ፍቅር እና ሌሎች ግጥሞች ማሰባሰቢያ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሚሚlove » Mon Mar 06, 2006 2:18 pm

----ጥላዬ ----

የቀደመው ቀር
ጀማሪው ፊተኛ
ፊተኛው ከኌላ
የኌላው አንደኛ
ያልዘቀጠው ወጣ
የወጣው ዘቀጠ:: . . . .

ፊት የወጣች ፀሀይ
በ - ምዕራብ ሰማይ
መጥለቂያው በር ላይ::
አዲሷ ከምስራቅ
በንጋት አልፋ ላይ
በማለዳ ርከን ላይ::
እርከኑ እስቲሰበር
በጭለማ በትር::

የቀደመው ሲቀር
የወጣው ሲዘቅጥ
ምዕራብ ሲጠልቅበት
ጎሕ ሲቀድ ለምስራቅ . . . .
እነሱን ሲታዘብ . . . . በወጣ - ዘቀጠ
ከገቡበት መቅረት
ከወጡበት መግባት
እንዴት ባመለጠ!?
ጥላዬ


ከወንድሙ አሊ የተወሰድ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Tue Mar 07, 2006 12:47 pm

---- ህሊና ሲናገር ----

አልቅሰሻል አሉኝ
እርርን
ድብንን::

ስለምን አለቀሽ!?
አልቆረጥሽም እንዴ? . . . .
እንባ ማቆሚያ አለው
የቆረጡ ለታ
አለሁኝ እንጂ እኔ
አልቅሼው አይወጣ
ሞቼው አይረታ::

ነፍስ ገዳይ እኔ
አንቺ ምን ሆንሽና
እኔው ለኔ ላልቅስ
እሹሩሩ ቢሉት
አይተኛ ህሊና ::

ከወንድዬ አሊ የተወሰድ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

ካነበብኩት

Postby ሚሚlove » Wed Mar 08, 2006 1:38 pm

----- ስንት ይሆን ቁጥራቸው -----

ምን አሉ? ይላሉ
ሌሎች ምንም ሳይሉ
እነሱ ነገሩን
እየፈለፈሉ
ፈልፍለው ነገሩን
ከወጡ በኌላ
እንዲህ አሉ ብለው
ሌሎቹን በመላ
ስም ይሰጧቸዋል
በሀገሩ በሞላ
ምን አሉ? የሚሉት
ሰው ያላወቀላቸው
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Wed Mar 08, 2006 2:29 pm

----- አንድ ፀሀይ ----

ጊዜው እየጠበቀ!
ከዋክብት ከሰማይ ሲረግፉ
የኔ እንባ በግርድፍ በግርፍፉ
ዱብ ዱብ ይል ነበር::
ጊዜ እየጠበቀ!
የተለኮሱ ረጃጅም ሻማዎች ሲጠፉ
የሀዘን ጋቢ አጣፊዎቼ
ከእየዬ ጋር እባጃለሁ::
ቢስ እያየብኝ
የሎስ እያንዣበበ
የልቤ . . መቃብር እቆፍራለሁ
ልቤን ምሼ ልቤ አፈር ውስጥ
ሰውንያክል እቀብራለሁ
ከዋክብትን እቀብራለሁ
ሽማዎቼ እቀብራለሁ::
ዛሬ ግን! ልቤ በሀዘን ጠበበ
እንባ ጅራቱም ወግ አጣ
ዛሬ ግን! ከጨረቃ የላቀ
ዛሬ ግን! ከእልፍ ከዋክብት የደመቀ
ዛሬ ግን! እንደ ፀሀይ ቢኖር ጠለቀ

ለሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን (ከአንዷአለም አባተ)
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Sat Mar 11, 2006 6:24 am

---- ሞት ----

የህይወት አጥር ድንበር
ለሁሉም የማይቀር ነገር
ሞት!
ከዚያ ከሳቁ አዳራሽ . . . ታድሜ
በደናግል ልቤ . . . . ታምሜ
ሀብቴን ብፋልገው
ሳቁን ፅልመት ወረሰው
ሳቅ ከእንባ ተዛመዶ
ሳይገኙ ተዋዶ
ሀብቴም ካፈሩ ባጆ
ወዳጁን ጥሎ ደረጀ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

ግሩም

Postby መቆያ » Tue Mar 14, 2006 4:58 pm

ዋው ግትሞችሽን እጅግ ወድጃቸዋለሁ
seek for good...........
መቆያ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Fri Feb 17, 2006 5:07 pm
Location: aa

Postby ሽብርተኛ » Tue Mar 14, 2006 5:36 pm

Image
Image
Image
ሽብርተኛ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 21
Joined: Fri Mar 03, 2006 2:17 pm
Location: Norge

Postby ሽብርተኛ » Tue Mar 14, 2006 5:37 pm

Image
Image
Image
ሽብርተኛ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 21
Joined: Fri Mar 03, 2006 2:17 pm
Location: Norge

እኔ አይን የለኝም

Postby እሪኩም » Sun Mar 19, 2006 10:13 am

ሠላም!

እኔ አይን የለኝም ወይንም ልብ:
እንደው ነካ ነካ ላንጠጋገብ::

ምንሸር የለሽም ጥይት ተሸካሚ:
እኔን ላታገኚን ተይ አንቺ አትድከሚ:: ----:-))))
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby ሚሚlove » Mon Mar 20, 2006 2:32 pm

ወድ እሪኩም ስላምታህን ተቀብያለሁ ባለህበት ሰላም ይብዛልህ እላለሁ:: ለመሆኑ የፃፍካት ነገር ሰምና ወርቅ ትመስላለች ለማንኛውም እስኪ እዚህ ጋር ግልፅ አድርገው::

ምንሸር የለሽም ጥይት ተሸካሚ :
እኔን ላታገኚን ተይ አንቺ አትድከሚ


እስኪ አንድ ግጥም አከል ላድርግ

------ምን ያሳርርሀል------

ምናለቢቀናው ትልቅ ቦታ በደርስ
ምን አንገበገበህ ከንፈርህን ለምን ነከስክ
ባርነቱን ትቶ ራሱን ከቻለ
በወዙ ከበላ ልመናን ከጣለ
እግዚአብሔርም ከረዳው ስኬትን ከሰጠው
ምን ያሳርርሀል ደክሞ ነው የበላው
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Tue Mar 21, 2006 5:52 am

---- መለኮቴ ----

ሰፈር ሳለሁ ድሮ
ያው የአገሬ ኑሮ
ይታወቅ ነበር
ትልቁ ሚስጥር
በጥቃቅን ነገር
አምልኮት ሲዘከር
ጋራ ቦስት ሲሉት
ሲያሰኘው ጎፍታ ኮት
በደመራ በአል
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Wed Mar 22, 2006 6:11 am

------ፍቅር ደግ ነበር ------

ተዋደው ሲለዩ
አንጀት ባያሳርር
የግር እሳት ሆኖ
ልብ ባያሻክር
የራስ ላልሆነ ሰው
መቁረጥን ቢያስተምር
ፍቅር ደግ ነበር
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ማህቡብ » Wed Mar 22, 2006 6:27 am

ሠላም ሚሚዬ !

እኖር ብዬ :
ብኖር ታድዬ !
ያውም እሰዬ :
አዋዬ ጋር ውዬ !

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ሚሚlove » Wed Mar 22, 2006 9:26 am

ወድ ማህበሩ ለዚህ ግጥምህ ከልብ የሆነ ጭብጨባዬ ካለህበት ይደረሰህ እያልኩ ከገባሁ ላይቀር አንድ ብዬ ልብውጣ

----- እንግዳ ----

እንዳ ነኝ አልኩኝ
እንግድነታቸው
እንግዳ ሆኖብኝ
እንግዳ አይደለሁም
እኔስ ቤተኛ ነኝ
የእነርሱ እንግድነት
እንግዳ አደረገኝ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Thu Mar 23, 2006 6:29 am

------ ፍቅር ------

ፍቅርማ ጥላ ነው
እንዴት ትከትለው
እንዴት ትጮኽለት
ኮቴው አይሰማም
ከአይናችን ሲሰወር
በፈረስ ፍጥነት::
ሺግዜ ፍቅር ይዞት
ሺግዜ የተሰቃየ
ሺግዜ የተሻለ ነው
አንዳች ፍቅር ካላየ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests

cron