by መልከጻዲቅ » Sat Sep 26, 2009 6:46 pm
የያዝነው የመስከረም ወር አዲስ አመት የባተበት አሮጌውን የተሰናበትበት በመሆኑ ባለፈው አመት ያጣናቸውን የኪነ ጥበብ ሰዎች ላፍታ መለስ ብለን እንቃኛቸዋለን::
*ድምጻዊ ሚኒልክ ወስናቸው(ከ1933-2001)
*ዐ. ምህረቶቹ በሙሉ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጥር ናቸው::
በልጅነቱ ወደ ሙዚቃ አለም የተቀላቀለው ድምጻዊ ሚኒልክ ወስናቸው የሙዚቃ ህይወቱ የጀመረው በ 18 አመቱ በ1951 በብሄራዊ ቲያቲር ቤት በድምጻዊነት በመቀጠር ነበር:: ህይወቱ እስካለፈችበት እስከ ታህሳሰ 25 ቀን 2001 ዐ.ም ድረስ በሙዚቃ ዘርፍ አስተዋጽኦ አበርክቷል::
* ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሰስ( ከ1933-2001)
ካሀምሳ አመት በላይ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ የነገሰው አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ በድንገተኛ ህመም ህይወቱ ያለፈው በዚህ ባሳላፍነው የኢትዮጵያን አመት ሚያዚያ 11 ነበር::
* አርቲስት ሲራክ ታደሰ ( ከ1938-2001)
መስከረም 8, 2001 ከዚህ አለም በሞት የተለየው አርቲስት ሲራክ ታደሰ ለበርካታ ታዋቂ ድምጻውያን ግጥምና ዜማ የሰራ ሲሆን ሲራክ የበለጠ የሚታወቀው በሰራቸው በርካታ ቲያቲሮችና የራዲዮ ድራማዎች ነበር:: ከነዚህም መካከል እርጉም ሀዋርያ , ውድቀት, ንጉስ አርማህ, መርዛማ ጥላ, ሀሁ በስድስት ወር, አምታታው በከተማ, ሀምሌት... ይገኙበታል::
* አርቲስት አለሙ ገ/አብ(1946-2001)
ሀምሌ 3 ቀን 2001 ከዚህ አለም በሞት የተለየው አርቲስት አለሙ በቲያቲር ትወና በፊልም በራዲዮና በቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች ከፍተኛ ዕውቅና ነበረው::
*ኮ/ል ለማ ደምሰው ( 1934-2001)
ከ1949 ጀምሮ እስከ 1966( በደም ግፊት የአልጋ ቁራኛ እስከሆነበት ) ድረስ በርካታ ዜማዎች በድምጽና በሙዚቃ መሳሪያዎች ተጫውቷል:: ነሀሴ 16 ህይወቱ ያለፈው ኮ/ል ለማ " ብቸኛ የፒያኖ ቃኚ " በመባል ይታወቅ ነበር::
*ድምጻዊ አንሙት ክንዴ( ሀብቱ ንጋቱ) (1956-2001)
ከጊሽ አባይ የኪነት ቡድን ጋር በመሆን በርካታ ስራዎችን የሰራው አንሙት ክንዼ የበለጠ በህዝብ ዘንድ የሚታወቀው አንቱዬዋ በተሰኘችው ሙዚቃዊ ድራማው ነው:: ድምጻዊ አንሙት በዋሽንት መሪ ድምጽ የተሰሩ 4 አልበሞች አሳትሟል::
*አርቲስት ደስታ ገብሬ(1932-2001)
የመጀመሪያ ሴት ተወዛዋዥ እንደሆነች የሚነገርላት የእስክስታ ንግስትዋ ደስታ ገብሬ ህይወቷ ያለፈው ህዳር 12 ቀን 2001 ነበር::
*አርቲስት ወጋየሁ ደግነቱ ( 1940-2001)
"እናት "በተሰኘው የሙዚቃ ስራው የሚታወቀው ድምጻዊ ወጋየሁ ደግነቱ ህይወቱ ያለፈችው ሀምሌ 10 ቀን 2001 ነበር:: ወጋየሁ ደግነቱ ድምጻዊ ብቻ ሳይሆን የግጥምና የዜማ ደራሲም ነበር::
ለሁሉም ነፍስ ይማር :!:
የዚህ ጽሁፍ ምንጭ ሉሲ ዛሬ ናት::
ያለፈውን አመት ስናስታውስ መንገድ ላይ የተላለፉ ሁለት ታምራቶችን እናያለን:: ባንድ ወቅት የዚህ መንግስት ከፍተኛ ባለ ስልጣን ሆነው የነበሩት ታምራት ከወህኒ ሲወጡ ክርስቶስን አየሁት ብለው ባደባባይ ሲናገሩ በለስ ያልቀናቸው ሌላው ታምራት ደሞ እኔ ክርስቶስ ነኝ ብለው ወደ ወህኒ ወርደዋል::