ፍቅር እና ሌሎች ግጥሞች ማሰባሰቢያ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ቤቲ_13 » Thu Nov 19, 2009 9:03 pm

ዋዉ....
Image
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby ሚሚlove » Fri Nov 20, 2009 7:42 am

ቤቲ_13 wrote:ዋዉ....


ቤቲዬ የኔ ቆንጆ ቤቴ ስትመጭ ምን ያህል ደስ እንደሚለኝ ታውቂያለሽ . . . ቆንጆ ምን ሆነሽ ነው እንዲህ ጥፍት ያልሽው. . . ቤትሽ ደሞ አይቼው አላውቅም . . . በሰላም ነው. . .
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ቤቲ_13 » Sat Nov 21, 2009 4:44 pm

ሚሚ......አለሁልሽ...ቤቴ የዘንድሮ ብርድ አጣሞት ነበር እስኪ ቀና አደርገዋለሁ....እረሶም ግርምታዬን ....ድንቅ--ታዬን በአክብሮት...አቀርባለሁ!!
Image
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

የሰው ሰውነቱ

Postby ሙሐመድ » Sun Nov 22, 2009 6:23 am

የሰው ሰውነቱ

ውጫዊ ውበቱ የደስ ደስ ቢኖረው
ከማር ቢጣፍጥም ያነጋገር ለዛው
ውስጣዊ ቁንጅና ቅንነት ከሌለው
ምድር ላይ ተፈጥሮ ኑሮ/በመሞቱ
ከቶ ከምን ላይ ነው የሰው ሰውነቱ?
ሙሐመድ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Wed Aug 11, 2004 2:10 pm
Location: ethiopia

Postby ትርንጎ* » Sun Nov 22, 2009 11:36 am

ሚሚlove wrote:ፀጥታ

ማውራት መቦለቱ
ሁካታ ጩሕቱ
በበዛበት አለም
ምናል ፀጥታም
በካሴት ቢታትም??


:lol: በጣም እንጂ...በደርዘን በገዛነው ነበር::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 716
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ሙዝ1 » Sun Nov 22, 2009 1:19 pm

ትርንጎ* wrote:
ሚሚlove wrote:ፀጥታ

ማውራት መቦለቱ
ሁካታ ጩሕቱ
በበዛበት አለም
ምናል ፀጥታም
በካሴት ቢታትም??


:lol: በጣም እንጂ...በደርዘን በገዛነው ነበር::


ሰላም ትርንጎሻ ... ስምሽን አይቼ ዘዉ ስል .... የዛሬ 6 አመት አካባቢ በአዲስ አበባዉ የFBE አዳራሽ የሰማሗትን ግጥም ዱቅ ብላ አየሗት ... አንባቢዉ(ባለግጥሙም እሱዉ ይመስለኛል) ከነ አለባበሱ ትዝ ይለኛል ... ... በሗላም በፕሬዚዳንት ኦፊስ በኩል የሚታተም የሆነ መጽሄት ነገር ነበረ ... የመጽሄቱ አዘጋጇን ልጅ አዉቃታለሁ ከዛ በሗላ ICRC እንደገባች አጫዉታኛለች ... በሷዉ መጽሄት አስነብባን ነበረ :wink:
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby የባድ ሰብ » Wed Nov 25, 2009 6:03 pm

ትርንጎ* wrote:
ሚሚlove wrote:ፀጥታ

ማውራት መቦለቱ
ሁካታ ጩሕቱ
በበዛበት አለም
ምናል ፀጥታም
በካሴት ቢታትም??

የሀገራችን ሰው አወይ ደግነቱ
ለዝምታ ወጪ ብዙ መመኘቱ:

:lol: በጣም እንጂ...በደርዘን በገዛነው ነበር::
የባድ ሰብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 135
Joined: Fri Nov 28, 2008 12:46 pm
Location: southafrica

Postby ሚሚlove » Fri Aug 13, 2010 4:01 pm

ስላም ለናንተ ይሁን በቅድሚያ . . .

ፍለጋ

እውቀትን ፍለጋ
ውበትን ፍለጋ
ገንዘብል ፍለጋ
ሲመቸኝ በፈረስ ሳይመቸኝ በግሬ
እድሜዬን በሙሉ ስንከራተት ኖሬ
የራሴን ፍለጋ
ስጀምር ዙሪያዬን ማየት አትኩሬ
እነሆ አገኘሁ
እውቀት ከሰፈሬ
ውበት በመንደሬ
ገንዘብ ከሀገሬ
ቸር ይግጠመን
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Wed May 11, 2011 7:04 am

የኔዋ ዋርካ

ምን ያህል እንደምውድሽ
ብታውቂ ካለሁበት በመጣሽ
ግና ብዙ ፍቅር አለሽእና
ከኔ ትንሽዋ ፍቅር የሌላው በለጠና
የኔን ፍቅር አስረሳሽ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ሚሚlove » Mon Sep 10, 2012 8:11 am

እዮሀ አበባዬ
መስከረም ጠባዬ
መስከረም ሲጠባ
አደይ ሲፈነዳ
እንኳን ሰው ዘመዱን
ይጠይቃል ባዳ

እዮሀ አበባዬ
መስከረም ጠባዬ
መስከረም ሲጠባ
ወደ አገሬ ልግባ

መልካም አዲስ አመት!!
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby Gosa » Mon Oct 15, 2012 5:16 am

ይሰየም ችሎቱ ላነሳው አምባጓሮ
ደረቱ ላበጠው በንጹህ ሰው ደም ከብሮ
ዙሪያው ጨልሞበት ለተጎዳው አፍቅሮ
ትዳሩ ሊፈርስ ያለው በቀጠሮ
ዳኛው ምን ሊጠቅመው ነው ቅስሙ አንዴ ተሰብሮ?
"አትጠጋት!" ብሎ ድንበር አስከብሮ
ማንን መጥቀሙ ይሆን ግራ ቀኝ አባርሮ?
አምላክ ሆይ ፍረደን አስታርቀን ዘንድሮ
ሽምግሌም የታል አይ የባዕድ ኑሮ!!
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests