ፍቅር እና ሌሎች ግጥሞች ማሰባሰቢያ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby yabanje » Tue Feb 07, 2006 11:49 am

ሚሚ
እኔን ለመጻፍ ያነሳሳኝ የአንቺ ግጥሞች ናቸው
ተባረኪ
ደህና ሁኚልኝ
yabanje
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Sat Jan 28, 2006 3:29 pm
Location: turky

ሰላም

Postby ነገርኩ/ዋ » Tue Feb 07, 2006 2:18 pm

ሚሚዋ ሰላም እንዴት ነሽ አንዳንዴም ሆነ በየጊዜው ሰውን በስሪው ታወድሽዋለሽ አይደል ደግሞ ይህ ቀን ደግሞ አንቺ ሊላ ከአሁን የበለጠ እንድትሰሪ የማወደሺዪ ቀን ነው

ላወድስሽ

ላወድስሽ በስሪሽ
በጣም ያምራል ጥበብሽ
ሚሚ ሰውን ትመክሪያለሽ
እርሱ ማስተዋልን ይጨምርልሽ
በጣም እኔን ማርከውኛል
ግጥሞችሽ መስታወቴ ሆነውኛል
በዚው ቀጥይ አድንቂያለው
ነገርኩሽ/ዋ ብየሻለው
ሰላም ሁኑ
ቸር ያሰማን
Last edited by ነገርኩ/ዋ on Wed Feb 08, 2006 3:37 pm, edited 1 time in total.
ነገርኩ/ዋ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 53
Joined: Thu May 26, 2005 4:53 pm
Location: egypt

Postby ሚሚlove » Tue Feb 07, 2006 3:35 pm

yabanje, ነገርኩ /ዋ ስለ አስተያየታችሁ አመሰግናለሁ ዛሬም ለወደፊቱም አስተያየታችሁ አይለየኝ እያልኩ አንድ ግጥም በመላክ የዛሬውን ፅሁፊን በዚሁ አበቃለሁ
----- ነወና ያንጊዜ -----

ቁረሽኝ ከስጋሽ
አውጂኝ ከደምሽ
አፅኚኝ ከአጥንትሽ
ቀምሪኝ ከሴልሽ
እናት አንቺ ሁኚኝ
ልባል እኔም ልጅሽ
ነውና ያንጊዜ ከልብ የማምንሽ
ፍቅሬን ፍቅር የምለው ባንቺ የምታመነው
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Thu Feb 09, 2006 8:44 am

-------ፍርዱን ለናንተ---------

በአንድ ተወስኜ
ለፍቅር ታምኜ
ስኖር ተቆጥቤ
ራሴን ጠብቤ
ፋራ ነህ ይሉኛል
እንዴት ይሻለኛል
እባካችሁ ሰዎች
ከዝሙት አሪፎች
ማነው አራዳ?
በመወሰኔ ሳልጎዳ
ፀፀት ወይ ሳልገጋ ዕዳ
ኸረ ፋራውስ ማነው?
አልጋ ላይ የተጋደመው
ፍርዱን ለናንተው
ለአራዶች ልተው
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Sat Feb 11, 2006 1:33 pm

ወይኔ ቤቴ ተረሳህ አንድ ቀን

----ውበትን ማን ፈጠረ----

ባንድ ቅድስ ሌሊት
የፍቅርን አምላክ ቀርቤ አይሁት
እሱም ጠጋ አለ
እንዲህ ሲል ጠየቅሁት
እባክህ ጌታዬ
አይነ ከብላላዋን
ዳሌዋ የኮራ
አፍንጫ ሰልካካ
ትንቡክዬ ገላ
.
.
.
.
ቀና ብዬ ባየው
እሱ በዚያ የለም
በጣም ተናደድኩኝ
እንቅልፍ ደግ ነገር
ደግሞ አሽለብኩኝ::
ጥቂት እንደተኛሁ
ተመልሶ መጣ
ከንቅልፌ ነቃሁኝ::
እሱም አየኝና
ቁልቁል አየኝና
አየኝ አየኝና
ምንም ሳይናገር
ተመልሶ ሄደ
ደግሞ ተሰደደ
አየሩ ድምፅ ሆነ
"ውበትን ማን ፈጠረ"
አይን አይደለምን!
አይንስ የማን ነው
የልብ አይደለምን!
ልብንስ ማን አዘዘ
ፍቅር አይደለምን!
ውበትስ ምንድነው
ማፍቀር አይደለምን . . . . ን. ን . ን "
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Mon Feb 13, 2006 8:05 am

---ከኔው ጋር ንዝንዝ ---

እኔው በራሴ አፍ

ይሆናል አይሆንም

ሀሳቦቼን ሳርም

ሀሳቦቼን ሳፈርስ

ሀሳቤን ስወቅስ

እኔው ሁለት ሆኜ

አንደኛውም ሳሞኝ

እርፍድ ይላል ጧቱም

ይመሻል ቀኑም

ለሊቱም ይነጋል

ምንም ምንም ሳልል

እራስን ሳልዳኘው

ነገ መጣ ሌላኛው
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby Jossy1 » Mon Feb 13, 2006 8:40 am

ሚሚlove wrote:---ከኔው ጋር ንዝንዝ ---

........
ሀሳቦቼን ሳርም
ሀሳቦቼን ሳፈርስ
ሀሳቤን ስወቅስ
እኔው ሁለት ሆኜ
አንደኛውም ሳሞኝ
እርፍድ ይላል ጧቱም
ይመሻል ቀኑም
ለሊቱም ይነጋል
ምንም ምንም ሳልል
እራስን ሳልዳኘው
ነገ መጣ ሌላኛው


በጣም ቆንጆ መልእክት ይዟል:: ይሄን ችሎታሽን የት ደብቀሽ ነው ሚሚሾ???
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby ሚሚlove » Mon Feb 13, 2006 1:56 pm

Jossy1 ከልብ አመሰግናለሁ ሰለ አስተያየትህ

----የማታ እንጀራ ስጠኝ----

የማታ እንጀራ ስጠኝ
የጠዋት አታስመርጠኝ
ዘግይተህ በኌላ አስጊጠኝ
ማታ በክብሬ ደብቀኝ
ከሰው በር አንተው አርቀኝ

ጉልበቴ ፀናቱን ይዞ
አቅሜም እንደ አቅሙ ተጉዞ
ያልጠየቀኝን ሳልመልስ
መንገዴን በወግ ልጨርስ

ለአይን እሳት አታስገርፈኝ
ማታ ማታ አመሻሹን ደግፈኝ
በጥላ እንዳልበረግግ
በረፋድ እንዳላጣ ጥግ

አልጠብቅ እርጥባን ከሰው
የማታ ምግቤን አርሰው

እንደ ንጋት ጠብቀኝ
አንገቴ እንዳለ ቀና
የወዳጅ ደጃፍ ሳልጠና
ዘራፍ እንዳልኩኝ አብቃኝ
ሲጨልም መንገድ አቅናልኝ
አደራ!
አደራ ጌታዬ አደራ
አትንሳኝ የማታ እንጀራ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Tue Feb 14, 2006 10:23 am

--- እናቴ ---

ሞትሽን አምኜ

መርዶ ብቀመጥ

በሰው ተከብቤ

አንገቴን ብደፋ

አምናና ካቻምናው

ትናንት እየሆነብኝ

ሳልሞት አልገልሽም

ልረሳሽ አቅተኝ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Tue Feb 14, 2006 3:15 pm

---- የህልም ደራሲ ----

አንቺ ልጅ
ስስምሽ ስላደርኩ ትላንት በህልሜ
ዛሬ ቶሎተኛሁ ልስምሽ ደግሜ
ታድያ ምን ያደረጋል የህልሜን
ደራሲ አትደሰት ሲለኝ ህልሜን
ገለባብጦ ስስሚኝ አሳየኝ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

ቕቕቕቕቕ

Postby ሳምሶን13 » Wed Feb 15, 2006 1:01 pm

Image

Image

Image
ሳምሶን13
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Wed Sep 15, 2004 3:48 pm
Location: sudan

Postby ሚሚlove » Wed Feb 15, 2006 4:12 pm

ሳምሶን 13 ወድ ያገር ልጅ ለመሆኑ በስህተት መሰለኝ ይህን ፖስት ያደረከው ባልሳሳት ለማደረግ የፈለከው ጃንሆን ቤት ወስጥ ይመስለኛል:: ለማንኛውም ከት አድርገውና ወስደህ እዛ ፔስት አድርገው እገረ መንገዴን አንብቤዋለሁ በጣም ነው የሚያስቀው ለካስ ብዙ ነገር ታውቃለህ እስኪ ሁል ግዜ እንዲህ ጀባ በለን!

አክባሪህ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Wed Feb 15, 2006 4:15 pm

--- በቃ -----

መቼም ሟች ነኝና
ስገባ ካፈሩ
ትንሽዬም ብትሆን
ሐውልት ብትስሩ
"የርሱ ነገር ቀረ
በቃ ተከተተ"
ብላችሁ ፃፉልኝ
"ሳይመቸው ኖሮ
ሳይመቸው ሞተ". . .
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

ሲደርስ የሚገባ

Postby ቡናማ » Thu Feb 16, 2006 12:30 pm

ሰላም ሚሚሻ::ዛሬም ከዚህ መጣሁ::

ሲደርስ የሚገባ

ጉንፋን ቢጤ አሞኝ ቢያደርገኝ ለንቁዋሣ
አንድና ሁለት ቀን ዋልኩኝ ሳልነሳ::
ለጎኔ የቀረበኝ አልጋው ተመችቶ
ስንፍና "ወዳጄ"ም አይሎ በርትቶ
መታከት መቅኒዬን ከጉልበቴ ጨምቆ
ርሀብ እያመሠኝ ወደአንጀቴ ዘልቆ
ህልምና ቅዠቴ በምግብ ታጭቆ
መብል እየጎመዠሁ በጠኔ ውስጥ ሁኜ
የራሴው ሆድ ጩሆ ነቃሁኝ ባንኜ::
እናት ንፉግ ብትሆን አለ አንድ ወቀሳ
እህት ብትከለክል አለ አንድ ወቀሳ
ሰው ራሱን ሲያስርብ ምን ይሉታል እሳ!?
ሰራተኛ ብትሰንፍ
ሚስት ሙያ አልባ ብትሆን - 'ሚለው ሰው አያጣ
ሰው ራሱን ሲበድል የሚያስጥል ኬት ይምጣ!?

ከህመም የሚፈውስ ምግብ ብቻ መስሎ በታሰበኝ ጥር 4,2005 የተፃፈ

በወዳጅነት እንቀጥል
ቡናማ
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

Postby ቡናማ » Thu Feb 16, 2006 12:44 pm

ሰላም ሚሚ::
ይህን ልልሽ መጣሁ...
Last edited by ቡናማ on Thu Feb 23, 2006 2:24 pm, edited 1 time in total.
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests