The Da Vinci Code Vs Passion Of Christ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

The Da Vinci Code Vs Passion Of Christ

Postby እሾህ » Thu Jan 19, 2006 3:02 am

ብዙም ሳይቆይ በፊት የወጣው ስለ እየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻ ሰአታት የሚያትተው Passion Of Christ ሞሽን ፒክቸር ከሚገባው በላይ ውዝግብን ያስነሳ እስካሁንም ክርክሩ ያልበረደለት ፊልም ነው:: ፊልሙን ዳይሬክት ያደረገው በ mad max, lethal weapon 1-4, breave heart በመሳሰሉት ፊልሞች መሪ ተዋናይ ሆኖ በመጫወት አድናቆትን ያተረፈው ጥብቅ ካቶሊክ እምነት ተከታይ እንደሆነ የሚነገርለት ሜል ጊብሰን ነው:: ፊልሙ በአብዛኛው ክርስትያን እምነት ተከታይ ዘንድ ይበል አሰኝቶ አድናቆትን ሲጎናጸፍ በአንጻሩ ሆሊውድን ከውልደት እስከጉልምስናው አሁን ድረስ እንዳሻቸው የሚያሽከረክሩትን ጨምሮ በመላው አይሁዳውያን ዘንድ ከባድ ምት አሳርፎባቸው ቁጣቸውን አሰምተዋል:: ምክኒያቱም በግልጹ ፊልሙ ላይ እንደሚታየው አይሁዳዊያንን እየሱስ ክርስቶስን አሳልፈው የሰጡ መጥፎ ህዝብ የክህደት ተምሳሌት አድርጎ አግዝፎ አስቀምጦዋቸዋልና ነው::ሜል ጊብሰን ጎበዝ ልባም የስነጥበብ ሰው ለመሆኑ ግን ሳላደንቀው አላልፍም:: ምንም እንኳን ለክርስትና ካለው ቀናኢነት ያልሆነ በሚመስል ሌላ አላማ/ አዝማሚያ ፊልሙን ቢያዘጋጀውም ያን ፊልም ለማዘጋጀት ከራሱ ኪስ እያንዳንዱን ወጪ በማውጣት ሪስክን የወሰደ አልፎ ተርፎም ፊልሙን ሙሉ ለሙሉ የዛን ወቅት እስራኤላዊያን ቋንቋ በነበረው አራማይክ ቋንቋ መሰራቱ ፊልሙ አትራፊ ይሆናል ወይ የሚል መጠይቅን ቢጭርም ባልተጠበቀ መንገድ ከፍተኛ ገቢን እጥፍ ድርብ አድርጎ ዝቆበታል:: ከራሱ ፍራንክ መድቦ የሰራበት ምክኒያቱ እንደ paramaount pictures, warner bros, columbia pic. ያሉ እያንዳንዳቸው የፊልም አምራች ኩባኒያዎች ይዞታቸው ፊልሙ ለጥቃት ያነጣጠረባቸው አይሁዳዊያኖች ስር ስለሆነ ነበር:: እነሱ ልጄ the pianist, jacob the liar, schindeler's list ያሉ ስለሆላኮስት የሚያትትቱ ከንፈር አስመጣጭ ፊልምን እንጂ እንዲህ እንዲህ አይነቱን ይጎመዝዛቸዋል እናጀውም ወደኪሳቸው ለመላክ አይደፍሩም:: እንግዲያው ከላይ በተንተን አድርጌ ያነሳሁት ነጥብ ወደዋናው ቲዎሪዬ ይምራኝና እንደሚታወቀው ባለፈው አመት በኒውዮርክ ታይምስ ቤስት ሴለር ሆኖ አለማቀፍ የመወያያ አጀንዳ የነበረና ያለ The Da Vinci Code የሚሉት ኖቭል መጽሀፍ ነበር:: መጽሀፉ ላላነበባቹ ዋናው አንኳር ነጥቡን ለመጥቀስ ያህል በፈረደበት እየሱስ ክርስቶስ ማን ነት ታሪክ ዙሪያ የሚያጥነጥን ሆኖ በአዲስ ኪዳን ላይ ሴተኛ አዳሪቱ የእርሱ ተከታይ የሆነችው መቅደላዊት ማሪያም በቅዱስ መጽሀፉ እንደተሳለችው ሳይሆን እውነታው የእየሱስ ክርስቶስ ሚስትና የሴት ልጅ እናቱ ናት በዚህም መሰረት ሆሊግሬይል ተብሎ በተለይም በካቶሊኮች ከባድ ከበሬታ የሚሰጠው እና የት እንዳለ የማይታወቀው እየሱስ በመጨረሻይቱ እራት ከደቀመዛሙርቶች ጋር ጠጥቶባታል የሚሉትን ጽዋ/ኩባያ ሳይሆን የየሱስን ዘር የተሸከመው የመቅደላዊት ማሪያም ማህፀን ነው:: እናም መጽሀፉ እውነተኛውን ሆሊግሬይል ፍለጋ ላይ ያተኮረ መሆኑ ነው እንዲህ:: በዚህ መፅሀፍ ክርስቲያኑ አለም በተለይም ካቶሊኮች( ሜል ጊብሰንን ያስታውሷል) ክፉኛ የተቆጡ ሲሆን አንዳንድ አገሮች የመጽሀፉን ስርጭት እንዳገዱ እየተሰማ ይገኛል:: እንደዛም ግን ቢሆን ይህ መጽሀፍ በሳውዲ አረቢያ አገር አረቢኛን ጨምሮ በበርካታ ቋንቋ ተቶርግሞ እየተነበበ ነው:: በዛ ብቻም ሳያበቃ columbia pictures የፊልሙን ራይት ከደራሲው ዳን ብራውን ላይ ተሽቀዳድሞ በመግዛት የዳይሬክተርነቱን ሀላፊነት the beautiful mind, apollo 13 የመሰሉ ግሩም ፊልሞችን ላዘጋጀው ለስመጥሩው ሮን ሀዋርድ ሲሰጥ በመሪ ተዋኒያንነት ለመስራት ደግሞ ድብን ያለ አይሁድ የሆነው ብሪልያንት አክተር ቶም ሀንክስ ወስዶታል:: እናም ታዲያ ሰዎች ምን ትላላቹ ዳቪንቺ ኮድ ሆሊውዶች/አይሁዳዊያን ፓሽን ኦፍ ክራይስት ያደረሰባቸውን ቁስል ሊበቀሉበት ያሰናዱት ወይስ? ቶም ሀንክስስ በእድሜም በችሎታም ተቀራራቢ የሆነው ካቶሊኩ ሜል ጊብሰን ማንነቱን ስለነካበት አጸፋዊ ምት? ሮን ሀዋርድን በ ዘቢውቲፉል ማይንድን ያጉረመረሙበትን አይሁዶች ለመካስ ይህንን ፊልም ሀላፊነት ወስዶስ ቢሆን?
ለማንኛውም አሁን በመጪው ሰመር ተጠባቂውን ዳቪንቺ ቾድ ፊልም ለማየት ያብቃን
አሜን
እሾህ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 74
Joined: Fri Oct 28, 2005 11:04 pm
Location: ethiopia

ሚል ጊብሰንም ሆነ ቶም ሀንክስ የፈለገ ቢደርሱ እውነቱን በቃሉ

Postby ዲጎኔ » Thu Jan 19, 2006 7:32 am

ሰላም ለሁላችን ይሁን
The passion የተሰኘውንና የክርስቶስን እስከመሰቀል ያደረሰውን የክርስትና እምነት መሰረት የሆነውን ፍቅሩን የሚገልጸውን የጊብሰን ፊልም አይተው ከሚያደንቁት ነኝ::

የዳቪንቼ ኮድን በጨረፍታ አይቼዋለሁ ግን ሁለቱም እውነት መሆናቸው የሚፈተነው በማይሻረው ቃልና በሚያስከትሉት የመለወጥ ሀይል ሲሆን ስለፓሽን በትንሹ የማውቀው በአሜሪካ አንዲትወጣት ሴትን ገድሎ በፍርድቤት ምርመራ ነጻ የተባለ ሰው በትክክል እርሱ መግደሉንና አሁን ፍርዱን ሊቀበል አንደተዘጋጀ የተናዘዘው የቀድሞው ነፍሰገዳይ ምስክርነት ነው::

የዳቪንቼኮድ ለውጥ ያስከትል እንደሆነ ምስክርነት ከሌሎች እንሰማለን:ለአሁኑ ግን ስለPassion እነሆ!
www.rbcdavincicode.org
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

ፊልም ሊሰራ ነው?

Postby አኒታ » Fri Jan 20, 2006 11:47 pm

ስላም ለጸሀፊው.. እኔ እንኳን መጽሀፉን እንጂ ፊልም እየተሰራ መሆኑን አላወኩም.. ለማንኛውም ዘመኑም እኮ ቅዠት ሆኖባቸዋል ሰው ሲፈራ እንዲህ ነው ሚያረገው.. እናም ልክ እግዚአብሄርን ማግኘት እንችላለን ብለው ትልቅ ፎቅ ሰርተው እንደተገነደሰው ነገር.. ዳቪንቺ ኮድም እንደዛ ነው.. የሆነ የቂም በቀል መጽሀፍ ይመስላል.. ስራዬ ብሎ ለመተንኮስ.. እንግዲህ ቶሎ ለንትርክ ሚነሱት አብዛኛውን ጊዜ የ ሀይማኖት ሰዎች ሰለሆኑ ነው እንደዚህ አይነቱ ነገር የተደጋገመው.. አትፍረድባቸው.. ግን እኮ ሁለቱም መጽሀፍና ፊልም ላይ እውነታ አሉ.. ግን ከ እውነታው ደግሞ ከታሪክ የራቀ የራስ ፈጠራም ይታያል.. እውነት ግን እግዚአብሄር ነው እኔ እንደማምነው.. ማን ያቃል.. ለምንስ ሞትን ሞክረው አይመለሱም ከቻሉ? እሷ ላይ ወራጅ አለ :lol: እስኪ ፊልሙን ጉድ ደግሞ እናየዋለና...
በኔ በኩል.. ክፉ አያሰማን .. ጠብን አያንሳ እንጂ.. ማንም ጫረው ማንም ተወነው.. ምን አገባኝ!
አክባሪያችሁ
አኒታ
ቺርስ በ አረንቻታ!
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Postby Monica**** » Sat Jan 21, 2006 5:33 pm

እሾህ
ጥሩ አርእስት ነው የከፈትከው!
የሚገርምህ ነገር ዋርካ ጄኔራል ላይ ከወር በፊት መስለኝ The Da Vinci code የሚለውን መጽሀፍ ያነበባችሁ ብዬ አንድ ፎረም ላይ ጠይቄ ነበር መልስ ሳላገኝ ስቀር ጊዜ ተውኩት እንጂ!
ለማንኛውም Passion of Christ ይሁዶቹን ከማጋለጡ በፊት ብዙ ስለክርስቶስ የተወሳስብ ችግር አላየሁበትም ማለት እችላለሁ!!
Dan Brown እኮ ጭንቅላቴን ነው ያዞረው.....በተለይ እንደኔ ጠንካራ faith ለሌላችው ክርስቲያኖች ለመጠራጠር ትልቅ በር ከፋች ነው :oops: :oops:
^ v symbols......all the Holly Grail business........Mary Magdalene!!!!By the way, I grow up hearing that she was a prostitute!!! የባስ ደሞ ክርስቶስ ልጅ አለው የሚለው ነገር አስደንብሮኛል.......
ዳን ግን ግራ አጋብቶኝ ስነበተ እውነቱን ግን መድሀኔ አለም ይወቀው! በዛ ላይ ባይብል ስዎች ስለጻፉት ለራሳችው እንዲመቻቸው አድርገው ሊሆን ይችላል የጻፉት በተለይ 1.618-PHI The Divine Proportion!!
እረ ይቅር ብቻ ግን እውነት ይሄ ነገር ሁሉ እውነት ከሆነ የቱን እንቀበል???
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby እሾህ » Sun Jan 22, 2006 10:17 pm

ዲጎኔ ስለነፍሰገዳዩ ምስክርነት ምናምን ያልከው አልገባኝም
-------------------------------------
አኒታ የፓሽንን አላውቅም ነገርግን ዳን ብራውን ዳቪንቺ ኮድን ሲፅፍ ጥልቅ ምርመራ እንዳካሄደና በመጻሀፉ የሚጠቀሱ እያንዳንዳቸው ቦታዎች ሳይቀር ያሉ እንደሆኑ ያስረዳል:: እሱ ያረገው ነገር ቀድሞ በቲዮሪ ደረጃ ለጥቂቶች ኮንስፓይራሲ የነበረን ኢሹ አስፋፍቶ አብራርቶ በኖቭል መልክ አቅርቦልናል::
---------------------------
ሞኒካ እምነትሽማ ባንዲት መጻሀፍ ሊፈተን አይገባውም:: ስለዲቫይን ፕሮፖርሽን ባንድ ማቲማቲክስ ኮርስ ላይ ሰምቸው ነበር በጠቅላላ ማለት ይቻላል ዳቪንቺ ኮድ መጻሀፍ በቲዮሪ የተሞላ ነው:: ባይሆን እኔን የሳበኝ የነኚ ሲክሬት ሶሳይቲ ነገር ነው::በበኩሌ ስለ ኢሉሚናቲ, ፍሪሜሶንስ, ፕራዮሪ ኦፍ ዛዮን በደንብ የተብራራልኝ በዳን ብራውን መጻሀፎች ነው:: ሰውየው ኤንጅል ኤንድ ዲመንስ ስለ ኢሉሚናቲ ጻፈና ዳቪንቺ ኮድ ላይ ስለ ፕራየሪ ኦፍ ዛየን አሳውቆናል:: ቀጣዩ ኖቨል ስለፍሪሜሶን እንደሆነና ሮበርት ላንግደን ከአውሮፓ ተመልሶ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ጀብዱዉን ይቀጥላል ይላሉ አርእስቱም the solomon key እንደሚባል ሰምተንለታል::
እሾህ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 74
Joined: Fri Oct 28, 2005 11:04 pm
Location: ethiopia


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests