ፍቅር እና ሌሎች ግጥሞች ማሰባሰቢያ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሚሚlove » Thu Oct 08, 2009 12:44 pm

ራዚ wrote:ሰላም ወገኖቼ!

እስኪ ለዛሬ አዲስ እንደመሆኔ
መጠን አንዲት አቺር ግጥም ጄባ ልበላቺሁ::

ገበሬው!
ገበሬው ገበሬው: ታታሪው አርሶ አደር!
ደከመኝ ሰለቼኝ: የማይለው ወታደር!
የኛ የኢትዮጲያ: የኢኮኖሚ ማገር!
ገበሬው እኮነው: አረ ማንም አይደል::

ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም አይደል :lol: :lol: [/u]


ሰላም ውድ ራዚ እቤቴ ድረስ ያለህን መተህ ጀባ ስላለከኝ ለልብ አመሰግናለሁ . . .

ወጣትነት

ቆሞ ላይጠብቀኝ እድሜ

ሳላግጥበት ከርሜ

ነገሩ ገብቶኝ ስቀና

ካጎነበስኩበት ስቃና

የኌሊት የጎተተኝ

ከጓደኞቼ ያሳነሰኝ

የወጣትነት ትኩስ ደሜ

ትዝ አለኝ ከንቱ ቀኔ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ራዚ » Thu Oct 08, 2009 2:59 pm

ሰላም ውድ ዋርካዊያን

ከጎአደኛዎ አንዱ (ዷ )

ምንኛ መናኝ ነው የራሱን የማይውቅ
ሰውንም ከሰው ጋር ሁሉንም የሚንቅ
ባልታሰበበት ቦታ ባልተጠየቀበት
ለወሬው ማጀቢያ ሁሉንም ሚደባልቅ ::

በሰወች ዘንድ ሲታይ ምሁር ለመምሰል
ጦርሜዳው አይቀረው ሁሉንም ሲያካልል
እከሌማ ካሉት ሰውን የሚያጣጥል
በነግሮች ሁሉ እራሱን የሚክብ
ለውጭው ሰው ምሁር ለቤቱ መሀይም ::

ሰለትዳር በለው ስለ ፖለቲካ
ሳይጠየቅ ገና ሁሉን የሚነካ
ለሰው ተራ አይሰጥ ወሬውን ሲከካ ::

ከተባለዕማ አንተ ምንታውቃለህ
አረ ጀሮ አይስማ ሚዘባርቀውን
ቁጭት ቂም እልህ አንቆት
አምጦ ትንፋሹን ታፍኖ በሙቀት
ከላይ ከታቺ ሲዘል ተደፈርኩ በማለት
እፍፍፍ ሲል ትንፋሹን ያዘለውን ሙቀት
ማየት መስማት ያኔ ይሆናል ስህተት
ትተውት መሄድ ነው ብለውት አትሳሳት ::

ዙሪያዎትን ቢያዩ ከጉአደኛዎ አንዱ (አንዷ ) የዚህ ግጥም አባል ይሆናሉ :;
ራዚ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 18
Joined: Tue Oct 06, 2009 12:28 am

Postby ሚሚlove » Mon Oct 12, 2009 6:39 am

ሰላም ላንተ የሁን ውድ ራዚ . . . ስለ ምክር አዘል ግጥምህ ሳላመስግን አላልፍም . . .

ጓደኝነት

ገንዘብ አለኝ ብሎ ቢኮራ
ስለትልቅነቱ ቢያወራ
አብረህ ራስህን ነቅንቀህ
በአድናቆት ከኪሱ ተወዳጅተህ
ከመብላት መጠጣቱ
ቁም ነገር አርገህ በጥዋቱ
ጓድህን አትከተል
ክስረቱ ላይ እልል አትበል::
ማታው ሳይድረስ ካሁኑ
"ነጋ!" ብለህ አብስረው
ሁንለት ብርሃኑ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby heyhello » Mon Oct 12, 2009 2:26 pm

interesting.... :shock: :shock:
heyhello
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Mon Oct 12, 2009 2:24 pm

Postby ሚሚlove » Wed Oct 14, 2009 9:11 am

heylello ሰላም ጤና ይስጥልኝ . . . አመሰግናልሁ አስተያየትዎ አይለየኝ . . .

ተጃጅዬ ይሆን

ውስጤ ሲጨናነቅ
ሲተነፍስ እምቅ
አንጀቴ ሲቆስል
ነገር ሳብሰለስል
ምክንያቱ ገብቶኝ ቤቴ መለወጡ
በፍቅር ጉምያ ልቤ መዳመጡ
መተኪያ አሰኘኝ የግዛቴ ንግስት
ዳግማዊተ ሄዋን የብቻዬ ንብረት::
ታዲያ በፍለጋ
ካንዳ ጋር ባወጋ
ሳትገባኝ ግዜ ማርሽ ብለዋውጥ
አጣማጄን ሽቼ አይኔ ቢቀላውጥ
ተጃጅዬ ይሆን?!
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Fri Oct 16, 2009 3:21 pm

ጠላትሽ አይኔ ነው

አብሬሽ ቁጭ ብዬ
አይኖችሽ እያዩኝ
ቃላትን አወጥተው
እየተማፀኑኝ
ራሴን ታዘብኩኝ
አይኔ ሌላ ቦታ አሻግሮ እያየብኝ
ጠላትሽ አይኔ ነው
እኔን አትወቀሽኝ
መላ ፍጠሪና አይኔን መልሽልኝ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Wed Oct 21, 2009 7:45 am

ወለም ዘለሙ

መሳ ለመሳ ጎራ ለይተው
ልብና እግር በጦር ተቋስለው
የነፍሴ ጉያ የውስጤ ክፍል
የገነቴ ቁልፍ የክብሬ ተክሊል
ፅናትን ሽቶ ድንበር ሲያስከብር
ትርፋማ ሆኖ ክልሉን ሲያጥር
ወለም ዘለሙ የስጋ ኩሊ
የቆመ ወዳጅ የሀጢያት ባሊ
ምኞት የሚሉት ደዌ ተመቶ
ውጭ ውጩን ይላል ንብረቱን ትቶ::

ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Mon Nov 02, 2009 7:51 am

ምን ይሰራል??

ሐብቱ ቢቆለል ሚሊዮን ቢቆጠር
ብሩ ከመኪና ሱቁ ቢደረደር
የወተት ላሞቹን ሺ ከብት ቢያስር
ምን ይሰራል ውዴ ሊሰጥሽ ካልቻል ዕውነተኛ ፍቅር?
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

ግጥም?

Postby newethiopia » Mon Nov 02, 2009 6:37 pm

ርእስ ስጡት

ጅምር ግጥም ነኝ
ፈጣሪ በልኡል ብእሩ የፃፈኝ:
አንቺን ከኔ ያገናኘው
ግጥሙ ቤት መቶ
አምሮ እንዲፈፀም ነው::
newethiopia
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 10
Joined: Thu Oct 15, 2009 5:02 pm

Postby ፓራጎን33 » Wed Nov 04, 2009 3:42 pm

ሰላም ሚሚና ሌሎችም:: ስለቀረቡት ግጥሞች ልትመሰገኑ ይገባል:: አንድ ነገር ግን ስላልገባኝ ነው የመጣሁት:: ግጥሞቹ በሙሉ የናንተ ናቸው? ምናልባት ካልሆኑ ምንጫቸውን ብትጠቅሱልን ጥሩ ስለመሰለኝ ነው::

ከአክብሮት ጋር

ፓራጎን
Never follow the path may lead, go instead where there is no path and leave the trail!
ፓራጎን33
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 29
Joined: Wed May 20, 2009 10:03 pm

Postby ሚሚlove » Thu Nov 05, 2009 12:46 pm

newethiopia -በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬ ይድረስ እያልኩ ግዜህን መሰዋት አርገው ያሎትን ስላካፈሉን በዋርካ እና በኔ ስም ከልብ እናመስግናለን ያለሎትን ከማካፈል እንዳትቦዝን ከወዲሁ እያልኩ አስተያየትዎም አይለየን እላለሁ::

ውድ ፓራጎን 33 በቅድሚያ ሰላምትዬ ካለህበት ይድረስ እላለሁ አሰተያየቶችህን ተቀብያለሁ ከልብ አመሰገናለሁ:: ከውደላይ ይንን በተመለከተ ለቀረበልኝ ጥያቄ መልስ ስጥቻለሁ ከሆነ ግዜ በዋላ ያሰባስብኳቸው ግጥሞች አሉ የነሱን ግጥም እስከነ ባለቤታቸው ላቀርባቸው ዝግጁ ነኝ ለድሮዎቹ ግን ያው ከላይ እንደተቆምኩት ይሆናል::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Fri Nov 06, 2009 12:57 pm

ብታውቂ

ስትሥቂ!
ጠፈርን እንደምታደምቂ
መንፈስን ከአዚም አሥራት
እንደምታላቅቂ
ብታውቂ!
ስትሰሚ!
አጥንት እንደምታለመልሚ
ታማሚ ልብ እንደምታክሚ
ብታውቂ!
ስታወሪ!
ዲዳ እንደምታናግሪ
መነኩሴውን ከሱባኤ
ፈላስፋውን ከጉባኤ
እንደምትጠሪ
ብታውቂ!
እንኳንስ በ'ኔ ልትሽቂ
ከራስሽ ጋር ፍቅር ይዞሽ
አይሽ ነበር ስትማቅቂ::

በዕውቀቱ ሥዩም
"ኗሪ አልባ ጎጆዎች"
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Mon Nov 09, 2009 2:54 pm

ፀጥታ

ማውራት መቦለቱ
ሁካታ ጩሕቱ
በበዛበት አለም
ምናል ፀጥታም
በካሴት ቢታትም??
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Fri Nov 13, 2009 2:10 pm

ጊዜም ይታዘባል

በህይወት መንገድ
ስንወጣ ስንወርድ
ስንሮጥ ስንደክም
ስንተኛ ስንቆም
ስንስፍር ስንለካ
ስንጨፍር ስናቦካ
በውጭ በቤት
ይህ ሁሉ ሲሆን
ይታዘባል ዘመን
ሲታሰብ ሲሰራ ሲባል
ግዜም ይታዘባል


ከግርማ ኃይሌ
የግጥም መድብል የተውሰድ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Wed Nov 18, 2009 9:34 am

ልዩነት

ከማላቀው ጠንቋይ ከማይጥመኝ ጎራ
ያቅሜን ስዳክር ስጨፍር ሳጓራ
እነርሱ አይገቡኝ እኔ አልገባቸው
እንደትንሽ ጦጢት አፍጥጬ ሳያቸው
ለካስ ልዩነት
በግል መታማቱ
ምክንያቱ ኖሯል የእንጥልጥል ልጥፉ
እጅ ማስረዘሙ እጅ ማጣጠፉ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 8 guests