ተናገር ወንበሩ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ተናገር ወንበሩ

Postby ጦሳ » Fri Jan 06, 2006 6:56 pm

ታሪክ ነው ጠያቂህ: ተናገር ወንበሩ?!
ከተቀመጡብህ: እነማን ምን ሰሩ?!
ወይንም አሰሩ?!

ችሎት የሚዋለው
ፍርድም የሚገኘው
ወይም የሚጠፋው
የየሰው ጉዳይ: ብይን የተሰጠው:
አልያም የተቀማው
በዛሬም ላይ ሆኖ
ትላንት የሚሆነው:
ከጥንት ጀምሮ: ነውና ከአንተው:
ተጠየቅ ወንበሩ!
እሰጥ አገባህን: መወራከቡን ተው!

ካንተ በየተራ; የተቀመጠውን:
ከፍርድህ ሚዛን ላይ አኑረህ እይና: የየግል ስራውን!
ወንበርህ ብይን ይስጥ: ለሁሉም ዋጋውን!
ወንበር ቶሎ ተነስ!
ብይን መቀበያ: ችሎትህ ሲጀመር:
ሁሉም ሊያየው ጎጉቱዋል:
ያጠፋው ሲቀጣ! ያለማው እንዲካስ!
እጅግ በመፈልግ ታሪክ ጠይቆሀል!

አዲስ አበባ: ታህሳስ 20: 1982
ጦሳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 16
Joined: Tue Dec 20, 2005 12:57 pm

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests