ለዋርካ ዝግጂት ክፍሎች!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ለዋርካ ዝግጂት ክፍሎች!

Postby ዋኖስ » Mon Dec 19, 2005 5:31 pm

:roll: በቅድሚያ ሠላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ!


በብዙ ዘመን ዋርካ ደምበኝነቴ የምታወቀዉ ዳሞት( ዋኖስ)

ነኝ:: ዛሬ አንድ ነገርን አሰብሁ :: በዋርካችን ዉስጥ

ብዙ አያሌ ትምሕርታዊ ፅሁፎች ተፅፈዋል:: በእነኝህ

ፅሁፎች ዉስጥ ምናልባት የፀኃፍቱ የቴክንክ ማነስም

ይሁን የ ፕሮግራሙ ችግር አላዉቅም የአማርኛ

ሥርዐተ-ነጥቦችን በአግባቡ ቦታ ና ሁናቴ ስንጠቀም

አይታይም:: ለምሳሌ የአማርኛ ነጠላ ሠረዙን

በእንግሊዝኛው (,) ኮማ ሲንጠቀም እንስተዋላለን::

በተለይ ድርብ-ሠረዙንማ ዐይቼዉም አላቅም ::ቅቅ

ምናለበት ይህ ድረ-ገፅ ቋሚ ሥለሆነ ለወደፊት

አማርኛን በእንግድነት ማለትም በአዲስ ቋንቋነት

የሚቀበሉት ተተኮ ትዉልዷቻችን ሙሉ የቋንቋው

ትምኅርት ይዳረስላቸዉ ዘንድ ... የተላለፍላቸዉም

ዘንድ ለሥርዐተ-ነጥቦቹ ቦታ የምንሠጥበት ሁናቴ

ቢመቻች::

1. ነጠላ-ሠረዝ

2. ድርብ-ሠረዝ

3. ሥላቅ

እንዲሁም ሌላ ካሉን::

ካሉ ደግሞ እንዴት እንደማገኛቸዉ ብትጠቁሙኝ

ምስጋናዬ ወደር የለዉም::

ከዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby Monica**** » Mon Dec 19, 2005 5:50 pm

ዋኖስ ሙት እኔ ካንተ አልደብቅህም! ባውቅ ኖሮ እነግርህ ነበር :lol: :lol:
ይልቅ ሥላቅ ምን ማለት ነው??????
እንደው ማፈሪያ አትበለኝና ነጠላ ስረዝና ድርብ ስረዝ ምን ላይ ነው ይምንጠቀመው???
መቼም አታሳፍረኝም
አክባሪህ ነኝ
ሞኒካ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ጌታ » Mon Dec 19, 2005 5:57 pm

ውድ ሞኒካ እንደምን ከርመሽልኛል, ለጥያቄሽ ሙሉ መልስ መስጠት ባልችልም ልሞክር::

ነጠላ ሰረዝ ማለት ሁለት ነጥብ (: ላይ የሀይፈን ምልክት (-) ያለበት ማለት ነው:: ጥቅሙም በእንግሊዘኛው እንደ ኮማ ሀሳብን ለመዘርዘር ይረዳል::

ድርብ ሰረዝ ደግሞ ከሁለት ነጥቦች ላይና ታች የሀይፈኑ ምልክት ሲኖረው አገልግሎቱ ከsemi colon ጋር የሚመሳሰል ይመስለኛል:: አይ የዛሬ ልጆች በቃ እኮ ይህን የፈረንጅ አፍ በልጅነታቹ ትለምዱና አማርኛችንን ረሳችሁ :cry:

ከተሳሳትኩ ልታረም:: በነገራችን ላይ ዋኖስ ኃሳብህን እኔም እደግፋለሁ::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

ቅቅ

Postby ዋኖስ » Mon Dec 19, 2005 6:38 pm

:roll: ቅቅ

ምን ላድርግ ብለሕ ነው አማርኛችን እኮ ጥልቅ-ባሕር ነዉ::

ብዙ ነገሮች ዐሉን :: ግና ተደበቁብን ብዙዎቻችን ይህን

ምልክት , (ካማ) እንደነጠላ ሰረዝ ሥንጠቀም ስለማይ

ነዉ:: ለምሳሌ ከአሁኑ ፅሁፍሕ ላይም አለች "ካማ". ቅቅ

ቦታዋ ነው? ጥያቄ ምልክትን ተካኅባት:: ቅቅቅ

በእዉነት ከሆነ ሥለ ሥርዐተ-ነጥቦቻችን አንድም ሠዉ

ጥንቃቄ አድርጎ ሲፅፍ አላይም:: አያሳዝንም!

አይገርምም! እናም እስኪ የሚያስተካክልልን ሠዉ ካለ

በትዕግስት እንጠብቅ:: ይህም አንድ ፈጠራ ነውና!!

በቴክኒኩ ጉዳይ እነ <U>ፎርጌት-ዚስ</U> እንዲሁም

እነ <U>አበባው</U>ሊረዱኝ ይችላሉ ብዬ

አስባለዉ::

በትጥቅማቸዉ በኩል አስፈላጊ ከሆነ በሠፊዉ

እመለሳለሁ::

መልካም ፈጠራ ለቴክኒካዉያን!

ከዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby 4get.this » Mon Dec 19, 2005 8:40 pm

ሰላም

እንደኔ እንደኔ: ጥያቄው ተገቢ ነው:: እስከማውቀው ግን: ይሄን የምንጽፍበትን (ገጹ ውስጥ የተገጠመውን ፕሮግራም) የሰሩት ሰዎች ብቻ ናቸው ያንን ማስተካከል የሚችሉት::

እስከዛ መጠበቅ የለብኝም ለሚል ደግሞ (ለስነ-ጽሑፍ አምድ ደንበኞችና ለመሳሰሉት) አንድ አማራጭ አለ:: ይኸውም፡ የራሱን አማርኛ መጻፊያ «ኪቦርድ» መጠቀም ነው።
  ያንን ለያዘ
 • ሁለት ነጥብ - ፡
 • ነጠላ ሰረዝ - ፣ ወይም ፥
 • ድርብ ሰረዝ - ፤
 • እንዲሁም አራት ነጥብ - ።
በትክክል መጠቀም ይችላል።
ልክ ሌላ ገጽ ላይ ወይም ሌላ ፕሮግራም ላይ እንደሚሰራው ይሰራል።

ከአክብሮት ጋር!!!!

ግ.ማ. በነገራችን ላይ: ግጥምም ሳትጽፍ እንዲህ በቀጭኑ የምትጽፈው ሆን ብለህ ነው?
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

ክንዴ መጣሕ የኔ ብርብራ!

Postby ዋኖስ » Mon Dec 19, 2005 8:48 pm

:roll: ክንዴ መጣሕ የኔ ብርብራ! አይሳንሽ!! ልበልሕ ይሆን!!

እንዴት እንዴት እስኪ ሠፋ ያለ ማብራሪያ ሥጥበት

ስሞትልሕ!! አልገባሕ አለኝ:: ቅቅ ሥላቁንስ ለምን

ተዉከዉ? ደግሞ በስተፊርማሕ ቦታ የፃፍካት አኃፅሮት

አልገባሕ አለችኝ:: መጠይቁስ ለእኔ ነዉ?

ለአፋጣኝ ምላሽሕ ምስጋናዬን በቁና ብያለሁ!!

ዋኖስ::
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

(ስላቅን አላገኘሁትም)

Postby 4get.this » Mon Dec 19, 2005 9:20 pm

በአፋጣኝ ባልመልስስ? ምስጋናው ይቀንሳል? :lol:

  እንግዲህ: በረዥሙ ልንዳው::
 1. ከዋርካ ውጪ (ለምሳሌ፦ MS Word, emails, ....) አማርኛ ለመጻፍ የምትጠቀምበት ሶፍትዌር እንዳለ አምናለሁ፤
 2. ይሄ ሶፍትዌር unicode compatible እንደሆነም አምናለሁ፤
  እነዚህ ሁለት ነጥቦች ካልተሟሉ ካሉቱ ነጻ (ከፈከግህም ባለገንዘብ :D) ሶፍትዌሮች አንዱን በመጫን እንዲሟሉ አድርግ።
 3. ከዚህ በኋላ እኔ ያደረግሁትን ልንገርህማ! እዚሁ ላይ post a reply አልኩት። አሁን ወደመጻፊያው ገጽ ወሰደኝ።
 4. ከዚያ የዋርካዋን መጻፊያ ወደ እንግሊዘኛ ቀየርኩት፤ (አስፈላጊ አይደለም፡ ግን እንጊለዘኛ ማስገባት ስፈልግ ሁለቴ መቀየር እንዳይኖርብኝ ነው)
 5. ከዚያ የዚያንኛውን (እኔ ኮምፒውተር ላይ የተጫነውን) ቋንቋ ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ ቀየርኩት።
 6. በቃ፡ እንደልብ ይሀው እጽፋለሁ። ሲያስፈልግ ስርዐተ ነጥቦችን እጠቀማለሁ። ለምሳሌ፦ እኔ ያለኝ comma ስጫን ነጠላ ሰረዝ ያደርግልኛል።
  እዚህ ጋር ግን፡ የዋርካ ገጽ ላይ የተገጠመው applet እነዚህን characters ስለማያውቃቸው የጥያቄ ምልክት ነው የሚያሳየኝ :!:
 7. በመሃል ስፈልግ ስፈልግ ወደእንግሊዘኛ እለውጠዋለሁ። የዋርካ ገጽ ላይ ያለውን መጀመሪያ እንግሊዘኛ ላይ ስላደረግሁት፡ መቀየር አያስፈልገኝም :idea: ስለዚህ ቋንቋ የማቀያይረው እኔ ኮምፒውተር ላይ ባለው ፕሮግራም ብቻ ነው ማለት ነው።
 8. መጻፊያው ገጽ ላይ በጥያቄ ምልክት ቢያልፋቸውም ቅሉ፡ ኮዱ ግን ዩኒኮስ እስከሆነ ድረስ፡ በኋላ ዩኒኮድ ፎንት ተጠቅሞ ለሚያየው በትክክል ይታያል ማለት ነው።

እኔ በአብዛኛው የምጠቀመው፡ http://keyboards.geez.org ያገኘሁትን ነው። ዩኒኮድ እስከሆነ ድረስ ግን፡ ማንኛውም መጻፊያ መስራት እንዳለበት አምናለሁ። manualዎቹ ላይ እያንዳንዱ ዝርዝር አለልህ።
መልካም እድል

----------
ግርጌ ፊርማ ላይ የጠየቅኩህ፦ እኔ ኮምፒውተር ላይ፡ ያንተ ጽሁፎች ሁሌም የግጥም መልክ ነው ያላቸው። ስድ ንባብ ስትጽፍም አንዱ መስመር በደንብ (እንደሌሎቻችን) ሳይሞላ ነው ወደሚቀጥለው የሚወርደው። እና ያ ሆን ብለህ እንደሆነ ማወቅ ፈልጌ ነበር? አንዴ ለምሳሌ፡ የሆነ ረዘም ያለ ነገር ጽፈህ፡ ገና ሳየው ከገጹ ብዙ ሲትረፈረፍ ጊዜ አፒታይቴ ተዘጋ :(
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

Postby ዋኖስ » Mon Dec 19, 2005 9:33 pm

:roll: ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ


እጂግ ከጄት ለፈጠነ መልስሕ በጣም አደንቃለሁ::

በመቀጠል ግን ሆን ብዬ ነው በዳብል ስፔስ ና በግጥም

መልክ የምፅፈዉ :: ቅቅቅ ከረዘመ እንዳልከዉ

የሥነ-ፅሁፍ ፍላጎቴን ማለትም "አፕታይት" ነዉ ያልከው

ይዘጋኛል:: ቅቅቅ

ዕናም በቀጣይ ግን አፕታይት ዘጊ ያልሆነ ዝጂግት

ለማድረግ እሞክራለሁ ቅቅቅ:: ለእንሽርሽሪት የሚያመች!!

ሥላቋን ደግሞ አምጣት እንጂ!! አይሳንሕም መቼም!!

<U>ሥላቋን</U>?
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby Monica**** » Tue Dec 20, 2005 9:56 am

ጌታ የኔ ቆንጆ

ተባረክ ለፈጣን መልስህ!
ጌታዬ ነጠላ ሰረዝና ድርብ ሰረዝማ ምን እንደሚመስል ካላወቅኩኝ የአማርኛ አስተማሪዬ ቲቸር........ እንዲሁም አያቴ መምህሬ ጸጥአርጋችው ይወቅሱኛል :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ባይሆን ምን ላይ ነው ነጠላ ሰረዝና ድርብ ሰረዝ የምናስገባው ነበር ጥያቄዬ ግጥም ላይ ይሆን??
ነጠላ ሰረዝ ኮማ ከሆነ ጌታ, ሞኒካ, ዋኖስ ወዘተ....ላይ ነው የሚገባው ድርብ ሰረዝ ምን ላይ ነው?????

ዋናው ነገር ሥላቅ ማለት ምን ማለት ነው??? ይሄንን አንተም አታውቀውም አይደል ጌታ :lol: :lol: :lol:
የምትወድህ
ሞኒካ ነኝ
:lol:
ጌታ wrote:ውድ ሞኒካ እንደምን ከርመሽልኛል, ለጥያቄሽ ሙሉ መልስ መስጠት ባልችልም ልሞክር::

ነጠላ ሰረዝ ማለት ሁለት ነጥብ (: ላይ የሀይፈን ምልክት (-) ያለበት ማለት ነው:: ጥቅሙም በእንግሊዘኛው እንደ ኮማ ሀሳብን ለመዘርዘር ይረዳል::

ድርብ ሰረዝ ደግሞ ከሁለት ነጥቦች ላይና ታች የሀይፈኑ ምልክት ሲኖረው አገልግሎቱ ከsemi colon ጋር የሚመሳሰል ይመስለኛል:: አይ የዛሬ ልጆች በቃ እኮ ይህን የፈረንጅ አፍ በልጅነታቹ ትለምዱና አማርኛችንን ረሳችሁ :cry:

ከተሳሳትኩ ልታረም:: በነገራችን ላይ ዋኖስ ኃሳብህን እኔም እደግፋለሁ::
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

...ለዋኖስ

Postby meggi » Tue Dec 20, 2005 1:35 pm

ከወገቤ ዝቅ ብዬ ሰላምታዬን አቀርባለሁ ልጅ ዋኖስ !!!! ለካ ብዙ ነገር አምልጦኛል:: ዋርካ ፎረምን እኮ አጥለቀለከው በዚህ እውቀት ባክህ:: የዋርካ ቻት መዘጋት ታዲያ የልጅ ዋሮስን ትምህርት በፎረም ማስፋፋት ሆነ አትለኝም? :lol:
Just want to pay my compliment as usual.
ከታላቅ አክብሮት ጋር
meggi
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Fri May 13, 2005 9:07 pm
Location: ethiopia

ሕምምምምምምምምምምምምም..

Postby ዋኖስ » Tue Dec 20, 2005 3:13 pm

:roll: ሕምምምምምምምምምም ምነው!!

የሚነሳ ዕቃ ዐለ እንዴ ዝቅታዉ! ለመሆኑ ከየሰሬቻው መዉጣት የተጀመረዉ በዕኔ ጩኸት ነዉ? ተመስገን ነዉ :: ሠላም መጊ ደሕና ነሽ? ታዲያ አንቺስ አንድ በይና! ሥለ ሥላቅ!!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby meggi » Tue Dec 20, 2005 6:22 pm

ታዲያ አንቺስ አንድ በይና ! ሥለ ሥላቅ !!

አይ ዋኖስ ምነው መልስ የምታሳጣኝ.. :lol: :lol: ይህንን ስራህን እያየሁና እየኮመኮምኩኝ ዝም ማለት ከብዶኝ ነው:: እየበሉ እየጠጡ ዝም....እንዳይሆንብኝ ብዬ ነው አለሁ ያልኩት....... በተረፈ አንተ እያለህ እኔ ምን ልበል::
ደሀና ሰንብት
meggi
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Fri May 13, 2005 9:07 pm
Location: ethiopia

ቅቅ

Postby ዋኖስ » Tue Dec 20, 2005 6:26 pm

:roll: ቅቅቅ

የዋርካ አፈ-ጉባዔ ነሕ ለማለት ነዉ? ምናልበት ብንተጋገዝ

ከጩኸቱ! ቅቅቅ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby crypto » Tue Dec 20, 2005 6:49 pm

ውድ ዋኖስ ጥሩ ነጥብ ነው ያመጣኸው:: እኔማ የመጻፊያ ስርአቱም ላይ ነው ችግሬ:: አንድ ፊደል ለመጻፍ እስከ አራት ቁልፎች የምንጫንበት ምክንያት አልገባኝም:: አብዛኛዎቹ መቀመሪያዎች በሁለትና ቢበዛ በሶስት ቁልፍ ነው የሚሰሩት:: ትንሽ ማስተካከያ ቢጤ ቢፈለግለት ጥሩ ነው:: የስርአተ ነጥቡን ነገር ግን 4get.this እንዳለው የቃላት መቀመሪያችንን በመጠቅም ማስተካከል ነው ዋርካዎች አንድ መፍትሄ እስኪሰጡን:

monicaዬ (ሳታውቂ አድናቂ አትርፈሽ ኑሮ)
ትምህርተ-ስላቅ የሚሉአት ይቺ i የምትመስለውን ነው:: እንዲህ መባሉአም የቃለ አጋኖ ግልብጥ ሁና (እንደው በመልክም በምግባርም) በመገኘቱአ ነው:: ቃለ አጋኖ ለማስረገጥ: በሀቅ ለማሞገስ የምንጠቀምበት ሁኖ ትምህርተ-ስላቅ ደግሞ በተቃራኒው ለመሸርደድ: ያደነቅን አስመስለን ለ"መሳለቅ" የምንጠቀምበት ነው:: አሁን አንዳንዱ ለዚህ መልሴ እኔን "አይ ጥይትii" እንደሚለኝ: :lol:
crypto
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Tue Dec 13, 2005 7:28 pm

Postby ባቲ » Tue Dec 20, 2005 10:02 pm

crypto wrote:ለዚህ መልሴ እኔን "አይ ጥይትii" እንደሚለኝ: :lol:

እኔ ግን አይ ጥይት!!! ብያለሁ ከልቤ::
ቆንጆ አድርገህ አብራርተኸዋልና!
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests