ፍቅር እና ሌሎች ግጥሞች ማሰባሰቢያ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ፍቅር እና ሌሎች ግጥሞች ማሰባሰቢያ

Postby ሚሚlove » Thu Jan 12, 2006 10:16 am

ለዛሬ በዚች አጭር ግጥም እጀምራለሁ::
ፍቅር
እንደማለዳ ፀሀይ ብርሀንስትፈነጥቅ
እንደ ባህር አልማዝ ስትፍለቀለቀለቅ
እንደ እሳት ላንቃ አብረቅርቃ
ከቀተር ፀሀይ በርታ ደምቃ
ስተጀምር ማለት ድንግዝግዝ
መባባት አይቀት መተከዝ
ግን ፍቅር ........
ፀፀት ትዝታን ድርድራ
ምኞትን ከህልም አዋቅራ
በብቸኝነት ስትማቅቅ
ቀን ከሌሊት አትል ስትጨነቅ
ፍቅር ......
ብርቅርቅታ ናት ታበራለች ቀን ጠብቃ
እንደጨለመች አትቀርም እንዳኮረፈች ተደብቃ
ውሎ ቢያደርም ታበራለች በህብረቀለማት አሸብርቃ::

ቸር ሰንብቱ
Last edited by ሚሚlove on Tue Jan 31, 2006 7:35 am, edited 1 time in total.
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Tue Jan 17, 2006 1:39 pm

"ይናገራል እንባ"

በክህደት በደል
በሽፍጥና ተንኮል
በሞት ሀዘን ጊዜ
እምነት በማጉደል
ሲታጣ ደጋፊ
የሰው ችግር አይቶ
ፍቅር ቃሉ ሲቀር
ተግባሩ ተረስቶ
ይናገራል እንባ
የውስጥን አውጥቶ

መልካም ንባብ ቸር ሰንብቱ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Tue Jan 24, 2006 1:16 pm

ውድ የዋርካ ታዳሚዎች የምትፈልጉትን ግጥም መፃፍ ትችላላችሁ..... አስተያየታችሁ አይለየኝ.....
( ........ ? )
እራሷ መሆኗን አወቀን
ኖረንም ሞተን ክብራችን
እውነት እንወዳታለን
ኢትዮጵያን ከልባችን?

ቸር ሰንብቱ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Wed Jan 25, 2006 2:03 pm

"ቃሏ ስሚ አጥቶ'
ያቺ ቀን ተረገም
ችቦ ይዞ ሲያዘግም
ንፋስ ባረገው እልም
ቀፈፈኝ እያለች
ንግግር አቆመች
ማን አይቶ ችግሯን
ንቀዋት እንቡጧን
ያዋክብዋት ጅመር
ውል ገብታ እንድታሰር
ቃሏ ሰሚ አጥቶ
ልጅ ገደለ አጋብቶ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Thu Jan 26, 2006 9:44 am

"ይሁዳ ምን ያደርግ "
ገና ሳይፈጠር ሰው ሆኖ ሳይመጣ
ከእናቱ ሆድ ሳለ የወጣለት እጣ
ንግድ ነበርና የቢዝነስ ጨዋታ
ያዋጣኛል ብሎ ቢሽጠው ያንለታ
ይሁዳ ምን ያድርግ ታክስ ይጣልበታ

በሌላ ግጥም እስክንገናኝ ቸር ሰንብቱ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

ሰላም

Postby ነገርኩ/ዋ » Thu Jan 26, 2006 2:25 pm

ሰላምና ጤና እመኛለው ! እንደምን አላቹውልኝ እኔ ደና
ነኝ እናንተ ደና ናቹ ? ሚሚ በጣም ደስ ይላላሉ ግምቹ
እኔስ እንዳትይ ደግሞ አንቺም ደስ ትያለሽ ምክንያቱም
ሰው
አያስጠላም ስራው ነው ሚያስጠላው እናም ያንቺም ስራ
ስለሚያምር አንቺም በስራሽ ነውና ምትመዘኝው ታምሪያለሽ
አሜን አትይም እንዼ !!! እንግዲ እኔም አንድ ግጥም ልበል
ግን '''''''ይህን ልበል

ግጥም

ህሊናን አጥቺ ሥኖር በከተማ
ማንም ሳይረዳኝ መሞቲ ተሰማ
ለህሊና ብዪ እንደ ሻማ ቀለጥኩ
ለሊላው ብርሃን ሳልሰጥ ብቻ አለኩ
መልካም ጊዜ ይሁንልን አሜን

ቸር ያሰማን !!
ነገርኩ/ዋ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 53
Joined: Thu May 26, 2005 4:53 pm
Location: egypt

Postby ሚሚlove » Fri Jan 27, 2006 8:19 am

ነገርኩ /ዋ እንደጉድ አሜን ብያለሁ ስለ አስተያየትዎ አመሰግናለሁ ለመሆኑ አንተ ልበል አንቺ ለዛሬ እርሶ በማለት መልክተን አቀርባለሁ ግጥሞት ከልብ ደስ የሚል ነገር ነው የልብን ሊነግር የሚችል ነገር አለበት አስተያየትዎ አይለየን እላለሁ በዚሁ አጋጣሚ እኔም እስኪ አንድ ጀባ ልበልዎ.......

ልጠራ በስምሽ
እቃቃ ብለን አፈር ያቦካነው
ሳር ቅጠል አንጥፈን አብረን የተኛነው
በልጅነት ለዛ ሁሉን ያሳለፍነው
ዛሬም ውስጤ አለ መቼ እረሳዋለው?
ያን ጊዜ ነበረ ያኖርኩሽ በልቤ
ገና ጨቅላ ሳለሁ የመረጠሽ ቀልቤ::
እንደወይን ተተክሎ ያጎመራው ፍቅርሽ
ባንቺ ውስጥ ይኖራል ይረዳዋልብሽ
ዛሬም አትራቂን ልጠራ በስምሽ

ቸር ስንብቱ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Sat Jan 28, 2006 8:50 am

-------የገበሬው ምርቃት --------
ከልጅ አመዳም
ከጥጃ ቀንዳም
ከሀምሌ በረዶ
ከዘመድ መርዶ
ከዘመድ ምቀኛ
ከአህያ ቀበኛ
ይጠብቃችሁ::
ከደጋ ብቅሉን
ከቆላ ጌሾውን
ይስጥልኝ::
ከጓሮ ማረስን
በቁና ማፈስን
ይስጥልን::
ከድንጋይ ጠፍጣፋን
ከአርሶ አደር ቀልጣፋ
ከዚህ ቤት አይጥፋ
አሜን::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby Ahmed » Sat Jan 28, 2006 11:20 am

ስለ ፍቅር ያቀረብሽው ግጥም ስሜትን ሚሰርቅ እጹብ ድንቅ ስራ ነው! በርቺ!
Ahmed
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 48
Joined: Tue Sep 23, 2003 8:25 am

ሰላም

Postby ነገርኩ/ዋ » Sat Jan 28, 2006 6:21 pm

ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንደምን አላቹ ? እኔ ደና ነኝ እናንተስ ?
እንደምን ነሽ ሚሚዪ አንተ በይኝ ግን አንድ ሰው ያለኝን ልንገርሽ ወንድ ነኝ አልኩት አላምንም አለኝ ለምን እለዋለው
ማየት ማመን ነው ካላየው አላምንም አንቺም እንደልጁ እንዳትዪኝ ብዪ ነው አመሰግናለው እናም እኔም አንድ ልበላ

እርፋ ነዋ

ሪሲን ልጠይቅ እንዴት እንደወደድኮት
ምግብ አልበላ እንቅልፋ አልተኛ አለኝ በቃ እያልኮት
ፋቅር እንዲ ያደርጋል ሹክ በሉልኝ ባካቹ
በቤታቹ ገብቶ ያስተናገዳቹ
መውደዴ እውነት ነው ሁሉም ይወቅልኝ
እርሶ የኔ ሄዋን ሆና ትኑርልኝ


አመሰግናለው ቸር ያሰማን
ነገርኩ/ዋ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 53
Joined: Thu May 26, 2005 4:53 pm
Location: egypt

Postby ሚሚlove » Mon Jan 30, 2006 10:06 am

ስለ Ahmed ስለ አስተያየትህ ከልብ አመሰግናለሁ አስተያየትህ አይለየኝ ነገርኩ /ዋ የፃፍካት ደስ የምትል ቢሆንም እስኪ አብራራትና እኛም መላ እንፈልግልህ.....

-------ይናገራል እንባ--------
በክህደት በደል
በሽፍጥና ተንኮል
በሞት ሀዘን ጊዜ
እምነትህን በማጉደል
ሲታጣ ደጋፊ
የሰው ችግር አይቶ
ፍቅር ቃሉ ሲቀር
ተግባሩ ተረስቶ
ይናገራል እንባ
የውስጥን አውጥቶ

ቸር ሰንብቱ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby Jossy1 » Mon Jan 30, 2006 12:10 pm

ፍ-ፍፁማዊ ህይወት
ቅ-ቅዱሳዊ ቅርበት
ር-ርካታ በአንድነት

ፍቅር
በአንዲት ቃል ትስስር
ሁለት ነብስ ማጣመር
ፍቅር
የእሷ ለእሱ መኖር
የእሱ በእሷ ህብር
30.01.2006

ማስታወሻነቱ ለሚሚlove
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby ሚሚlove » Mon Jan 30, 2006 3:27 pm

Jossy 1 አንተ የተባረክ ልጅ የፃፍክልኝ ግጥም እንዲያው ውድድድድድድ ነው ያደረኳት ከልብ ነው የማመስግነው ምናለ አንዳንዴ ብንቀያየር ምን ያህል ደስ ባለን ነበር..... እስኪ ከመውጣቴ በፊት አንድ ጀባ ልበል
------ ለጋ -------
ጥሬ እንቦቀቅላ
መንገድ ላይ ተጥላ
የዘመድ ሳያንሳት
ባዕድ እየደገማት
ጥሬ ስጋ ይዞ
እሳት ልትገዛ
ዛሬም እዛው ጋር ነች
የአይቶ አላፊውን ቁጥር እያበዛት
የነገን ፈተና ታይፕ እየመታች

ቸር ሰንብቱ ከብዙ መውደድ ጋር
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Tue Jan 31, 2006 7:21 am

Jossy 1 በየቀኑ ባነበብኩት ቁጥር እንዴት መስለህ ደስ የሚለኝ ብቻ እንዲህ በቀላሉ ተወርቶ መግለፁ ይከብዳል እስኪ.....
----- ለቀማ ------
ነቃሁኝ ተኝቼ
ትዝብትን ጠጥቼ
የማይካን ሊካን
በማይካን ሊካን
እንዳይሆን ሆነና
ሁሉም ተተወና
በጩሕት አፈና
ጊዜውም ከፋና
ከመራራ ጎዳና
ከፅልመት ከተማ
አንድ ባንድ ለቀማ
ጆሮን እየሰማ
ዛሬማ በሀገሬ
ሰውም ሆነ ጥሬ

ቸር ሰንብቱ ከብዙ መውደድ ጋር
Last edited by ሚሚlove on Fri Feb 03, 2006 7:13 am, edited 1 time in total.
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Wed Feb 01, 2006 11:25 am

"" የራሱን ኑሮ ትቶ
የሰውን ጀርባ ሲያጠና
ይህው ዛሬም እዚያው አለ
እንደሆነ የሰው ጭራ""


----- ሆኖ ቢሆን ኖሮ ----
ቢሆን ኖሮ
ይሄ ቢኖር ኖሮ
ያኛው ቢቀር ኖሮ
ቢሆን ኖሮ
እንዲህ ሆኖ ቢሆን ኖሮ
እንዲያ ሆኖ ቢሆን ኖሮ
ኖሮ --- ኖሮ --- ኖሮ
ምን ትመስል ነበር ይሆን?
ዘንደሮ::

---- መገላገያው -----

ጨቅላው ከሆድ
እንዲያ ሲፈራገጥ
መውጫው ሰአት ቀርቦ
ይችን አለም ሊረግጥ
ሲቦርቅ ነበር ማየቱ
የወደፊት ምቱ
ፊትም ርግዛቱ
ግን ተቀደመና
ባጭሩ ተቀጠፈ
በመገላገያው
ከመሬት አረፈ::

ቸር ሰንብቱ በሌላ ግጥም እስክንገናኝ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests