ፍቅር እና ሌሎች ግጥሞች ማሰባሰቢያ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ቡናማ » Thu Feb 16, 2006 12:50 pm

--- እናቴ ---

ሞትሽን አምኜ
መርዶ ብቀመጥ
በሰው ተከብቤ
አንገቴን ብደፋ
አምናና ካቻምናው
ትናንት እየሆነብኝ
ሳልሞት አልገልሽም
ልረሳሽ አቅተኝ
------------------------------------

ሚሚ

የእናትን ነገር ብታነሺ ልቤ መንቦጫቦጭ ቢጤ ጀመረና ቢቀለኝ ብዬ እቺን ልል ተመልሼ መጣሁ ::

-----እማዬ---

"ልጅ ቢደርስ ቤት ይፈርስ" - ተረት ነው ሽሙጫ
ትልቅሽን ላድግ ነው ያስዳህሽኝ ለሩጫ::

ነሐሴ 20,1991 አ .አ

የፅህፈት ቀለም መረጣ ስንጎዳጎድ መልእክቴ ሳላጠናቅቀው ሾልኮ ተልኮብኝ ነው::ይቅርታ እንግዲህ

በወዳጅነት እንቀጥል
ቡናማ
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

Postby ሚሚlove » Fri Feb 17, 2006 12:54 pm

ቡናማ ወድ ብሮ ስለ አስተያየትህ ከልብ አመሰግናለሁ ያልምድህ

---- አበሻኛ ---

እንደ አምላክ ካሌንደር
እንደሱ መትሮ
የቀኑ ርዝመት
በምዕተ አመት ቆጥሮ
ጅብዱ መስራት ይሆን
የአበሻ ቀጠሮ . . .?

ከብዙ መወደድ ጋር
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ብልግና? » Fri Feb 17, 2006 3:49 pm

ሚሚ ሚሚሻ
የቄራ ዉሻ
አናት አናቱዋን
በመደቆሻ
በመደቆሻ
በመደቆሻ
ብልግና?
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 649
Joined: Fri Feb 03, 2006 6:51 am

Postby ሚሚlove » Mon Feb 20, 2006 11:21 am

ብልግና ? ወድ ያገር ልጅ ይህን ያክል አማርሬሀለሁ እንዴት ምን አደርጌህ ይሆን እንዲህ ያልከኝ ለማንኛውም እኔ ግን ምክንያቱም ስላልገባኝ ነገርን ነገር ይፈታዋል ብያለሁ:: ለማንኛውም ሙዚቃ ወደበኌላ እጋብዝሀለሁ . . .

--- ይታየኝ ነበር ---
ቅናት ዕድገት ቢሆን
ችግር ቢያስወግድ
ሐሜት ጥሩ ሆኖ
ሰዎችን ቢያዋድድ
ክፋት ደስታ ሆኖ
ሐብትን ቢያጎናፅፍ
ጉራ ተግባር ሆኖ ሀገር ቢለማ
ውሽት እውነት ሆኖ
ጩኽት ቢያስተጋባ
ጭቅጭቅ ጦርነት
ቢተኩ በስላም
እንዴት ያለ ነበር
ሕይወት በዚህች አለም
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ብልግና? » Mon Feb 20, 2006 11:35 am

ሚሚlove wrote:ብልግና ? ወድ ያገር ልጅ ይህን ያክል አማርሬሀለሁ እንዴት ምን አደርጌህ ይሆን እንዲህ ያልከኝ ለማንኛውም እኔ ግን ምክንያቱም ስላልገባኝ ነገርን ነገር ይፈታዋል ብያለሁ:: ለማንኛውም ሙዚቃ ወደበኌላ እጋብዝሀለሁ . . .


ይሄ ነገር ፍለጋ ይመስላል:: እረ እኔ ሚሚLove አላልኩም እንዴት በየትኛዉ ወሰን ተገናኝተን አማርርሻለሁ::አንድ ቻት ሩም በስድብ የምትነቁረኝ ግማሽ ሞክሼሽ አለች ለሱዋ ነበረ የተኮስኩት ለካ ሌላ አቁስያለሁ- ጥይቱ የሚያቆስል ከሆነ::
ብልግና?
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 649
Joined: Fri Feb 03, 2006 6:51 am

ለሚሚ

Postby ቡናማ » Mon Feb 20, 2006 2:14 pm

ሰላም ሚሚሻ::ቡናማ ነኝ

ይህችን ግጥም ስላንቺ ላንቺ ሰድጃታለሁ...

Blackberry Sweet
----------------
Black girl black girl
Lips as curved as cherries
full as grape bunches
sweet as blackberries

Black girl black girl
when you walk you are
magic as a rising bird
or a falling star

Black girl black girl
what's your spell to make
the heart in my breast
Jump stop shake

በወዳጅነት እንቀጥል
ቡናማ :wink:
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

Postby ሚሚlove » Wed Feb 22, 2006 9:34 am

ወድ ቡናማ መጀመሪያ ላይ እቤቴ መጥተህ ይህን ቃል ስትናገር ግራ ገብቶኝ ነው:: ለኔ ካልሆነ ግን አሁን ሀሳቤን አንስቻለሁ ጥይቱም በኔ ላይ ምንም ነገር አላደረሰም
ወድ ቡናማ ከልብ አመስግናለሁ:: ያልምድህ

---- ሽበት ተናፈቀ ----

በግዜው በወቅቱ
የመጣውን ነገር
መቀበል ተስኖን
እንዲያ ስንሸበር
መስተዋት ሰር ቆመን
ተፋጠን ከራስ ጋር
ነጭ በማየታችን
ውስጥ አንጀታችን ሲያር
ነጭ እንዳልነቀልን
ከጥቁር መካከል
እንዳላፈርንበት
እንዳልተቀባን ከል
ሰው ማርጀት አቅቶ
ለማርጀት ጊዜ አጥቶ
ሽበት ተናፈቀ
የሚሸብት ጠፍቶ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Wed Feb 22, 2006 3:27 pm

---- መልሶ ላይቀዳው ----

ውበት ሲደበዝዝ
ሰው ሲከዳ
የራሴ ነው ያሉት
ስጋ ሲሆን ባዳ
ደጅም ይናፍቃል
ስቀሩ ከጓዳ
ኑዛዜ የለውም
ያልተበላ እዳ
ሰው ራሱ ባመጣው
አካሉን ከጎዳው
ምንድነው ቁንጅናው
የውበት ፋይዳው
እንደ ደፉት ዉሀ
መልሶ ላይቀዳው
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሳምሶን13 » Wed Feb 22, 2006 5:35 pm

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
Image
ሳምሶን13
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Wed Sep 15, 2004 3:48 pm
Location: sudan

Postby ሚሚlove » Thu Feb 23, 2006 8:09 am

ወድ ሳምሶን የላከው ግጥም ግማሽ ድረሰ አንበብኩት ነገር ግን ሁሉንም ለማንበብ አልቻልኩም ምክንያቱም ሊከፍትልኝ አልቻለም ለማንኛውም ሰለተሳትፎህ አመስግናለሁ በርታ::


ጦጣ አህያ ጋልባ.....
በጠጠር በታኝ መተተኛ በኮኮብ ቆጣሪ ታጅባ!
መሰስ ብላ መዲናችን ስትገባ.....
የዘረኝነት ተስቦዋን...በሽትዋን ልታጋባ
በለሆሳስ በጉምጉምታ - ድጋፍ አይሉት ነቀፌታ
በቃል አልባ የሩቅ ትዝብት ... በምን አገባኝ ዝምታ
እንደ አይናፋር ልጃገረድ..... እያየናት በጨረፍታ
በማእዘናቱ ቅርንጫፍ .... እዋርካችን ላይ ሰፈረች
ልሳናችንን ሸንሽና ..... ዘር ተዘር ደም እያቃባች
የጫካዋን ጭቅቅትዋን --- እላያችን አራገፈች
በጨለምተኛ እጀ ሰብ -- በወኔ አመንምኔ ደቀን.
ለዚህ ባበቃን በሽታ -- በለዘብተኝነት ነሁልለን
ከ13 አመታት በኋላ -- እንሆ ዛሬ እኛም አለን
የውሾቹ ጩህት ዋይታ _ ለአፍታ ከጉዞ እንደማይገታው
እንደ ግመሎቹ አረሆ -- በርሃውን እንደሚያርሰው
እንሆ ጦጢት በዋርካችን....ዛሬም እንዳሻት ትዋባለች
የሰራዊቱ ግርማ ሞገስ -- ተረት ተረት ነው ትለናለች
ይህንን ጥግ _ ከዚያ ጥጋግ- አቆላልፋ አነቃቅፋ
በወፍ ዘራሽ - መረን ሃረግ- እንዳይፈታ- አጠላልፋ
ህያው ገድላ በድን አቅፋ፣ ሺ ቅራኔዎችን ቀፍቅፋ
የግዙፉን ዋርካ ሞገስ .... እንደ አዳል በግ ቆዳ ገፋ
ከወዲህ ጫፍ ተወርውራ..... እውዲያኛው ላይ ተስባ
የዘር ሃረጉን ግማጅ ጫፍ .... በየቅርንጫ ላይ መርባ
ይህንን ጥግ...ከዚያ ጥጋግ... አቆላልፋ ...አነቃቅፋ
በወፍ ዘራሽ - መረን ሃረግ.... እንዳይፈታ- አጠላልፋ
እንደ ሙሽሮች ...ክንድ ትሥር ...እንደ ተላላፊው ጉርሻ
አንዱን ካንዱ እያቋለፈች በተብታቢ በኪሮሻ......
ይገታኝ ዘንድ የሚቻለው - ሃያል የለም ትለናለች
እንደ ግመሎቹ አረሆ -- ጦጢት ዛሬም ትዋባለች ...
ይታክተን ካልሆነማ የግፍ አመታትን መቁጠር
አንድ ብለን እንደ ጀመርን ሌላም ሌላም ....መጨማመር
እንደ ጦጢት ትብትብ ሃረግ እለት በለት እንደሚያድገው
አሃዝማ ይቀጥላል ...ይብላኝ እንጂ ለቆጣሪው....
እድሜውማ አብሮ ይንራል...ይጭንቀው እንጂ ለኗሪው
የውሾቹ ጩህት ዋይታ _ ለአፍታ ከጉዞ እንደማይገታው
እንደ ግመሎቹ አረሆ -- በርሃውን እንደሚያርሰው
እንሆ ጦጢት በዋርካችን....ዛሬም እንዳሻት ትዋባለች
የሰራዊቱ ግርማ ሞገስ -- ተረት ተረት ነው ትለናለች
ከዚህ ቅርንጫፍ ተወርውራ እወዲያኛው ትተማለች....
ይገታኝ ዘንድ የሚቻለው - ሃያል የለም ትለናለች
ጦጢትን አይነት መሰሪ በዋርካችን መረን ለቀን
የአንበሳውን ግሳት እንጂ የክርኑን ሃይል ባያድለን
በዚህች በመናኛ እንስሳ.....መነዳቱ ሳይታክተን
ከ 13 አመታት በኋላ መኖር ካልነው ዛሬም አለን
የውሾቹ ጩህት ዋይታ _ ለአፍታ ከጉዞ እንደማይገታው
እንደ ግመሎቹ አረሆ -- በርሃውን እንደሚያርሰው
እንሆ ጦጢት በዋርካችን....ዛሬም እንዳሻት ትዋባለች
የሰራዊቱ ግርማ ሞገስ -- ተረት ተረት ነው ትለናለች
ከዚህ ቅርንጫፍ ተወርውራ እወዲያኛው ትተማለች....
እንሆ ጦጢት ዛሬም አለች......
በሳ/አ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby እንደፈከደ » Sat Feb 25, 2006 4:26 am

ሚሚ love የግጥምሽ መልዕክቶች ደስ ይሉኛል እና እኔም ልሞክር::

መች አጣነው ብለሽ ጦጢት መሰልጠኗን
ከዛ ክፉው አውሬ ከእባብ መወገኗን
እውነት ነው አይተናል አገር መመረዙን
ወዲህ ተሽሎክሉኮ ወዲያ መተንኮሉን

ያገሳው አንበሳ ክርኑን ምናገኘው
እባክሽ እህቴ ግቢና ነካኪው

አንበሳ ሲተኛ ቢሆን ነው ነገሩ
ፍርድ መገምደሉ በሀገር በመንደሩ

መልካም ቀን::
እንደፈከደ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 110
Joined: Mon Jan 09, 2006 12:37 am
Location: USA

Postby ሚሚlove » Tue Feb 28, 2006 3:37 pm

እንደፈከደ አመስግናለሁ አትጥፋ ስራ ስለበዛብኝ ነው እሺ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Wed Mar 01, 2006 8:27 am

----ድንቄም ተወሰኑ!----

ትናንት ከእንትና
ሌላ ቀን ነውና
በጣም የሚደላ
በቃ አዲስ ገላ
አንድ ለአንድ ተወሰን
ብሎኛል ዘመኑ
አዲስ በየቀኑ
"አንድ ለአንድ ሆነ
ድንቄም ተወሰኑ"
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Fri Mar 03, 2006 4:18 pm

----ቀላል ወርቅ ----

ቀለበት ነበረኝ
ቃልኪዳን ቋጠሮ
ቀለበት ስፈታ
ከዳኑ ተሰብሮ
ጨዋታው ፈራርሶ
ዳቦው ተቆራርሶ . . . .
ከጣቴ ሳወጣው
አተኩሬ ባየው
ወርቅ አልመስልህ አለኝ . . . .
ለካስ ቃሉ ኖሯል?
በውበት ያስጌጠኝ
ክብር ያላበሰኝ
ማዕረግ የነበረኝ
ቃል ሲቀር
ሲሰበር
ወርቅነቱ ቀለለኝ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Sat Mar 04, 2006 12:34 pm

---- ፍቅር አመረረ -----

ፍቅር ኮበለለ . . . የገባበት እንጃ
ውሸትና ክህደት
ቅናት ከጅልነት
ባጫሩት መነሻ

ፍቅር ሸፈት አሉ . . . በደንቆሮ ዋሻ
አልልፈሰፈስም
አልንገላታም
አልገብዝ ብሎ ንቆ የእጅ መንሻ

አፈረሳታ ውጡ!
ፍቅር እኮ ከዳ . . . ሕይወት ኮሰኮሰ
ሲጠቃቀሱበት
ሲፈታተሉበት
ሲንዱት . . . ሲያፈርሱት
ስሙን ሲፍቁት . . . ሰርዘው ደልዘው

ነፈፋ እንጂ ፍቅር . . . ከፍቶት ተሰደደ
አጋድመው ሲግጡት
አንጋለው ሲድጡት
ቀስተው ሲያጎብጡት
አልተጥመለመለ . . . አላጎበደደ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests