አቤት ያች ሌሊት!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

አቤት ያች ሌሊት!

Postby ጦሳ » Mon Dec 26, 2005 2:44 pm

ደሳሳ ጎቹዋችን : ጨለማ ውጡዋት:
ውራጅ ነጠላችን : ብርድ አሽንፉዋት:
በስትንፋስ መልሰን : እኛ እያሞቅናት:
ተኝታ ላያችን : ልናሳልፋት:
በቀደም ሌሊቱዋን : እንደጀመርናት:
የእኔ አካል - በሱዋ ውስጥ:
የሱዋ በእኔ ውስጥ ቀልጦ : ተዋህዶ:
እንደ ሰም ስንነድ : ቦግ ባለው ብርሀን!
ድቅድቁ ጨለም : ላፍታ ተወግዶ!
ያካል ፍትጊያችን : ድንገት እሳት ጭሮ:
እኔና ፍቅርዬን : አንድ አረገንና : አቆላልፎ : አሳስሮ :
የትካዜ ክምር አመድ ሲሆን ነዶ :
ዋሽንቱን ሲነፋ : ኪሩቤል ከሰማይ : መሀላችን ወርዶ !
ልባችንን ያሬድ : በማራኪ ዜማው : በፍስሐ አርዶ !
ክዋክብት ሲረግፉ : መሬት ስትሆን ቁና :
ያለንባት መንደር ተለወጠችና :
የሰለጠነውን : ከተማውን ሆና :
ገብተን ከፎቅ ህንፃ : እጅግ ከሚል ደስ :
ተክቶት ጄንዲያችን : ባለሰፍነግ አልጋ የሚያነፈላስስ !
ደረብ አረግንና ያማረ ብርድ ልብስ : የሚለሰልሰ :
ምቾት ግብር ገብተን : ነጭ ጤፍ ስንቆርስ :
ከፍቅር መዲና : መሀል በመድረስ :
ችግር : ቼነፈርን የረሳንባት :
ዬዬሌክትሪክ መብራት : የሚበራባት :
ውሀውም በቡዋንቡዋ : የሚሳብባት :
ሁሉ ተትረፍርፎ : ሁሉ ሞልቶባት :
የድሎት አክርማን : የቀጨንባት :
አቤት ያች ሌሊት ! የሌሌንባት !
እንደት ትጥም ነበር !?
እንደት ትሞቅ ነበር !?
ማለፍ አሳልፎ : ለብርድ ባይሰጣት !
አቤት ያች ሌሊት ! የሌሌንባት !
ጦሳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 16
Joined: Tue Dec 20, 2005 12:57 pm

Postby ዲያና » Sat Oct 04, 2014 3:11 pm

lol!
Pray for Oneness!!!
ዲያና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 364
Joined: Tue Mar 09, 2004 2:25 am


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests