ከብርና ከፍቅር የቱ ይበልጥአል

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ትምህርት » Thu Jan 12, 2006 8:50 pm

ሰላም

ይቅርታ ጥያቄውን ባለቤቱ ቢያብራራልኝ ደስ ይለኛል! ሳይገባኝ እንዳልቀባጥር ስለፈራሁ ነው!

እኔ የገባኝ ከሁለት ነግሮች አንዱን እንድመርጥ ብጠየቅ:: ማለትም በጣም የምወዳት ልጅ በግራ በኩል: ገንዘብ በሌላ በኩል ተቀምጦ ከሁለቱ የትኛውን ትመርጣለህ ነው ጥያቄው?

አብራራ(ሩ)ልኝ
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

Postby ትህትና2 » Thu Jan 12, 2006 10:02 pm

ላህ wrote:ለአፈ-ጉባኤእንደ ገንዘብ ዋና ፍቅርን ፈጣሪና አጠናካሪ አለ ትላላችሁ ? ይህቺ አባባልህ ገርማኝ ነው ሁለት ሀሳብ አላት ገንዘብ ፍቅርንም ይፈጥራል ያጠናክራልም የምትል ትመስላለህ ይቅርታ አድርግልኝ እንጂ ገንዘብ ፍቅርን መፍጠሩን አልስማማበትም ምናልባት ያጠናክራል የሚለው ጋ እስማማለሁ::


እዛ በራሴ መልስ ለአፈ-ጉባኤ እንደገለጽኩት ገንዘብ ጀነራሊ መውደድን ያጠናክራል ብዬ አምናለሁ. ሰው ሰራሽ ነገር ግን በተፈጥሮ እንደዱብ እዳ መጥቶ የሚወረውን ፊሊንግ እንደማይፈጥር ብዙ ሰው ይስማማል በተለይ እዛ አለም ዉስጥ ኖሮ የሚያቅ.

በሌላ መልኩ ደሞ አንተ ራስህ አንድ ሰውን ውሰድ.ይህ ሰው ራሱን ለማኖሪያ በቂ ገንዘብ የለውም ይባል. የሚወዳት ልጅ ገንዘብ የሌላት ትኑር. አንዲት ሌላ ደሞ ገንዘብ ያላት እሱን የምትሻ ሴት ትኑር. ወዴቷ የሚሄድ ይመስልሀል ? ፍቅር በመፋቀር ደረጃ እና አንድ-ላይ-ህይወትን-ከመኖር አንጻር ይለያያል ነው የምለው. አንድ ላይ ሳይኖሩ ጀስት ያላቸውን emotional bond ብቻ ነው የሚንከባከቡት. ትዳር የመሰለው ወይ አብሮ-የመኖር ህይወት ሲመጣ ግን ፍቅሩ ከሂወታቸው 'አንድ' ክፍል ብቻ ነው የሚሆነው. ሌላ 5 ነገር ሊኖር ይችላል ትዳሩን ለማቆም የሚያስፈልጋቸው. እዚህ ላይ ነው የነገሩ አንኳር የሚመጣው. እልም ያለ ፍቅር ይኖራቸው. ኤሌትሪካቸው ስላልከፈሉ ተቆርጧል. ይህ የሚፈጥረውን ፍረስትሬሽን እና የመንፈስ-ጨንቀት ትልቁ 'ፍቅራቸው" ሊገታው ይችል ይመስልሀል ?ጀነራሊ ማለቴ ነው. ፍቅር ከሌላቸው ከፕሎች ሞር ራሳቸውን ቶለሬት ያደርጉ ይሆናል. ግን ጀነራላይዝ ሊደረግ የሚችለው እውነታ የሚመስለኝ ለኑሮ "በቂ' የሆነ ገንዘብ እስከሌለ ድረስ.....ፍቅሩም አደጋ ላይ ነው. ኮክሬት የሆነው ነገር ከአብስትራክቱ ጎልቶ ይታያል.

-ለትዳር ከሆነ ፍቅር ብቻ,ያለ በቂ ገንዘብ ህይወትን ለመኖር, የሚሰራ አይመስለኝም.
- ለፍቅር ሀይወት ብቻ ከሆነ ገንዘብ ያን ያህል ዲሳይሲቨ ሚና አይጫወትም ይሆናል.

-በሌላ መልኩ ሲገለጽ ደሞ , "ፍቅር" የሚባለው 'ደስታ' እንደማለት ነው ከሰማሁት. ማለት ደስተኛ እንደሆኑ ነው የሚናገሩት በዛ አለም ያሉ ስዎች. ገንዘብ ግን "የህሊና/የመንፈስ/ኢኮኖሚክ ነጻነት" ማግኛ ነው. ደስተኛ ሳትሆን (ማለት everyone has the Urge to be fulfilled by others የሚለው ሳይሟላልህ ) መኖር ትችላለህ. ግን ከገንዘብ አይነት የሚመጣው 'የመንፈስ እርካታ/ነጻነት" ግን ሳይኖርህ ሚዝረብል ነው የምትሆነው ከፍቅር ይልቅ. በመንፈስ የወደቀ ሰው ደሞ እንደሞተ ነው. የማያቁት ሀገር አይናፍቅም አሉ አበው. ከህብረተሰብ ጋር ስትኖር ,በስራ ባልደረቦችህ , በሀይማኖትህ ኮሚኒቲ ,በቤተስብህ ዙሪያ የምታገኘው ፍቅር አለ. ያካክሳል ማለቴ ሳይሆን "ፍቅር" የሚባለው 'ገንዘብ' ካለው አማራጭ መተኪያ ሰብስቲቱትስ ያነሰ ነው ህይወትን በተመለከት.
ትህትና2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1362
Joined: Sun Jan 09, 2005 1:47 am
Location: ethiopia

Postby ባቲ » Fri Jan 13, 2006 1:56 am

ሰላም,

ትምህርት:- የቱ ይልቃል መሰለኝ ጥያቄው::

ብር.... ተግተው ከሰሩ ይገኛል
ብር..... በውርሥ ይገኛል
ብር.... ባንክ ተዘርፎ ይገኛል
ብር..... ካዚኖ ተቆምሮ ወይም ፓወር ቦል አሸንፎ ይገኛል
ወዘተርፈ......

ፍቅር ግን ከፍቅር ወዲያ በምንም አይመጣም, ስለዚህ ፍቅር ከውድ በላይ ወድ በመሆኑ ሳቢያ ሁሌም በላጭ ነው የሚል ዕምነት አለኝ::
ቻዎ
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Postby ብስክሌት » Fri Jan 13, 2006 6:24 am

ለትምህርት

እሱማ "ሲያገጣጥም ግጥም ግጥም" የሚባለው ነው:: ሰኔና ሰኞ አልጋ ውስጥ! እኔም ሁለቱንም ስጡኝ:: አለበለዚያ ገንዘቡን:: እርቦኝ ጠውልጌ ቢል እያሯሯጠኝ በየትኛው ጎኔ ነው ፍቅርን የማደንቀው? ብሩን ስጡኝና እግሬ እስኪቀና ተጉዤ የምወዳትን የምትወደኝን እፈልጋታለሁ!!
ብስክሌት
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Fri Jan 13, 2006 6:01 am

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests