ተአምረ ማርያምን ወይንስ ተአምረ ሜሪን? ክፍል ሁለት (ክፍል 2

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ተአምረ ማርያምን ወይንስ ተአምረ ሜሪን? ክፍል ሁለት (ክፍል 2

Postby ግሸንማርያም » Sat Jan 14, 2006 5:38 pm

ተአምረ ማርያምን ወይንስ ተአምረ ሜሪን ??? ::

በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ውድ የተከበራችሁ ክርስትያኖች ወገኖቼ ፡፡እግዚአብሔር አምላክ ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሳው ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ ያዋጃቹ ክርስትያኖች በእግዚአብሔር ስም እንደምን ቆያችሁኝ ? የጠበቀን ሕይወቱን የሰጠን በቀጥተኛይቱ ሐይማኖት ሰው አድርጎ ለፈጠረን ለጌቶች ጌታ ለነገስታ ንጉስ አለምን በቃሉ ብቻ ፈጠር ብሎ የፈጠረ ፡ ምንም የማይሳነው አልፋ ኦሜጋ ኢየሱስ እርሱ እግዚአብሔር ክብር ምስግና ለዘለአለሙ ይግባው አሜን ።

ይህን ሐያል አምላክ በድንግልና ወልዳ በቅድሳና ላሳደገችልን ለቅድስተ ቅዱሳን ለንጽህይተ ንጹሃን ለወላዲተ አምላክ በታላቁ ሊቀ መልአክት ቅዱስ ገብርኤል የተቀደሰ አንደበት ጸጋን የተመላሽ ደስ ይበልሽ ተብላ የተመገነች ፡፡በመጥምቀ መለኮት እናት በቅድስት ኤልሳቤት አንቺ ብሩክ ነሽ የመሐጸንሽም ፍሬ እሱ እግዚአብሔር ብሩክ ነው ብላ ያመሰገነቻት ፡፡እራሱዋ ቅድስት ድንግል ማርያም እራሱዋ ምስጋናዬ በአንዲት ቅድስት በኤልሳቤት እና በአንዱ ቅዱስ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ብቻ ተመስግኜ አላበቃም እረ ገና ትውልዱ ሁሉ ብጽህይት ይሉኛል ብላ የተናገረች ገናናይቱ የ እግዚአብሔር እናቱ የአለም ሁሉ አማላጅ ቅድስት ንጽህይት ድንግል ማርያም ክብር ምስጋና ውዳሴ ይግባት አሜን ።

እግዚአብሔር አምላክ ያከበራቸው ቅዱሳን አበው ነቢያት ወ ሐዋርያት ጻድቃን ወ ሰማእታት እንዲሁም እግዚአብሔር የመረጣችው እና የሾማቸው ቅዱሳን መላእክት ክብር ምሳጋና ውዳሴ ይግባቸው አሜን ።

ቅዱስ ሚካኤል የወገኖቻችንን አሳች ከይሲ ዲያቢሎስን በክርስቶስ መስቀል እራስ እራሱን ይቀጥቅጠው አሜን ። ይቀጠቅጠውማል ደግሞ ራእይ ም 12 ቁጥር 7 -10 ።

የተከበራችሁ ውድ ክርስትያኖች ፡ ባለፈው ሳምንት የአምላክ እናቱ የሁላችን አማላጅ ስለሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም ተአምር በአጭሩ ተማምረን ነበር ። የመጀመሪያውም የ እመቤታችን ድንግል ማርያም የተአምር መጸሐፍ ፡ መጸሐፍቅዱስ መሆኑን ተመልክተናል ። የመጀመሪያውም የቅድስት ድንግል ማርያም ተአምር እግዚአብሄርን መውለዱዋ ነው የሉቃስ ወንጌል ምህራፍ 2 ቁጥር 5 - 9 ። ከዚያም ደግሞ የድንግል ማርያም ድምጽ ብቻ በመጸሐፍቅድስ ውስጥ ጽንስ ሲያሰግድ ወይም የቅርቦቹ መጸሐፍቅዱሶች እንደሚሉት ቅድስት ድግንል ማርያም በድምጹዋ ብቻ የ 6 ወር ጽንስ ማዘለሉዋ ይታወቃል የሉቃስ ወንጌል ምህራፍ 1 ቁጥር 39-45 ።


እንግዲህ ውድ ክርስትያኖች መጸሐፍቅዱስ የቅድስት ድንግል ንጽህይት ማርያምን ክብር በግልጽ አስቀምጦታል ። ይህንን ለምሳሌ ያህል ገለጽኩላቹ እንጂ ስለ ድንግል ማርያም በመጸሐፍቅድስ ውስጥ በምሳሌ በቅኔ አድርገው ነቢያቱ ይናገሩላት ነበር ። ያንን ግን ለመዘርዘር እኔ አቅሙ የለኝም ።፡የመንፈስቅዱስ ገላጭነት ያስፈልጋል ። ወደ ፊት ግን ከ እናንተ ጸሎት ጋር እራሱን በቻለ ርእስ እንመጣበታለን ዲያቢሎስም ከነ አሽከሮቹ በድጋሜ ያፍራል ።

ገድላት ፡፡ድርሳናት ፡፡ተአምራት ፡ የመጸሐፍቅድሱ ልጆች የመንፈስቅዱስ ጽሁፎች በሚለው ትምህርታችን ውስጥ ፡ መጸሐፍቅዱስ እራሱ የገድል መጸሐፍ እንደሆነ ፡፡ መጸሐፍቅዱስ እራሱ የተአምር መጸሐፍ እንደሆነ ፡ መጸሐፍቅዱስ እራሱ የድርሳን መጸሐፍ እንደሆነ እግዚአብሔር አስተምሮናል ። ለከሐዲያኑ ግን ይሄ አይዋጥላቸውም ። እኛን ግን ለምን መጸሐፍቅዱስ የሚያዛችሁን ትቀበላላቹ ? ለምን ተአምረ ማርያም ? ለምን ገድለ ቅዱሳኑን በሙሉ ትቀበላላቹ እያሉ ይሰድቡናል ፡፡ይሳለቁብናል ። ከ እኛ ግን አሁንም የስድብ ቃል አይወጣም ። ለማኝ ያሉት ኢየሱስ ለፍርድ ሲመጣ ያኔ የስድባቸውን ዋጋ በግድ ይቀበሉዋታል ።


ከሐዲያን እኛን ለምን ከመጸሐፍቅድስ ሌላ ትቀበላላቹ እያሉ እንደሚሰድቡን የታወቅ ነው ። እነሱ ግን ከመጸሐፍቅድሱ ውጪ ብዙ መጻሕፍትን ይቀበላሉ ። በተለይ ነጮቹ የጫሩት መጸሐፍት ከሆነ ተሽቀዳድመው ነው የሚቀበሉት ። እኛን ግን ለምን የቅዱሳኑን ገድል ተቀበላቹ እያሉ የግብረ ሰዶም ከሚፈጽመው ፓስተራቸው ጀሞር እስከ ተራ የዋህ ተከታያቸው ድረስ በክርስትያኖች ላይ የስድብ ውርጅብኝ ያወርዳሉ ። ከ እኛ ግን አሁንም የስድብ ቃል እንዳይወጣ አደራችሁን ።


ይህን ያህል ለመግቢያ ካልኩዋቹ ዘንድ ወደ ተነሳሁበት ርእስ ልውሰዳቹ ። ዛሬ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ የምንመለከተው ፕሮቴስታንቶች የሚቀበሉትን የሐሰት ተአምረ ማርያምን መጸሐፍ ይሆናል ።

አሁንም የቀደሙ የአባቶችን ጉባኤ የባረከ አምላካችን መንፈስቅዱስ የእኛንም ጉባኤ ይባርክ ይምራ አሜን ።

ተአምረ ማርያምን ወይንስ ተአምረ ሜሪን?፡ ?፡ ?


ተአምረ ማርያም ለምን ይጥፋ ስትሉ አንድ ነገር ካጠፋን አንድ ነገር መተካት አለባቹ አይደለም እንዴ ? ። ተመልከቱ አንድ ነገር ካጠፋን ቶሎ አንድ ነገር መተካት አለብን ።
ለምሳሌ ያህል እያንዳንዳቹ ጣኦት ማምለክ ተዉ አታምልኩ ቢባል ፡ በልባቸው ውስጥ እግዚአብሐር እንዲገባ ነው ። ምክንያቱም በጣኦቱ ላይ የሚያድረው ሰይጣን ሲሆን ሰይጣን ደግሞ የእግዚአብሐር ተቃራኒ ነው ። ሳጥናኤል ማለት እራሱ የስሙ ትርጉም የ እግዚአብሔር ጠላት ማለት ነው ።

ወይንም ደግሞ የጣኦት ሰባኪዎች ተነስተው እግዚአብሔርን ማምለክ ተዉ ብለው ቢሰብኩ ፡፡በሰዉ ልብ ውስጥ ጣኦት ለመክተት ነው ።

እንዲሁም ዛሬ ተአምረ ማርያም ይጥፋ የሚሉ ሰዎች አሉ ። እነሱም ፕሮቴስታንቶች ናቸው ።፡
ታዲያ ተአምረ ማርያም ይጥፋ ሲባል እነሱ ምን ሊሰጡን ነው እንደሚፈልጉ ወይንም ምን እንዲተካ እንደሚፈልጉ ግልጽ ነው ? ይሀንን እንመለከታለን።


ለምሳሌ አሁን የማቀርብላቹ ፕሮቴስታንቶች ከመጸሐፍቅድስ ውጪ ከሚቀበሉዋቸው መጻሕፍት መካከል አንዱና ዋነኝ ሲሆን ርእሱም “” በመለኮታዊ ራእይ ሲኦል ሲገለጽ ይላል “” መጸሐፉ ። ደራሲዋ ሜሪ ትባላለች የጣሊያን ተወላጅ ናት ። ይሄ መጸሐፍ ሜሪ ባክስተን የተባለች ደራሲ የጻፈችው ሲሆን ተአምረ ሜሪ ያልኩዋቹ መጸሐፍም ይሄ ነበር ፤ በኢትዮጵያ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተደጋገመ 6 ጊዜ ታትሟል ::


ተአምረ ሜሪ ሲጀምር እንዲህ ይላል

የዚህ መጸሐፍ መታሰቢያነቱ ፡ ለአብ ፡ ለወልድ ፡ ለመንፈስቅዱስ እንዲውል ተሰጥቶአል ይላል ።
የዚህ መጸሐፍ መታሰቢያነቱን በደንብ አድርጋችሁ ተመልከቱልኝ ወገኖቸ ። መታሰብያነቱ ለአብ ለወልድ ለመንፈስቅዱስ ተሰጥቷል ብላለች ::


የተከበራችሁ ክርስታኖች ፡ ይህ ተአምረ ሜሪ ያልኩዋቹ መጸሐፍ የሚያወራው ሜሪ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር 40 ቀንና 40 ሌሊት በሲኦል ውስጥ ስትንሸራሸር ነው ። አንድም ቀን ግን ገነት አልሄደችም ።

ዛሬ ፕሮቴስታንቶች ተአምረ ማርያም እንዲቃጠልና እንዲጠፋ ያዝዛሉ ይናገራሉ ። ይሄ ግን ጣሊያናዊቱዋ ደራሲ የደረሰችውን መጸሐፍ ግን በ እልልታ ይቀበሉታል ።

ውድ ክርስታኖች ይሄ ተአምረ ሜሪ የሚለው መጸሐፍ የሚያወራው በጠቅላል ውሸት ብቻ ነው ። እስቲ እንመልከተው መጸሐፉ ሲቀጥል እንዲህ ይላል ።

ሜሪ በመንፈሴ ሆኘ ወደ ሰማይ ተወሰድኩ ትላለች ። ስትቀጥል እንዲህ ትላለች ፡፡ በህይወታቸው አንድ ወቅት ኢየሱስ በየምሽቱ እየገለጸላቸው ለ 40 ሴቶች ይህ ተገልጾላቸዋል ፡፤ እንደውም ኢየሱስ ለ 40 ቀንና ለ 40 ሌሊት በየምሽቱ ከመኝታ ቤቴ እየመጣ ኢየሱስ ወደ ሲኦል ይዞኝ ይሄድ ነበር ።፡ትላለች ወይዘሪት ሜሪ ።

ሲኦል ደግሞ ምን እንደትምትመስል ስትናገር ሜሪ እንዲህ ብላለች፡

እግዚአብሄርን ማወደስን ከውስጤ መፍለቅ ጀመረ ፡ ወዲያውኑ በቅስበት መላ ሕይወቴን ለአላማው ልሰዋለት ወሰንኩ ፡ ሰዎችንም ከሐጢታታቸው እንዲድኑ ልረዳቸው ወሰንኩ፡ አሁን በሲኦል ውስጥ ከኔ ጋራ የለው ቅዱስ የ እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ይብላል ፤ በመንፈሴም አውቄያለሁ ፡ ትላለች ወይዘሪት ሜሪ ።

ተመልከቱ ወገኖቼ ፡ ኢየሱስ የሜሪ መኝታ ክፍል መጥቶ ነው ታሪኩ የሚጀምረው።


ሜሪ ስትቀጥል እንዲህ ብላለች ፡ ከኢየሱስ ጋር ሆና ሜሪን ምን አጋጠማት ?

ከኢየሱስ ጋር ሆኜ ድቅድቅ ጨለማ ዋጠን ። ትላለች ሜሪ ።

ወገኖቸ አስተውሉ ፤ እንዴት ኢየሱስን ድቅድቅ ጨለማ ይውጠዋል ? ጨለማና ብርሃን ምን ህብረት አለው ። ኢየሱስ እኮ ብርሃን ነው ። ወገኖቼ አይደለም ኢየሱስ አንዱ መልአክ ቢወርድ ምድር ሁሉ ብርሃን ሆነች ይላል ራእይ ምህራፍ 18 ቁጥር 1 ጀምሮ ። አስተሉ ውገኖቼ እንዴት ከኢየሱስ ጋር ሆና ጨለማ ይውጣታል ያውም እኮ ድቅድቅ ጨለማ ነው ዋጠን ያለችው ? ማስተዋል ያስፈልጋል ። ጥሩ እስቲ ሜሪን እንስማት እንስማት ።

የሜሪ መጸሐፉ ይቀጥላል ፡ ድቅድቅ ጨለማ ከኢየሱስ ጋር በሲኦል ውስጥ ዋጠን ። በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ አሰቃቂና ትንቻሽን የሚሰርቅ ግማት መጣ ፡ በነዚህ መሽዋለኪያዎች ግርግዳዎች ላይ ሕይወት ያላቸው ቅርጾች ተለጥፈዋል ። መልካቸውም ጥቁር ግራጫ ነው ። ከኢየሱስ ጋር በማለፍ ላይ እያለን ነፍሳቶቹ እየተንቀሳቀሱ ይጮሁብን ነበር ። ባይነግረኝም እንኩዋን ኢየሱስ ፡፡እኔ ሜሪ እርኩስ መንፈስ መሆናቸውን አወቅኩ ።

ወገኖቼ ፡ ይህ መጸሐፍ በአጠቅላይ የሚያወራው ሲኦል ውስጥ ሜሪ 40 ቀን ስትንሸራሸር ሰይጣን በሲኦል ውስጥ እንዴት አይነት ስልጣን እንዳለው የሚናገር መጸሐፍ ነው ።

ወገኖቼ ሰይጣን እራሱ በሲኦል ውስጥ ይቃጠላል ። ስልጣን የለውም ።


ሜሪ ስትቀጥል እንዲህ ብላለች ፤ ሲኦል ልክ ሰው ይመስላል እንደውም የተጋደመን ሰው ይመስላል ። ሜሪ እንዲህም ብላለች ኢየሱስ መለሰልኝ ፡ የወንጌል አገልጋዮች የሆኑ ሰባኪያን አሉላቸው ።፡ስለ እኔ የሚማሩበት ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎች አሉ አለኝ ኢየሱስ ተላለች ሜሪ ። እዚህ ጋር ወገኖቸ ስለ ኮምፒውተሩም እየገለጸላት ይመስለኛል ።

ሜሪ ትቀጥላለች ፡ አምነው ይድኑ ዘንድ ሰራተኞችን ልኬያለሁ ። ወንጌል ሲሰበክላቸው ካለመኑ ። ከሞት የተነሳ ሰው ቢላክላቸውም አያምኑም ።

አስተውሉ ወገኖቼ ይህች ጽሁፍ ከመጸሐፍቅዱስ ጋራ ስለ አል አልአዛርና ስለ ኔዊ የተነገረውን ለማመሳሰል ነው ።ሜሪ ትቀጥላለች ፤ ከዚህ ቡሃላ አጋንንቶቹ በጣም ተናደዱና ኢየሱስን መሳደብ ጀመረ ። ትላለች የሲኦል ቱሪስቱዋ ሜሪ ።

አስተውሉ ፡ ኢየሱስን እዚህ ላይ እያስናቀችው ነው ሜሪ ። ኢየሱስን አጋንንቶቹ ፊት ለፊት ሰደቡ ነው ይምትለው ። ወገኖቸ ሰይጣን ገና ከሩቅ ሲያየው ቅዱሱ የ እግዚአብሔር ልጅ አታጥፋን እያለ የሚንቀጠቀጥለት አምላክ እኮ ነው ። እስቲ ሜሪን እንስማት ትቀጥላለች

ሜሪ ስትቀጥል ፡ ከዚህም ቡሐላ እርኩስ የሆነ የጌታን ክብር የሚያጎድፍ ቃላትን በኢየሱስ ላይ መናገር ጀመረ። ኢየሱስን መስደብም ቀጠሉ አጋንንቶቹ ትላለች ሜሪ ።

ሜሪ ስትቀጥል ፤ የእሳቱ ነበልባል ሲያጥለቀልቀውና የሞተውን የበሰበሰውን ስጋውን እና አጥንታቸው በታላቅ ሰቆቃ ውስጥ እየተበጣጠሰ መውደቅ ሲጀምር ነፍሱ በታላቅ ሰቆቃ ውስጥ ሆና ተመለከትኩዋት ።

አስተውሉ ክርስትያኖች ፡፤ ስጋውና አጥንቱ በሲኦል ውስጥ እየተበጣጠሰ ሲወድቅ አየሁኝ ትለናለች ሜሪ ። ለመሆኑ ሰው ሲሞት ከነ ስጋውና አጥንቱ ነው እንዴ ወደ ሲኦል የሚሄደው ? ስጋ እኮ መቃብር ውስጥ እኮ ነው ያለው ። ወደ ሲኦልና ወደ ገነት እኮ የምትሄደው እኮ ነፍስ ብቻ ናት ። አስተውሉ ውገኖቼ ፡ስጋና አጥንት እዚህ ምድር ነው የሚቀረው ። ሜሪ ግን የምትለን ስጋቸውን
አጥንታቸው እየተቆራረጠ ይወድቅ ነበር ትለናለች ። ይህንን መጸሐፍ አንብቤ ስጨርሰው ሜሪ ጥሩ የሆረር ፊልም ያየች ነው የመሰለኝ ። መጸሐፉ እንዳለ ተረት ተረት ነው ።


ሜሪ ትቀጥላለች ፤ እንደገና ወደ ሴቲቱ ተመለከትኩ ትላለች ። በዚህ ጊዜ ነበር አንድ እግር ብቻ ነበር እዳላት የተገነዘብኩት ። በዳሌ አጥንቶቹዋ ላይ ቀደዳዎች ያሉ ይመስላል ። እኔም ኢየሱስን እነዚህ ምንድናቸው ብዬ ጠየቅኩት ፤

ኢየሱስም መልሶ ልጄ ሆይ በምድር በነበረች ጊዜ ይህች ሴት በካንሰር በዙ ስቃይ ነበረባት ። ሕይወቱዋን ለማዳን የቀዶ ጥገና ሕክምና ተደርጎላታል ። ሕይወቱዋ በሙሉ ጎምዛዛ ነበር ። የ እኔ የሆኑ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱዋ በመምጣት ላድናት እንደምችል ነግረዋታል ። እርሱዋ ግን የሄንን ያደረገብኝ እራሱ እግዚአብሔር ስለሆነ ወንጌልንም አልቀበልም ንሰሐም አልገባም በማለት አሻፈረኝ አለች ። ግን በሕይወቱዋ አንድ ጊዜ አውቃኝ ነበር ። ከዚያ ቡሐላ ግን ጠላችኝ ይላል ።


አስተውሉ ወገኖቼ ፡ ሴትየዋ ምድር ላይ ካንሰር ስለነበረባት ፤ በሰማይ ላይም ዳሌዎቹዋ የተበሳሱ ነበሩ ትላለች ሜሪ ። ወገኖቼ አስተውሉ ፡ ይህች ሴት እኮ ሞታለች ከሞተች ደግሞ አጥንቱዋ መሬት ውስጥ ነው ያለው ። እንዴ እናስተውል እንጂ ሰማይ የሚሄደው እኮ ነፍስ ነው ።

ወገኖቼ እንግዲህ ተአምረ ማርያምን ይጥፋ ይቃጠል ብለው የማርቲን ሉተር ልጆች ፕሮቴስታንቶች እየለፈፉ ይገኛሉ ። በጎን ደግሞ ሌላ ተአምረ ሜሪ የሚባል ፡ የ እውነተኛይቱን የማርያምን ተአምር ወይም ተአምረ ማርያምን የሚተካ ብለው ያሰቡትን የጣሊያን ደራሲ የደረሰችውን ተረት ሊሰጡን እኛ ተአምረ ማርያምን እስከምንጥል ድረስ እየጠበቁን ነው ። እና ግን ተአምረ ማርያም አንጥልም :: ሲያምራቸው ይቅርርርር ::


በአጠቅላይ ይሄ ተአምረ ሜሪ ያልኩዋቹ መጸሐፍ ከመጸሐፍቅዱስ ጋር ምንም መስማማት የሌለው ።፡እንደውም ኢየሱስን እየተሰደበ እየተናቀ ሰይጣን እንደት አይነት ብርቱ ስልጣን እንዳለው የሚተርክ መጸሐፍ ነው ። ይህ መጸሐፍ የሚገርማቹ የፕሮቴስታንት አማኝ በተባለ በ እያንዳንዱ ቤት ውስጥ ይገኛል 6 ጊዜም ደጋግሞ ታትሟል ። የቅድስት ድንግል ማርያም ክብር ብትነግሩዋቸው ግን አይቀበሉዋችሁም ። እንደውም ስለ ድንግል ማርያም ክብር ከነገራቹሀቸው እንዲህ ይሉዋቹሀል " ድንቅ ነው "" ተመልከቱ ማመስገን አይፈልጉም ስለ ጽንሱ መዝለል : ትውልዱ ሁሉ ብጽህት ይለኛል እነሱ ጋር የለም :: ድንቅ ነው ብለው ይሄዳሉ :: ይሄንን ጣሊያናዉቱዋ የደረሰችውን መጸሐፍ ብትሰጡዋቸው ግን ፡፡ ትልቅ ሽልማትን ይሰጡዋቹሃል ።
ይሄ ከላይ የሰፈሩት ሁሉ ላዋቂውች ነው ። ለልጆችም ግን የተዘጋጀ በዚያው ላይ ይገኛል እንመልከተው ።


ፕሮቴስታንቶች ሕጻናት ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲጠሉ ምን አዘጋጅ ?፡ ?፡ ?

ይሄ መጸሐፍ ለልጆች መጸሕፍቅዱስ ይላል :: ። 5 የ እምነት ድርጅቶች ተካፍለውበተል ።

የድርጅቶቹም ስማቸውም በቅድመ ተከተል።
1ኛ . የቃለ ሕይወትድርጅት
2ኛ . የመካነ ኢየሱስ ድርጅት
3ኛ . የገነት ድርጅት
4ኛ . የሙሉ ወንጌል ድርጅት ።
5ኛ . የመሰረት ክርስቶስ ድርጅቶች ናቸው ::


ይሄ መጸሃፍ ከመጸሐፍቅዱስ ጋር ምን መስማማት አለው ? በግልጽ እንመለከተዋለን ።

ልጆች ስለ ድንግል ማርያም ምን ሰምተው እንዲያድጉ ፕሮቴስታንቶች ምን ያስተምራሉ ?

የጽህፉ ርእስ ሲጀምር - ልጃገረቲቱ ማርያም ይላል ።
ተመልከቱ ርእሱ እራሱ ልጃገረቲቱ ማርያም ይላል ።

መጸሐፉ ይቀጥላል ፡ በሰሜናዊው እስራኤል በገሊላ አውራጃ በናዝሬት ከተማ ማርያም የምትባል አ አንዲት ልጅ አገረድ ነበር እርሱዋም ተራ ልጅ አገርድ ነበረች ይላል :: እዚህ ላይ ነው እንግዲህ የቅድት ድንግል ማርይም ክብር ።

አስተውሉ ፤ ተአምረ ማርያም ለምን ይጥፋ ብትሉ ፡ ይሄንን ሊተኩላቹ እነሱ ተዘጋጅተዋል ።

ወገኖቼ እረ መጸሐፍቅድስ ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽህይት ናት ። ቡርክት ናት ። የ እግዚአብሔር እናት ናት ፡ ድምጹዋ እራሱ ጽንስ ያሰግዳል ያዘልላል ፡፡ትውልድ ሁሉ ብጽህይት ይላታል ነው የሚለው ። እነሱ ግን ተራ ልጃ ገረድ ብለዋልታል ። ታዲያ ጽሁፋቸው መጸሃፍ ቅዱስን አይጻረርም ?

መጸሐፉ ይቀጥላል

ይህች ተራ ልጃገረድ ማርያም እንደሌሎቹ ልጃገረዶች እንጀራ በመጋገር ፤ በመፍተልና ፤ ውሃ በመቅዳት እናቱዋን ትረዳ ነበር ። ይላል መጸሐፉ ።


አስተውሉ /color] ፤ እንዴ ፕሮቴስታንቶች ከመጸሐፍቅዱስ ውጪ ምንም መጸሐፍ አንቀበልም ይሉ አይደል እንዴ ? ይሄንን ታዲያ ከየት አመጡት ውሃ ትቀዳ ነበር መጸሀፍቅዱስ አይልም ፡ እንጀራም በመጋገር ትኖር ነበር መጸሐፍቅዱስ አይልም ። እኔ የሚገርመኝ ግን መከጸሐፍቅዱስ ውጪ ምንም አንቀበልም ይሉ አይደል እንዴ መጸሐፍቅዱስ ድንግል ማርያም እንጀራ ትጋግር ነበ አይልም ። ስለዚህ ይህን ልብ ወለድ ከየት እንዳመጡት ቢነግሩን ። ምክንያቱም መጸሐፍቅዱስ ውስጥ አልተጻፈምና ?

ደግሞ ማርያም እንጀራ ትሸጥ ነበር ብለዋል ። ደግሞ እስራኤሎች እንጀራ የት ያውቃሉ ? እንጀራ ምን እንደሆነ እንኩዋን አያውቁም ። እባካቹ በግድ አታስቁኝ ፕሮቴስታንቶች ።


የተከበራችሁ ክርስትያኖች በእኛ ጋር ስትመጡ ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም እናቱዋ ቤት አላደገችም ። እንጀራም ሸጣ አታውቅም ። እኔ እንደሚመስለኝ ግን ይህንን መጸሐፍ ወደ አማርኛ የተረጎመው ፓስተር ምን አልባት እናቱ እንጀራ ሳይሸጡ አይቀርም :: ድንግል ማርያም በ 13 አመቱዋ ዋላጆቹዋ ለቤተ ክርስያን ሰጡዋት ፡፡ 13 አመት ደግሞ በ ቤተ ክርስያን ውስጥ ኖረች ። 13 እና 3 ሲደመር አስራ አምስት ይሆናል ።፡በ 15 አመቱዋ ቅድስት ድንግል ማርይም አለማትን በቃሉ ብቻ የፈጠረውን የሁሉ ፈራጅ እና አምላክ እግዚአብሔርን ውለደችልን ።፡ክብር ይግባት አሜን ።


መጸሐፉ ይቀጥላል ፡ የማርያም እድሜዋ ለጋብቻ በደረሰ ጊዜ ውላጆቹዋ ዮሴፍ ለሚባል ለአንድ የከተማው አናጢ ሊድሩዋት ተዘጋጅተው ነበር ያላል መጸሐፉ ።

አስተውሉ ፤ መጸሐፍቅዱስ ይሄንን አይናገርም ። ፕሮቴስታንቶቹ ይሄንን ከየት አመጡት ? ምክንያቱም እነሱ ከ 66ቱ ውጪ ምንም አንቀበልም ብለዋል ይሄም እምነታቸው ነው ። ስለዚህ ይሄንን ታርክ ከየተ አመጡት ? ደግሞ ስለ እናቱዋና ስለ አባቱዋ ሊድሩዋት ነበር ቅብርጥሴ እያሉ የሚያወሩት እንደት አውቀው ነው ?

ወገኖቼ ተመልከቱ ። ይሄ ሁሉ ከመጸሐፍቅዱስ ውጪ የሆነ ትምህርትን ማን እንደሚያስተምር ተመልከቱ ። የ እኛን ቤተ ክርስትያን ለመንቀፍ በጣም ያሰፈስፋሉ ። የ እነሱን ልብ ወለድ የት ደብቀው ነው የ እውነተኛይቱን ቤተ ክርስትያን የሚሰድቡት ። ልብ ያለው ልብ ይበል ።


መጸሐፉ ይቀጥላል ፤ ዳሩ ግን አንድ ቀን ፍጹም ያልተለመደ ነገር ሆነ ፡ ማርያም ስለ ወደፊቱ ሰርግ እያሰበች የተለመደውን የ እለት ስራዋን እየሰራች እያለች ቀና ስትል አንድ እንግዳ ሰው ቆማአል ።

[color=red]አስተውሉ ወገኖቼ ይሄ ሁሉ መጸሐፍቅዱስ ያልዘገበው በሰይጣን መንፈስ የተጻፈ መጸሐፍ ነው ። ሰይጣን ደግሞ ከምንግዜውም በላይ ይደነግጣል ። ምክንያቱም ማታለያው እየታወቀበት ስለሆነ ።

መጸሐፉ አሁንም ይቀጥላል ፤ እርሱም እኔ ከ እግዚአብሄር መልእክተኞች መልአኩ ገብርኤል ነኝ ። እኔም ከ እግዚአብሔር ዘንድ ለአንቺ የሚሆን መልእክት አለኝ አላት ;
ማርያምም ጆሮዋን ማመን አቃታት ። መልአኩም በመቀጠል አትፍሪ እግዚአብሔር ስለ አንቺ ሁሉን ያውቃል … ።

ማርያምም እኔ አልገባኝም ።ምን እኔ ገና አላገባሁም አለችው ይላል ተአምረ ሜሪ ።

አስተውሉ ፡ መጸሐፍቅድስ ላይ ስትሄዱ ግን ቅዱስ ገብርኤል አምላክን ትወልጃለሽ ሲላት ፡ ድንግል ማርያም እኔ ወንድ ስለማላውቅ ይሄ እንዴት ይሆናል ነው ያለችው።
በድንግልና እንደምትኖር ስለምታውቅ ነው ያንን ያለችው ።፡


ወገኖቼ ይሄ የሚያወራው ጸሐይን ስለተጎናጸፈችው ፡፡ጨረቃ ከ እግሮቹዋ በታች ስላሉላት ፡ ክዋክብት ስለ ከበቡዋት ስለ እግዚአብሔርን እናት ስለ ድንግል ማርያም አይደለም ይሄ መጸሃፍ የሚያወራው ። ዲያቢሎስ ሌላ ማርያም ስሎአል።

መጸሐፉ ይቀጥልና እንዲህ ይላል ፤ ማርያምም ይህንን ስትሰማ እግዚአብሔር የሚለውን ነገር ማመን እንደምትችል አወቀች ። ማርያምን ላይገባት ይችላል ግን እግዚአብሔር የሚፈልገውን አደርጋለሁ አለች ። ይላል መጸሐፉ ።

እንግዲህ ይሄ ነው ለልጆች ተብሎ የተዘጋጀው መጸሐፍ ።

እንግዲህ በፕሮተስታንቱ አለም የማርያም ክብር ይህን ይመስላል ። በ እናንተ ፊት ግን እንዴ የጌታችን እናት እኮ ናት እናከብራታለን ሊሉዋቹ ይችላሉ ። የሚያከብሩዋት ግን ተራ ሴት እያሉ ነው ። የሚያከብሩዋት ግን እንጀራ ትሸጥ ነበር እያሉ ነው ። የሚያከብሩው ግን ማርያምን ምንም አይገባትም በማለት ነው ።

እንጀራ ትሸጥ ነበር ፡ እንጨት ትፈልጥ ነበረ ማመን አቃታት ባል ልታገባ ነበር የሚል ከመጸሐፍቅድስ ውስጥ የሌለ የጣሊያን ተረት ተረትን እኛ አንቀበልም ። ይሄም ደግሞ የዲያቢሎስ ግሳት ነው ።

በዚህ መንፈስ የተያዙትን ወገኖቻችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ነጻ ታውጣቸው ። ዲያቢሎስ እንዴት እንደሚጫወትባቸው በሚቀጥለው ትምህርታችንም የምንመለክተው አለ።
የዚህን መጸሐፍ የመጨረሻ ክፍል በጥቂት ቀናት ውስጥ እመለስበታለሁ ።


በሚቀጥለው ክፍላችን ደግሞ የሜሪ መጸሐፍ ማጠቃለያ ፡ ስለ ቅዱስ ገብርኤልና ስለ ቄሱ ዘካርያስ ምን ጻፉ ? ፕሮቴስታንቶች መልአክትን ለምን ይጠላሉ ? እንዲህም ድንግል ማርያም ከዚህ ውጪ ለምን ይጠሉዋታል ? የሚለውን እንመለከታለን ።

በዘወትር ጸሎታቹ አባታችን ሆይ ስትሉ ሐይለ ሚካኤል እያላቹ አስታውሱኝ ።

የ እግዚአብሐር ቸርነት የ እመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት
የጻድቃን የሰማእታት ጸሎትና ምልጃ እንዲህም በረከት
የቅዱሳን መላእክት አማላጅነትና ተራዳይነት ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን።

ወስብሐት ለ እግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር ።
ግሸንማርያም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 366
Joined: Mon Aug 15, 2005 8:11 pm
Location: ethiopia

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests