የተረት ያለህ:- ለልጄ :: የምችላት አለቀችብኝ:-

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የተረት ያለህ:- ለልጄ :: የምችላት አለቀችብኝ:-

Postby ንፋስ » Tue Jan 17, 2006 12:34 am

የተረት ያለህ:- ለልጄ

የምችላት አለቀችብኝ:-
ንፋስ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Thu Dec 29, 2005 1:01 pm

Postby ትትና » Tue Jan 17, 2006 8:34 am

ለልጅዎ

ተረት ተረት
የላም በረት

አንድ በሬና እንቁራሪት ነበሩ:: ሲኖሩ ሲኖሩ አንድ ቀን እንቁራሪቱ በበሬው ትልቅነት በጣም ይቀናና እንዴት እንዲህ ትልቅ ልትሆን ቻልክ ብሎ ይጠይቀዋል::
በሬውም:- እኔ ስፈጠርም ትልቅ ሆኜ ነው የተፈጠርኩት ይለዋል::
እንቁራሪት ግን አላመነውም ስለዚህ እንዲሁ ወደላይ በመነፋፋትና በመንጠራራት ትልቅ የሚኮን መስሎት ወደላይ መለጠጥ(መነፋፋት) ጀመሬ
በሬውም:- እባክህ መንቁራሪት ሆይ እንደዚህ በመነፋፋት እኔን ልታክል አትችልምና ይቅርብህ ብሎ ይመክረዋል::
መንቁራሪቱ ግን አልሰማ ብሎ መነፋፋቱን ቀጠለ ትንሽ ቆይቶ ተወጥሮ ተወጥሮ ተወጥሮ ዷ ብሎ ፈነዳ ይባላል::

አየሽ/ህ ሚሚዮ/ማሙሽዮ የኔፍቅር ያላቅም መንጠራራት ጥሩ አይደለም ደሞም በተሰጠን ነገር ደስተኛ መሆን እንጂ በሌላ ሰው መቅናት ጥሩ አይደለም ለክፉ ይዳርጋል::

አሁን ሳሚኝ/ሳመኝና ወደመኝታ::

ሰላም እደሪልኝ/እደርልኝ የኔ ወርቅ::
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby ንፋስ » Tue Jan 17, 2006 9:04 am

ሰላም እደሪልን :- ከተረት ድህነት ይሰውር::
ንፋስ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Thu Dec 29, 2005 1:01 pm

ተረት ተረት..

Postby አኒታ » Wed Jan 18, 2006 12:52 am

ለሚሚሽሽ ወይም ለባቡሽ..
አንድ አሞራና አንድ ቅል ነበሩ..
ሲኖሩ ሲኖሩ ሲኖሩ ሲኑሩ.
ድንገት ኮሽ አለና
አሞራው በረረ....ቅሉም ተሰበረ ይባላል...
ተረቴን ውሰጂው አፌን በእጅሽ እንዳትነኪው.. ቅቅቅቅ
አየሽ ሚሚ.. ኦር ማሙሽ.. ንፍስ የሆነች እናት/አባት አለህና እንደ አሞራው በረህ ቀነኒሳን ሪከርድ ስበር..
ቺርስ ይቀጥላል...
አክባሪህ/ሽ
አኒታ
ጡረተኞች መሀበር.. የአባባ ተስፋዬ አክስት ቅቅቅቅ...የቼሪ ቅድም አያት :lol:
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Re: የተረት ያለህ:- ለልጄ :: የምችላት አለቀችብኝ:-

Postby እንሰት » Wed Jan 18, 2006 2:18 am

ንፋስ wrote:የተረት ያለህ:- ለልጄ

የምችላት አለቀችብኝ:-

ሊንኩ ጠፋኝ እንጂ እዚህ ዋርካ ላይ የአለቃ ገብረሀና ተረቶች አሉልህ አትምና ለልጅ የሚሆነውን እየመርጠክ ተርክለት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ንፋስ » Thu Jan 19, 2006 8:38 am

ሰላም አኒታ:- እንዴት ነው ለልጄ ስል የጡረተኛ ማህበር አባል የምሆነው :lol: በጣም አመሰግናለሁ::

ትትና ና እንሰትም እነሆ ምስጋናዬ::
ንፋስ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Thu Dec 29, 2005 1:01 pm

ተረት....ተረት

Postby ፋብል » Thu Jan 19, 2006 9:37 am

አንድ እጅግ የራበው ውሻ ነበር:: ምግብ ፍለጋ ብዙ ከዞረ በሁዋላ አንድ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ጥሩ ስጋ ያለው አጥንት አገኘ:: ያገኘውን ሌሎች መጥተው ይካፈሉኝ ይሆናል ብሎ ስለሰጋ ተደብቆ ለመብላት ረጅም ጉዞ ጀመረ:: በመንገዱ ላይ አንድ ወንዝ አጋጠመውና ሊሻገር ሲል ሌላ ጥሩ ስጋ ያለው አጥንት የያዘ ውሻ አየ:: የውሻውን አጥንት ቀምቶ መብላት በጣም ስላማረው አፉን ሲከፍት ስጋው አምልጦት ወንዙ ይዞት ሄደ - ጥሩ ስጋ ይዞ ያየው የራሱን ምስል ነውና::

ተረቴን ተማ(ሪ)ርበት ;. የአፌን አዳምጥ(ጭ)በት::
ፋብል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 22
Joined: Tue Jan 17, 2006 8:11 pm

Postby ማህቡብ » Thu Jan 19, 2006 9:50 am

ለሚሚ/ለሙጩ

ታሪኬ ባጭሩ.......

ሰኞ ተረግዠ ማክሰኞ ተወለድኩ እሮብ ክርስትና ተነሳሁ
ሀሙስ ትምህርት ቤት ገባሁ ....... :lol: :lol: :lol:

ከአክብሮት ጋር
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 265
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests