡን የእለትተለት ኑሮ ይመለከታል:: እንደውም ገፀ-ባህሪያቶቹን የምታውቃቸውን ነው የሚመስልህ በሌላ አንፃር ቆንጆዎቹን ያየህ እንደሆነ እንደውም ከአክሽን ፊልም የተወሰደ ነው የሚመስለው: በእርግጥ ጦቢያ እስታይል ይጠቀም ማለቴ አይደለም::
-
ቀስት1
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 82
- Joined: Thu Jan 12, 2006 8:21 am
by እንሰት » Wed Jan 18, 2006 2:13 am
እኔ የተዋጣለት ስራ ነው እላለሁ::የፊልም አክሽን ነው ካልክ ይሁን::ግን ለፊልም ጥሩ ጽሁፍ ከሆነ እስኪ ለሠርቅ ዳ. ጠቆም እናድርገው:: ወደ ፊልም ቀየረው ብለን::አዲሱን መጽሀፉን አንብበህለታል? "የቃየን መስዋእት" ይላል:: አስገራሚ መጽሀፍ ነው::ሰመመንን አንብቤዋለሁ እሱም ቢሆን እኮ ስለሳይኮቴራፒ ያወራ የለም እንዴ? ይልቅ ያንን ዘፋኝ ወድጄው የቀረሁት በሰመመን ምክንያት ነው "እረ መላ ምቱ ዘመድ ወዳጆቼ..."
መልካም ንባብ
-
እንሰት
- ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1213
- Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
- Location: united states
by ቀስት1 » Wed Jan 18, 2006 2:50 am
እንሰት: የቃየን መስዋእትም ያው ነው ግን እንደ ዲቴክቲቭ ነገር ነው:: የሲሳይን ድርሰቶችን በሙሉ አንብቢአለሁ:: የመጨረሻ ድርሰቱ ደሞ "" ረቂቅ አሻራ "" ይባላል እሱም ግሩም ነው::ከሰመመን በፊት ጉዞው: ከሰመመን ቀጥሎም ግርዶሽ: ትንሣኤ: የቅናት ዛር እና ከሌሎች ደራሲዎች ጋር ደሞ ያወጣው የሕይወት ጠብታዎች ውስጥ "" አዲሱ ፕሮጀክት"" የመሳሰሉት ይገኛሉ:: ሁሉም ገፀ-ባህሪያቶቹን የማውቃቸው ነው የሚመስለኝ:: እስቲ አንተም ጨምርበት::
Last edited by
ቀስት1 on Sat Jan 21, 2006 7:25 am, edited 1 time in total.
-
ቀስት1
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 82
- Joined: Thu Jan 12, 2006 8:21 am
by እንሰት » Wed Jan 18, 2006 11:59 pm
ቀስት1 wrote:እንሰት: የቃየል መስዋእትም ያው ነው ግን እንደ ዲቴክቲቭ ነገር ነው:: ...
የቃየን ... ነውቃየል በስህተት የምንጠቀምበት ነው:: ከጽሁፍህ እንደተረዳሁት የንባብ ጣእማችን የተለያየ መስለኝ::ለማንኛውም ሲሳይም የማከብረው ደራሲ ነው:: ረቂቅ አሻራን እንኩዋን ብዙም አልወደድኩትም:: ማን እንደሰመመን እና እንደ ጉዞው?
ቡባ
ያንተን ሀሳብ እኔም እጋራለሁ::የለቢያው መሪ መሀሙድ ጋዳፊ ሀሳቡን ጀምሮት ባጭር ተቀጨ::ለማንኛውም የሚደገፍ ጠንካራ የፓናፍሪካኒዝምን ሀሳብ ያስተላለፈ ድንቅ መጽሀፍ ነው::
-
እንሰት
- ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1213
- Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
- Location: united states
by ዩፎ » Thu Jan 19, 2006 1:57 am
ቆንጆዎቹ እንደስሙ ቆንጆ ነው - ለኔ:: ሪሰርች ተሰርቶበት የተጻፈ ነው የሚመስለው - በዚያ ላይ ደግሞ የጸሀፊውን ውብ የኢማጂኔሽን ችሎታ ያሳያል::
የሲሳይን 'የቅናት ዛር' በሚመለከት ከማልወዳቸው መጽሀፎች ውስጥ አንዱ ነው::
-
ዩፎ
- ኮትኳች

-
- Posts: 132
- Joined: Sat Dec 25, 2004 10:29 pm
- Location: united states
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: No registered users and 1 guest