በህይወት ለመጀመሪያ ጊዜ ስላፈቀርነው ወንድም ሆነ ሴት እናውጋ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

በህይወት ለመጀመሪያ ጊዜ ስላፈቀርነው ወንድም ሆነ ሴት እናውጋ

Postby ጣሴ » Tue Jan 17, 2006 1:15 pm

በእውነት ነው ምላቹሁ በህይወቴ የዛሬ 14 አመት ገደማ በጣም የምወዳት ቆንጅዬ ሴት ገጠመችኝ እሳን ለማገኘት ያልሆንኩት ያልደረሰብኝ ስቃይ የለም እኔ 18 ቀበሌ ልጅ ስሆን እሳ የ42 ቀበሌ ልጅ ናት በመሀላችን አስፓልት ነው ሚለየን ምንም የደሀ ልጅ ብትሆንም ለኔ ልዩ ሴት ነበረች እስካሁንም ለኔ ልዩ ናት ትዝ ይለኛል የዛኔ በኢት..አቆጣጠር በ1986አ.ም የ8 ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ እሳን ካየሁ በሀላ ሚኒስትሪ ሁለት ጊዜ ወድቅያለሁ ሀሳበ ሁሉ እሳ ጋነበር ቤቴ ውስጥ ሆኔ መሽቶ እስኪ ነጋ በጣምም ይጨንቀኝ ነበር በሳ ጉዳይ ካልተጣላሁት ጎረምሳ የለም እሳን ለማግኘት በራሴ ላይ ትልቅ ችግር እየፈጠርኩ ሄድኩ ከቤተሰብ ጋር ያለመስማማት ተፈጠረ ጸባዬ ሁሉ ተቀየረ ቤተሰቦቼ እኔን ይናፍቁኝ ጀመር ውሎዬ ከሳ ጋር ሆነ ጠዋት እነሳና ወደሳ ሰፈር እቤታቸው ፊትለፊት መገተር ሆነ ስራዬ ታሪካን ስታጫውተኝ ለሳ ልገልጽላት የማልችለው ፍቅር ያዘኝ እንቅልፍ ነሳችኝ ቤቴ ውስጥ ምንም ነገር አልጥም አለኝ የሚያሳስበኝ ምን ጊዜም የሳ ችግር ብቻ ነው ስለቤተሰቦቻ ጠይቅያት እናታ በህይወት አለመኖራቸውን እህት ወንድም እንደሌላት አባታ በፖለቲካ ችግር እስር ቤት መሆኑን እና በእንጀራ እናት መቅረታን ገለጸችልኝ እንጀራ እናታም በጣም እንደምትበድላት ነገረችኝ እኔም አይዞሽ ከጎንሽ ነኝ እላት ነበር እንጀራ ናታ እንጀራ በመጋገር ሲሆን ኑራቸውን ሚገፉት ልጅታ ደግሞ የተጋገረውን እንጀራ አምጥታ እኛ ሰፈር ነበር ምትሸጠው አንድ ቀን ትዝ ይለኛል በጣም ስለምወዳት ፎቶ በቀለ ሄደን ፎቶ አብረን መነሳት አለብን ብያት ቀጠሮ ይዘን ሄደን በሀይለኛው ሁለት የቁም ፎቶ ጭንቅላት ለጭንቅላት ተደጋግፈን ተነሳን የዛን ቀን ማዘራ ሀይለኛ ቁጥጥር ይቆጣጠራት ስለነበር ጉሊት ፈልገው አጣት መሰለኝ ለሶስት ቀን ያህል መምጣት ተወች ምን ይዋጠኝ የዛን ቀን የጀመረኝ በሽታ ልክ እንደ እርጉዝ ሴት ጠናብኝ በጣም ተረበሽኩ ምሽት ያበሳጨኝ ጀመር የዛን ጊዜ ከምሽት ይልቅ ንጋትን ብቻ እመርጥ ነበር ሲነጋ አድፍጬ በራቸው ላይ መጎለት ጀመርኩ በጠዋት እየተነሳው ብቻ ከሶስት ቀን በሀላ ወደመደበኛው ስራዋ ተመለሰች እኔም መንገድ ላይ እየጠበካት የያዘችውን መሶብ በጭንቅላቴ እየተሸከምኩላት ወደ ገበያው ማድረሴን ተያያዝኩት የያዘችው እንጀራ እንዳያድር ብዙ እጥርላት ነበር ብቻ ቅቅቅቅ ገበያተኛ ሲመጣ ሰርገኛ ነው ቀጭ ቀጭ አይልም አረ ጥሩ እንጀራ ነው ማለቱን ተያያዝኩት ተመስገን እንጀራውም ቶሎ ቶሎ ማለቅ ጀመረ በንደዚህ አይነት ሁኔታ በጣም እንዋደድ ጀመር ትምህርቴን ብዙም መከታተል ትቻለሁ በመሀል አንድ ቀን አባቴ የክፍለ ሀገር ሹፌር ስለነበር ነብሱን ይማረው ሞሰባን ተሸክሜላት ያየኛል አይቶኝ እንዳላየ ሆኖ አለፈኝ ወደቤት ገባ እኔም በጣም ደነገጥኩ መኪናውን ሳየው ቶሎ እሳን አድርሼ ተመልሸ ቤቴ ገባሁ ሰላም አልኩት እሱም ሰላም አለኝ በጣም ሀይለኛ ስለነበር ሁላችንም እንፈራዋለን ሰላም ካለኝ በሀላ ምን እንዳለኝ ታውቃላቹሁ ስማ ልጄ አልታይም ብለህ ከምትሰራው ስራ እታያለሁ ብለህ ብትተወው ይሻልሀል ብሎኝ ዝም አለኝ እኔም እሺ አልኩት እያሳሳቀ ነበር የተናገረኝ ፋዘርም አንድ ቀን አድሮ ወደስራው ሄደ እኔም በጣም ስለምወዳት በወቅቱ አንድ እንጀራ ዋጋው ስሙኒ ነበር አጠገባ ስራ እየተቀመጥኩ የአንድ ብር ከሰባ አምሳንቲም እንጀራ አጠገባ ቁጭ ብዬ እየገዛሀት እበላ ነበር እኔም እሳም ሆነን በቃ ምን ልበላቹሁ እኔ ግን በዛን ሰአት ለፍቅራችን መስዋት መክፈሌ ነው እንሸጥና እንጀራውን ካላለቀ ችግር እንደሚደርስባት ስለማውቅ በቃ እኔው እራሴ እየገዛሁ አብረን ሜዳው ላይ እንበላ ነበር ቁንጣን እስኪይዘን ድረስ በእውነት ነው ምላቹሁ ከሳ ጋር በንደዚህ አይነት ኑሮ ስንገፋ ከርመን እንደተለመደው አባቴ ምን ያህል ሀይለኛ እንደሆነ ነግርያቹሀለሁ እኔ በሌለሁበት ወንድሜን ደብተሩን አምጣ ይለዋል የሁለታችንንም የኔን ደብተር ሲከፍተው ውስጡ የኔንና የሚሚን ፎቶ ያየዋል ልክ እንደፈረደብኝ ወደ ቤት ስገባ ቤቱ ጸጥ ጭር ብላል ማን የት ምኑጋ እንዳለ አይታየኝም ከውጪ ስለገባሁ የሰማሁት ያባቴን ድምጽ ብቻ ነው እሱም ናአ ናአ ወደዚህ የሚል እኔም አቤት ብዬ ገባሁ የቤቱ በር ተቆለፈ ጎረቤት መጥቶ እንዳይገላግለን :cry: :cry: :cry: ከዛው አምጣ ደብተሮጭን አለኝ አመጣሁለት ትምህርት ለምድነው ማትማረው የኔ ጎረምሳ ብሎ ተውኝ ዋጋዬን ሰጠኝ ቦታ ሳይመርጥ አገራችን ትዝ ካላቹሁ ብረ ምጣድ አለ በጣሳ ሻውር መውሰጃ እሱ ላይ ሳሙና አረፋ ተመታና እዛ ላይ ሆኜ የዱላ መአት ወረደብኝ ብድግ እያልኩ ቁጭ ብረምጣዱ ላይ ሆኜ በመጨረሻም ዱላውን ስላልቻልኩት በጣም ስለበዛብኝ ቤት ውስጥ በገመድ ታስሬ ስለነበር እንደበግ ቤት ውስጥ መቀመጥ ስላልቻልኩ የታሰርኩትን ገመድ በጥሼው እሳን ፍለጋ ወደሰፈራ ሄድኩኝ በወቅቱ ስነግራት በጣም አዘነች አለቀሰች የት አባቴ ልውሰድህ አለችኝ በወቅቱ እሳም ሆነች እኔም ችግር ላይ ነን ያለነው ምንም ገንዘብ አልነበረኝም ከእንጀራው ሂሳብ ላይ አጉድላ 3ብር ሰጠችኝ ከዛው ዘመድጋ ሄድኩ ለምን እሳን ማየት ነብሴ ይፈልጋል ግን ሊመጣ የሚችለውን ችግር እያሰብኩ ብዙ ጊዜ ሆነን ከሳም ከቤተሰብ ጋርም ሳንገናኝ እዚህ ያለሁበት አገር እህት ነበረችኝ ደብዳቤ ጽፌላት ሁሉንም ነገር ጨረስኩ ከአገር ለመውጣት ሁለት ቀን ሲቀረኝ ይቅር ይቅር እንድንባባል ከቤተሰብ ጋር አስታረቁኝ እሳንም አግኝቻት በጣም አዘነች መቼ እዛ ቴሌፎን ችግር ታውቁታላቹሁ በስደት ላይ ሆነን ሶስት ጊዜ አቀረቡልኝ በአራተኛው እንዲህ አይነት ስም አናውቅም ይሉኛል እና የመጀመሪያ ፍቅር አያድርስ ነው የአንድ ብር ከሰባምሳንቲም እንጀራ በየጊዜው ያስበላል ብላቹሁ አታምኑኝ ይሆናል እና እናንተም የደረሰባቹሁን እስኪ ጻፉት ወደዚህ ለመራሽኝ እህቴ እድላዊት በጣም ነው ማመሰግንሽ አክባሪሽ ጣሴ ጣሱካካካ
ጣሴ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Wed Dec 29, 2004 4:44 pm
Location: united states

Postby ጫልቱዬ » Tue Jan 17, 2006 1:23 pm

ጣሱካ እንደገና ባነበውም ግን ታሪኩ አሳዛኝም አስቂኝም ነው እንጀራ በቁንጣን ስትበላ አሳዘንከኝ እስቲ አስበው እንጀራው ስሙኒ ከሆነ አንተ በቀን የስዋን ንግድ ለማጦፍ የብር ከ75 እየበላህ ግን ደረቁን ነበረ
በሳቅ ነው የሚትኩት ሳነበው ግን ፍቅር እኮ ያለው እንደውም እንደዚኢ አይነት ሰው ጋር ነው ግን እስቲ ይቺን የመጀመሪያ ፍቅርህን አፈላልጋት ለትዳርም ሳይሆን የሚያሳዝን ላይፍ ነበራት ብዙ አጫውተሀኛል
በል በርታና በደንብ እዚም አጫውተን
አክባሪህ ጫላ ከጫንጮ
this is hilinayeeeee i love all
ጫልቱዬ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Sat Jul 16, 2005 3:48 pm
Location: ethiopia

ፍቅር በፍቅር ሲጣፋ መልሱ የለም

Postby dgcom » Tue Jan 17, 2006 1:48 pm

አንድ ጊዜ እግር ጥሎኝ ከነጣሴ ሰፈር ስደርስ አጎንብሳ ማሽላ ስታበጥር የነበረች ልጅ በድንገት አቓቓሟ ቀልቡዋ ሳበኝ ተወርውሬ እንደ ጦር ጠጋ ብዬ ለመጠየቅ ሞከርኩ በድንገት ቀና ብላ በገለባ የተዋበው ፊቷ በፎሮፎር ያጌጠው ጸጉሯ ብታሳየኝ የመውደድ ቴምፕሬቸሬ ተነሳ ከዚያም ፈጠን ብዬ በአራዳ የገበሬ እግር የመሰለው መዳፏን የሙጥኝ ብዬ ጛደኛ ከሌለሽ ላስተዳድርሽ ብላትስ <መጫት >
ነኝ ብላኝ የጣሴን የተጨመቀውን ሱሪ ይዛ ለጣሴ መቅሰስ ልትሰራለት ገባች እኔም የጣሴ እህት መሆኑዋን ተረድቼ በሁለተኛ ዙር እንደምመለስ እርግጥ አርጌ ከመንደሩ ተሰወርኩ ከዚያን ቀን ወዲህ ፍቅር አንድ ብሎ ጀመረኝ
dgcom
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 278
Joined: Thu Jan 20, 2005 4:44 pm
Location: ethiopia

Re: ፍቅር በፍቅር ሲጣፋ መልሱ የለም

Postby ጫልቱዬ » Tue Jan 17, 2006 1:52 pm

dgcom wrote:አንድ ጊዜ እግር ጥሎኝ ከነጣሴ ሰፈር ስደርስ አጎንብሳ ማሽላ ስታበጥር የነበረች ልጅ በድንገት አቓቓሟ ቀልቡዋ ሳበኝ ተወርውሬ እንደ ጦር ጠጋ ብዬ ለመጠየቅ ሞከርኩ በድንገት ቀና ብላ በገለባ የተዋበው ፊቷ በፎሮፎር ያጌጠው ጸጉሯ ብታሳየኝ የመውደድ ቴምፕሬቸሬ ተነሳ ከዚያም ፈጠን ብዬ በአራዳ የገበሬ እግር የመሰለው መዳፏን የሙጥኝ ብዬ ጛደኛ ከሌለሽ ላስተዳድርሽ ብላትስ <መጫት >
ነኝ ብላኝ የጣሴን የተጨመቀውን ሱሪ ይዛ ለጣሴ መቅሰስ ልትሰራለት ገባች እኔም የጣሴ እህት መሆኑዋን ተረድቼ በሁለተኛ ዙር እንደምመለስ እርግጥ አርጌ ከመንደሩ ተሰወርኩ ከዚያን ቀን ወዲህ ፍቅር አንድ ብሎ ጀመረኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
this is hilinayeeeee i love all
ጫልቱዬ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Sat Jul 16, 2005 3:48 pm
Location: ethiopia

Postby ጣሴ » Tue Jan 17, 2006 2:03 pm

ጫልቱዬ wrote:ጣሱካ እንደገና ባነበውም ግን ታሪኩ አሳዛኝም አስቂኝም ነው እንጀራ በቁንጣን ስትበላ አሳዘንከኝ እስቲ አስበው እንጀራው ስሙኒ ከሆነ አንተ በቀን የስዋን ንግድ ለማጦፍ የብር ከ75 እየበላህ ግን ደረቁን ነበረ
በሳቅ ነው የሚትኩት ሳነበው ግን ፍቅር እኮ ያለው እንደውም እንደዚኢ አይነት ሰው ጋር ነው ግን እስቲ ይቺን የመጀመሪያ ፍቅርህን አፈላልጋት ለትዳርም ሳይሆን የሚያሳዝን ላይፍ ነበራት ብዙ አጫውተሀኛል
በል በርታና በደንብ እዚም አጫውተን
አክባሪህ ጫላ ከጫንጮ
አይ ጫላ ጫላ ብሎ ጉራጌ አላየሁም የዛን ጊዜ እንጀራ ስሙኒ ከሆነ :lol: የብር ከሰባ አምሳንቲም አይደለም የ350 ቢበላ ምን አለበት ደግሞ የሳን ንግድ ለማጣጣፍ ደረቁን የንጀራው ስም ደረቅ እንጀራ ይባል እንጂ እንጀራው ውስጥ የሚገኘው ሚሚ የተባለ ድብቅ ጣፋጭ ንጥረ ነገር አለው ስለአስተያየትሽ በጣም ነው ማመሰግነው ፍቅርም ላይፍም ከመጀመሪያ ጋር ደስ ይላል ላልሽው በጣም አመሰግናለሁ አክባሪሽ ጣሴ ጣሱካ ካካካካካካአካካአ :D
ጣሴ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Wed Dec 29, 2004 4:44 pm
Location: united states

ውይ ጣስዬ ምስኪኑ

Postby ብጡ » Tue Jan 17, 2006 3:01 pm

ሀይ ጣስዬ እንደምን አለህልኝ የኔ ጣሱካ ካካካካ
ኦ! ታሪኩ በጣም ነው ያሳቀኝ እንዲሁም ያሳዘነኝ:: በእውነት እንዴት የሚያሳዝን ነገር ነው::
ጣስዬ! ቆይ ግን ለምን በቤተሰቦች ህ በኩል እንዲያገኛት አታደርግን ዛሬ እኮ እራስህን ችለሀል እና አድራሻዋን ይቀበሉና ይንገሩህ የሚሆነውን ነገር አድርግ::

ግን ከምር ሰው ጉድ እስኪለኝ ነው ያሳኩት ታውቃለህ አብሶማ 1ብር ከ75 ሳንቲም እንጀራ ለዚያውም ደረቁን ስትበሉት ቅቅቅ ለነገሩ ሚሚዬ ማወራረጃ አለች ልህ ሲያንቅ እሳን ሳም ታደርግ እና በምራቍዋ ትውጣለህ ቅቅቅቅ::
ቴንኪው ግን ሀሳብህን ስላካፈልከን:;

ቡጡ ቀብጥ ነኝ
ብጡ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 12
Joined: Mon Sep 13, 2004 2:34 pm
Location: united states

Postby ማህቡብ » Tue Jan 17, 2006 5:00 pm

ሠላም :- ወንድም ጣሴ
በጣም አስደሳች እና አሳዛኝ የፍቅር ገጠመኝ ነበር :: ሚሚ እውነተኛውን ፍቅር ነበር ያካፈለችህ.... የተደበቀ የመንፈስ ሀብትህ ሆኖ እንዲኖር ::

"" እውነተኛ ፍቅር የምትገኘው ጎንበስ ብለው ከሚገቡባት ደሳሳ ጎጆ ነው ""

ከአክብሮት ጋር
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 265
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Re: ፍቅር በፍቅር ሲጣፋ መልሱ የለም

Postby ጣሴ » Tue Jan 17, 2006 5:05 pm

dgcom wrote:አንድ ጊዜ እግር ጥሎኝ ከነጣሴ ሰፈር ስደርስ አጎንብሳ ማሽላ ስታበጥር የነበረች ልጅ በድንገት አቓቓሟ ቀልቡዋ ሳበኝ ተወርውሬ እንደ ጦር ጠጋ ብዬ ለመጠየቅ ሞከርኩ በድንገት ቀና ብላ በገለባ የተዋበው ፊቷ በፎሮፎር ያጌጠው ጸጉሯ ብታሳየኝ የመውደድ ቴምፕሬቸሬ ተነሳ ከዚያም ፈጠን ብዬ በአራዳ የገበሬ እግር የመሰለው መዳፏን የሙጥኝ ብዬ ጛደኛ ከሌለሽ ላስተዳድርሽ ብላትስ <መጫት >
ነኝ ብላኝ የጣሴን የተጨመቀውን ሱሪ ይዛ ለጣሴ መቅሰስ ልትሰራለት ገባች እኔም የጣሴ እህት መሆኑዋን ተረድቼ በሁለተኛ ዙር እንደምመለስ እርግጥ አርጌ ከመንደሩ ተሰወርኩ ከዚያን ቀን ወዲህ ፍቅር አንድ ብሎ ጀመረኝ
:evil: :twisted:እኝኝኝኝ ምነው ወዳጄ በዚህ አባባልህ ብዙ ነገር ተምርያለሁ ጠላት መስለህ ወዳጅ መሆንህን አረጋግጫለሁ የጣሴ እህት ላልከው ደግሞ :twisted: :evil: ተሳስተሀል እህቶቼን ሰብስቤ ደጄኔ የሚባል ሰው አፍቅራቹሀል ብዬ ብጠይቃቸው ህም ያመዋል አረ ደጄኔ የሚባል ጋደኛ የለንም ነው ያሉኝ ምናለ ባረገልህ ከእህቶቼም አልፌ ጎረቤትም ጠየኩ ልህ ለምን ብትል ሰው በፍቅር ሲሰቃይ እኔ ወንድምህ ማለፍ አልወድምና ብታምንም ባታምንም ላንተ ብዙ ደክምያለሁ ግን እንዲዋጥልህና እንድታምነኝ የምፈልገው እኔ ጣሴ በዘራችን ፎሮፎር የሚባል ነገር የለብንም አንተ ፎሮፎር ትላለህ :D :D :D ጸጉረ ከርዳዳም የለብንም ወደራስህ ጉዳይ ልመለስና እህቴ መስላህ ያፈቀርካት ሰራተኛችንን ነው :D :D :D ይሄን በማወቄ ደስስስስ ብሎኛል የጣሴ እህት ነኝ ያለችው ደግሞ ቅቅቅቅ እራሳን መስቀል ስለፈለገች ብቻ ነው አንተ አልገባህም እንጂ እሳ የመውደድ ቴምፕሬቸርህን ለማነቃቃት ነው :D :D :D የኔ ሞኝ ታድያ የነ ጣሴ ሰራተኛ ነኝ ልትልህ አምሮሀል አትሳሳት የሳ ቆንጆ አየህ ጎበዝ ፍቅር ቦታ አይመርጥም ይልሀል እዚህ ላይ ነው :D :D :D ወዳጅህ ጣሴ ጣሱካ የኩባያው ጋደኛ ነኝ :evil: :twisted: እኝኝኝኝ
ጣሴ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Wed Dec 29, 2004 4:44 pm
Location: united states

Postby ጫልቱዬ » Tue Jan 17, 2006 5:16 pm

ጣሱካ እንግዲ የኔን አሶርተሽ ያንቺን ዝም አልሽ እንዳትለኝ ትንሽ ስለመጀመሪያው ፍቅሬ ስለገበየው ላውጋህ በጥቂቱ
ይሀውልህ ገበየው በጣም የልጅ አዋቆ ታታሪ ልጅ ነበረ እና ጫማ ይጠርጋል ሰፈራችን እና በቃ ፎንቃ ጥልፍ አርጎኝ ይቺን ሰንደል ጫማየን ሳስጥርግ ነው የምውለው ነበር ገበየው እንጀራውን እንጂ እኔን ከምን ቆጥሮ ለመን በቀን 4 ግዜ ጫማዋንስ ታስጠርጋለች ብሎ ወደዋላ መለስም ብሎ አላሰበም ነበር በቃ ሲብስብኝ አፍረጥርቼ ነግሬው ቡጥዬን ታቃት የለ ለስዋ ደብዳቤ አሲዠ ልኩዋት
በቃ ከዛማ ምን ልበልህ የኔና የገበየው ፍቅር ውይይይይይይይይይይይይ በቃ እና የማረሳው በቃ እንዳልኩህ ልጁ ታታሪ ነው እዛው ከሊስትሮው አጠገብ አሹቅ መሸጥ ጀመረ እና ይህን አሹቅ በፍሊት ክዳን የ50 የ50 እየገዛን ስንለው እናመሻለን
እናም እቤት የነቁብኝ ለሊት አልቻሉኝም በቃ ድምጽ የሌለው መሳሪያ ስተኩስ ነው የማድረው ነበር የኔና የገበየው ፍቅር አይረሳም ውይይይይይይይይይይይይይ እንባ እንባ አስባልከኝ ግን ገበየውን ባረሳውም ያስከተለብኝ የሆድ እቃ መታወክ እስከዛሬ አብሮኝ አለ የገበየው ማስታወሻ በል ይህን ያህል ካልኩህ ደሞ ሌላውን በ ፒኤም አጫውትሀለው
ጫላ ከጫን :lol:
this is hilinayeeeee i love all
ጫልቱዬ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Sat Jul 16, 2005 3:48 pm
Location: ethiopia

Postby ጃንሚዳ » Tue Jan 17, 2006 10:11 pm

:lol: :lol: ወዳጄ ጣሴ ጎረምሳ እያለክ ነው ይሄ ይህ የሆነው
በጣም ይገርማል :!: ዕኔ እንኳን ደሜ የተንተከተውው በአባትህ ላይ ነው :!: ዕንደው ስንት ዕንጀራ ቢበላ ነው :?: ዕንዲህ ዕንደቀበሌ የኳስ ቡድብ ብረት ምጣድ ላይ ሻወር ያስወሰደህ :lol: አንተ እንኳን ስንት እንጀራ እንደምትበላ ከነዋጋው ነገርከን ይሄ መኪና ዘዋሪ ፋዘረህ ግን ስንት ዕንጀራ ቢበላ ነው :?: ደግሞስ ሌላው ቢቀር ከናንተ እንዳይገዛ ማዕቀብ አታደርጉበትም ነበር::አይዞህ የደረሰብህን በደል ሁሉ ለአጋዚ ጦር ነገሬ ፋዘርህን ደዴሳ ወይንም አንድ ቦታ ወስደን እንመረምራለን ብለውኛል::
ወዳጅህ ጎረምሳው ነኝ ፊርማዬ ችክችክችክችክችክች
ጃንሚዳ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 414
Joined: Tue Apr 06, 2004 10:19 am
Location: sao tome and principe

Postby ማህቡብ » Wed Jan 18, 2006 9:03 am

ግንቦት 12 1976 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር
....... በውስጤ ልታልቅ የተቃረበችዋን የተስፋ ጭላንጭል በልቤ ቁዋጥሬ ነበር ወደ ቀጠሮየ ቦታ ለመሄድ ዝግጅት ያደረግኩት ::

እንዲህ ነበር ልቤ ውስጥ ያለው የፍቅር ወላፈን ቀስ በቀስ መላው አካላቴን እንደሚያዳርሰው እና ፍቅሩዋን የተጠማው
ልቤ የድሉ ባለቤት እንደሚሆን በመተማመን ነበር ጉዞየን
የቀጠልኩት :: ልቤ ከቦታዋ መውጣት እንደፈለገች የምታሰማው ትርታ በግናባሬ ከሚወርደው ላብ ጋር ተዳምረው ደህና መሆኔን ያጠራጠራት ገነት ምነው በደህና
ነው ስትለኝ ነበር ቀጠሮ ቦታው መድረሴን በውል ያወቅኩት

ይቀጥላል
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 265
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ጫልቱዬ » Wed Jan 18, 2006 10:41 am

ማህቡብ wrote:ግንቦት 12 1976 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር
....... በውስጤ ልታልቅ የተቃረበችዋን የተስፋ ጭላንጭል በልቤ ቁዋጥሬ ነበር ወደ ቀጠሮየ ቦታ ለመሄድ ዝግጅት ያደረግኩት ::

እንዲህ ነበር ልቤ ውስጥ ያለው የፍቅር ወላፈን ቀስ በቀስ መላው አካላቴን እንደሚያዳርሰው እና ፍቅሩዋን የተጠማው
ልቤ የድሉ ባለቤት እንደሚሆን በመተማመን ነበር ጉዞየን
የቀጠልኩት :: ልቤ ከቦታዋ መውጣት እንደፈለገች የምታሰማው ትርታ በግናባሬ ከሚወርደው ላብ ጋር ተዳምረው ደህና መሆኔን ያጠራጠራት ገነት ምነው በደህና
ነው ስትለኝ ነበር ቀጠሮ ቦታው መድረሴን በውል ያወቅኩት

ይቀጥላል


ማህቡብዬ አንተንም አናዘዘህ አይደል የጣሱ ትዝታ በል ጨርሰው አክባሪህ እህትህ ጫልቱ
this is hilinayeeeee i love all
ጫልቱዬ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Sat Jul 16, 2005 3:48 pm
Location: ethiopia

Postby ጣሴ » Wed Jan 18, 2006 11:47 am

[quote="ጃንሚዳ"]:lol: :lol: ወዳጄ ጣሴ ጎረምሳ እያለክ ነው ይሄ ይህ የሆነው
በጣም ይገርማል :!: ዕኔ እንኳን ደሜ የተንተከተውው በአባትህ ላይ ነው :!: ዕንደው ስንት ዕንጀራ ቢበላ ነው አይዞህ የደረሰብህን በደል ሁሉ ለአጋዚ ጦር ነገሬ ማነው ስምህ እንካን ማነህ ቸክቸክቸክ ችክ አትበል በቅድሚያ ለመቸክቸክ የቾከልክ ትመስላለህ ጃንሚዳ ነህ ስምህ ባህሪህን ይገልጻል የኛ ለፍርድ ቾካይ ለነገሩ ደምህ መንተክተኩ ላንተ ከባድ ነው ለምን ብትል ያለ አባት ነው ያደከው መሰለኝ :lol: እኛ ግን በዚህም በዚያም ያባትን ፍቅር አይተነዋል :: :D ምታሳዝነው ግን አንተ ነህ አባቴን ለአጋዚ አሳልፈህ ልትሰጠው ማሰብህ አይይይ ከነሱም ለይቼህ አላይህም ለምን መአቀብ አትጥሉበትም የስንት እንጀራ ቢበላ ነው ላልከው እንዳንተ ያለ አባት አላደኩም እሱ በሰጠኝ ገንዘብም ነበር በብር ከሰባ አምሳንቲም እየገዛሁ ለፍቅርቻን መስዋት ስሆን የነበረው ነብሴ በተረፈ ነዘነዝኩህ መሰለኝ ግን አንድ ነገር ልምከርህ አባት ያለህ አይመስለኝም እና ያሳደጉህን ሰዎች አባቴን አሳውቁኝ ብለህ ጠይቃቸው ያባትን ፍቅር ማወቅ አለብህ አይ እንዳንተ ይደበድበኛል ብለህ አትፍራ ከኔ ታሪክ በይበልጥ ያንተ ያለ አባት መቅርት ያሳሰበው ጣሴ ጣሱካ የ ኩባያው ጋደኛ ነኝ
ጣሴ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Wed Dec 29, 2004 4:44 pm
Location: united states

ህይ

Postby ኤፌሶን » Wed Jan 18, 2006 12:57 pm

ሀይ ጣሱካካካካ እንዴት ነህልኝ የኔ አመዳም በናትህ ከምር ነው ይሄ ታሪክ እስኪ ዐዎ በለኝና ልደሰት እንዴት የሚያስደስት ታሪክ መሰለህ ያስነበብከን እኔ በበኩሌ መጀመሪያ ሳኩኝ ትንሽ ቆይቼ ደሞ አንጀቴን በላህው በቃ ግን ከምር ደስ የሚል ነገር ነው ጣሱካ ሙት እውነተኛ ከሆነ ማለት ነው በርግጥ ትሩ ፍቅር ነው ልጄ በአንድ ቀን ሰባት እንጀራ ያውም ደረቅ የሚያስበላ ሆ ሆ ፍቅር ሁሉን ይችላል ፍቅር ይታገሳል የሚባለው ለካ እውነት ነው ለነገሩ እውነተኛ ፍቅር የሚገኘው ከፍሰሀ አዳራሽ ሳይሆን ዝቅ ብለው ከሚገቡባት ደሳሳ ጎጆ ነው የሚባለው ነገር ለካ አለ ከምር ግን አንድ ጥያቄ ጣሱ ከልብ አሁንም የምታስባት ከሆነ ለምን አትፈልጋትም ምን ችግር አለው ምልህ ከልብ ካለቀሱ ነውና እስኪ ሞክር በናትህ የልጅነት ፍቅር እኮ እጅግ በጣም ጣፋጭ ነው ፕልስ ጣሱ ፈልጋት
አክባሪህ ኤፊ
ኤፌሶን
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 64
Joined: Mon Aug 23, 2004 12:56 pm
Location: united states

Postby ማህቡብ » Thu Jan 19, 2006 7:46 am

ካለፈው የቀጠለ

ገነት ሀይለሉል ነበረች የመጀመሪያውን ፍቅር ያካፈለችኝ
ከገነት ጋር አንድ ክፍል ላይ የምንማ ቢሆንም ዛሬ ግን በልቤ
ለረጅም ጊዜ ደብቄው የነበረውን ቃል ልተነፍስላት ወስኛለሁ
ችግሩ እንዴትና ከምን ነው የምጀምረው ? ያለኝን ሀይል በማሰባሰብ ገኒ በማለት ጀመርኩ
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 265
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests