የዋርካ ፈሊጥ (

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የዋርካ ፈሊጥ (

Postby እንቁየ » Wed Dec 14, 2005 6:36 am

ውስጥ ለውስጥ
ካመቸም በግልጥ
ነገር በነገር መፍለጥ
ማስሪያ የሊለው ልጥ
ዝንታለም ብጥብጥ
የዋርካ እድምተኛ ፈሊጥ::
ከዚህም ከዚያ መሻኮት
ላለመስማማት መስማማት
አንዱ ለሊላው አይጨነቅ
የተጣላ ቂሙን አይፍቅ
ሀቁን በማተቡ አይጠብቅ
ሀሳዊ መሲህ መናፈቅ::
ታናሽ ታላቅን አክብሮ
ወገን ተወገን ተባብሮ
እውነትን በእውነት ተናግሮ
ያለጭንቅ እመሽበት ታድሮ
ድሮ.....ድሮ.....ያኒ ...ድሮ
እንዲያ ነበር ..የእኛ ህይወት የኛ ኑሮ

የዋርካ ቻት ሩም መከፈት ለናፈቃቹህ የዋርካ ወዳጆቸ ጽናኛ ትሆን ዘንድ

ናፋቂ አቹህ
እንቁየ......የባህር ውስጥ እንቁ
እንቁየ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 111
Joined: Tue Feb 03, 2004 6:49 am

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests