የምትወዱት ሰው ሲለያችሁ.......

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የምትወዱት ሰው ሲለያችሁ.......

Postby ቁም ነገር2 » Wed Jan 11, 2006 10:30 am

በጣም እጅግ በጣም ነው የምወዳት:: ጥንትም አሁንም.......አሁን አሁን ካጠገቤ ሳጣት ምናለ ምን ያህል እወዳት እንደነበረ አሁንም እንደምወዳት ባወቀችልኝ.....ምናለ ለሷ ያለኝን ስሜት በፊት ከገለጽኩላት የበለጠ መግለጽ በቻልኩ.....ምነለ ጥቂት ጊዜ ኖሮኝ ላደርግላት ስመኘው የኖርኩትን ነገር ባደረኩላት እላለሁ:: ደሞ ትንሽ ቆይቶ ..... በወቅቱ የቻልኩትን ሁሉ አድርጌያለሁ የተቀረውን አምላክ አልፈቀደም እላለሁ:: ዞሮ ዞሮ ግን ስሜቱ ያው ነው መቆጨት ማዘን መተከዝ:: የእናት ሞት የዘላለም የእግር እሳት:: መጽናኛ የሌለው ማስረሻ የሌለው የዕድሜ ልክ በሽታ::........አቤት በተለይ አውዳአመት ሲሆንማ....ማስጠላቱ....ቀኑ መጨለሙ ሰውሁሉ መደበሩ.....የማይገፋውን ቀን ለመግፋት የውሸት ሳቅ መገልፋጥ መገልፈጥ ውስጥ እያረረ......ደግሞ እሱ ሲደክም....ቀኑን ለመርሳት ጥቅልል ብሎ መተኛት......እህህ ....እንቅልፉስ ሲገኝ አይደል.........
ቁም ነገር2
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 451
Joined: Wed Sep 07, 2005 7:24 am
Location: ethiopia

Postby ትትና » Wed Jan 11, 2006 12:23 pm

መቼስ ምን እልሀለሁ እግዚአብሄር መጽናናቱን ይስጥህ እንጂ! የናትስ ነገር እንዲህ ቀላል አይደለም:: እኔ እዚህ አገር ከመጣሁ ጊዜ ጀምሮ ቀን ከሌሊት እንቅልፍ የሌለኝ በናቴ ሀሳብ ነው:: ምን ያህል በየደቂቃው በየሰአቱ እንደምትናፍቀኝ ተመልሼ አገኛት ይሆን አይሆን የሚለው ነገር ሳስበው ገና ይዘገንነኛል::
እና ሀዘንህ ቀላል እንደማሆን አምናለሁ ግን ደሞ እግዜር የፈጠረውን ወሰደ ብለን ካልተቀበልነው እንዴት ይቻላል ስለዚህ እባክህ ለመጽናናት ሞክር::

እግዚአብሄር ካንተ ጋር ይሁን
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby ቁም ነገር2 » Thu Jan 12, 2006 8:02 am

አመሰግናለሁ ትትና

ማሪያምን ትወዳታለህ ወይ? ቢሉት ወድጄ ነው የምወዳት ከግንድ የሚያላጋ ልጅ እያላት አለ አሉ ሰውየው:: መጽናናቱን ፈለጉም አልፈለኩም መጨረሻ ላይ የማይቀር ነገር ነው:: ሰው ለመርሳት የማይሆነው ነገር የለም:: you may take a lot of measures but it takes time. ሞኒካ እዛኛው ቤትሽ ውስጥ ያነሳሽውን ሀሳብ እዚህ ብቀጥለው ፓተንቴን ተቀማሁ እንደማትይኝ እርግጠኛ ነኝ :roll: :roll: አበሻና ነጮች በሀዘን ላይ ያለን ሪያክሽን ልዩነት ሊኖር የቻለው ከአኗኗር ሁኔታችን ይመስለኛል:: በልጅነታችን አብዛኛውን ጊዜ የምናጠፋው እናታችን ቀሚስ ስር ይመስለኛል:: በተለይ ደግሞ እናት ስራ ከሌላት ከትምህርት ቤት መልስ ከሷ ጋር ቤት ውስጥ ስንጎዳጎድ እናመሻለን ህፃን ሆነንም ታናሽ እስኪወለድ ድረስ እግር እግሯን እየተካተልን እስከ 3 እና 4 አመት ድረስ ጡት እንጠባለን:: ያ ደግሞ በእናት እና ልጅ መካከል ያለውን ቦንድ የሚያጠናክር ፋክተር ነው:: ሌላው እንደ ባህል የያዝነው ለቅሶ ላይ ለረጅም ጊዜ ፍራሽ አንጥፎ መቀመጥ ሀዘንን ከሚያባብሱ ነገሮች አንዱ ነው:: ለቅሶ ያልደረሰ ሰው በመጣ ቁጥር አብረን እንድናለቅስ ይጠበቅብናል:: ነጮቹ ግን እንደኛ ሳይሆን they avoid stress while we Ethiopians invite stress. መሰረታዊ ልዩነታችን እዚህ ላይ ይመስለኛል::

ቁም ነገር2
ቁም ነገር2
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 451
Joined: Wed Sep 07, 2005 7:24 am
Location: ethiopia


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests