ይህን ያውቁ ኖሯል ?

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ይህን ያውቁ ኖሯል ?

Postby ማህቡብ » Sat Jan 28, 2006 7:38 am

ውድ ተሳታፊዎች :- የዘዎትር ሠላምታየን በማስቀደም.... በዚህ አምድ ላይ የታሪክ መዝገብ አገላብጣችሁ ያገኛችሁትን በመጻፍ ለሌላው ያሳውቁ ::

***እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ 1196 ንጉስ ቢያባው የያኔ ሴሎን ያሁንዋ ስሪላንካን ለመምራት ዘውድ በደፉ ከሁለት ሰአታት በሁዋላ አንድ ሰው ገደላቸው, በታሪክ ላይም ንጉስ ቢያባው አገራቸውን ለሁለት ሰአት በመምራት ይታወቃሉ ::

*** ለረጅም ጊዜ በትረ ስልጣን ይዘው የቆዩ የአለም መሪ የግብጹ ፋሮ/ንጉስ ሄፔ ሁለተኛው ናቸው እኒህ የግብጽ ፋሮ 2310 አመተ አለም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ6 አመታቸው ዘውድ ጭነው ለ94 አመታት ግብጽን
ገዝተዋል ::

***የወረቀትን ገንዘብ ለመጀመሪይ ጊዜ በጥቅም ያዋለቸ አገር ማን እንደሆነች ታውቃላችሁ ? የወረቀትን ገንዘብ በጥቅም ላይ ያዋለችው የመጀመሪያ አገር ቻይና ናት ጊዜው ከክርስቶስ ልደት በፊት 910 አመተ አለም ::


ከአክብሮት ጋር
Last edited by ማህቡብ on Tue Mar 19, 2013 2:34 pm, edited 8 times in total.
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ሚሚlove » Sat Jan 28, 2006 8:22 am

* እስከመጨረሻው የህይወታችን ፍፃሜ ድረስ ከስጋዊ የአካላችን ክፍል ውስጥ እድገቱን የማያቆመው አፍንጫችን ብቻ ነው::
ውድ ማህቡብ ባልከኝ መሰረት እነሆ ጀባ ብያለሁ

* ጎሽ የተባለው እንስሳ ከቁልቁለት ይልቅ በዳገት በፍጥነት ይጓዛል

* ፓብሎ ፒካሶ (ኢጣሊያዊ ታዋቂ ስአሊ) በብርድ ጊዜ ሰውነቱን የሚያሞቀው የሳላቸውን ውብ ሰዕሎች በእሳት እያጋየ ነበር::

* በቀን 25,000 ጊዜ ያህል የአይናችንን ሽፋኖች እያዘጋን እንከፍታለን ::

ቸር ስንብቱ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ማህቡብ » Mon Jan 30, 2006 6:25 am

*** በካንሰር/ነቀርሳ በሽታ አንድ ሠው ከተለከፈ የመኖር እድሉ በጣም የመነመነ ነው :: ካንሰርን በፍጹም መፈወስ አይቻልም, ሆኖም ግን በወቅቱ ከታወቀ በሽታው ወደ ሌላው የሰውነት ክፍል እንዳይዛመት የተለያዩ የህክምና እርምጃወችን መውሰድ ይቻላል:: በዩናይትድ እስቴትስ በካሊፎርኒያ ክፍለሀገር የሎንግ ቢች ተወላጅ ሚስስ ዊኒኖና ሚስድሬድ ሜሌንግ በካንሰር ነቀርሳ ተለክፈው እንደኤሮፓዊያን አቆጣጠር 1918 ከዛም በ1933 ከዛም በ1966 ከዛም በ1968 በሽታው እንዳይዛመትባቸው አራት ጊዜ ቀዶ ጥገና ተደረገላቸው, ያም ሆኖ ነቀርሳውን ከሰውነታቸው ለማጥፋት አልተቻለም ቀዶ ጥገና በተደረገላቸውም ቁጥር አበቃላቸው መሞታቸው ነው እየተባለ ለህይዎታቸው በጣም ይፈራ ነበር ሆኖም ሚስስ ሜልድሬድ ሜሌንግ ሀኪሞችን እስከዛሬ በሚያስገርም ሁኔታ ካንሰሩ ሰውነታቸውን እየበላ በሚያስደንቅ አኩዋሁዋን ለ105 አመታት ሊኖሩ ችለዋል ::

በመጨረሻም የሚገርመውና የሚያሳዝነው እኒህ ባልቴት የሞቱት በነቀርሳው ሳትሆን ባልታሰበ የጉንፋን በሽታ
ነው::

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Mon Jan 30, 2006 1:38 pm

*** ቡና, ሻይ, ውሃ, ቢራ, ወይንጠጅ, የአልኮል መጠጥ በብዛት የሚጠጣባቸው አገሮች የት የት እብደሆኑ ታውቃላችሁ ? ቡና በብዛት የሚጠጣበት አገር ፊላንድ ሻይ በብዛት የሚጠጣበት አገር ኤርላንድ ውሃ በብዛት የሚጠጣበት አገር ዩናይትድስቴትስ ቢራ በብዛት የሚለጋበት አገር ጀርመን ወይንጠጅ በብዛት የሚጠጣበት አገር ፈረንሳይ ከባድ አልኮል በብዛት የሚጨለጥበት አገር ሆላንድ ውስጥ ነው ::

ባሁኑ ሳአት ግን ቡና በብዛት የሚጠጣበት ሞኒካ ቆንጆ ቤት ነው : :D :D :D :D :D

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ጌታ » Mon Jan 30, 2006 7:06 pm

የተከበርክ ማኅቡብ

በጣም ቆንጆ ትምህርታዊ ርዕስ ከፍተሃል:: ሁሉም ያለውን ይዞ ሲመጣ ዋርካውያን ዕውቀታችን እንደሚተኮስ ጥርጥር የለኝም::

ባንድ ወቅት ቢራ በብዛት የሚጠጣበት አገር ቼኮዝሎቫኪያ ነው ሲባል ሰምቼ ነበር:: ኮትኳች ፓን ሪዚቆ ምን ይል ይሆን?
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Jan 30, 2006 7:46 pm

ጌታ wrote:
ባንድ ወቅት ቢራ በብዛት የሚጠጣበት አገር ቼኮዝሎቫኪያ ነው ሲባል ሰምቼ ነበር:: ኮትኳች ፓን ሪዚቆ ምን ይል ይሆን?


መምሩ ....ልክ ብለሀል....ቢራ በብዛት የሚጠጣባት አገር የተባበረቺው ፌደራል ጀርመን ነች.......ግን በአማካይ ውጤት ማለት በአገሪቱ ዜጋ አማካይ የወር ያመት የቢራ ፍጆታ ከሄድክ ...ቼክ ሪፐብሊክን በዚች ምድር የሚወዳደራት እስካሁን አልተፈጠረም ...ቼኮች ላገራችንም ...ሀረርቢራንና በደሌንም መስርተው እየጋቱ ናቸው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ዶማው2005 » Mon Jan 30, 2006 8:28 pm

I got some...
there r 293 ways 2 make change fo a dollar....100 pennies, 4 quarters....etc..
Every citizen of Kentucky iz required by law 2 take a bath once a year.... :lol: ...
ዶማው2005
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1650
Joined: Sat Jun 04, 2005 11:19 pm
Location: United States

Postby ክሪስታል » Mon Jan 30, 2006 8:43 pm

በእንግሊዘኛ ቋንቋ ውስጥ ብዙ ፊደላትን በመያዝ ረጅሙ ቃል:

pneumonoultramicroscopicsilicovolcanoconiosis

አነባበቡና ትርጉሙን ከታች ይመልከቱ:

Main Entry: pneu·mo·no·ul·tra·mi·cro·scop·ic·sil·i·co·vol·ca·no·co·ni·o·sis
Pronunciation: 'n(y)ü-m&-(")nO-"&l-tr&-"mI-kr&-'skäp-ik-'sil-i-(")kO-väl-'kA-nO-"kO-nE-'O-s&s
Function: noun
Inflected Form: plural pneu·mo·no·ul·tra·mi·cro·scop·ic·sil·i·co·vol·ca·no·co·ni·o·ses /-"sEz/
: a pneumoconiosis caused by inhalation of very fine silicate or quartz dust
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

አያድርስ

Postby ክሪስታል » Mon Jan 30, 2006 9:21 pm

በማስረጃ የተረጋገጡ ናቸው የሚባሉ እና ወፋፍራም ስዎች (extremely obese ones) ብዙ ጊዜ ሰለባ የሆኑበት የአውሮፕላን ውስጥ መጥፎ አጋጣሚ አለ ...... እሱም በአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ የሚገጥማቸው ነው ...... እና ምንድነው ...እ.. መጸዳጃው ላይ ተቀምጠው ሳለ toileቱን flush በሚያደርጉበት ሰአት የሚፈጠረው vacuum action ፊንጢጣቸውን መጥጦ (እንደ ሹራብ) በመገልበጥ ማውጣቱ ነው ....

አያድርስ ነው መቼም ... ደግሞም ዘረጦ ላለመሆን አንድ ጥሩ ምክንያት...በተለይ ብዙ ጊዜ በአየር የሚጓዙ ከሆነ::
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

Postby ማህቡብ » Tue Jan 31, 2006 10:49 am

**** አይናችን የተራቀቀ የሰውነታችን አካል ነው, ጤነኛ አይን በሚገባ ብርሃን ያለበት በተለያዩ ቀለማት ያሼበረቀ አካባቢን በሚቃኝበት ወቅት 10 ሚሊዮን የተለያዩ የቀለም አይነቶችን አበጥሮና አንጠርጥሮ ለማየትና ለመለየት ይችላል :: እዚህ ላይ እንግዲህ የሚያስገርመው ነገር በቴክኖሎጅ ተራቀው የተሰሩ የፎቶ ኤሌክትሪክ ካሜራዎች እንኩዋን የሠው ልጅ አይን በተፈጥሮ የሚያያቸውን የቀለም አይነቶች ግማሹን እንኩዋን ለመለየት ሃይል የሌላቸው መሆኑ ነው :: የሣይንስና የቴክኖሎጅ ሂደቶች ምንም ተራቀው ቢቀርቡም አንዳንዴ የተፈጥሮ የሠው ልጅ ህዋሳት ከቴክኖሎጅ በላይ ሊሆኑ ይችላሉ ::

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Jan 31, 2006 10:55 am

የተከበርክ ማኅቡብ

በጣም ቆንጆ ትምህርታዊ ርዕስ ከፍተሃል :: ሁሉም ያለውን ይዞ ሲመጣ ዋርካውያን ዕውቀታችን እንደሚተኮስ ጥርጥር የለኝም ::

ወንድሜ ጌታ :- ስለመልካም አስተያየትህ አመሰግናለሁ ::

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ቡናማ » Tue Jan 31, 2006 3:18 pm

ስለ ስፔናዊው ፓብሎ ፒካሶ የተጠቀሰውን ስለማረም ስል ነው ይህን የምጽፍ ::
በመሰረቱ Pablo Picasso ያን ያህል ሰሎቹን ቀዶ እሳት እስከመሞቅ ያዳረሰ ድህነት ላይ ደርሶ እንደነበር የትም ቦታ ላይ አልተወሳም :: ያም እንኳ ለሰአሊ ህይወት ሊታሰብ የሚችል ቢሆን በርሱ ህይወት ዘመን ተፈጸመ ተብሎ በእርግጥ አልተሰማም :: ሌላው የመረጃ ስህተት የምለው እርሱ ስፔናዊ እንጂ ጣሊያናዊ አይደለም ::
መቸም picassoን ካነሳነው አይቀር እኔም ጥቂት ማስታወሻ ላዋጣ ::
በስነ -ጥበብ የስልት መጠሪያዎች ውስጥ የምናውቀውን Kubism ከ George Braque ከተሰኘ ሰአሊ ጋር የጀመረ ሲሆን : ያም ያሳሳል ዘይቤ ተፈጥሮን ዘልማዳዊ በሆነው መልኩ ብቻ ከመመልከት አልፎ ተመልካቹ በቆመበት አንድ ቦታ ላይ ሁኖ አንድን ቁስ ወይም መልከአምድር የተለያየ ጉኑን (መልኩን ) ማየት የሚያስችለውን ጥበብ የማመላከት ሁኔታ ነበር ::ይህንንም ለማጉላት ላሳሳል ዘይቤው የተጠቀሙባቸው Art Elements እንደ Cylinder,cone,Pyramid etc... መሰሎች ነበሩ ::ጊዜ (Time) በዚህ Experiment ውስጥ ፋይዳው ያነሰና የተፈጥሯዊ አገልግሎቱም ተለውጦ ያም ሲባል እንደ The fourth dimention ያለውን ክስተት መፈጠር ከማጎልበት ያልዘለለበትም ሁኔታ ነበር ::ይህም ስንል በስእሉ ላይ የሚያርፈው ብርሀን የግድ የምናውቀውን ጥላና ብርሀን አሳይ ሊሆን አይገባውም ማለት ነው::
ይሄ ኩቢዝም ሁለት አይነት ትንታኔ ወይም ልምምድ ሲኖረው እነርሱም Facet Cubism(analytical) & Collage Cubism(synthetical) በመባል ይታወቃሉ ::
በሁለቱ መንገዶች መሀል ያለው ልዩነት earthy Colours ከመጠቀም ወደየተለያዩ ቁሳቁሶችን በዝርግ አካል ላይ ደራርቦና ለጣጥፎ ወደመስራት (Collage Technique):እንዲሁም ደማማቅ ቀለሞችን መገልገል የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል ::
በኌላም ዠርኒካ የተሰኘውን ሰእሉን በአንድ ወቅት ተደርጎ የነበረ አለም አቀፍ እክስፖ ላይ አሳይቶ በዚያም የሀያኛው ክፍለ ዘመን ድንቅ ሰአሊ ለመሰኘት በቅቷል ::
ስለ እዚህ አምድ መከፈት አድናቆቴን እየገለጥኩ በወዳጅነት ያሰንብተን በማለት ላሁኑ በዚሁ አበቃሁ ::
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

ካሽተቱስ አይቀር እንደ.....

Postby እንታደስ » Wed Feb 01, 2006 1:16 am

ካሽተቱስ አይቀር እንደ...[b]

ወንድ የሳትራትን የመስለ የማሽተት ችሎታ ያለው እንስሳ ማስብ የማይሆን ነው::
ወንድ የሳት ራት በሽታ በመመራት ብቻ ሴቷ የሳትራት በማይሎች ርቀትም ላይ ብትሆን እንኳን ያለምንም ችግር ያገኛታል::
ሴቶቹ ግን የዚህን ያህል አነፍናፊ ናቸው ማለት አይደለም::
ሴቷ የሳት ራት ወንዱን የምታባብልበትን ሆርሞን ሆዷ ውስጥ ባለ እጢ ታከማቻለች:: በጣም ትንሽ ከሆነው
(ግራም) ከዚህ ሆርሞን በጥቂት እየቆነጠረች ወደ ውጪ የምትለቅ ሲሆን ይህም ሆርሞን በአንድ ማይል ርቀት ላይ ከጥቂት ሞለኪውሎች በላይ አይገኝም::

ቢሆንም ግን እነዚህ ጥቂት ሞለኪውሎች ወንዱን የሳት ራት በፍቅር ለመንደፍ ከአንቴናው ጋር ተባብረው በቂ ናቸው::
ወንዱም ቢሆን አትኩሮቱ ሁሉ የዚህን ብናኝ መአዛ በመፈለግ ላይ ያተኮረ ነው::የዚህን የሳት ራት የማሽተት ችሎታ መቀናት ግን የዋህነት ነው:: ምክንያቱም ከዚህ ከሴት
የሳትራት ጠረን በስተቀር ምንም ማሽተት አይችልምና::
እንታደስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1043
Joined: Mon Jan 24, 2005 5:46 pm
Location: Europe

Postby ዩፎ » Wed Feb 01, 2006 3:10 am

ማህቡብ ስለኢንፎርሜሽኑ ታንክዩ:: እኔ የተለየ ሀሳብ አለኝ:: ብዙ ቀለማትን ከሶስቱ መሰረታዊ ቀለሞች ሳይወጣ (ሰማያዊ አረንጉዋዴና ቀይ) ሊያይ ይችላል:: ከዛ ውጪ ግን አይን ምንም ማየት አይችልም :wink: ለዚህም ነው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች (ምሳሌ x-ray) የምንጠቀመው - የአይንን ድክመት ለመሸፈን:: እናም ቀለምን በመለየት ችሎታው አይን የሚደነቅ አይደለም ለማለት ነው:: :wink:


ማህቡብ wrote:**** አይናችን የተራቀቀ የሰውነታችን አካል ነው, ጤነኛ አይን በሚገባ ብርሃን ያለበት በተለያዩ ቀለማት ያሼበረቀ አካባቢን በሚቃኝበት ወቅት 10 ሚሊዮን የተለያዩ የቀለም አይነቶችን አበጥሮና አንጠርጥሮ ለማየትና ለመለየት ይችላል :: እዚህ ላይ እንግዲህ የሚያስገርመው ነገር በቴክኖሎጅ ተራቀው የተሰሩ የፎቶ ኤሌክትሪክ ካሜራዎች እንኩዋን የሠው ልጅ አይን በተፈጥሮ የሚያያቸውን የቀለም አይነቶች ግማሹን እንኩዋን ለመለየት ሃይል የሌላቸው መሆኑ ነው :: የሣይንስና የቴክኖሎጅ ሂደቶች ምንም ተራቀው ቢቀርቡም አንዳንዴ የተፈጥሮ የሠው ልጅ ህዋሳት ከቴክኖሎጅ በላይ ሊሆኑ ይችላሉ ::

ከአክብሮት ጋር
ዩፎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 132
Joined: Sat Dec 25, 2004 10:29 pm
Location: united states

Postby ዳጋፉፍ » Wed Feb 01, 2006 5:32 am

በመጀመሪያ እያዝናና የሚያስተምር አምድ ስለተከፈ ለባለ ቤቱ አመሰግናለሁ::ይሄውላችሁ እንግዲህ....

ፍቅር የተቃራኒ ጾታዎች ግጭት ወይም መሳሳብ ነው የሚሉ የስነ ልቦና ጠቢባን እንዳሉ ሁሉ:"ፍቅር ራስን ከመውደድ የሚከሰት ነገር ነው" የሚሉም አሉ::"ፍቅር ሰብአዊ ርህራሄ ነው" የሚሉቱ የቀድሞ የስዊድን ንጉስ ይጠቀሳሉ::ንጉሱ "ፍቅር ሰብአዊ ርህራሄ ነው"የሚል እምነት ስላላቸው እስከ ፍጻሜአቸው በፍቅር አብረው የኖሯቸው ስድስት(6) ሚስቶች ነበሯቸው::ከስድስቱ ሁለቱ አይነ ስውራን:ሁለቱ እግር-አልባ:ሁለቱ ደግሞ መስማትና መናገር የተሳናቸው ነበሩ::
"ሳይንቲስቶቻችሁ ሰው እንዴት በህይወት እንደሚኖር ያስተምሯችኋል፡እኔ ደግሞ ሰው እንዴት በህይወት እንደማይኖር አሳያችኋለሁ" ጆሴፍ ስታሊን
ዳጋፉፍ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 108
Joined: Thu Jul 14, 2005 3:49 am
Location: ዩ ኤስ አሜሪካ

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest