ይህን ያውቁ ኖሯል ?

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby መልከጻዲቅ » Tue Nov 18, 2008 12:44 am

*******የቤተ-መንግስት ጥሪ********

[i]ጊዜው እንደኛው የዘመን ስሌት በ1941 ዐ.ም ሲሆን ወራቱም ክረምት ነበር:: ንጋት ላይ የጀመረው የካፊያ ዝናብ አላቆመም:: በዚህ ጊዜ ነው ስድሳ የሚሆኑ ከቀ/ኅ/ስ : ከተፈሪመኮንንና ከጀኔራል ዊንግት የተውጣጡ ተማሪዎች በሶስት ካሚዮኖች ተጭነው ቤተ-መንግስት የደረሱት:: እልፍኝ አስከልካዩ ተማሪዎቹን በተርታ ካሰለፈ በኌላ ወደጃንሆይ ልዩ ጽ/ቤት እየመራቸው እግረ-መንገዱንም ጃንሆይ ፊት ሲደርሱ እጅ መንሳት እንደሚጠበቅባቸው አስረግጦ ነገራቸው:: ወቅቱ ክረምት በመሆኑ የጃንሆይ ክፍል ከእሳት ማንደጃው በሚወጣው ሙቀት ከዳር እስከዳር ፏ ብሏል:: ንጉሰ-ነገስቱ ካማንደጃው ፊት-ከተዘጋጀላቸው መደብ ላይ በግርማ ሞገስ ተቀምጠዋል:: በግራና በቀኝ በኩል መኴንቱ ቆመዋል:: ጃንሆይ ንግግራቸውን በቀልድ ጀመሩ:: "" ምንድነው ይሄ ሴራ?"" አሉ ጃንሆይ:: ቀልድ መሆኑን ለተማሪዎቹ ለማሳወቅ ወይንም የንጉሱን አክብሮት ለማግኘት መኴንቱ ሁሉ ባንድ ላይ ፈገግ አሉ:: ጃንሆይ ንግግራቸውን ቀጠሉ:: "" እናንተ አሁን ልጆች ናችሁ ስለአየር ሀይል ጥቅም ቡዙ አታውቁም:: ምናልባት አየር ሀይላችን ትንሽ ስለሆነች ይሆናል እዚያ ለመግባትና ለመቀጠር የማትፈልጉት የእንጊሊዝ ሮያል አየር ፎርስ ማልታን በጀግንንነት የተከላከሉት በሁለት አይሮፕላኖች ብቻ ነበር::"" አሉ:: ከጃንሆይ ንግግር በኌላ ተማሪዎቹ የተለያዩ ጥያቄዎች አቀረቡ:: በኍላ የኮሌነልነት ማዕረግ ያገኘውና ጌታሁን እጅጉ የሚባለው አንደኛው ተማሪ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቀረበ: "" ግርማዊ ሆይ እኔ መሀንዲስ ሆኜ ድሀ ቤተ-ሰቦቼን መርዳት ነው የምፈልገው"" አለ:: አንደኛው ተማሪ ደሞ እጁን አውጥቶ "" ግርማዊ ሆይ እኔ ገበሬ መሆን እፈልጋለሁ"" አለ:: ጃንሆይም "" መሀንዲስነት የሚፈልገው የአይሮፕላን መሀንዲስ መሆን ይችላል የቤተሰብ ችግር አለብን ያላችሁ ደግሞ ጉዳዩ ባሰፋ በኩል ይቅረብልንና ርዳታ ይደረግላችኌል ማወቅ ያለባችሁ ሀገራችሁን ካልተከላከላችሁ መሬታችሁ ከተነጠቀ የት ሆናችሁ ነው የምታርሱት?"" በሚል መሪ ቃል ተማሪዎቹን አሰናበቱ:: ይሄ እንደተፈጸመ በልፍኝ አስከልካዩ ""እጅ ንሱ"" ተብለው በመጡበት አኴኌን ወደ የት/ቤታቸው ተመለሱ:: ተማሪዎቹ መኪና ላይ ከመጫናቸው በፊት ግን አየር ሀይል ውስጥ እንዲቀጠሩ ለማበረታታትና ተጨማሪ ፍላጎት ለማሳደር ጄነራል አሰፋ ለተማሪዎቹ እንዲህ አሉ "" አሁን ት/ቤት ተዘግቷል የሶስት ወር እረፍት አላችሁ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከታወቀው የወታደር ልብስ ሰፊ ኤድዋርድ ጋራብዲያን ዘንድ እየሄዳችሁ የገብርዲን ዮኒፎርም በልካችሁ አሰፉ:: "" አብዛኛዎቹም እንደተባለው አደረጉ::[i]
መኮንን በሪ አቪየሽን በኢትዮጵያ
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ቢሌ » Tue Nov 18, 2008 9:41 am

መልከጻዲቅ በጣም የሚገርምና የሚያስደንቅ ጊዜ ነበረ በንጉሱ ጊዜ:: በነገራችን ላይ ኮሎኔል ጌታሁን እጂጉ ደርግ ስልጣን ሲይዝ የወሎ ክፍለሀገር አስተዳዳሪ አድርጎአቸው ነበር: በአካል አውቃቸዋለሁ አሁን ግን የት እንዳሉ አላውቅም::

ምስጋና ይገባሀል::

ቢሌ::
ቢሌ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 586
Joined: Wed Aug 18, 2004 7:29 am
Location: united states

Postby መልከጻዲቅ » Mon Jan 19, 2009 5:25 am

**************************ከጳውሎስ ኞኞ ትዝታዎች*************************


ጥያቄ : ህዳር 23 በወጣው አምድ ላይ ያላገባች ሴት ወይዘሪት ስትባል ያላገባው ወንድ ምን ይባላል? ለተባለው ጥያቄ ""ኮበሌ "" የተባለው የተለየ መጠሪያ ስም ቢሰጠው መልካም ይመስለኛል:: በቤገምድር ኮበሌ ማለት ያላገባ ማለት ነው:: እስከነዘፈኑ እንኴን
"" ጉብጉብ ያለው ጡቷ እንደ ዳቦ
ያባብላታል ኮበሌው ከቦ""
እየተባለ ይዘፈናል:: ምን ትላለህ?

የጳውሎስ መልስ : እኔ መቼም የሚያገባኝ የለም እንጂ ነገሩ በጣም ጥሩ ነው:: ታዲያስ ምድረ ወንደ ላጤ ! በዚህ አትስማሙም? እስቲ ጀምሩት ከኛ እኩል አቶ መባሉን ተዉትና ኮበሌ እከሌ ተባሉ እስቲ::

ጥያቄ: በዛሬ ጊዜ የሆድን ሚስጥር የሚነግሩት ጔደኛ ያለ ይመስልሀል?

የጳውሎስ መልስ : ሞልቷል:: ቢያወራውም ባያወራውም የሚነገረው ሞልቷል::

ጥያቄ : ተበሳጭቻለሁ:: ደብረ ሊባኖስ ሄጄ የህይወቴን ፍጻሜ በዚያ ለማድረግ ስላሰብኩ የሚያስፈልገውን ነገር ንገረኝ::

የጳውሎስ መልስ: የሚያስፈልገውማ አንድ ልብስ ብቻ ይዘሽ መሄዱ ነው:: እንደኔ ግን ባትሄጂ መልካም ይመስለኛል:: ብስጭት የትም ቢሆን አይጠፋምና ከዚሁ ሆነሽ እግዚአብሄርን ማገልገል ትችያለሽ::

ጥያቄ : ከምን ተነስተህ እንዴት እዚህ ደረስክ?

የጳውሎስ መልስ : ከምንም::

ጥያቄ :: በየመንገዱ ላይ ሶስት የመጫወቻ ካርታ እየደረደሩ የህዝቡን ገንዘብ የሚግፉ ቁጭ በሉዎች ለምን አይያዙም?

የጳውሎስ መልስ: ገና ልጅ ሆኜ ጀምሮ ሲያዙ ሲወጡ ሲወጡ ሲያዙ የኖሩ ናቸው:: አሁን ደሞ ትንሽ ሲበራክቱ ይያዙ ይሆናልና መጠበቅ ነው::
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby መልከጻዲቅ » Mon Jan 19, 2009 5:35 am

**************************ከጳውሎስ ኞኞ ትዝታዎች*************************


ጥያቄ : ህዳር 23 በወጣው አምድ ላይ ያላገባች ሴት ወይዘሪት ስትባል ያላገባው ወንድ ምን ይባላል? ለተባለው ጥያቄ ""ኮበሌ "" የተባለው የተለየ መጠሪያ ስም ቢሰጠው መልካም ይመስለኛል:: በቤገምድር ኮበሌ ማለት ያላገባ ማለት ነው:: እስከነዘፈኑ እንኴን
"" ጉብጉብ ያለው ጡቷ እንደ ዳቦ
ያባብላታል ኮበሌው ከቦ""
እየተባለ ይዘፈናል:: ምን ትላለህ?

የጳውሎስ መልስ : እኔ መቼም የሚያገባኝ የለም እንጂ ነገሩ በጣም ጥሩ ነው:: ታዲያስ ምድረ ወንደ ላጤ ! በዚህ አትስማሙም? እስቲ ጀምሩት ከኛ እኩል አቶ መባሉን ተዉትና ኮበሌ እከሌ ተባሉ እስቲ::

ጥያቄ: በዛሬ ጊዜ የሆድን ሚስጥር የሚነግሩት ጔደኛ ያለ ይመስልሀል?

የጳውሎስ መልስ : ሞልቷል:: ቢያወራውም ባያወራውም የሚነገረው ሞልቷል::

ጥያቄ : ተበሳጭቻለሁ:: ደብረ ሊባኖስ ሄጄ የህይወቴን ፍጻሜ በዚያ ለማድረግ ስላሰብኩ የሚያስፈልገውን ነገር ንገረኝ::

የጳውሎስ መልስ: የሚያስፈልገውማ አንድ ልብስ ብቻ ይዘሽ መሄዱ ነው:: እንደኔ ግን ባትሄጂ መልካም ይመስለኛል:: ብስጭት የትም ቢሆን አይጠፋምና ከዚሁ ሆነሽ እግዚአብሄርን ማገልገል ትችያለሽ::

ጥያቄ : ከምን ተነስተህ እንዴት እዚህ ደረስክ?

የጳውሎስ መልስ : ከምንም::

ጥያቄ :: በየመንገዱ ላይ ሶስት የመጫወቻ ካርታ እየደረደሩ የህዝቡን ገንዘብ የሚግፉ ቁጭ በሉዎች ለምን አይያዙም?

የጳውሎስ መልስ: ገና ልጅ ሆኜ ጀምሮ ሲያዙ ሲወጡ ሲወጡ ሲያዙ የኖሩ ናቸው:: አሁን ደሞ ትንሽ ሲበራክቱ ይያዙ ይሆናልና መጠበቅ ነው::
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ማህቡብ » Mon Mar 02, 2009 3:52 pm

ሠላም ለዚህ ቤት! በተለይ ትምርታዊ መጣጥፎችን በዝች የተረሳች ቤት ብቅ እያልክ የምታቃምሰን የተከበርክ መልከጻዲቅ:: በርታልን እኔም እንደ መስቀል ወፍ ብቅ እያልኩም ቢሆን የማገኛትን ጄባ እላለሁ:: እስቲ ስለ ካፋ ክፍለሐገር ትንሽ........


የከፋ ምድር አማካኝ ከፍታው ከባሕር ጠለል በላይ አምስት ሽህ ጫማ ሲሆን በቦጆቦ ወንዝ አካባቢ በጫታ እና በደቻ ወረዳዎች ደቡባዊ ጫፍ አካባቢ ሦሥት ሽህ ጫማ እና ከዛም ያነሰ ቦታ ይገኛል:: አቀማመጡም ከበስተ ምስራቅ ከጎጆቦ ወንዝ ጄምሮ ከፍ እያለ ይሄድና ሻራድ በሚባልበት አካባቢ ሲደርስ ከፍታው ዘጠኝ መቶ ሽህ ጫማ ይደርሳል ይህ በንዲህ እያለ ካፋ ስሟ ሲነሳ የደኗ ውበት እና በውስጧ ልዩ ትርጉም ያላቸው እጽዋት የያዘ ሆኖ ከነዚህ ዋነኛዎቹና የታወቀው በታሪክ ለመጄመሪያ ጊዜ የተገኘው እና ለአለም ያበረከተችው ገጸ በረከቷ "ቡና" ነው ስሟም ከብዙ በጥቂቱ በአለም ዙሪያ ኮፊ----ካፌ እነዚህ ስሞች ደግሞ ካፋ ከሚለው የተገኙ እንደመሆናቸው ካፋ በየእለቱ በሚሊዮን በሚቆጠሩ የአለም ቡና ወዳጅ ሕዝብ ከንፈር እና አፍ ሳይነሳ አይውልም:: ምክኒያቱም ስለ ከፋ ሲነገር ስለ ቡና በተገቢው መጠን ባይነገር ትክክል አይሆንም እና በመጠኑ ቢሆንም ስለዚህ እና ስለተገኙ ጉዳዮች ማስታወስ ተገቢ ነው::

ካፋ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን በአፍሪካ አሕጉር ከፍተኛ የቡና አገርም ነበረች ብሩስ በ1804 በጻፈው መጽሐፍ "ቡና" በካፋ ለመገኘቱ ከብዙ የታሪክ ጻሃፊዎች አንዱ ማክስ ግሩል የተባለው ጻሃፊ ከአለም ሕዝብ ባብዛኛው ለመጄመሪያ ጊዜ በዝች ሐገር በካፋ የበቀለውን ፍሬ ቡና ጭማቂ ስለሚጎነጭ የካፋ ስም አመቱን በሙሉ ቢያንስ አንድ ጊዜ በአለም ሕዝብ ይጠራል ብሏል:: ቡና የተገኘው እና መታወቅ የጄመረው ታሪክ መመዝገብ ከጄመረበት ጊዜ ጄምሮ ሲሆን አጠቃቀሙ ወደ መላው ደጋማው የኢትዮጵያ ግዛት የተሰራጨው ከዚሁ ከካፋ እንደነበር እና በፔርሺያ ባሁኑ ኢራን መታወቅ እንደ ጄመረ ማክስ ግሩል በ1932 በጻፈው መረጃ ይገኛል::

እንዲሁም ላንድ የተባለው የታሪክ ጸሀፊም ቡና በካፋ ስለመገኘቱ የብሩስን ሐሳብ ያጠናከረ ሲሆን ከሁለት ምዕተ አመት በፊት ብሩስ እንዳስተዋለው ካፋ የቡና ተክል መገኛ መሆኗን በጹሁፉ አጠናክሯል:: ካፋ በየአመቱ 350 ሽህ ኪሎ ግራም የሚመዝን ቡና ወደ ውጭ ትልክ ነበር በዚሁም ኦርየንት የቡና ምንጭ ካፋ ስለመሆኑ ለዘላለም ሲታወስ የሚኖር መሆኑን በመግለጽ ጽፏል:: የቡናን ከካፋ አወጣጥ እና አሰረጫጨት በተመለከተ ይኸው ጻሀፊ ግሩል አንድ የአረብ ሠው ከካፋ በማውጣት እና በደቡብ የመን እንዳስተከለ ማክስ ግሩል በ1912 በጻፈው መጽሐፉ ያትታል ይሁን እንጅ በአረብ አገሮችም አሁንም በመነሻው ቦታ የተሰጠውን ሥያሜ በመያዝ ቡና ተብሎ እስከዛሬ ይጠራል::

የካፋ ምድር ከታደለችው የተፈጥሮ አየር ንብረቷ ጋር ሲደመር የተጠቀሱት ጥቂቱ ብቻ ናቸው ብዙ ባለሃብቶች ወደዛ አካባቢ በሰማሩ ውጤታማ ሊያደርጋቸው እንደሚችል አያጠራጥርም::
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Re: እስቲ ፍቅርን እንይ

Postby ሀዲዱ » Mon Mar 02, 2009 10:09 pm

ተወዳጁና ታዋቂው አስተማሪዬ ይብራዕ እንዳስተማረኝ ከሆነ ፋንታ ማለት

FANTA -- ---- Arabs Never Taste Alcohol ይለዋል :: አረቦች አልኮል ስለማይጠጡ ለነሱ ተብሎ የተዘጋጀ መጠጥ ነው ይለዋል :: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ሀዲዱ


ቡናማ wrote:ውድ የዚህ አምድ ወዳጆች
እንደምን ከረማችሁ?

የኮካ ኮላ ካምፓኒ ፋንታ የተባለውን ተወዳጅ መጠጥ Fantasy ከሚለው የእንግሊዘኛ ቃል ቆርጦ በማውጣት እንደሰየመው በቅርቡ ሰማሁ::ላስተውሎት ከጠቀመ ብዬ ነው ያነሳሁት::
ዛሬ ከተጨዋወትን ስለ ፍቅር ቢሆንስ ብዬ ነው የመጣሁ::
ፍቅር በግሪክኛና በላቲንኛ የተለያየ አተናተን አለው::መጠሪያዎቹም Philia, eros, agape, storge and xenia ይባላሉ::እነርሱንም ለመተንተን ያህል;

Agape;(በግሪክኛ s'agapo ማለት I love you የሚል ትርጓሜ ይሰጣል)
እናም ይሄ የፍቅር ቃል እውነተኛን,ፍጹማዊ የሆነን እንደመለኮታዊ ያለውን አይነት ፍቅር ይወክላል::ይሄው አገላለጽ ለላቲንኛው Caritas በይዘቱ ሲቀርብ በጥቅል መሰኛ እንደ Love of a soul ይታወቃል::
Eros (erota በግሪክኛ being in Love እንደማለት)
ይህ በስጋዊ መፈላለግ ላይ የተመሰረተና በተመሳሳይ ምኞት የታጨቀን(ሽፍደታዊ) ፍቅር ይወክላል::

Philia-ይህ ፍጹም የሆነንና የጤናማ ጓደኝነት ቅርርብን ለመጥራት ሲሆን ያም ቤተሰባዊ,ማህበራዊ ና መሰል የሆነን በእኩልነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተን ፍቅር የሚያወሳ ነው::

Storge-በዘመናዊው ግሪክኛ አወሳሰድ እንደ በፍቅር መጠመድ አልያም መማረክን ለመግለጽ ያገለግላል::

Xenia-ይህም እንክብካቤን የተሞላ ፍቅር መስጠት እንደማለትን ሲገልፅ አንድን ፍፅምና የተሞላ በእንግዳና ተቀባዩ መሀል የሚፈጠረን መንፈሳዊ ህብረት(አብሮነት),በጎነትን ይጠቅሳል::በጎን ነገር ለሌላው በማድረግ የሚገኝን የምስጋና ብልፅግና መጥሪያነት ያገለግላል::
እንደ John Alan Lee's "Love styles" ደግሞ ፍቅር እንዲህን መሳይ ጥቅል ትንታኔ አለው::

Eros (romantic love)- a passionate physical love based on physical appearance and beauty.

Ludus (game playing)- love is played as a game; love is playful; often involves little or no commitment and thrives on "Conquests".

Storge (companionate love)- an affectionate love that slowly develops, based on similarity and friendship.

Pragma (pragmatic love)- inclination to select a partner based on practical and rational criteria where both benefit from the partnership.

Mania (possessive love)- highly emotional love; unstable; the stereotype of romantic love; its characterstics include jealousy and conflict.

Agape (altruistic love)- selfless altruistic love; spritual

በነገራችን ላይ እንደ Susan S. Hendrick የተሰኙ የሳይኮሎጂ ፕሮፈሰር ግኝት ከታየ ወንዶች በተለይ ወደ ludic/ludius/ ና manic/mania/ የፍቅር አይነት ሲያዘነብሉ ሴቶች ደግሞ ወደ storgic/storge/ ና pragmatic/pragma/
ያመዝናሉ::
ወይ ፍቅር አያ አያልቅበት...
እንዳነጋገረ የነበረ,ያለና የሚኖር ታላቁ የሰው ልጆች የእውቀት ገበታ
ወዳጆች እኔ በኛው ባገሪኛው እወዳችኌለሁ በማለት ለዛሬ
ጣጣዬን በዚሁ ጨረስኩኝ::
በወዳጅነት እንቀጥል::
ቡናማ
የሰቆቃውና የመከራው ማለቂያ ፤ ማብቂያ በእግዚአብሄርና በእኛ አንድነት ይሆናል
ሀዲዱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 891
Joined: Fri Jul 13, 2007 8:58 pm
Location: Here

Postby ሀዲዱ » Mon Mar 02, 2009 11:12 pm

በአለም ትልቁ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሚገኘው የት ነው ተብሎ በአድማስ ራዲዮ ተጠይቆ ---- መልሱ ካምቦዲያ መሰለኝ የተባለው :: በእርግጥም ካምቦዲያ :: ..................... የቅርብ ጊዜ ተራንስሚሽን ነውና ገብታችሁ አድምጡት ::

ሀዲዱኤዲ wrote:ጥሩና አስተማሪ መድረክ በመክፈትህ እያመሰገንኩ ለዛሬ:

- ማንኛውም size ያለውን ወረቀት እኩል ቢያጥፉት ከ8 ጊዜ በላይ ለማጠፍ አይቻልም
- በአለም ላይ ትልቁ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሚገኘው በቫቲካን ሳይሆን በአፍሪካ በኮትዲቯር ያሞሱክሮ ከተማ እንደሆነ ያውቃሉ
- ከአዛርባይጃን እና አፍጋኒስታን በስተቀር የተቀሩት ስማቸው በ A የሚጀምሩ ነጻ አገሮች የመጨረሻ ፊደላቸው A እንደሆነ አስተውለዋል
- 7ቱ አህጉራት በእንግሊዝኛ ሲጻፉ የመጃመሪያና የመጨረሻ ፊደላቸው ተመሳሳይ ነው
የሰቆቃውና የመከራው ማለቂያ ፤ ማብቂያ በእግዚአብሄርና በእኛ አንድነት ይሆናል
ሀዲዱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 891
Joined: Fri Jul 13, 2007 8:58 pm
Location: Here

Postby ሀዲዱ » Mon Mar 02, 2009 11:58 pm

ከምር እነዚህ ነጮች ሲባሉ ምን አይነት ሰይጣኖች ናቸው እባካችሁ :?: :?: :?: :?: :?: :?: :?:

HIV ን ለመከላከል ከነጭራሹ መሸለት ጥሩ አማራጭ ነው ይሉናል :!: :!: :!: :!: :!: :!: :!:

ታዲያ ለምን ከራሳቸው መጀመሪያውኑ አልጀመሩም :?: :?: :?: :?: :?: :?: :?: :?:

የሚገርመው ደግሞ የደንቆሮዎቹ ጥቁሮች እነሱን ሰምቶ ለመሸለት ወረፋ መያዝ :!: :!: :!: :!: :!: :!: :!:

ምን አይነት የተበላሸ አለም ነው እባካችሁ ያለነው :?: :?: :?: :?: :?: :?: :?:

የፈጣሪ ያለህ


ፀሃፊው ባቀረበው ሊንክ ግቡና አንብቡ


ራሴን ጠላሁ

ሀዲዱመልከጻዲቅ wrote:*******************በዛምቢያ ሉሳካ የአመቱ የኤይድስ ቀን እንዲህ አለፈ*************************

ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ (ማጣቀሻ ) ተጭናችሁ የምታዩት ሰውዬ ኬኔዲ ጎንዳዊ ይባላል:: ጎንዳዊው በዜና አቅራቢነት ደቡብ አፍሪካ ላለው የሬድዮ ጣቢያ ተመድቦ የሚሰራ ሲሆን ፎቶውና ዜናው..... እንደሚገልጹት ከሆነ... አቶ ኬኔዲ በምስክሮች ፊት የወንድ ብልቱን ማስቀንጠሱን ነው: :shock: ጎንዳዊ በዚህ አድራጎቱ እጅግ ቡዙ የስልክ የኢ-ሜይልና የጽሁፍ መለክቶች ደርሰውታል... ለዚህ... አልፋና ኦሜጋ ለሌለው ግርዛት ሉሳካ ወደሚገኘው ጤና ጣቢያ ሲሄድ....አጅበውት የመጡ ምስክሮች ነበሩት... የቢቢሲ የዜና ሰዎች:: ከኬንያ ከዩጋንዳ ከደቡብ አፍሪካ ያገኘውን መረጃ መሰረት አድርጎ በላንሰት የህክምና ጆርናል ላይ የወጣ አንድ የሳይንስ ጽሁፍ እንደዘገበው ".......በፍቃደኝነት....መሰለብ......ወንዶችን በኤድስ የማስያዝ እድሉን በእጅጉ ይቀንሳል..." ይላል:: ዋና መቀመጫው ኬንያ የሆነውና በተባበሩት መንግስታት ድርጀት የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጠው የጤና ማእከልም ይህንን ጥናት እንደሚያምንበት ገልጾ ተጨማሪ ምክር ሲሰጥ...."መሰለብ ብቻውን ሙሉ ውጤት አያስገኝም....ይልቁንም ከአንድ ሰው በላይ የወሲብ ጎደኛ አለመያዝ......ከጋብቻ በፊት ምንም አይነት የወሲብ ግኑኝነት አለማድረግ.....Abstinance......., ኮንደም መጠቀም.......የመሳሰሉት ከተጨመሩበት ግቡን ሊመታ ይችላል...ይላል:: ወደ ጎንዳዊ እንመለስ...... :arrow:.... ጋዜጠኛ ኬኔዲ ራሱን ለመስዋትነት ለማቅረብ ያነሳሳው ዋናው ጉዳይ....ዛሬም በኤይድስ ጉዳይ ላይ ህብረተሰቡ ግልጽ ውይይት ማድረግ ሳልልቻለ ነው:: " ይህ ደግሞ.....".ይላል....ጎንዳዊ....."ይህ ደግሞ ችግሩን አባሰው....እንጂ አልቀነሰውም....." በመቀጠልም ሲያስረዳ..... በአንድ አመት ብቻ በተለያየ ጊዜያት የኤይድስ ምርመራ ያደርጋል.....ከዙህ ሁሉ መሳቀቅና ስጋት....የተሻለው መፍትሔ ግን አንድ ፊቱኑ መሸለት ነው:: " በተለይ...በተለይ እኛ ...ጋዜጠኞች በዚህ ጉዳይ ላይ ግንባር-ቀደምነታችንን ማሳየት አለብን ይላል....ኬኔዲ ጎንዳዊ:: ጋዜጠኛ ጎንዳዊ ወንድነቱን ካስረከበ ቦሀላ መኪናውን እየነዳ ወደ ቤቱ ያለምንም ችግር እንደደረሰ በመኩራራት ገልጾአል:: ተቀማጭነታቸው ናይሮቢ ኬንያ የሆኑት David Alvnik ...በዩኒሴፍ የኤይድስ የጥናት ማእከል ከፍተኛ አማካሪ ሲሆኑ እሳቸው እንደገለጹት........ዩኒሴፍ ኤይድስን ለመከላከል........በፍቃደኝነት ዋነኛውን.. መሳሪያቸውን ማስረከብ የሚፈልጉትን....እንደሚያበረታታና እንደሚደግፍ ያለማቅማማት ገልጸው..... "ችግሩ...." አሉ, "ችግሩ በድሀዋ የአፍሪካ አህጉር ....የተሞላ መሳሪያ ያላቸው የመሸለቻ ቦታ በብዛት አለመኖራቸው ነው.... :roll: በዛምቢያ ብቻ የወንድ ብልታቸውን ለመሰጠት ወረፋ የሚጠብቁ ወንዶች መኖራቸውንና ይህም ሁኔታ ከፍተኛ የስራ መጎአተት በመፍጠሩ....መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ በመግባት እርዳታ ሰጭዎችንና በጎ አድራጊዎችን በቂ መሳሪያ እንዲያቀርቡ መወትወት እንዳለበት David Alvnick የአፍሪካ የኤይድስ ጥናትና ምርምር ከፍተኛ አማካሪ አሳስበዋል:: Ouch.....Ouch.....Ouch........ :!: :!:

http://www.msnbc.msn.com/id/22043754/
የሰቆቃውና የመከራው ማለቂያ ፤ ማብቂያ በእግዚአብሄርና በእኛ አንድነት ይሆናል
ሀዲዱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 891
Joined: Fri Jul 13, 2007 8:58 pm
Location: Here

Postby ይታየዋል » Sat Mar 07, 2009 10:18 pm

እንዴ እንዴ እንዴ ሀሪፍ ነገር ነች አስቀምቅሜ ይህንን አርስት ለከፈተው አምሰግናለሁ በማለት ያለማቆረጥ ሌላም ነገር ለሚያቀርብለን መልኬ ጻዲቅ ለሆነው ሰላምታየን በማልቀድም ሌሎችን ትሳትፉ ግብዣ እያረኩ ይህችን አንድ ልበል መቼ እንደሆነ አላውቅም አንድ ነገር የማውቀው ግን እኔ በዚያን ዘመን አልተወልድኩም ነገሩ እንዲህ ነው አዲስ አበባ ውስጥ አሉ ለመጀመሪያ ግዜ መኪናን ያስገቡት ንጉስ ስማቸውም ባላውቅም ነገር ግን ትረካው ይሄ ነው
አዲስ አበባ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ መኪና ገብቶ ሲሽከርከር በዚያን ግዜ የነበሩ አባቶቻችን መኪናዋን ከመፍራት የተነሳ በፍርሀት ደንግጠው ሮጠው አምልጠዋል አሉ:: ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ምን ይታወቃል ምን ታይቶቸው መኪናውን ለመጀመሪያ ግዜ ሲያዩ የሮጡት መኪናን ነድቶ በማያውቅ አዲስ ሾፌር ጎማ እንዳይበሉ ይሆናል 8)
ይታየዋል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 429
Joined: Fri Aug 03, 2007 3:54 am

Re: እስቲ ፍቅርን እንይ

Postby yodit » Sun Mar 08, 2009 12:11 pm

[quote="ሀዲዱ"]ተወዳጁና ታዋቂው አስተማሪዬ ይብራዕ እንዳስተማረኝ ከሆነ ፋንታ ማለት

FANTA -- ---- Arabs Never Taste Alcohol ይለዋል :: አረቦች አልኮል ስለማይጠጡ ለነሱ ተብሎ የተዘጋጀ መጠጥ ነው ይለዋል :: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ሀዲዱ
ሰላም ሀዲዱ
ጋሼ ይብራእ ረስተውት ነው ወይስ? ቅቅቅቅቅ አባባሉ እንዲህ መስለኝ ካተሳሳትኩ ""Foolish Arabs Never drink Alcohole"
mlkam qoyta
yodit
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 360
Joined: Sat Oct 25, 2003 9:43 pm

Postby መልከጻዲቅ » Sun Mar 08, 2009 10:09 pm

ይታየዋል እንደጻፈ(ች)ው:

አዲስ አበባ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ መኪና ገብቶ ሲሽከርከር በዚያን ግዜ የነበሩ አባቶቻችን መኪናዋን ከመፍራት የተነሳ በፍርሀት ደንግጠው ሮጠው አምልጠዋል አሉ :: ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ምን ይታወቃል ምን ታይቶቸው መኪናውን ለመጀመሪያ ግዜ ሲያዩ የሮጡት መኪናን ነድቶ በማያውቅ አዲስ ሾፌር ጎማ እንዳይበሉ ይሆናል


ይቺ አባባልህ ፈገግ አድርጋኛለች:: :D
ካነበብኩት ላካፍላችሁ::

***************አሁንስ እንደምንም ብሎ መንገስ ይሻላል**********************

በንጉሱ በሚኒልክ ዘመን የሆነ ነው:: ንጉሱ አራት ኪሎ የሚገኘውን ቤተ መንግስታቸውን ባንድ የውጭ መሀንዲስ እያሰሩ ነበር:: ዳግማዊ ሚኒልክ ታዲያ ሁልጊዜ ጃንሜዳ እየተገኙ " ፍርድ ትጔደለ ድሀ ተበደለ"" ለሚል አቤቱታ አቅራቢ ዳኝነት ሲሰጡ ይውሉና ችሎቱ እንዳለቀ ወደ ሚያሰሩት ቤተ መንግስት በመሄድ ግንባታውን ይመለከቱና ይጎበኙ ነበር:: ታዲያ እኚህ ሚንልክ በመጡ ቁጥር በግንባታው ዙሪያ አስተያየት ይሰጡ ነበር::

አንድ ቀን እንደተለመደው ጃንሜዳ ሲያስችሉ ውለው ወደ ሚሰራው ቤተ መንግስት ሄደው ግንባታውን ተመለከቱ:: "" ስማ አንተ ...! ማነህ መሀንዲሱ..."" አሉ ሚኒልክ ::

"" አቤት!"" አለ መሀንዲስ::

"" ይሄ ግንብ ለምን ተጣመመ? "" ጠየቁ ሚኒልክ ::

መሀንዲሱም "" ንጉስ ሆይ ይስተካከላል አስተካክላለሁ"" ብሎ መለሰ::
በሁለተኛውም ቀን ሚኒልክ ግንባታውን ሲገበኙ ስህተት ተመለከቱ::

"" ስማ አንተ መሀንዲስ የዚህ ጠርዝ እንጨት ምነው ወደውጭ ዘመመ?"" አሉት:: በሁኔታው የተደናገጠውም መሀንዲስ ወደ ግንቡ እየተመለከተ
"" ንጉስ ሆይ አስተካክላለሁ"" አለ::

በሶስተኛው ቀን መሀንዲሱ በጥንቃቄ ሲሰራ ዋለ:: በልቡም ዛሬ ንጉስ ሲመጡ በህንጻው ላይ ምንም ስህተት ሲያጡ ያመሰግኑኛል እንደውም ይሸልሙኛል ቢያንስ ማርቴሬዛ ብር እሱም እንኴን ባይኖር አንድ መቶ ግራም ወርቅ አያጡልኝም ሲል አሰበ:: ይሄን እያሰበ ልቡ በደስታ ሞቀች::
ጃንሆይ ሚኒልክ ከጃንሜዳ መጡና ግንባታውን መመልከት ጀመሩ:: "" ስራው ጥሩ ነው:: ተሰርቷል:: ግን ምነው ይህቺ ድንጋይ አቀማመጧ ተበላሸ?"" ብለው ያፈጠጠች ድንጋይ በከዘራቸው ለመሀንዲሱ አመለከቱት:: በሁኔታው የተበሳጨው መሀንዲስም "" ንጉስ ሆይ አሁንስ እንደ ምንም ብሎ መንገስ ሳይሻል አይቀርም "" አላቸው ይባላል::
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Re: እስቲ ፍቅርን እንይ

Postby ሀዲዱ » Mon Mar 09, 2009 3:03 am

ሰላም ዮዲት :!:

እንዳንቺ አባባል ከሆነማ FANTA ሳይሆን FANDA ሊባል ነው ማለት ነው ::
ዋርካዋ ባለጌ ነገር ተናገርክ ብላ በራስዋ ጊዜ አጠፋችብኝ እንጂ F የሚለውን ሲምቦል ሪፕሬዘንት የሚያደርገው "ፋክን" -- የሚለውን ፀያፍ ቃል ነው :: ታዲያ ምን አሳቀሽ :?: ሎጂክ ከተከተልን የማንኛችን ወደእውነቱ ይጠጋል :?:

ሰላም ሁኚ

ሀዲዱyodit wrote:
ሀዲዱ wrote:ተወዳጁና ታዋቂው አስተማሪዬ ይብራዕ እንዳስተማረኝ ከሆነ ፋንታ ማለት

FANTA -- ---- Arabs Never Taste Alcohol ይለዋል :: አረቦች አልኮል ስለማይጠጡ ለነሱ ተብሎ የተዘጋጀ መጠጥ ነው ይለዋል :: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ሀዲዱ
ሰላም ሀዲዱ
ጋሼ ይብራእ ረስተውት ነው ወይስ? ቅቅቅቅቅ አባባሉ እንዲህ መስለኝ ካተሳሳትኩ ""Foolish Arabs Never drink Alcohole"
mlkam qoyta
የሰቆቃውና የመከራው ማለቂያ ፤ ማብቂያ በእግዚአብሄርና በእኛ አንድነት ይሆናል
ሀዲዱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 891
Joined: Fri Jul 13, 2007 8:58 pm
Location: Here

Postby ማህቡብ » Sun Apr 26, 2009 11:24 am

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው!!

መስከረም -ሁለት ሺሕ (ዘመኑ በሙሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ ) የያኔዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳት ቢል ክሊንተን ከኩባዉ መሪ ፊደል ካስትሮ ጋር ድንገት ሳያስቡት ያዉም ለቅፅበት ያደረጉት ወራት በዘለቀ -የትችት፣ ወቀሳ ማዕበል የሚገፋ «ተዓምር» ነበር -የሆነዉ።ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማም ከትችት ወቀሳ አያመልጡ ይሆናል።ሰሞኑን ያሉት መደረጉን -የጀመሩት ዳር መዝለቁን በያኙም በርግጥ ጊዜ -ና ሁነት ነዉ።ከአይዘናወር -እስከ ቡሽ ከነበሩት አስር -ቀዳሚዎቻቸዉ ሥሕተት የመማራቸዉ ብስለት፤ የደደረዉን ዉልግድ -ለማረቅ -የመድፈራቸዉ ጀግንነት ያስደንቅ ይሆናል።ተዓምር ግን አይደለም።ሐቅ እንጂ።ሐቁ መድረሻችን፣ የሐቫና ዋሽንግተን ግንኙነት ዳራ -ጉልሕ፥ የአሜሪካ እዉነት ስስ -አብነታችን፣ የአሜሪካኖች ጉባኤ መነሻችን ነዉ -ላፍታ አብረን እንቆይ::
--------------------------------------------------------------
ፊደል ካስትሮ የመሯቸዉ አማፂዎች በ 1959 ሐቫናን -እስኪቆጣጠሩ ድረስ እንደዘበት አይተዋቸዉ የነበሩት የዋሽንግተን መሪዎች ዳግመኛ -አልተዘናጉም።ዋሽንግተኞች በነካስትሮ፣ በነቼ -ጉቤራ ርዕዮት፣ገድል -ድል ልቡ የሸፈተዉ የደቡብ አሜሪካ ወጣት ኮሚንስት ቺሊ ላይ በሕዝብ ምርጫ ሥልጣን ሲይዝ በጄኔራል አጉስቶ ፒኖሼ አስጨፈጨፉት።

የኒካራጓ ሶሻሊስቶችን በኮንትራ አማፂያን ለማስደፍለቅ አሜሪካዉያንን ካገቱት ከቴሕራን እስላማዊ አብዮተኞች ጋር እስከመዋዋል ደርሰዋል።ጥቅምት 1983 ቤርናርድ ኮርድ የመሯቸዉ የግሪናዳ ኮሚንስቶች -የጠቅላይ ሚንስትር ማዉሪሲ ቢሾፕን መንግሥት አስወግደዉ ትንሺቱን ሐገር ተቆጣጠሩ።ሳምንት ግን አልቆዩም።

የዩናይትድ ስቴትስና የተባባሪዎቿ ጦር ግሪናዳን ወርሮ -ከስልጣን አስወገዳቸዉ።አስፈጠማቸዉም። ለረጅም ጊዜ የዋሽንግተን ታማኝ የነበሩት የፓናማዉ ገዢ ጄኔራል ማኑኤል ኑርኤጋ በ 1980ዎቹ ማብቂያ ዉልፊጥ ቢሉ -የአሜሪካ ጦር ማንቁርታቸዉን ይዞ -ወሕኒ ወረወራቸዉ።ዩናይትድ ስቴትስ ሲሻት ጦሯን -እያዘመተች፣ ሲፈልጋት የቦጎታ መንግሥትን እየረዳች፤ የኮሎምቢያ ጫካዎችን መደብደብ ማስደብደቧ የአደንዛዥ እፅ -ተክል ዝዉዉርን ከማጥፋት ይልቅ የኮሚንስቶችን እንቅስቃሴ ለመግታት በርግጥ በእጅጉ ጠቅሟታል።

ሶቬት ሕብረት በተፈረካከሰች፣ አለም ኮሚንዝምን እርም ባለበት በ 1999 የቬኑዙዌላ ሕዝብ የመረጣቸዉ ሁጎ ራፋኤል ሻቬዝ ፍሪያስ ዳግማዊ ካስትሮ -መሆናቸዉ ለትልቂቱ ሐገር ትላልቅ መሪዎች ትልቅ ራስ ምታት ነዉ -የሆነዉ።ፕሬዝዳት ቢል ክሊንተን የሻቬዚን መርሕ -አላማ ቢያዉቁቱም ወደ ኒዮርክ ያቀኑት ሻቬዝ የትልቅ -ሐገራቸዉ ያፍንጫ -ሥር መዥገር መሆን -አለመሆናቸዉን ሳይወስኑ ነበር።


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአመአቱ ጉባኤ ያለዉ -የመሪዎች ጉባኤ ለክሊንተን የመጨረሻዉ፤ ለሻቬዝ የመጀመሪያቸዉ፣ ለካስትሮ ምናልባት አርባኛቸዉ ነበር።።የአለም መሪዎች ከምሳ -እረፍት ወደ ጉባኤዉ አዳራሽ እየተመሙ ነዉ።ክሊተን እያወጉ -ሲያዘግሙ፣ ካስትሮ ቀደም፣ ሻቬዝ ከተል ብለዉ ደረሱባቸዉ።ካስትሮ -እጃቸዉን ዘረጉ።ክሊንተንም።ተጨባበጡ።የኒዮርክ ተዓምር።መስከረም -ስድት ሁለት ሺሕ።

ተዓምሩ ለሰላም ጥሩ ጀምር በሆነ -ነበር።ሥልጣናቸዉን ለማስረከብ የአራት ወር እድሜ የቀራቸዉ ክሊንተን በጅምሩ ሊቀጥሉ ቀርቶ የጅምሩን ጥሩ -መጥፎነት ለማስተንተን እንኳን በርግጥ ጊዜ አልነበራቸዉም።«በቃ -ድንገት ሆነ» ብለዉ -አለፉት።

ለሌላዉ ግን አይዘናወር ከካስትሮዋ ኩባ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ካቋረጡበት ከ 1960 ጀምሮ፣ በካስትሮዋ ኩባ ሰበብ ሰወስተኛዉን የአለም፤ የመጀመሪያዉን የኑክሌር ጦርነት ለመግጠም የቆረጡት፣ ካስትሮን ለማስወገድ የቤይ ኦፍ ፒግ ተዋጊዎችን ያዘመቱት፤ ማዕቀብ የጣሉት፣ ካስትሮን ለማስገድል ስድስት መቶ -ሰላሳ ስምንት ጊዜ የወሰኑት የስምንት ቀዳሚዎቻቸዉን ዉግዘት ክሊንተን አረከሱት ነበር -ፍቺዉ።በዘጠነኛ አመቱ በቀደም ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ አሜሪካዊ -ኩባዉያን ኩባን እንዳይጎበኙ፥ለወዳጅ ዘመዳቸዉ ገንዘብ እንዳይልኩ፣የሚደነግገዉን ደንብ ማላላታቸዉ -በአክራሪ አሜሪካዉያን ዘንድ ብዙ ያስወቅስ -ያስተቻቸዉ ይሆናል።

አላማዉ ግን ቃል አቀባይ ሮበርት ጊብስ እንዳሉት ዲሞክራሲ፥ ሰብአዊ መብትን መደገፍ ነዉ።

«ሁላችንም ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የምንመኘዉ ለዜጎችዋ በሙሉ የሰብአዊ መብት፥የፖለቲካ እና የምጣኔ ሐብት ነፃነት መሠረት የሆኑት የዲሞክራሲያዊ እሴቶች የሰፈኑባት ኩባ እንድትኖር ነዉ።ፕሬዝዳንት ኦባማ ዛሬ የወሰዱት እርምጃ ይሕን አላማ ከግብ ለማድረስ ይረዳል ብለዉ -ያምናሉ።»

በክሊንተንን ድንገተኛ ጅምር ላይ የተሰነዘረዉ ጠንካራ ትችት የጅምሩን ጥሩ መጥፎነት ለማስተንተ ብቃቱ፤ ፍላጎቱ፤ ብስለቱም ላልነበራቸዉ ለፕሬዝዳት ጆርጅ ቡሽ አጓጉል መርሕ ጠንካራ መሸፈኛ ነበር -የሆነዉ።የቡሽ መስተዳድር በሐቫና እና በካራካስ፣ መሪዎች ላይ ሲዝቱ፤ ብራዚልን ከሜክሲኮ ሲያላትሙ፣ ቦሊቪያ ላይ «ሳልሳዊ ካስትሮ» ስልጣን ያዙ።ኢቮ ሞራሌስ።

የቡሽ መስተዳድር የኩባ፤ በቬኑዝዌላ እና የቮልቪያ ገዢዎችን ለማዳከም ኮሎምቢያን የመሳሰሉ ታማኞቹን ሲያስተባብር፥ በ 1980ዎቹ የሬጋን መስተዳድር ሊያጠፋቸዉ ሲባትል ከቅሌት የተነከረባቸዉ ዳንኤል ኦርቴጋ ዳግም የኒካራጉዋ መሪ ሆኑ።«አራተኛዉ ካስትሮ።» ኦርቴጋ « ...ኦባማ ተጠያቂ አደሉም»
ኦርቴጋ ባለፈዉ ቅዳሜ ፖርት ኦፍ ስፔን ለተሰየመዉ የአሜሪካ ሐገራት ጉባኤ ባደረጉት ንግግር የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ያሉት ሥርዓት በደቡብ አሜሪካ ሕዝብ ላይ ፈፀመ ያሉትን በደል -ሲዘረዝሩ -ሁለት አብነት ጠቅሰዉ ነበር።የሬጋን መስተዳድር በኒካራጓ -፣የኬኔዲ በ 1961 ቤይ ኦፍ ፒግስ በተባለዉ ዉጊያ በኩባ ሕዝቦች ላይ ፈፀሙ ያሉትን ግፍ።ኦባማን ግን ለዚሕ ግፍ አይጠየቁም ነዉ -ያሉት -ኦርቴጋ።

«የሰወስት ወር ሕፃን እያለሁ ለተሰራዉ» መለሱ -ኦባማ «እኔን ተጠያቂ ባለማድረጋ
ቸዉ» አመሰግናለሁ።የሰወስት ወር ሕፃን -አይደለም ጨርሶ ከመወለዳቸዉ በፊት ጀምሮ የፀናዉን የኩባና የዩናይትድ ስቴትስን የጠላትነት ግንኙነት መለወጡ እራሳቸዉ ኦባማ እንዳሉት ከባድ፥ጊዜ የሚጠይቅም ነዉ።

«ዩናይትድ ስቴትስ ከኩባ ጋር አዲስ ግንኙነት እንዲጀመር ትሻለች።ዘመናት ያስቆጠረዉን አለመተማመን ለማስወገድ ብዙ ርቀት መጓዝን እንደሚጠይቅ አዉቃለሁ።ይሁንና ካዲሱ ዕለት ለመድረስ መሠረታዊ የሆኑ እርምጃቸዉን መዉሰድ እንደምንችል አዉቃለሁ።»

የቡሽ መስተዳድር በ 2006 የተመረጡትን የቺሊ ፕሬዝዳት የወዝሮ ቬሮኒካ ሚሼላ ባችቤት የሪያን ግራ ዘመም መንግሥትን ለማዳከም ከፔሩና ከአርጀቲና ጋር ለማናቆር ሲባትል ከቺሊዋ መሪ ጋር ፆታም የፖለቲካ መርሕም የሚጋሩት ወይዘሮ ክርስቲና ኤሊዛበት ፈርዲናንዴስ ኪርቺነር የቦኒስ አይሪስን ቤተ -መንግሥት ተቆጣጠሩት።የቡሽ ባለሥልጣናት ክሪችኒር -እንዳይመረጡ ፥ለምርጫ ዘመቻቸዉ ከቬኑዝዌላዉ ፕሬዝዳት ሁጎ ሻቬዝ አንድ ሚሊዮን ዶላር ተቀብለዋል በማለት እስከመወንጀል ደርሰዉ ነበር::
የአርጀቲና ሕዝብ ዋሽግተኖችን ሰማቸዉ -ታዘባቸዉ።ሴትዮዋን ይበልጥ ወደዳቸዉ መረጣቸዉም።ኦባማን ኦርቴጋ -ለአልወነጀሏቸዉም፥ፕሬዝዳት ጆርጅ ቡሽን ዳቢሎስ በማለት ይሳደቡ የነበሩት ሁጎ ሻቬዝ ለኦባማ መፀሐፍ ነዉ -ያበረከቱላቸዉ።በቡሽ መስተዳድር አቂመዉ የነበሩት ከቦልቪያ እስከ አርጀንቲና፥ ከብራዚል እስከ ቺሊ ያሉት ሐገራት መሪዎችም በታላቅ አክብሮት ነዉ -የተቀበሏቸዉ።ራኡል ካስትሮ ደግሞ የሁሉንም አሉት -እንደራደር።

«ለዩናይትድ ስቴትስ እናገራለሁ።በሁሉም ጉዳይ ለመደራደር ዝግጁ ነን።ሥለ ሰብአዊ መብት፥ሥለ ፕረስ ነፃነት፥ሥለ ፖለቲካ እስረኞች -እዉነት እላችኋለሁ -ሥለሁሉም።ድርድሩ ግን በእኩለት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት።ሉአላዊነታችን መቼም ቢሆን ሊያጠራጥር አይገባም።»

ይሕ አይነቱ ምላሽ ኦባማ የክሊተንን ደመነሳዊ -ጅምር በበሳል -መርሕ ለመተካት -ለመጣራቸዉ፤እስከ ክሊንተን የዘለቀዉን ጅምላ ስሕተት በነጠረ -እዉነት ለማረም -ለመሞከራቸዉ፣ የቡሽን የስምንት አመት የጥፋት ጉዞ ቀና ፈር ለማስያዛቸዉ ጥሩ እማኝ ነዉ።ይሕ ቢቀር ሰባ -ከመቶ የሚበልጠዉ አሜሪካዊ ሐገሩ ኩባን ከመሳሰሉ ጎረቤቶቿ ጋር መልካም ግንኙነት እንድትመሰርት ይፈልጋል።ኦባማ ሌላ አላደረጉም። የመረጣቸዉን ሕዝብ ፍላጎት ማስፀም እንጂ።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby መልከጻዲቅ » Wed Jun 03, 2009 10:10 pm

*******************ከጳውሎስ ትዝታዎች********************

ለመሆኑ ስለቤት አከራዮችና ዘብናናነት ያጋጠመህ ነገር አለ? እኔስ እዳ ገብቻለሁ:: የቤቱ ጌታ እዚያው አጠገብ ስላለ በየምሽቱ እየሰከረ እየመጣ በስድብ ሲጠዘጥዘኝ ያመሻል:: እንዳንለቅ ባዶ ቤት ማሟሸቱን ጠላን:: እንዳንክሰው ስራ መፍራቱን ጠላን:: እጃችንን እንዳንሰነዝር እግዜርን ፈራን:: ምን ይሻላል ትላለህ?

የጳውሎስ መልስ:- ጌታው( የቤቱ ባለቤት) ቢታገሱ መልካም ነው:: የድሮ ሰዎች እንኴን ሲያወሩ ቤት የእግዚአብሄር ነው ይላሉና ለተከራያችሁበት ቢያዝኑላችሁ መልካም ነበር:: ያለዚያም የቤት ኪራይ ደንብ እስኪወጣ መጠበቅ ነው:: ወደፊት ተስፋ ይኖር ይሆናልና እስከዚያው ተቻችሎ መኖር ነው::

እኔ የምለው በአለም ላይ ሰው ባይፈጠር ኖሮ አለም ምን ትሆን ነበር ትላለህ?

የጳውሎስ መልስ:- ምንም!

በሲጃራና በቢራ ላይ ዋጋ የጨመረበት ምክንያት ምንድነው? የሚመለከተውን ክፍል ጠይቀህ ትነግረኛለህ?

የጳውሎስ መልስ:- የቅንጦት ነገሮች ናቸው ተብለው ነው:: የውስኪውን ዋጋ ከፍ እስካላደረጉ ድረስ እኔን አይመለከተኝም::
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby መልከጻዲቅ » Wed Jun 03, 2009 10:13 pm

*******************ከጳውሎስ ትዝታዎች********************

ለመሆኑ ስለቤት አከራዮችና ዘብናናነት ያጋጠመህ ነገር አለ? እኔስ እዳ ገብቻለሁ:: የቤቱ ጌታ እዚያው አጠገብ ስላለ በየምሽቱ እየሰከረ እየመጣ በስድብ ሲጠዘጥዘኝ ያመሻል:: እንዳንለቅ ባዶ ቤት ማሟሸቱን ጠላን:: እንዳንክሰው ስራ መፍራቱን ጠላን:: እጃችንን እንዳንሰነዝር እግዜርን ፈራን:: ምን ይሻላል ትላለህ?

የጳውሎስ መልስ:- ጌታው( የቤቱ ባለቤት) ቢታገሱ መልካም ነው:: የድሮ ሰዎች እንኴን ሲያወሩ ቤት የእግዚአብሄር ነው ይላሉና ለተከራያችሁበት ቢያዝኑላችሁ መልካም ነበር:: ያለዚያም የቤት ኪራይ ደንብ እስኪወጣ መጠበቅ ነው:: ወደፊት ተስፋ ይኖር ይሆናልና እስከዚያው ተቻችሎ መኖር ነው::

እኔ የምለው በአለም ላይ ሰው ባይፈጠር ኖሮ አለም ምን ትሆን ነበር ትላለህ?

የጳውሎስ መልስ:- ምንም!

በሲጃራና በቢራ ላይ ዋጋ የጨመረበት ምክንያት ምንድነው? የሚመለከተውን ክፍል ጠይቀህ ትነግረኛለህ?

የጳውሎስ መልስ:- የቅንጦት ነገሮች ናቸው ተብለው ነው:: የውስኪውን ዋጋ ከፍ እስካላደረጉ ድረስ እኔን አይመለከተኝም::
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot], Google [Bot], Google Adsense [Bot] and 3 guests