Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by Biny » Fri Dec 16, 2005 10:33 am
ጽጌረዳ አበባ የበቀለብሽ
ሻባኝና ውስኪ የተረጨብሽ
አንቺ ማዘጋጃ ምን ግፍ አለብሽ
የወያኔ ቁምጣ ተሰቀለብሽ
መንጌ በለንቦጩ ሰብስቦ ይዞን
መሌ በለሀጩ አዝረከረከን
በሉ ከተመቻች ሁ የምታውቁትን ጣል ጣል አርጉ እኔም እመለሳለሁ
Luv
-
Biny
- መንገደኛ

-
- Posts: 6
- Joined: Fri Sep 12, 2003 6:42 am
- Location: ethiopia
by kebi » Fri Dec 16, 2005 11:54 pm
መንጌ በለንቦጩ የሰበሰበንን:
መለስ በለሀጩ አዝረከረከን:: ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
በጣም ትክክል::
-
kebi
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 95
- Joined: Mon Feb 14, 2005 6:29 am
- Location: sweden
by Biny » Sat Dec 17, 2005 8:28 am
ሰውዬውን መሳል ፍላጎት ያላችሁ
የንድፍ መሳሪያ ከተሟላላችሁ
እሱን እንኮአን መሳል በጣም ቀላል ነው
ፍየሊቱን ስሎ ቀንዷን ማጥፋት ነው
Luv
-
Biny
- መንገደኛ

-
- Posts: 6
- Joined: Fri Sep 12, 2003 6:42 am
- Location: ethiopia
by dgcom » Sat Dec 17, 2005 3:06 pm
እንዳልተበላበት
እንዳልተጠጣበት
የኢሰፓ ቢሮ ፓንት ተሰጣበት.
ፈረሴን ሽጬ ላሜን ሳስማማ
ወያኔ መጣ በነጠላ ጫማ...
ነጭም ሆነ ጥቁር ቅማል ካገኛችሁ
የወያኔ ንብረት ነው ትጠየቃላችሁ..
-
dgcom
- ኮትኳች

-
- Posts: 280
- Joined: Thu Jan 20, 2005 4:44 pm
- Location: ethiopia
by ዲጎኔ » Sun Dec 18, 2005 11:29 pm
ወያኔ ቅጥ አጣ ለየለት ክፋቱ
ታዳጊ ረሸነ ባስራራት አመቱ
ያልተገራ ፈረስ ኢሀድጊ ብላችሁ
ምሁር ዲሞክራቱን ጠፈነገላችሁ
እምዬ ኢትዮጵያ ሞኝነሽ ተላላ
በታኝሽ ወያኔ ቅርስሽን ሲበላ
ሻቢያና ወያኔ መስረቅን ያውቃሉ
መካፈሉ ላይ ግን አምረው ተጣሉ
አባሄርማን ኮህን እጅግ ተታለሉ
ወያኔና ሻቢያ ባድሜ ላይ ሲጣሉ
የወያኔ ስርቆት እጅግ አይን አውጥቷል
ከካዝና አልፎ ተርፎ በምርጫ ተደግሟል
አስረስ ዜናዊን ከቶ ማን ያምነዋል
ታማኝ ተለጣፊን ስኩዋር ያቀምሰዋል
በሰበሰ ብሎ ከርቸሌ ያወርደዋል
ሀገር አለኝ ብዬ እኔስ አልፎክርም
ባንዲራ አለኝ ብዬም ለማንም አልነግርም
የአንድነት ሰንደቄን ሳላያት አልሞትም
-
ዲጎኔ
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 4752
- Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
- Location: united states
by አፈ-ጉባኤ » Mon Dec 19, 2005 7:18 pm
አንቺ አዲስ አበባ ሞኝ ነሽ ተላላ
ያጸዳሽ እያለ ጋሽ አበራ ሞላ
ወያኔው አርከበ ሽልማቱን በላ::
ከጥቂት ማሻሻያ በቀር ስሙን የዘነጋሁት የዋርካ ተሳታፊ ያርከበን መሸለም በማንቋሸሽ ከጻፈው የተወሰደ::
-
አፈ-ጉባኤ
- ኮትኳች

-
- Posts: 302
- Joined: Tue Mar 15, 2005 5:20 pm
- Location: united states
by kebi » Wed Dec 21, 2005 2:09 am
አዎ ትክክል ነው የሰራ ቀርቶ ያልሰራ በላ:.
-
kebi
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 95
- Joined: Mon Feb 14, 2005 6:29 am
- Location: sweden
by Biny » Fri Dec 23, 2005 11:25 am
1 2 3 4 ኤርትራ የኛ ናት (ሄይ ሄይ)
5 6 7 መለስ ነው የሸጣት (ሄይ ሄይ)
8 9 10 መንግስቱ ይመስክር
ደርግንም አየሁት ከእግር እስከ ራሱ
ወያኔንም ደገምኩ ከእግር እስከራሱ
እናጤ ቴዎድሮስ ንጉሱ ንጉሱ
እነ ልጅ ተፈሪ ንጉሱ ንጉሱ
መቃብር ደርምሱ ተነሱ ተነሱ
ቸር ይግጠመን እስቲ
Luv
-
Biny
- መንገደኛ

-
- Posts: 6
- Joined: Fri Sep 12, 2003 6:42 am
- Location: ethiopia
by ቁም ነገር2 » Wed Jan 11, 2006 11:55 am
ለወያኔ መፈንከቻ
ድንጋይ አምጡ ከኮምቦልቻ
የወያኔ ምልክቱ
ግንባሩ ላይ ጭቅቅቱ
-
ቁም ነገር2
- ኮትኳች

-
- Posts: 451
- Joined: Wed Sep 07, 2005 7:24 am
- Location: ethiopia
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: No registered users and 1 guest