ይድረስ ለመጽሀፍ ቀበኞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ይድረስ ለመጽሀፍ ቀበኞች

Postby ቺፍ » Fri Jan 06, 2006 1:24 am

ሰላም

በአገራችን ላለፉት ጥቂት አስረት አመታት በርካታ መጻህፍት በትርጉምም በፈጠራም ታትመው ቀርበዋል. እየቀረቡም ነው. ስለመጻህፍቱ ይዘት ስናስብ ሁሌም የማይረሳን ትዝታ ገጽባህርያት እና ፕሎት ትተው ያልፋሉ.

አንዳንዶቻችን ለመጻህፍቱ ያለን ቅርበት በማይልስ ሲለካ ለሌሎቻችን ግን ስንዝር የሚሆንበት ወቅት አለ.

እዚህ ላይ ላነሳ የፈለግሁት በሀገራችን በቅርብም በሩቅም የታተሙ መጻህፍትን በማስተዋወቅ ረገድ ችሎታው ያላች ሁ እንድታስተዋዉቁን ለማለት ሲሆን በገበያ ላይ ካሉም አድራሻቸዉን እና ዋጋቸዉን እንዲሁም የደራሲዉን ማንነት ከነችሎታው ብታስተዋዉቁን ከፈተኛ ጥቅም ለአንባብያብ ልታበረክቱ እንደምይችሉ ለመጠቆም ነው.

ምናልባት ከዚህ ቀደም ይህ ሙከራ ተደርጎ እንደሆነ ባላዉቅም በአዲስ መልክ ብንጀምረው እና ብናጠናክረው ምን ይመስላች ሁዋል?? ብዙ ድረገጾች ላይ አሰሳ አድርጌ ስለሀገራችን መጻህፍት አይነት እና ደራሲያን እንዲሁም ማንነት የሚገልጽ አላገኝሁም. ምናልባት አማዞን ዶት ካም ሂድ አንዳትሉኝ እሰጋለሁ. ከላይ እንዳልኩት የራሳችንን በራሳችን አንደበት እና ክሂሎት ማካፈል የምትችሉ እባካች ሁ ያነበባችሁትን አካፍሉን. ማህበራዊ--ኢኮኖሚያዊ---ፖለቲካዊ-----ወታደራዊ----በሁሉም ዘርፍ ያነበብነዉን እንካፈል.

ከአክብሮት ጋር

ቺፍ
ቺፍ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 71
Joined: Tue Aug 24, 2004 10:47 pm
Location: united states

ሰላም

Postby አኒታ » Sun Jan 08, 2006 5:07 pm

ሰላም ቺፍ.. በርግጥ ብዙ ግልባጭ! (ትርጉም) ቢሆኑም የሀገራችን መጽሀፍት ግን ጥሩዎችም አሉ ወደፊትም እንደሚኖሩ ተስፋው አለኝ.. ግን ያልገባኝ ምን መጽሀፍ አድናቂ ነህ? ፖለቲካውን? ወይስ ፊክሽኑን? ለማንኛውም.. ብዙ ጥሩ ደራሲዎች ነበሩ.. ግን አሁን ወደ ትርጉሙ የገቡት ደራሲያን ስላሉ ትንሽ ያስጠላ ጀመር እንጂ ሞልቷል መጽሀፍትማ.. ለማንኛውም ከፈረንጁ ጥቀሽ ካልከኝ ሰሞኑን የወጣው አወዛጋቢውን መጽሀፍ ደስ ብሎኛል.. (the davenchy code) ምናልባት ካላነበብከው.. አንብበው.. ከ ሪያሊቲ ጋር የተያያዘ መጽሀፍ አስደሳች ነው ይህ ግን አወዛጋቢ ከመሆኑም በላይ.. ደራሲው ምን ታይቶት እንደጻፈው ግራ ያጋባል! ለማንኛውም እስኪ ሰለምታደንቃቸው መጽሀፍት አንድ ሁለት በለኝ..
አክባሪህ
አኒታ
ቺርስ በቅራሪ!
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Postby ቁም ነገር2 » Mon Jan 09, 2006 11:15 am

ቺፍ እንኳን አደረሰህ

አንተ ያልከውን መረጃ ለዛሬ ባልሰጥህም ከሀገራችን መጽሀፍት ላይ ያስገረሙኝን አንዳንድ ነገሮች አንተ በከፈትከው ቀዳዳ ገብቼ ጠቆም ላድርግ:: ከዚህ በታች ያለውን ጽሁፍ ያነበብኩት በሀገራችን ለህፃናት የተተረጎመ የተረት መጽሀፍ ላይ ለህጻናት እንደምክር ከተጻፈላቸው የቀነጨብኩት ነው

.................በአሜሪካ ሀገር ድንቅ ችሎታ ያላቸውን 7 ልጆች..... ጋዜጣ አውጥቶ ነበር:: ከነዚህ ውስጥ ባው ዋው በሙዚቃ ችሎታው, የ14 አመቱ ለነቢዮንሴ ልብስ ዲዛይን የሚያደርገው ልጅ, በ15አመቱ ለፒኤችዲው የሚያጠናው ልጅ እና በ19 አመቷ ድምፃዊ የፊልም አክተርና ሞዴሊስት የሆነችው ማንዲ ሙር ይገኙበታል:: የኛ ሀገር ልጆች ግን 18 አመት እስኪሞላቸው ት/ቤት ከመመላለስ በቀር ምንም ቁም ነገር አይሰሩም:: በልጅነታቸውም ቢሆን በየመንገዱ ኳስ ሲያለፉ እና ባልና ሚስት እየተባባሉ በቆርኪ አፈር ሲሰፍሩ ይውላሉ:: ወይም ደግሞ እናትህ... የሚለውን ቃል ሲያስተጋቡ ይውላሉ:: ይህ ቃል በአሁኑ ጊዜ በሀረርጌ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ቅዱስ ቃል ሆኗል:: ለነገሩ ሽማግሌውቹም ቢሆኑ ከረንቡላ ቤት ጠረጴዛ ታቅፈው ሲያሞቁና ድንጋይ ሲወራወሩ ነው የሚውሉት::..................


በመጨረሻው ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል

ልጆች እነዚህን መጽሀፎች ገዝታችሁ አንብቡ

-ጤና አዳም
-የደሀ ሞግዚት
-ሀኪም ለራሴ
- ነጭ ሽንኩርት


ህም..............እነኚህ ሁሉ የባህላዊ ህክምና መጽሀፍት ናቸው
ቁም ነገር2
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 451
Joined: Wed Sep 07, 2005 7:24 am
Location: ethiopia

Postby ላህ » Wed Jan 11, 2006 3:49 am

እስኪ ቤቱ ሞቅ የሚል ከሆነ በዚህ ልጀምር
ትኩሳት [b]በስብሀት ገብረእግዚአብሄር
ከመጽሀፉ መግቢያ ላይ የወሰድሁት
በዚህ በግዕዝ በሚቀደስበት ቅኔ በሚዘረፍበት ሰምና ወርቅ በተትረፈረፈበት በሀበሻ አገር የሚታሰብ 'ንጂ የማይነገር አለ, የሚደረግ 'ንጂ የማይነገር አለ, የሚነገር 'ንጂየማይጻፍ አለ:: ባህል እንበልና እንለፈው....
ጥሩ ነው ወጣትነት መሆን ገንዘብ ባይኖርህም ጤና ይኖርሀል, መልክ ባይኖርህም አንጎል ይኖርሀል ደስታ ባይኖርህም ንዴት ይኖርሀል, እውቀት ባይኖርህም ጉራ ይኖርሀል,.....መጨቆን ቢበዛብህ ሬቮሉሽን ታነሳለህ,.....መኖር ቢያስጠላህ ወይም ቢያቅትህ ራስህን ትገድላለህ::....ሰው ባያውቀውም ቅሉ ታሪክ ይኖርሀል : ወጣት ነህና......
ከመጽሀፉ የተወሰደ
ላህ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 151
Joined: Fri Oct 29, 2004 2:03 am
Location: ethiopia

Postby እንቁየ » Wed Jan 11, 2006 6:33 am

እረሱ ጥሩ ጅምር ነው ያልተረዳኝ ነገር በዚህ ወቅት ብዙ የአገር ውስጥ የተጻፉ መትሀፎች አለሁ እስቲ ጥቂቶችን ለማስታወስ ልሞክር

ከጥቁር ስማይ ስር
ካሳንችስ ዘ ካሳንችስ
ማህሊት
አረም የበዛባት ችግኝ
እና የአቶ ስብሀት ድርስቶች
እግረመንገድ 1እና ሁለት
ለአቶ ስባህ መታስቢያ
የቀሩትን በሚቀጥለው
መልካም ቆይታ
እንቁየ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 111
Joined: Tue Feb 03, 2004 6:49 am

Postby ቺፍ » Wed Jan 11, 2006 10:55 pm

አኒታ
እንቁየ
ላህ
ቁምነገር
እንኩዋን ለብርሀነ ልደቱ አደረሳችሁ

ሀሳብችሁን በመሰንዘራችሁ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል. አመሰግናለሁ. በርቱ.


አኒታ.

ብዙ ጥሩ መጻህፍት አሉን ባልሽው እስማማለሁ. ለምን አንድ ሁለቱን አታስተዋውቂንም????ጠቅለል ባለ ሁኔታ ጥልፍልፉን ሁኔታ ማስተዋወቅ ይከብድሻል??ደራሲዉን ስራዉን እስከምትችይው ድረስ መግለጽ መቻል ትንሽ ዉለታ እንደከፈልሽ አይሰማሽም???? የኔ ፍላጎትም አንባብያን ያነበቡትን በራሳቸው አካሄድ መግለጽ መቻላቸዉን ማየት ነው. እና ፈቃደኛ ከሆንሽ ከምትወጂው እና ከምትጠይው ሁለቱን መርጠሽ ብታስተዋውቂን.

davinchi's code ባለሁለት ክፍል ዲቪዲ ተከራይቼ አይቸዋለሁ. ሚስጥር ያዘለ አንዳንዱንም ለመረዳት እስከሚያስቸግር ድረስ ደጋግሞ ማየትን የሚጠይቅ ነበር. ፊልሙ አብስትራክት ነው የሆነበኝ. በዳቪንቺ እና በእየሱስ መካከል የሁለት ወይ የሶስት መቶ አመት ልዩነት አለ. ብዙ ጉዳዮችን አብስትራክት አድርጎ በሰእል ደብቆት መኖሩ ሲገርመኝ በሌላ በኩል ሚስጥር የተባሉት ነገሮች ሚስጥርነታቸዉን ለማመን ይከብደኛል. አከራካሪ--አወዛጋቢ ናቸው.

ሀገራችን ዉስጥ በርካታ ትርጉም ህትመቶች መበራከታቸው ቢያስደስትም ""ከራስ በላይ ነፋስ "" ነዉና ፈጠራዉን ለምን እንደረሱት ወይም እንደከበዳቸው ማን ሊነግረን እንደሚችል አይገባኝም. ለምሳሌ እንዳንፈጥር የሚከለክል ባህል--ህግ--መንግስት--ፖሊስ---ዳኛ ይኖር ይሆን ወይስ ይቺ ፈጠራ እንደስጋ ወደሙ የምንቀበለው ይሆን???? አልገባኝም.

አኒታ. ስለምታደንቃቸው መጻህፍት አንድ ሁለቱን ብለሽኛል. መልሴ THE FRENCH KISS ወይም THE SATANIC VERSES እንደማይሆን እርግጠኛ መሆን ትችያለሽ.

ይቀጥላል.
ቺፍ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 71
Joined: Tue Aug 24, 2004 10:47 pm
Location: united states

Postby ቺፍ » Wed Jan 11, 2006 11:21 pm

ቁም ነገር2 wrote:ቺፍ እንኳን አደረሰህ


.................................... የኛ ሀገር ልጆች ግን 18 አመት እስኪሞላቸው ት/ቤት ከመመላለስ በቀር ምንም ቁም ነገር አይሰሩም:: በልጅነታቸውም ቢሆን በየመንገዱ ኳስ ሲያለፉ እና ባልና ሚስት እየተባባሉ በቆርኪ አፈር ሲሰፍሩ ይውላሉ:: ወይም ደግሞ እናትህ... የሚለውን ቃል ሲያስተጋቡ ይውላሉ:: ይህ ቃል በአሁኑ ጊዜ በሀረርጌ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ቅዱስ ቃል ሆኗል:: ለነገሩ ሽማግሌውቹም ቢሆኑ ከረንቡላ ቤት ጠረጴዛ ታቅፈው ሲያሞቁና ድንጋይ ሲወራወሩ ነው የሚውሉት::..................


በመጨረሻው ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል

ልጆች እነዚህን መጽሀፎች ገዝታችሁ አንብቡ

-ጤና አዳም
-የደሀ ሞግዚት
-ሀኪም ለራሴ
- ነጭ ሽንኩርት


ህም..............እነኚህ ሁሉ የባህላዊ ህክምና መጽሀፍት ናቸው


ሰላም ቁምነገር

እንደመርፌ አእምሮን የሚሸነቁር ከፍተኛ አባባል ነው የሰነዘርከው. የእኛን ህጻናት ከም እራቡ ህጻናት ጋር ለማነጻጸር ያደርግህእው ሙከራ እንዲህ በሶስት መስመር የሚታለፍ እንዳይመስልህ. ያነሳህእው ነጥብ ከፍተኛ እና መሰረታዊ የሀገራችን እንዲሁም የመላው ታዳጊ ሀገሮች ችግር በመሆኑ ምን እናድርግላቸው??? ምን ይሻላል የሚለው የፖለቲካ እና የፖሊሲ መፍትሄ የሚሻ በምሆኑ እዚች መድረክ ላይ ባናነሳት የሚሻል ይመስለኛል. ብዙ ደራስያን የማህበራዊ ህይወታችን ቀጥተኛ ነጸብራቅ የሆኑትን ህጻናት በብእራቸው ማንሳታቸው የሚጠበቅ ስለሆነ ጥቂት አስተዋጾ አድርገው እንደሆነ እንጂ ገና የተነካ አይመስለኝም.

አንዳንድጊዜ ግን በራሳችን መስፈርያ መስፈርን የመሰለ የለም. የእኛ ህጻናትን በራሳችን መነጽር ስንመረምራቸው ገና በልጂነት ከባድ ሀላፊነት መሸከመን---የህይወት ዉጣ ዉረድን መቁዋቁዋም--ድፍረት እና ጀግንነትን---ታላላቆችን ማክበርን--ትሁት እና አይናፋርነትን ---ሀይማኖት እና ቁምነገርን ተላብሰው ስለሚያድጉ እንደምእራቡ ዋልጌ እና ቅብጢ መሆን አይችሉም. የአሜሪካው ትእግስታቸው ካለፈ የመሀል ጣታቸዉን አዉጥተው F******* ማለታቸዉን ማንም አይወድላቸዉም. እንዲህ እንዲህ አይነቱን ማህበራዊ ጉድፍ የመጥረግ ሀላፊነት የደራሲያን እና የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያወች ይሆናል.

በነገራችን ላይ በህጻናት ችግር/አስተዳደግ ላይ የተመሰረተ መጽሀፍ አላነበብኩም. እዚህ አለሁበት አገር
HARRY POTTER በተሰኘ ታዳጊ ህጻን ገጽባህርይ ላይ ተመርኩዛ አንዲት እመቤት በተከታታይ መጻህፍት እያሳተመች ሚሊዮነር ሆናለች. አሁን በቅርቡ ከፍተኛ ክሪቲክ ቀርቦባት በቲቪ ላይ ትንሽ ችግር ፈጥረዉባት ነበር. የትችቱ መንስ ኤ የመጽሀፉ ይዘት ስለእርኩስ-መንፈስ ስለጥንቁልናና---አስማት የመሳሰሉት ሁዋላ ቀር ድርጊቶች በመሆኑ መከለከል አለባት የሚል ክርክር ነበር.
በልጅ አመካኝቶ ይበላላ አንጉቶ ነዉና ግለስብዋ በመጽሀፍም-በቪድዮም--በዲቪዲም ብዙ ብር አፍሳበታለች.

ትንሽ ዘግየት ብዬ መልስ ስለሰጠሁ ይቅርታ እየጠየቅሁ
ተሳትፎህን እንድትቀጥል በርታልን እላለለሁ.

ቺፍ
ቺፍ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 71
Joined: Tue Aug 24, 2004 10:47 pm
Location: united states

Postby ቺፍ » Wed Jan 11, 2006 11:33 pm

ላህ wrote:እስኪ ቤቱ ሞቅ የሚል ከሆነ በዚህ ልጀምር
ትኩሳት [b]በስብሀት ገብረእግዚአብሄር
ከመጽሀፉ መግቢያ ላይ የወሰድሁት
በዚህ በግዕዝ በሚቀደስበት ቅኔ በሚዘረፍበት
ሰምና ወርቅ በተትረፈረፈበት በሀበሻ አገር
የሚታሰብ 'ንጂ የማይነገር አለ,
የሚደረግ 'ንጂ የማይነገር አለ,
የሚነገር 'ንጂየማይጻፍ አለ::
ባህል እንበልና እንለፈው....
ጥሩ ነው ወጣትነት መሆን
ገንዘብ ባይኖርህም ጤና ይኖርሀል,
መልክ ባይኖርህም አንጎል ይኖርሀል
ደስታ ባይኖርህም ንዴት ይኖርሀል,
እውቀት ባይኖርህም ጉራ
ይኖርሀል,.
....መጨቆን ቢበዛብህ ሬቮሉሽን ታነሳለህ,.
....መኖር ቢያስጠላህ ወይም ቢያቅትህ ራስህን ትገድላለህ::....
ሰው ባያውቀውም ቅሉ ታሪክ ይኖርሀል : ወጣት ነህና......
ከመጽሀፉ የተወሰደ


ላህ ምስጋናየ ይድረስህ.
አመራረጥ ስትችልበት. እንደ እሳት ፍም ዉስጥ ዉስጡን የሚፍሙ ሀሳቦችን ነው መርጠህ ያወጣህው.
ደራሲ ስብሀት ታላቅ ችሎታ የነበረው ደራሲ ነው. ለተከታዩ ትዉልድም የሚኖረው አስተዋጾ እንዲህ በቀላሉ የሚለካ አይመስለኝም.

ከላይ ያሉትን የስብሀት ሀሳቦች ስናያቸው ተቃራኒ ጽንሰሀሳቦች ተገናኝተው ዉብ የሆነ መል እክት ሊሰጡን እንደሚችሉ ያሳያል. ይህ ደግሞ ከፍተኛ ችሎታ ነው.

ላህ ምን ይመስልሀል??????

ቺፍ
ቺፍ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 71
Joined: Tue Aug 24, 2004 10:47 pm
Location: united states

Postby ቺፍ » Wed Jan 11, 2006 11:37 pm

እንቁየ wrote:እረሱ ጥሩ ጅምር ነው ያልተረዳኝ ነገር በዚህ ወቅት ብዙ የአገር ውስጥ የተጻፉ መትሀፎች አለሁ እስቲ ጥቂቶችን ለማስታወስ ልሞክር

ከጥቁር ስማይ ስር
ካሳንችስ ዘ ካሳንችስ
ማህሊት
አረም የበዛባት ችግኝ
እና የአቶ ስብሀት ድርስቶች

እግረመንገድ 1እና ሁለት
ለአቶ ስብሀት መታስቢያ
የቀሩትን በሚቀጥለው
መልካም ቆይታ


ሰላም እንቁየ

ከአቶ ስብሀት በስተቀር የተቀሩትን መጻህፍት አላየሁዋቸዉም. እንዲያዉም አንዳንዶቹ የመጻህፍት
ርእስ መስለው አይታዩኝም.

ጥቂቱን ባጪር ባጪሩ አስተዋዉቀና???????

አክባሪ ቺፍ
ቺፍ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 71
Joined: Tue Aug 24, 2004 10:47 pm
Location: united states

Postby ላህ » Thu Jan 12, 2006 1:55 am

ለቺፍ
ሰላምታየ ባለህበት ይድረስህ
አወ ያለምንም ማመንታት የጋሽ ስብሀት አድናቂ ነኝ በጣም ውብ የሆኑ ነገሮችን አይቼበታለሁ ለወደፊቱም ብዙወቹ ያገኙበታል የሚል እምነት አለኝ::
ለዛሬ ደግሞ ቆየት ወዳለው የጋሽ ስብሀት ስራ ልውሰዳችሁ
አምስት ስድስት ሰባት [b]
ከስብሀት ገ/እግዚአብሄር [i]

ፌቆ ስትዘል አግኝቼ በልቼ መጣሁ::
ሰባች ጎፈየች?
ሳትታረድ መጣሁ::
የሆነስ ሆነና ስምህ ማን ነው?
ላገር አይመች
ማን አወጣልህ?
ጎረቤቶች
የናትህ ስሟ ማን ነው?
ሳልወለድ ሞተች
የሆነስ ሆነና እግዚሀርን አይተኸዋል አላየኸውም?
አወን አይቸዋለሁ
ቀይ ነው ጥቁር?
ተከናንቦ ነበር
ረዥም ነው አጭር?
ቁጭ ብሎ ነበር::
ላህ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 151
Joined: Fri Oct 29, 2004 2:03 am
Location: ethiopia

Postby ቁም ነገር2 » Thu Jan 12, 2006 7:12 am

እንዴት ነህ ቺፍ

ከላይ ያሰፈርኩት የኔ ሀሳብ አይደለም እንድ ለህፃናት the Arebian nightsን የተረጎመ ደራሲ?(ተርጓሚ?) ለሀገራችን ህፃናት በምክር መልክ የመጽሀፉ መግቢያ ላይ ያሰፈረው ነው:: እኔ ራሴ የጽሁፉ አላማ ከኛ ሀገር አብዛኞቹ ልጆች ጋር አልሄድ ቢለኝ እናንተም እንድትደመሙበት ብዬ ነው ያቀረብኩት::
ከሁሉ የገረመኝ ደግሞ scientifically proven ያልሆኑ አሉባልታ ቢጤ የሚመስሉ በደራሲው የተጻፉትን የባህል ህክምና መጽሀፍትን ህፃናቱ እንዲያነቡ recommened ማድረጋቸው ነው::

ስብሀት :?: እንደ ኤሚኒየም Mister controversy ብላቸው ደስ ይለኛል
ቁም ነገር2
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 451
Joined: Wed Sep 07, 2005 7:24 am
Location: ethiopia

Postby እንቁየ » Thu Jan 12, 2006 12:54 pm

ወዳጀ ለአስተያየትህ አመስግን አለሁ ትክክለኛ የመጽህፍት ስም ነው እስቲ ዛሪ ከጥቁር ስማይ ስር ከሚለው ትንሽ ጀባ ልበልህ

ከጥቁር ስማይ ስር
ደራሲ
እንዳለጊታ ከበደ

ምጣድ

ከርቀት አንድ ስባኪ ድምጽን አስጭሆ የመዝጊያ ጠሎት ስነስራት ያካኢዳል:......

"የእለት እንጀራችን ስጠን ዛሪ""

'አሚን ' አለች ፈግ ብላ :: አልጋዋን አየችው የእለት እንጀራዋን የምትግግርበት::
አሁን የምትኖርበት ክፍል ነፍሳቸውን ይማረው የእናታ ነበር :: እናታ ከክፍላቸው ወንድ ሁሉ ይተኛበት የነበር አልጋ አሁን አለ:: አሁንም የመክፈል አቅም ካላቸው ጋር::
ልጅቱም ትተኛበት አለች:: በተረገዘችበት የሽቦ አልጋ ላ ነው እንጀራዋን እየጋገረች ያለችውው::
'
እንቁየ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 111
Joined: Tue Feb 03, 2004 6:49 am

Postby ሳተርን » Thu Jan 12, 2006 4:32 pm

ምናልባት ልጅ ሆኝ ስላነብብኩት እንደሆነ አላውቅም "አደፍርስ" በዶ/ር ዳኝአቸው ወርቁ ምን ጊዚም አልረሳውም;; ይህ መጽህፍ ከፍቅር እስከ መቃብር ቀጥሎ በተለየ መልክ የአንድን ህብረተሰብ ጥልቅ የኑሮ ይዘትና በዘመኑ ያለውን አስተሳሰብ በሚያምር ታሪክ ታጅቦ ና በበለጸገ ቅዋንቅዋ አሽብርቆ የቀረበ ነው;; በጊዘው በዩነቨርስቲ አማርኝአ ፋኩልቲ ውስጥ እንደ text ያገልግል እንደነበረ ሰምቻለሁ;; ለራሰ አንድ ኮፒ ለማስቀረት ባለመቻለ ሁለ እቆጫለሁ;; እንደምሰማው ከሆነ ደራሲው ለማባዛት ፈቃደኝአ እንዳልሆኑ ነው
ሳተርን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 397
Joined: Wed Dec 28, 2005 6:12 pm

Postby ቺፍ » Thu Jan 12, 2006 11:30 pm

ሰላም ሳተርን እና ሌሎችም

መድረኩ ሞቅ ሞቅ እያለ ምሆኑን እያስተዋልኩ ነው. ደስ የሚል ተሳትፎ ጀምረናል.

ያነበብነዉን ማካፈል ከፍተኛ አስተዋጾ ነው ብየ አምናለሁ.
በአንድ በኩል ትዝታን ማጫር ሲሆን በሌላ በኩል የደራስያንን ዉለታ እንደመክፈል ይመስለኛል. ከሁሉ በላይ ትኩስ ደራስያንን የምያበረታታ እና ሞራል የሚሰጥ በመሆኑ የምናበረክተው ድርሻ ከፍ ያለ ነው ብየ አምናለሁ.

አኒታ ከላይ ያነሳችው ሀስብ ጉልህ ችግር ነው. ግልባሽህ ወይም ትርጉም ገበያዉን አጥለቀለቀው ብላናለሽ. ትክክል ነው. ግን ሁኔታዉን በቅርበት ካየነው አንድ መሰረታዊ ችግር የሚያንጸባርቅ ይመስለኛል. የመፍጠር /ወይም ወጥ የሆነ ስራ ማቅረብ አስቸጋሪ የሆነበት ጊዜ ወይም ዘመን ላይ ደረስን ወይ?? ብለን እንድንጠይቅ እንገደዳለን. እኔም ከላይ እንዳልኩት እንዳንፈጥር የሚከለክለን ባህል--መግስት--ህግ--ዳኛ እና ፖሊስ አለ ወይ ብየ ነበር.ለመፍጠር ምን ምን ባህላዊ እና ፖለቲካዊ ቅድመ ሁኔታዎች ያስፈልጋሉ. በአደባባይ መፍጠር ባንችል ዉስጥ ዉስጡን መፍጠርስ አንችልም ወይ??

በእርግጥ አፈናና እስራት እንዲሁም ሳንሱር በሰፈነበት ሁኔታ የደራስያን ወጥ የሆነ ስራዎችን መጠበቅ አንችልም. የፖለቲካ ሁኔታዎች አፋኝ ሲሆኑ ደራስያን እና ጸሀፍት ምቹ ሁኔታ እስኪያገኙ ድረስ በተግስት መጠበቅ ይገደዳሉል.

እንግዲህ እህታችን አኒታ ገበያዉን ትርጉም አጥለቀለቀው ካለችን የመፍጠር እና ወጥ የሆኑ ስራወችን የማቅረብ እድሉ የተመናመነበት አፋኝ ሁኔታ ሊኖር ይችላል ብለን እንድናምን እንገደዳለን ማለት ነው.

በሌላ በኩል ዛሬ ወቅቱ ነጻ ገበያ ነው ስለሚባል ብቻ መጻህፍትን እየተረጎሙ መቸብቸብ አይነተኛ የገቢ ምንጭ የሆነ ይመስላል. ስለዚህ ሁሉም ፈጣን ገቢ አግኝቶ የግል ህይወትን ማመቻቸት እንጂ በመስዋእትነታቸው የህብረተሰቡን አይን መግለጥ የሚፈልጉ ወይም ሻማ መሆን የሚችሉ ባለሙያወች የሉንም ማለት ነው.

ለዚህ አስተያየቴ ምንጭ የሆነችው እህቴ አኒታ ምን መልስ እንደሚኖራት ባላዉቅም ችግሩ የጋራ ሊሆን እንደሚችል ግን ሳልረዳው አልቀረሁም.

ለማንኛዉም መድረኩን ለዚህ አይነቶቹ መስረታዊ ችግሮች መወያያ ሊያገለግለን ስለሚችል መጻህፍትን/ደራስያንን ከማስተዋወቅ ጎን ለጎን ለፈጠራ ስራዎች መጎላበት ይበጃል የምትሉትን ሀሳብ ሁሉ እንድት ሰነዝሩ ለማበረታታት እወዳለሁ.

አክባሪ
ቺፍ
ቺፍ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 71
Joined: Tue Aug 24, 2004 10:47 pm
Location: united states

Postby ላህ » Sat Jan 14, 2006 3:26 am

እስኪ ዛሬ ደግሞ ቆየት ወዳለው ደራሲ ስራ ልውሰዳችሁ ....
አልወለድምከአቤ ጉበኛ
ይህቺን መጽሀፍ ሁለቴ ነው ያነበብኍት አንዴ ነፍስ ሳላውቅ በልጅነት ቤት ወድቃ አግኝቻት ሁለተኛው ነፍስ ካወቅሁ በኍላ....ለነገሩ አሁን ነፍስ አውቄያለሁ???
ሰወች ሁሉ ከአራዊት ባህሪይ ተዘምዶ ያለውን አካላቸውን ከመለኮት ተዘምዶ ባለው መንፈሳቸው ስልጣን ስር እስኪያውሉት በጎ ምግባር ክፉና ትዕቢተኛ ፍላጎትን ድል እስኪያደርግ ድረስ, ንጹህ የሆነ ሰላማዊና ቅዱስ ኑሮ ሊገኝ አይችልም ::
ሶክራትስ "መኳንንት! ልጆቼ ባደጉ ጊዜ ቅጧቸው, ከደግ ስራ በፊት ለገንዘብ የሚያስቡ ከሆነ እኔ እንዳሰቃየኍችሁ አሰቃይዋቸው::እነሱ ምንም ሳይሆኑ ምኖች ነን ብለው ራሳቸውን ካከበሩም እኔ እንዳሳፈርኍችሁ አሳፍሯቸው ሊያስቡት የሚገባቸውን አላሰቡምና! ምንም ሳይሆኑ ራሳቸውን ዋጋ እንዳለው ነገር በመቁጠራቸው::......
"አንተ ማነህ ?" አለኝ ቄሱ
ሰው ነኝ አልሁት
ከየት መጣህ?
ከናቴ ሆድ
ማን ፈጠረህ?
ሁሉን አስተካክሎ የፈጠረ
ሀይማኖትህ ምንድን ነው?
ሁሉን በፈጠረ ፈጣሪ ማመን
በምን ሁኔታ? በማንስ ትምህርት?
በፍጹም ስሜት ራሱ በሰጠኝ ትምህርት
ክሪስትያነ ነህ?እስላም? ወይስ አይሁዳዊ ነህ? ቡዲስት? ወይስ በሌሎች ሀይማኖቶች የምታምን?
ሁሉንም አይደለሁ:: በፈጣሪ ብቻ የማምን ነኝ::
ሀይማኖት የለህም ማለት ነዋ?
የሀይማኖት ክፍል የለኝም እንጂ ሀይማኖትስ አለኝ::
ላህ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 151
Joined: Fri Oct 29, 2004 2:03 am
Location: ethiopia

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests