ፍቅር እና ሌሎች ግጥሞች ማሰባሰቢያ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሾተል » Tue May 15, 2007 3:48 pm

ልጠራ በስምሽ
እቃቃ ብለን አፈር ያቦካነው
ሳር ቅጠል አንጥፈን አብረን የተኛነው
በልጅነት ለዛ ሁሉን ያሳለፍነው
ዛሬም ውስጤ አለ መቼ እረሳዋለው?
ያን ጊዜ ነበረ ያኖርኩሽ በልቤ
ገና ጨቅላ ሳለሁ የመረጠሽ ቀልቤ::
እንደወይን ተተክሎ ያጎመራው ፍቅርሽ
ባንቺ ውስጥ ይኖራል ይረዳዋልብሽ
ዛሬም አትራቂን ልጠራ በስምሽ


ውዱዋ ሚሚ ሎቭ

የግጥም ስብስብ ቤትሽን ገና ዛሬ ነው ያየሁትና ገና ከመጀመርያው ማንበብ ስጀምር ወደታች እንደወረድኩ ከላይ ያጣቀስኩትን ግጥም አየሁትና ልቤ ደነገጠ::ለሚን በዪኝ?

የልጅነት ፍቅሬ የድሮዋ ማለት ነው አጋጣሚ የፍቅር ቀስቃሽ ደብዳቤ ባለፈው ጥቅምት አካባቢ ጽፋልግን ነበር ታድያ ጽሁፉ በዚህ ግጥም ነው የሚጀምረው......ታድያ ሎኬሽንሽን ሳየው ከኢትዮዽያ ይላል እንዴ እራስዋ የድሮዋ ነች እንዴ ብዬ ልቤ ድንግጥ አለ...እረ ማነሽ..

እግዚአብሄር ምስክሬ ነው የእውነቴን ነው የምልሽ.....አንቺ እሱዋ ካልሆንሽ ይሄ ግጥም እንዴት በእጁዋ ገባ?ዘፈን ሆኖ ወጥቶ ነበር ወይስ......

መልስሽን በጉጉት እጠብቃለሁ....

እሱዋ አንቺ ከሆንሽ የምህጻረ ቃሉ ይሄ ነው...y.b

ግጥምሽን ተወጥቼው የምለው ይኖረኛል...

አንዳንዴም የአቅሜን እቸራለሁ..


ካክብሮት ጋ


ሾተል.......y.b ከርቀት ሆኜ ትዝ አልሽኝ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሚሚlove » Mon Jun 04, 2007 10:11 am

ሰላምታዬ ከያላችሁበት ይድረሳችሁ እላለሁ. . . . .
ሾተል በቅድሚያ እንኳን ድህና መጣህ እላለሁ:: ስለ አስተያየትህ ከልብ አመሰግናለሁ::

ውድ ሾተል ከታች ያጣቀስካት ልጅ አለመሆኔን ላረጋግጥልህ እውዳለሁ:: መልሴ በመዘግየቱ ግን በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ ሁኔታዎች ስላልተመቻቸልኝ ነው::

እስኪ ለዛሬ ከገባይ ላይቀር አንድ ብዬ ልውጣ

~~~~~~ ሰርቶ ስለማግኘት ~~~~~~

"እውቀትና ገንዝብ ከተያዘ በእጅ
ድንጋይ መልክ ያወጣል እንኳን የሰው ልጅ::"
"ድህነት እብድ አይደለም ዘሎ ሰው አያንቅ
ሰነፍ ሰው ካገኘ አያነቃንቅ::'
ማጣት ጠገበና ወጣቱን ሰደበው
ለማግኘት ነግሬ ሳላስደበድበው::'
"አባቴ ትልቅ ነው ይላል የሰው ሞኝ
ትንሹም ትልቅ ነው እንጀራ ሲያገኝ::'

ቸር ስንብቱ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ደምስሰው » Thu Jun 07, 2007 7:55 pm

ዋው ሚሚ....tres tres bien.,......አድናቂሽ ነኝ.......
እስቲ እኔም ትላንት ማታ የጫርኩትን ላስነብባቹ.

ውርስ እንከ መፍረስ

በጭፍን ጥላቻ.......በኩራት ተራራ
ባትመድቢኝም.... እኔን ከሰው ተርታ
አስረክቤሻለው...የልቤን ትርታ

ጌጥም አላፊ ነው....ብርም አላፊ ነው.
መላ አካላቴን ግን...ላንቺ አወርስሻለው.

ጎፈሬዬን እንኪ....የኔው ግን ይመለጥ
ይሄ ዞማ ጸጉርሽ....ይበልጥ እንዲያምርበት....

ፍቅርሽ አሰቃይቶት...ማዲያት ከሚያወጣ
ጉንጬንም ውሰጅው...ለኔ የለውም ሚና

ጆሮዬም ይከተል......ስላመረው ጤና
]ያለፍቅርሽ ዜማ...ደንቆሮ ነውና

ጥርሴንም ውሰጅው....አይጠቅመኝም በውነት
ስቆ አያቅምና ....አንቺ የሌለሽበት

ልቤን እንዳልሰጥሽ...ከሄደ ቆይቷል
አንቺን እያሰበ...አንቺን ሲል ይሞታል.

መለየት ካቃተሽ...የፍቅሬን ምንነት
እንኪ ኩላሊቴን...ልቤን አጣሪበት

እባክሽ ልእልት ሆይ...ይህንን ግን ስሚኝ
መላው አከላቴን.... ሰጠውሽ ሳይገደኝ
ሁሉን ውሰጅና...አይኔን ግን ተይልኝ
አንቺን ብቻ ማየት ....ስለሚያኖረኝ.... :!:

ዲ ቱ ዘ ኤም :arrow: ደምስሰው...
ይመቻቹ
ደምስሰው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 195
Joined: Fri Feb 23, 2007 1:00 am
Location: canada

Postby yammi » Fri Jun 08, 2007 12:12 am

ውድ ሚሚ love

የግጥም አምድሽን ከሚከታተሉት አንዷ ነኝ:: ዛሬ ግን ብቅ ያልኩት አስተያየት ለመስጠት ነው :: ብዙ ጊዜ ያንቺ ያልሆኑት ስራዎች ላይ የገጣሚውን ስም አብረሽ ብትጠቅሺ ሰው ግራ እንዳይጋባ ይረዳዋል ብዬ አስባለሁ:: ለምሳሌ ባትመጪም ቅጠሪኝ በሚል ርእስ ያሰፈርሽው ግጥም የቴዎድሮስ ጸጋዬ ግጥም መሆኑ አልተገለጸም........እንዲሁም ተቆርጧል:: ምናልባት የግጥሙ መቆረጥ ሙሉ መልእክቱን እንዳያስተላልፍ ያደረገዋል ለማለት ነው::

ደምስሰው

ግጥምህ ውብ ነው::ግን የ በእውቀቱ ስዩም ይስጥሽ የሚለው ግጥሙን ሙሉ ሀሳብ የያዘ ነው ..ከቃላቶቹ ልዩነት በስተቀር.. እና ከ.............ሀሳብ የተወሰደ ብለህ ብትጨምርበት ምን ይመስልሀል?

ያሚ
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ደምስሰው » Fri Jun 08, 2007 6:30 pm

ያሚ
ላስተያየትሽ አመሰግናለሁ....(let's assume ሴት ነሽ)
እውነቱን ለመናገር ግን......ምንጩ ከየት እንደሆነ አሁን ገና ነው ያወኩት.
አንዱ ጀለሴ ነው ""አንድን ሴት አካልህን ሁሉ ሰጠሀት አይንህን ብቻ እንድታስቀርልህ በግጥም ንገራት ያለኝ""
ከዚ በመነሳት.....ጋሽ ሀዲስ ፍቅር እስከ መቃብር እንዳሉት ሁሉ...እኔም ውርስ እስከ መፍረስ ብዬ የጻፍኩት..
ቢሆንም ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ.
besides ይቅርታ መጠየቅ ያስከብራል እንጂ ክብር አያስቀንስም........እናም በድጋሚ ይቅርታ!
ይመቻቹ
ደምስሰው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 195
Joined: Fri Feb 23, 2007 1:00 am
Location: canada

Postby ደምስሰው » Fri Jun 08, 2007 6:30 pm

ያሚ
ላስተያየትሽ አመሰግናለሁ....(let's assume ሴት ነሽ)
እውነቱን ለመናገር ግን......ምንጩ ከየት እንደሆነ አሁን ገና ነው ያወኩት.
አንዱ ጀለሴ ነው ""አንድን ሴት አካልህን ሁሉ ሰጠሀት አይንህን ብቻ እንድታስቀርልህ በግጥም ንገራት ያለኝ""
ከዚ በመነሳት.....ጋሽ ሀዲስ ፍቅር እስከ መቃብር እንዳሉት ሁሉ...እኔም ውርስ እስከ መፍረስ ብዬ የጻፍኩት..
ቢሆንም ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ.
besides ይቅርታ መጠየቅ ያስከብራል እንጂ ክብር አያስቀንስም........እናም በድጋሚ ይቅርታ!
ይመቻቹ
ደምስሰው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 195
Joined: Fri Feb 23, 2007 1:00 am
Location: canada

Postby ሶምራን » Thu Jun 21, 2007 9:54 am

በመከባበሩ በመደጋገፉ ብመተሳሰቡ
ለሁሉ የሚመች ኣራማጅ ቢክቡ
ያለፈን በፀፀት መጭን በቂም በቀል
ከመቀበል ይልቅ በይቅርታ ቢቅል
ተጣልቶ ከመቅረት ፍቅር ቢደላደል
ለራስ የወደዱት ማካፈሉ ቢቻል

ሶምራን
ሶምራን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Thu Mar 16, 2006 12:51 pm
Location: N/A

ምነው

Postby ዋኖስ » Thu Jun 21, 2007 4:48 pm

ምነው ማጣፊያው አጠረሕሳ ወዳጄ! ዝጋዉ እንጂ ስንኙን! ጥሩ ጂምር ነበረች!!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ቤቲ_13 » Sat Sep 22, 2007 6:33 pm

Imageሚሚዬ ምንም ብትጠፊም ስራሽ ዉስጤ ነዉና በመዘግየት ግን ባለመቅረት ጥሩ አመት ጥሩዎን ሁሉ ባለሽበት እመኝልሻለሁ
ናፋቂሽና አድናቂሽ
Image
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby ሚሚlove » Wed Sep 30, 2009 10:48 am

ሰላም ቤቶች ከበዙ ግዜያት በዋላ ብቅ ብያለሁ. . . የሀገሬ ሁኔታው ቀዝቀዝ አለ መሰለኝ መስመሩንም ለቀቁልን እልል እያልኩ እኔም የምውድው ቤት ለመመለስ በቅቻለሁ::

ሁሌም መለየትን አልፈልግም ከናንተ እናተ ለኔ ታስፈልጉኛላችሁ ምክራችሁ ሁሌም ለኔ ገንቢ ነው!!

ድምስሰው:- በቅድሚያ ግዜህን መሰዋት አርገህ እቤቴ ድረስ መተህ ያለህን ስላቀረብክ ከልብ አመሰግናለሁ ተሳትፎህ ይቀጥል እላልሁ. . .

yammi:- ውድ ያገር ልጅ ከዚህ ቀደም አስተያየት ላይ ጠቀስ አርጌው ነበር . . . ኪድ እያለሁ ያስባሰብኳቸው ፅሁፎች አሉ ባለቤታቸው እነማን እንደሆኑ አላውቃቸውም በልጅነት ገዜ ግን አስባስቤ ከደብተሬ አኖራቸው ነበር ያን ግዜ ውስጤን ይገልፅልኛል ብዬ የማሰባስባቸው ፅሁፎች ባልቤቶቹ ስማቸውን ባቅ ንሮ ተቆም አረጋቸው ነበር በሰአቱ ግን እንዴት አሰባስቤ እንደፅፍኳቸው እኔ ነኝ የማቀው . . . አንዱን ጠቆም ለማረግ ያከለ "ከሱቅ ማሚ እቃ ትገዛ እና የዛ እቃ ተጠቅልሎ የመጣበት ጋዜጣ ላይ የተፃፈ ነበር ባለቤቱ ስም አልተጠቀሰም ግጥሙ ደሞ ልብ የሚነካ ነበር ያን ፅፌ ነበር እንሆ ከዛ ውስጥ ለናተ ንባብ ያበቃሁት"

የግጥም መድብሌ ላይ ያሉት ግጥሞች የድሮ ስለሆኑ ያን የከሌ ነው ማለት አልችልም እንደተረዳሽኝ ተስፋ አደርጋለሁ ከአዳዲሶቹ ግን ተቆም ማረጌ የማየቀር ነው::

ሶምራን:- ውድ ምክር አዘል ግጥምህን ቤቴ ድረስ ምተህ ስላሰፈርክ ከልብ አመስግናለሁ ተሳትፎህ አይለየኝ እላለሁ በዚሁ አጋጣሚ::

ዋኖስ:- ያገር ልጅ አንዳንዴ ግጥም ትጅምረው እና ማለቂያው ሊችግር ይችላል ያን ደሞ እኛም ልናግዘው ይገባል ከቻልን የተቻለንን ተቆም ብናድርግ ያለህን ሞንጭር ጭር ብናደርግ . . .

ቤቲ_13:- ውዴ ምን ያህል እንደናፈቅሽኝ ለመግለፅ ቃላት ያጥረኛል ብቻ ዳግም መጥቼ መልስ ለመመለስ በመብቃቴ በጣም ድስ ነው ያለኝ. . .

ምኞትሽ ተሳክቶ
ቃልሽ ተብላልቶ
ካለሁበት ድርሶኛል
የምወደው ቤቴ ተከፍቷል
ላወራ ያለኝን
ለናተ ያሰባሰብኩትን
ደስታና ሀዘኔን ላካፍላችሁ
እነሆ መጥቻለሁ!!
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ቤቲ_13 » Mon Oct 05, 2009 12:46 pm

ሚሚ ተመለሰች.........?እለለእልልልልልልልል በጣም ደስ አለኝ ከስኳር መጠቅለያዉ ሆነ ግድግዳ ላይ ከተለጠፈዉ ላይ እያነበብኩ የማመጣው ያልሻቸዉ ንፍቅቅቅቅቅ ብሎኝ ነበር ጥፍት ስትይብኝ አይ ይቺ ልጅ በስኳር ሻይ መጠጣት አቆመች ወይስ...ጋዜጣ ግድግዳ ላይ የሚለጥፍ ጠፋ እያልኩ ነበር .....እረገጠኛ ነኝ አሁን እኔስ ብለሽ በ 2002 አዲስ ለዉጥ...ሆነና አንቺና ዋርካ..ለማየት የሆነ ደስታ ነገር ይጭራል.....
እንኳን ደህና መጣሽ ...
በይ ቶሎ ቶሎ ያጠረቃቀምሽዉን መድበል ቅቅቅ
Image
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby ከርታታው88 » Mon Oct 05, 2009 5:55 pm

ሚሚ.....ወዲያ ወዲህ የምትይውን ተይና ቁምነገር ስሪ እስቲ....ሚስት ሚስት ብዬ ልሞት ነው:: እስቲ የገባት ቺክ ከአዲስ አበባ ፈልጊልኝ:: ጉዋደኝነትሽ ለመቼ ነው:: ቀላል እንዳልመስልሽ የት ይደርሳል የተባልኩ ላጤ እንኝ::
በትምህርት ሰከንደሪ በጥሻለሁ; እድሜ ቫት ሳይደመር ጎልማሳ ደረጃ ላይ ይገኛል; ደሞዝ ለጊዜው ዝቅተኛ:: በአመሌ "መሬት" ከሚባሉት እመደባለሁ:: በፍቅር ሥራ አንድ አንዶች "ሊቀ ወሲብ" ይሉኛል::
በይ እንግዲህ አንድ ውለታ የምትውያለት ቺክ ካለች ዱቅ አድርጊያት:
ከርታታው88
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Tue Jan 10, 2006 7:43 pm

Postby ራዚ » Tue Oct 06, 2009 1:22 am

ሰላም ወገኖቼ!

እስኪ ለዛሬ አዲስ እንደመሆኔ
መጠን አንዲት አቺር ግጥም ጄባ ልበላቺሁ::

ገበሬው!
ገበሬው ገበሬው: ታታሪው አርሶ አደር!
ደከመኝ ሰለቼኝ: የማይለው ወታደር!
የኛ የኢትዮጲያ: የኢኮኖሚ ማገር!
ገበሬው እኮነው: አረ ማንም አይደል::

ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም አይደል :lol: :lol: [/u]
ራዚ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 18
Joined: Tue Oct 06, 2009 12:28 am

Postby ሚሚlove » Thu Oct 08, 2009 9:06 am

ቤቲ_13 wrote:ሚሚ ተመለሰች.........?እለለእልልልልልልልል በጣም ደስ አለኝ ከስኳር መጠቅለያዉ ሆነ ግድግዳ ላይ ከተለጠፈዉ ላይ እያነበብኩ የማመጣው ያልሻቸዉ ንፍቅቅቅቅቅ ብሎኝ ነበር ጥፍት ስትይብኝ አይ ይቺ ልጅ በስኳር ሻይ መጠጣት አቆመች ወይስ...ጋዜጣ ግድግዳ ላይ የሚለጥፍ ጠፋ እያልኩ ነበር .....እረገጠኛ ነኝ አሁን እኔስ ብለሽ በ 2002 አዲስ ለዉጥ...ሆነና አንቺና ዋርካ..ለማየት የሆነ ደስታ ነገር ይጭራል.....
እንኳን ደህና መጣሽ ...
በይ ቶሎ ቶሎ ያጠረቃቀምሽዉን መድበል ቅቅቅ


ቤቲዬ እንኳን ደህና ቆየሽኝ ይህው ይዜልሽ ከች በያለሁ!!
ያልገባው ወዳጄ

አልሰማኝ ያል የቅርቤ ሰው
ተው ተውን ወልዶ ሆድ ቢያስብሰው
"ህፃን አታርገኝ ሽበቴን እይ
ድርሰህ አትሁን ሰው አሰቃይ::"
ብሎ ቢነግረኝ ልክ ልኩን
ለሱ ንግስና የቆምኩትን
የልብ ወዳጁን አስቀየመኝ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Thu Oct 08, 2009 9:38 am

ከርታታው88 wrote:ሚሚ.....ወዲያ ወዲህ የምትይውን ተይና ቁምነገር ስሪ እስቲ....ሚስት ሚስት ብዬ ልሞት ነው:: እስቲ የገባት ቺክ ከአዲስ አበባ ፈልጊልኝ:: ጉዋደኝነትሽ ለመቼ ነው:: ቀላል እንዳልመስልሽ የት ይደርሳል የተባልኩ ላጤ እንኝ::
በትምህርት ሰከንደሪ በጥሻለሁ; እድሜ ቫት ሳይደመር ጎልማሳ ደረጃ ላይ ይገኛል; ደሞዝ ለጊዜው ዝቅተኛ:: በአመሌ "መሬት" ከሚባሉት እመደባለሁ:: በፍቅር ሥራ አንድ አንዶች "ሊቀ ወሲብ" ይሉኛል::
በይ እንግዲህ አንድ ውለታ የምትውያለት ቺክ ካለች ዱቅ አድርጊያት:


ውድ ከርታታው88 ሰላም ላንተ ይሁን በቅድሚያ . . .

በመቀጠል ሚስት ላልከው ላንተ የሚሆን እስካሁን አተህ ነው እንዲያው አያያዙን አልውቅበት በለህ ነው እንጂ . . . መቼስ ላንተ የምትሆን ሞልታለች ታዲያ አያያዙ ላይ ፈዘዝ ካለከ መሸብለሏ አይቀሬ ነው

እስኪ ከግጥሙ ደሞ ጀባ ልበልህ . . .
ቆም ላንዲት አፍታ

በአለም ሩጫ መሀል በሌለለበት ፋታ
በሕይወት ግርግር በሕይወት ጋጋታ
አረፍ ለዝክር ቆም ለትዝታ
ረገብ ከጥድያው ጉዞን ትንሽ ገታ::

ትንሽ ተመስጦ ያንድ አፍታ ጥሞና
በሚነደው ሻማ እጽብ ብርሃን ፋና::
ገሸሽ ከሩጫው ቆም ላንዲት አፍታ
ለሚወዱት ዝክር ለራስ ሰው ትዝታ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 10 guests