ቅኝ ገዛ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ቅኝ ገዛ

Postby ዘብሔረ ኢትዮጵ » Wed Dec 21, 2005 10:21 am

ጠልቶ ከተጠላ በሁዋላ በሕዝብ ጫንቃ ተጫነና
በብሔር ብሔረሰብ ትንኮሳ በዲሞክራሲያዊ ምሰላ
ዘመናዊ ባርነት በሕዝብ ላይ ጫነና
ቅኝ ገዛ::

በጭፍን ጠባብነት ታውሮ የጠመንጃ ቂጥ እራስ ሆነና ህሊናው ተዘጋ
ትላንትን እና ዛሬን አደባልቆ ፈርቶ እያስፈራ በንጹሀን ርሸና ተሰማራ
ሁሉን በሁሉ ሆንኩላቹ በሚል መሪር ፍጽምና
በጠመንጃ ቂጥ እየተነዳ ያገሩን ዜጋ እንደ ባእድ እንደ አውሬ በላ
በልቶ ጠግቦ በጠመንጃ ቂጡ እያገሳ ህሊናው ከተደፈነበት በሁዋላ
እንደገና ቅኝ ገዛ::
ዘብሔረ ኢትዮጵ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 10
Joined: Mon Oct 31, 2005 12:24 pm
Location: England.An E.Y.Aldada literature,formerly Tabour.Ecitizen. A concern as reflected by an ex EU staff.

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests