ሳይበር ኤክስፓንሽን

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ሳይበር ኤክስፓንሽን

Postby ሳምቻው » Fri Jan 20, 2006 3:44 am

ውድ ሳይበር ቲም ,

የሳይበር የመወያያ መድርኮችን ያለምንም ኤዲቲንግ ,በነጻ በብቃት እና በስፋት በማናቸውም ርእስ -ጉዳዮች ላይ ትልቅ ማስ እንዲጠቀምበት በማስቻላችሁ ትመሰገናላችሑ ::ምንም እንኳ ከምትሰጡት የአገልግሎት ስፋት አንጻር ከማስታወቅያ የሚገኝው ገቢ (ሪተርን ኧርኒንግ ) አናሳ መስሎ ይታየኛል :: ሆኖም ለጥሩ ማርኬተር አሴቶቹ ደንበኞቹ ናቸውና በርቱ ..... ::

የመወያያውን መድረክ ለማስፋት ከዚህ ቀጥሎ ያለውን አምድ ብትጨምሩ ድህረ -ገጻችሁን ይበልጥ ተነባቢና ተውዳጅ ያደርገዋል ብዪ አስባለሁ :: ምናልባትም የሀገር ቤት የንግድ ድርጅቶች ምርታቸውን እና ያ `ገልግሎት መስጫ ተቋሞቻቸውን ለማስታዋዋቅ የተሻለ ፖቴንሽያል ኦውድየንስ እና " ሴንስቲፍ "ቦታ ያገኛሉ ::

1. ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ

ይህ አምድ ቢታከል መድረኩን መሰረታዊ በሆኑ የቢዝነስ እና የምጣኔ -ሀብታዊ ትምህርቶች ከማገዙም በላይ ከሀገራችን ወጣት ነጋዴዎች ጋር ጥሩ የልምድ ልውውጥ ለመፍጠር ያስችላል :: በዘመናዊ ማርኬቲንግ , በኢንፎርሜሽን ; ቢዝነስ -ኣውት 'ሶርሲንግ ,በኢኮኖሚ ፖሊሲዎች : በግሎባላይዜሽን , በጥሬ ሀብት 'ና በሂዩማን -ሪሶርስ , በኢንፍሌሽን 'ና ዲፍሌሽን , በኢንፖርት ና 'ኤክስፖርት , በሎጅስቲክስ እና ማቴሪያል ሙቭመንት እውቀቶች ላይ ብዙ ብዙ ልምዶችን መለዋወጥ ይቻላል ::በዋርካ ያደፈጡ በርካታ ምሁራን አሉ :: እውቀታቸውን እንጠቀምበት ..... ::

ስዎም እውቀቱን በመማማር በጋራ ያስፋ , ከጉዳዩ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ድርጅቶች ደግሞ ምርታቸውን እና ሰርቪሳቸውን በአምዱ ስር ያስተዋውቁ :: የመድረኩ ጥራት ድርጅቶች < ቆይ አንዴ ! > እስኪባሉ ድረስ ምርቶቻቸውን በአምዱ ስር ለማስተዋወቅ በወረፋ እንዲጋፉ ሊያደርግ ይችላል :: ዋናው ""ማርኬት "" ግን መድረኩን ማሳዋብ ነው ..........

በመጨረሻም ብዙ የአለም የፋይናንስ ሚዲያዎች እና አናሊስቶች ደጋገመው የሚጠቅሱትን የዘመኑን ዝነኛ አባባል ተናግሬ ዞር ልበል :-

"" Let us share our wealth to the world ! ""

የቻይናው ፕሬዘዳንት ለአውሮፓ 'ና አሜሪካ መንግስታት በሽርደዳ ከተናገሩት ..... የተቀነጨበ ...:: በዚህ አባባል የላቲን እና የአፍሪካ መሪዎች እጅግ እንደረኩበት ይነገራል ::

አክባሪያችሁ
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests