ለዋርካ ዝግጂት ክፍሎች!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ስላቋ

Postby 4get.this » Thu Dec 22, 2005 8:00 pm

ስላቋን ፍለጋ ሄድኩኝና ...
ዩኒኮድ.ኮም ላይ የኢትዮጵያን ባየው ጭራሽ ስላቅ የሚባል ነገር ማግኘት አቃተኝ:: :cry:
አንድ አማራጭ ግን አለ:: እሱም: inverted exclamation mark እሚሏትን ፈልግና: ኮፒ እያደረግህ ተጠቀም::

የተሻለ መፍትሄ እንደምታገኝ ተስፋ በማድረግ
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

በቅድሚያ ምስጋናዬ ...

Postby ዋኖስ » Fri Dec 23, 2005 7:09 am

:roll: በቅድሚያ ጊዜሕን ሠዉተሕ ፍንጪ በማግኘትሕ ና

በመሥጠትሕ ምስጋናዬ ወደር-አልባ ነው:: በመቀጠል

በዚሁ አምድ ላይ ሌላም ልጠይቅና እንማማር:: መቼም

አቻልም እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ:: ረዳት ከፈለግሕ

የሚያግዝሕ ያን "አበባው" የሚባል ልጂ ፈልግልኝ::

1.ኛ አገራችን ኢትዮጵያ ካሉት የአፍሪካ ኃገሮች የራሷ

የሆነ ፊደልና ቁጥር እንዳላት መለያዋ ነዉ:: ይሁን

እንጂ ይህ ቁጥሯ በተለምዶ "<U>የቄስ-ቁጥር</U>"

እየተባለ ከመጠራት ዉጪ በመፅኃፍ ቅዱሳችን ዉስጥ

እንዲሁም በሌሎች አዋለድ መፅኃፍት ዉስጥ

ቤተክርስቲያን ስትጠቀምበት እናያለን:: እኒሕን ቁጥሮች

ልክ እንደ ማንኛዉም "አረቢክ" ቁጥር ለመፃፍ ምን

ማድረግ እንዳለብኝ የምታዉቁ ካላችሁ ብታስረዱኝ

ደስታዉን አልችለዉም::

ከብዙ ብዙ ምስጋና ጋ!!

ዳሞት!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby 4get.this » Fri Dec 23, 2005 11:41 am

እነዚህን ማለትህ ነው? ፩፪፫፬፭፮፯፰፱
ያው ባለፈው እንደነገርኩህ ለስርአተ ነጥቦቹ እንደምትጠቀመው ነዋ::

ይልቅ ይሄን አስመርኩዞ ስመኘው የነበረው: List ላይ በ 123 ... እና abc ፋንታ ፩፪፫ እና ሀ ለ መ ... ቢሆኑ ነበር:: ያንን ግን phpBBን ካልጎረጎሩት ማስተካከል የሚቻል አይመስለኝም::
በርታ: ለቋንቋህ ያለህ አክብሮት ይበል የሚያሰኝ ነው:: ማዕረግህን ሳላየውለመልስ ገባሁ ... አንተ አለቃ መሆን አለብህ :)
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

መጣሕ ክንዴ!!

Postby ዋኖስ » Fri Dec 23, 2005 5:01 pm

:roll: አይዋ መጣሕ!! እግዚያብሄር ይስጥሕ:: አዎ እኒሕን

ማለቴ ነበር:: ታዲያ ምነዋ ማብራሪያዉ አነሰ? በደምብ

ይብራራልን እንጂ ምንም እንኳ ብጠይቅም ብዙ ልንማር

የምንፈልግ እንኖራለን ና::ለብልጥ አንድ ቃል ይበቃል

ብለሕ ከሆነ ጥሩ:: ብልጥ ከሚባለዉ ማዕረግ ስንደርስ

ኃሳብሕን እየቆረጥሕ ትፅፋለህ:: ለጊዜዉ ግን ማብራሪያ

እንፈልጋለን እኔ ና መሠሎቼ::

ከብዙ ብዙ ምሥጋና ጋ!!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Dec 24, 2005 6:40 am

ሰላም 4get.this:-
እነዚህን የኢትዮጵያ ቍጥሮች ከዚህ በፊት ጠይቄህ አስረድተኸኝ እንደነበር አስታውሳለሁ::ሞክሬ ግን አልሆነልኝም::ደግሞ መጠየቁን አፍሬ ትቼው ነበር:.አሁን ዋኖስ ካነሳው ዘንዳ እስቲ ለኛ በሚገባ መልኩ አብራራው::በድጋሚ ማስቸገር ባይሆንብኝ::የቄስ ቍጥር አልቸው ዋኖስ!እኔ እንኳ የግእዝ ቍጥር ሲባሉ ነበር የማውቀው::
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1033
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

ለዘርዐይ

Postby 4get.this » Sat Dec 24, 2005 3:31 pm

ዋኖሴ:
ለብልጥ ሳይሆን ... ለውሃ አጠጪ አይሻልም ነበር? :lol: :lol: :lol:

ለስርአተ ነጥቦቹ እንዳልኩህ ሌላ ኮምፒውተሬ ላይ የተጫነ keyboard አለ:: ልክ እዚያ ላይ እንደገለጽኩት አደረግሁ ... አሁን ግን ለቁጥር ነው የተጠቀምኩት::
  እንግዲህ: ድጋሚ በረዥሙ ልንዳው::
 1. ከዋርካ ውጪ (ለምሳሌ፦ MS Word, emails, ....) አማርኛ ለመጻፍ የምትጠቀምበት ሶፍትዌር እንዳለ አምናለሁ፤
 2. ይሄ ሶፍትዌር unicode compatible እንደሆነም አምናለሁ፤
  እነዚህ ሁለት ነጥቦች ካልተሟሉ ካሉቱ ነጻ (ከፈከግህም ባለገንዘብ :D) ሶፍትዌሮች አንዱን በመጫን እንዲሟሉ አድርግ።
 3. ከዚህ በኋላ እኔ ያደረግሁትን ልንገርህማ! እዚሁ ላይ post a reply አልኩት። አሁን ወደመጻፊያው ገጽ ወሰደኝ።
 4. ከዚያ የዋርካዋን መጻፊያ ወደ እንግሊዘኛ ቀየርኩት፤ (አስፈላጊ አይደለም፡ ግን እንጊለዘኛ ማስገባት ስፈልግ ሁለቴ መቀየር እንዳይኖርብኝ ነው)
 5. ከዚያ የዚያንኛውን (እኔ ኮምፒውተር ላይ የተጫነውን) ቋንቋ ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ ቀየርኩት።
 6. በቃ፡ እንደልብ ይሀው እጽፋለሁ። ሲያስፈልግ ስርዐተ ነጥቦችን እጠቀማለሁ። ለምሳሌ፦ እኔ ያለኝ comma ስጫን ነጠላ ሰረዝ ያደርግልኛል።
 7. ለቁጥሮች ደግሞ፡ ከፊቱ apostroph አስገባና 1 2 3 ... ስነካ ፩ ፪ ፫ ይሰጠኛል።apostroph (') መግባት ያለበት ለእያንዳንዱ ቁጥር ነው:: ለምሳሌ: ፳፬ ለመጻፍ '20'4 ማለት ነው።
  እዚህ ጋር ግን፡ የዋርካ ገጽ ላይ የተገጠመው applet እነዚህን characters ስለማያውቃቸው የጥያቄ ምልክት ነው የሚያሳየኝ :!:
 8. በመሃል ስፈልግ ስፈልግ ወደእንግሊዘኛ እለውጠዋለሁ። የዋርካ ገጽ ላይ ያለውን መጀመሪያ እንግሊዘኛ ላይ ስላደረግሁት፡ መቀየር አያስፈልገኝም :idea: ስለዚህ ቋንቋ የማቀያይረው እኔ ኮምፒውተር ላይ ባለው ፕሮግራም ብቻ ነው ማለት ነው።
 9. መጻፊያው ገጽ ላይ በጥያቄ ምልክት ቢያልፋቸውም ቅሉ፡ ዩኒኮድ እስከተጠቀመ ድረስ፡ በኋላ ዩኒኮድ ፎንት ተጠቅሞ ለሚያየው በትክክል ይቀርባል ማለት ነው።


አንድ አይነት መጻፊያ እየተጠቀምን ካልሆነ የምትጠቀሙበትን መጻፊያ ማኑዋል ማገላበጥ ... ወይም "በአቦ ሰጠኝ" መሞከር ይኖርባችኋል ማለት ነው።

ይህ ካልሰራላችሁ ልወቀው::

----------------------------------
@ ዘርዐይ
ከዚህ በፊት መጠየቄን አላስታውስም:: ብትጠይቅም ግን እንዲብራራ መጠየቁ ምንም ችግር የለውም:: ገጽ 1 ላይ ያለውን ሁለተኛውን ጽሑፌን አይተኸው ነበር? አሁን ግልጽ እንደሚሆን ተስፋየ ነው።

እሱንና manualዎቹ ላይ መጨረሻ ላይ ያለውም መረጃ በመጠቀም ቁጥሮቹን መጻፍ እንደምትችል አምናለሁ:: ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ: ያቅሜን ለመሞከር አሁንም ዝግጁ ነኝ::

ያንን ነገር በቃ ተውከው? በጀማሪ እንዳትሸነፍ ፈራህ እንዴ? :lol: (ዋርካዎች እዚሁ ላይ ለአዲሱ አመት? ቢገጥሙልን ምንኛ ጥሩ ነበር)

ከአክብሮት ጋር
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

ሕምምምም...

Postby ዋኖስ » Sat Dec 24, 2005 4:00 pm

:roll: ሕምምምም..የኔ ኮምፑተርማ ንክችም አለደርጋት

አለኝ:: ችግሩ መሟላት ያለበት ነገር አለ መሰለኝ:: በዚህ

አጋጣሚ ግን ሳላመሰግን ባልፍሕ አንድ ቀን ዉኃ

ሲጠማኝ ጣትሕ እወድቃለሁና አመሰግናለሁ::
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby 4get.this » Sat Dec 24, 2005 4:18 pm

ሶፍትዌር install አድርግ ሲባሉ ከሚያስጠላቸው ምድብ ካልሆንክ ...

ያልኩህን ሶፍትዌር ጫነውና ሞክር:: እሱ መስራቱን እርግጠኛ ስትሆን:

የዋርካ መጻፊያ ገጽ ላይ ና ... (ቋንቋውን እንግሊዘኛም አደረግከው አማርኛ ችግር የለውም)

ያንን ሶፍትዌር active አድርገው

አስት ዝም ብለህ እነ , ; : . '1 '2 '3 ... ምናምን ነካካና preview በለው::
የwindows ተጠቃሚ ካልሆንክ (ለምሳሌ mac) ግን አጀንዳው ሌላ የሚሆን ይመስለኛል::
መልካም የሰንበት እድል
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

Postby ዘርዐይ ደረስ » Mon Dec 26, 2005 9:24 am

ሰላም 4get.this:-
ማብራሪያው የገባኝ መስሎኛል::እንግዲህ ስጠቀምበት ነው እርግጠኛ መሆን የምችለው::እንደ ዋኖስ ዓይነት ችግር ካላጋጠመኝ ማለት ነው::ዋርካን በአግባቡ ለመጠቀም እንድንችል ለምታደርገው ጥረት ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው::በተረፈ ያንን ረስቼው ሳይሆን ተግባራዊ ለማድረግ የሚቻል መስሎ ስልልታየኝ ነው::መፍትሔ ይሆናሉ ያልኳቸው መንገዶች ሊሆኑ አልቻሉም::ባንተ በኩልስ እንዴት ነው?
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1033
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby 4get.this » Mon Dec 26, 2005 11:20 pm

ዘርዐይ ደረስ wrote:በተረፈ ያንን ረስቼው ሳይሆን ተግባራዊ ለማድረግ የሚቻል መስሎ ስልልታየኝ ነው::መፍትሔ ይሆናሉ ያልኳቸው መንገዶች ሊሆኑ አልቻሉም::ባንተ በኩልስ እንዴት ነው?
ገባኝ!
በኔ በኩል እንደሌላ አማራጭ ... የሆነ ፎረም ላይ games አይቼ ነበር:: ዋርካ እርሱን ብትጭንልን ... ምናልባት የማይረባ ወሬ በማውራት የምናጠፋውን ጊዜ ወደዛ እናሻግር ነበር:: እኔና አንተም ይለይልን ነበር:: :wink: እኔ ግን ያንን ለማድረግ የጊዜ እና/ወይም bandwidth ችግር ሊኖር ስለሚችል: ብዙ ተስፋ ስለማላደርግ አልጠይቃቸውም::

ቸር እንቆይ
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests