ድካም አደከመኝ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ድካም አደከመኝ

Postby ሀዱድ » Fri Jan 20, 2006 11:41 pm

ቀና ብየ ባስብ ተኝቸ ባልመው
አልመጣልኝ አለ የፍቅርህ አላማው
ተነስቸ አልደውል በቀን ስናፍቀህ
ቀኔ ለሊት ሆኖ እንዳልቀሰቅስህ
አንተ ትነሳለህ ተኝቸ ሳልምህ

ሳላይህ ሳታየኝ በቃልህ እንዳምንህ
ያደረከው ጥረት ላንተ ተሳክቶልህ
ልቤን አደከምከው ሳልቀምስ ከከንፈርህ

አንተ እርቀህብኝ ምኞቴን ባላገኝ
አይንህን የማየት አምሮት ቢያስጨንቀኝ

አበባ በሬላይ በስምህ ተከልኩኝ
ሰወጣ ስገባ አንተን እንዲመስለኝ
ብቅ እያልኩ አያለሁ ሰው እንዳይነካብኝ

እንቡጥ የነበረው ፍቅርህ ፍሬ አፍርቶ
አንተን ይጠብቃል ቀጣፊውን አጥቶ

ቀጥፌ ባሸተው ጨፍኘ አይኖቸን
ፍቅርህ በጣም ጠማኝ አማረኝ ደረትህን

ወሀ እያጠጣሁኝ እኮተኩታለሁ
የልቤ አበባነህ በህይወቴ እስካለሁ
ሌላ አያይም ልቤ ላንተ እታመናለሁ
ከኔ > ላንተ
ሀዱድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jan 08, 2004 9:05 pm
Location: uk

Postby ይሁኔ » Sat Jan 21, 2006 12:43 am

ሀይይይይይይይይይይ ሀዱድ ደህና ናሽ ?
ነው ሰሞኑን በግጥም ዋርካን አስጨነቃችሁት? ቆንጆ ነው ደስ የሚል ስነ-ግጥም ለማን ነው ለመሆኑ ለኔ እንዳይሆን ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ . ቀልዴን ነው ለአረሩ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው
ምን ይሁን መቅናት ብቻ ነው ያለኝ እድል ለኔ ማን ይጻፍልኝ ቅቅቅ ለሁሉም ቀጥሉበት እንደ ሊዲና ጂሚ
ደህና ሁኝ እህታችን የአረሩ ፍቅረኛ
ይሁኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 144
Joined: Sat Sep 17, 2005 5:45 pm
Location: india

ሰላምታ

Postby ማህቡብ » Sat Jan 21, 2006 7:40 am

ልብሽን ሲጨንቀው ድካም ሲያደክምሽ

እንዲህ እንዳሁኑ ብቅ ብቅ ካልሽ

መፍትሄ አይጠፋውም መጥፋቱን ካቆምሽ
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Re: ድካም አደከመኝ

Postby ዋኖስ » Sat Jan 21, 2006 7:44 am

ሕሕሕሕምምምምምምም==== እረ! ፅናቱን ይስጥሽ!!==
Last edited by ዋኖስ on Sat Jan 21, 2006 4:11 pm, edited 1 time in total.
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ሀዱድ » Sat Jan 21, 2006 1:07 pm

ማን ነቱን ለመገመት መጣርህ ያስደንቀል እና አሳቀኝ በጣም አንተ እንዳልከው ቢሆን እንዴት ደስ ባለኝ
እንደገና ገምት ይሁኔ
ድግሞ አትቅና እሽ እንደው ጽሁፉን ብቻ ለማድነቅ ወይም ላለማድነቅ ብቻ ሞክር
የሚጽፍህ (የሚጽፍልህ ይስጥህ አምላህ እሽ :!:
ሀዱድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jan 08, 2004 9:05 pm
Location: uk

Postby ሀዱድ » Sat Jan 21, 2006 1:12 pm

ሄይ ዋኖሴ :!:
ካላገኘሁት አልጽናናም ቅቅቅቅቅ
Last edited by ሀዱድ on Sat Jan 21, 2006 4:30 pm, edited 1 time in total.
ሀዱድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jan 08, 2004 9:05 pm
Location: uk

Postby ሀዱድ » Sat Jan 21, 2006 1:35 pm

እመላለሳለሁ በቀን ሀያ ጊዜ
ከዋርካ ስር ጥሎኝ የያዘኝ አባዜ

ቅርንጫፉ ሰፊ ጽሀይ እንዳይመታኝ
ቁጭ ብየ ተሰደድኩ ይህ ዋርካ ጉድ ሰራኝ
መች ይሆንልኛል እሱን ሀይ ካላልኩኝ
ስወጣ ስገባ ሰውቹ ታዘቡኝ

ሂጂ ተኝ ብይ እያለ የሚያዘው
በልቤ የያዝኩት አንድ ሰው እሱ ነው

እራሴን ስረሳ በደስታ እሱን ሳይ
ይጨነቅልኛል እሱ ከኔ በላይ

ሁልጊዜም ያንችው ነኝ ሆዴ ሂጂ ተኝ
በላሽ ጠጣሽ? ብሎ ሚጠይቀኝ
ብትታመሚ እንኩዋን ከጎንሽ የለሁኝ

እንዳትጎጂብኝ እራስሺን ጠብቂ
ምንም ደስ ቢለኝ ጫዋታሽ ስትስቂ
ርሀብሽ ጥማትሽ ለኔ ነው ስትርቂ

እሱነው የኔውድ ልቤን የማረከው
ጊዜያቶችን አይቶ መክዳት የማያውቀው

አሁንም ከኔ> ለአንዱ ለእሱ
Last edited by ሀዱድ on Sat Jan 21, 2006 4:29 pm, edited 1 time in total.
ሀዱድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jan 08, 2004 9:05 pm
Location: uk

ናፍቆት

Postby ማህቡብ » Sat Jan 21, 2006 1:55 pm

አቤቱ ፈጣሪ ያራዊቶች ጌታ

እንዲህ ድክም ስትይ አይቶ በዝምታ

ያንችን ዶሴ ሳይከፍት ይዞ በቆይታ

ቢሆንም ይፈርዳል የማታ የማታ

እስትንፋሽሽ ካለ ካወቅኩ መኖርሽን

ፈልጌ አስፈልጌ አስመጣለሁ ልጁን
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

ሆድየ

Postby ARERU » Sat Jan 21, 2006 8:28 pm

የበረረው ልቤ ውቂያኖስ አቁዋርጦ
አልመለስ አለኝ ቀረ በዛው ቀልጦ

መልሽልኝ እንጅ ያለልብ ከምኖር
ባይሆን አንዳንድ ጊዜ እየመጣ ይደር

አንች መልከ መልካም ያገሬ ወዘሪት
ፍቅርሽ አደገኛ በጉልበት ሚያንኩዋትት

አልደርስበት አልኩኝ እራቀኝ መንገዱ
ጋራው ሸንተረሩ ያ ውጣ ውረዱ

ያለሽበት ሀገር ከውቂያኖስ ማዶው
ይጠብቅ ከንግዲህ አደራ አደራ ነው
እስከምንገናኝ ተስፋየ በሱ ነው

አረርሻ::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby ሀዱድ » Sat Jan 21, 2006 11:53 pm

ይሄ እርቆ መኖር ተስፋየን ጨረሰው
መንፈሴ ተርቦ አቅሌን አድከመው

ውቅያኖስ ተራራ መልኪያ የርቀት
ፍቅር ካሸነፈ ቅርብ ነው በእውነት

አንተም ከዚያ ጽና እኔም ከዚህ ልጽና
ቃል እንዳይሰበር እንዳንሆን ወና

ቃልህ ቃል ሆኖብኝ ዙሪያየን አጥሮኛል
በጂ በግር ቢመጡ ማን ይደርስብኛል
ያንተ ቃል ስላለኝ እኮራበታለሁ
ስምህ ሁሌ ላይ ነው አስከብርሀለሁ

ኩሩው ወንድ ነትህ አክብሮትህ ለሰው
ለጠላህው ጅንን ማር ነህ ለውደድከው
አንተን መከተሌን ማሰብ እንዴት ልተው

ሌላ አልከጂልም ባንተ በቃው ልቤ
አንጥፌበታለሁ ስምህን ከትቤ
ተመላለስበት ያንተው ነው ሀሳቤ

ከኔ >ለሱ
ሀዱድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jan 08, 2004 9:05 pm
Location: uk

ለናፍቆትሽ

Postby እንቁየ » Mon Jan 23, 2006 5:06 am

ጨረቃ ስትወጣ
በክዋክብት አጀብ
ሀሳብ እሽሽሩሩ
የትዝታ ወጀብ:
መልሀት አይጥልም
ማእበል በርትቶ
አእምሮ ውብ ሀሳብ
ልብን ፍቅር ሞልቶ::

ይህ ጨለማ አልፎ ጸሀይ
ስትወጣ ነገ እስክንተያይ
በሀሳብ እንዋኝ
እኒ ወደአንች ልምጣ
አንች ወደ እኒ ነይ
ናፍቆት ተውኒ ይሁን
ጊዚ ባህር መድረክ
እኛ እንደተዋናይ::

መልካም ቆይታ
እንቁየ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 111
Joined: Tue Feb 03, 2004 6:49 am

ከምወዳት ግጥሜ { ትንሿን} ቅምሻ}

Postby ዚና » Mon Jan 23, 2006 6:15 am

ፍቅር'

ፍቅርሽ አድጦኝ ብወድቅ እመቀመቅ ብገባ

ልቤም ቢያለቅስ የእውነትን እንባ ቢያነባ

ህሊናየ ቢቆስል ውስጤ በድቀት ቢደማ

ስበራ ስቀልጥ ብውል እንደ ጧፍ እንደሻማ

ገላየ ለአንች ቢውል ለጥጥ መደፊያሻ አውድማ

ፍቅርሽ ልቤን ቢወጋ እንደጦር እንደካስማ

ትዝታሽ በልቤ አይኔ በገላሽ ከዋለ

ተፈጥሮሽን ሲያደንቅ ህሊናየ ካበለ

ቅን ፍርድን አጣሞ ለአንች ከአንች ከዋለ

የኔን ህላዌ ወስዶ ለአንች ከሰጠ ካደለ

እኔነቴን እረስቼ በፍቅርሽ ወድቄ ስገኝ

አንች ጨካኝ የእለት እንጀራ ነሳሽኝ::

ለምወዳት እጮዬ } ከተጻፈው የተወሰደ} በሃገር እርቀት ምክነያት መገናኝት ባለምውቻላችን ]ብሶቴን ስገልጽ}
ዚና ከትንሿ ቤቴ ቸር አሰሙኝ ለኢትዮጵያ ሰላም::
ዚና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 203
Joined: Sun Mar 06, 2005 9:19 pm
Location: united states


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest