ይህን ያውቁ ኖሯል ?

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሚሚlove » Wed Feb 01, 2006 11:16 am

ለወድ ብናማ በመጀመሪያ በጣም አመስግናለሁ ሰለ እርማትህ Picasso ስፔናዊ መሆኑን ያወቅኩት አሁን ነው ኢንተር ኔት ላይ አንተ ፖስት ካደረክልኝ በኃላ ገብቼ ያነበብኩት እሱም እንዲህ ይላል 1881-1973, Spanish painter and sculptor.....
Creative presentation featuring works, a biography, genealogy, and exhibition list courtesy of the Picasso Administration. Also in French and Spanish.
እኔ በመጀመሪያ ያነበብኩት መፅሄት ላይ ነበር :: እና ስለደነቀኝ እኔም ለዚሁ አምድ አቀረብኩት ስለማስተካከያህ አመሰግናለሁ :: ቀጥለህም ስላቀረብክልን ገልፅ አድናቆቴን በዚሁ አቀርባለሁ ::

እስኪ አንድ ለበላችሁ .......
ሴት እርግብ ብቻዋን ከሆነች እንቁላል አትጥልም ሌላ ሴትም ሆን ወንድ እርግብ አጠገቧ ካለግን የመሀፅን እንቁላሏ ይክፈታል:: አለበለዚያ ትልቅ መስታወት እጎኗ ማስቀመጥ ያስፈልጋል:: እርግቧ ምስሏን ካየች እንቁላል መጣሉላይ አትጨነቅም::

ቸር ሰንብቱ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ማህቡብ » Wed Feb 01, 2006 11:32 am

ውድ ዩፎ :- ስለእርማቱ እታመሰገንኩ ምናልባት ካነበብኩት የተሻለ ያንተን ተመሳሳይ እስካኝ አንተ በሰነዘርከው ሀሳብ እንቆይ :: እሚፈለገው መማማሩ ስለሆነ በድጋሚ ላመሰግንህ ወዳለሁ ::

***በአለም በጣም ውድ የሆነው ምግብ የትኛው ነው ብላችሁ መልሱ ምን ይመስላችሁዋል ? እሽ ብዙ አታስቡ መልሱ ሮያል ዲሉክስ ካቭያር የሚባለው ነው :: ይህ ምግብ የሚሼጠው እየተመዘነ ሲሆን, አንድ ኪሎ የሮያል ካቭያር ዋጋ አብድ ሽ ሰላሳሁለት ዶላር ገደማ ነው :: በኢትዮጵያ ገንዘብ ደግሞ አንድ ኪሎ ለሚመዝን ለዚሁ ምግብ ከሁለት ሽ ብር በላይ ማውጣት ያስፈልጋል ማለት ነው :: በነገራችን ላይ ይህ በአለም ውድ የሆነው ሮያል ዲሉክስ ካቭያር የተባለው ምግብ ምን ይሆን ብላችሁ ለምትጠይቁ ብታምኑም ባታምኑም የአሳ እንቁላል ነው ::


ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ሰምፔር » Wed Feb 01, 2006 2:01 pm

ንስር ካረጀ በሁዋላ ተመልሶ ወጣት እንደሚሆን ያውቃሉ?

ያረጀ ንስር በህይወቱ መጨረሻ ዘመናት ላባዎቹ እድገታቸዉን ይገቱና ቀለማቸው ተለውጦ ቀስ በቀስ መዉደቅ ይጀምራሉ::አፉ ይዶሎድማል:: ጥፍሩም ይደንዛል, አስቀድሞ ይበርበት የነበረዉን ከፍታ መዝለቅ ያቅተዋል; እንደጎልማሳነቱ በአፉ ምግቡን መዘነጣጠል ይታክተዋል: በጥፍሮቹም ምግቡን መያዝና መጨበጥ ይሳነዋል:ለንስሩ በተፈጥሮ ስሜቱ (ደመነፍሱ) በኩል ከፍ ብሎ ወደ ተራሮች መብረርና ብቻዉን የሚቆይበት (የሚደበቅበት) ዋሻ ማግኘት አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑ የሚገለጥለት በዚህ ወቅት ነው:: በዋሻ ቆይታው ንስሩ የቀድሞ ላባዎቹን አፉንና ጥፍሮቹን ጨርሶ እስከሚያስወግዳቸው ድረስ ከአለት ጋር ይታከካል:.ይህ ወቅት ለንስሩ ምንም ምግብ የማይበላበት; ውኃም የማይጠጣበት የጾም ወቅት ነው::በጣም ረጅም አድካሚና ፈታኝ የብቸኝነት ሕይወት ነው:. በተፈጥሮ ስሜቱ ላባዎቹ፣ አፉና ጥፍሮቹ ቀስ በቀስ እንደገና እንደጎልማሳነቱ ጊዜ ሆነው እንደሚበቅሉለት ስለሚያውቅ በተስፋ ይጠባበቃል::
ንስሩ ይህን የመሰወር ጊዜ በድል ፈጽሞ ክንፎቹን በመዘርጋት ለአለም ሁሉ እንደገና ለመታየት ብቅ በሚልበት ጊዜ ገና ለጋ ወጣት ይመስላል። ክንፎቹ ታድሰዉለታልና ጥንት ያውቃቸው በነበሩት ከፍታዎች ሁሉ ላይ እንደልቡ እንደገና ይበርባቸዋል::
ሰምፔር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 57
Joined: Mon Jun 20, 2005 3:06 pm
Location: ethiopia

Postby ማህቡብ » Thu Feb 02, 2006 1:28 pm

*** በአለማችን ከተለያዩ ሀገሮች የሠራተኛውን መብት የሚያስከብሩ የሙያተኛ ማህበር ተቁዋቁመው ይገኛሉ, እንደዛ ከሆነ ዘንዳም ትልቁ ወይንም በብዛት አባላት ያለው የሙያተኛ ማህበር በየትኛው ሃገር የሚገኝ ይመስላችሁዋል ? መልሱ በፖላንድ የሚገኘው አሁን የታገደው የሶሊዳሪቲ የሞያተኞች ማህበር ነው::

ይህ የሞያተኞች ማህበር እንደ አውሮፓዊያን አቅጣጠር በ1980 አመተ ምህረት ሲመሰረት 800 ሚሊዮን አባላት ነበረው ::


ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ቡናማ » Thu Feb 02, 2006 3:26 pm

የእዚህን አምድ መከፈት በጣም አስደሳች ሁኖ ነው ያገኘሁት::ለመማማር የሚያመችና አግባብ ባላቸው አስተያየቶች(አስተያየት ሰጪዎች) የታጨቀ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ::
ለዛሬ ላዋጣ ያሰብኩት ይህን ይመስላል::
Marcel Duchamp ስለተሰኘ ፈረንሳዊ ሰአሊ ብዙም እውቂያ ያለው መግለጫ እንደነ ቫንጎህ ና ፒካሶ ባብዛኛው አይስጥም::እንደኔ ግምት ግን ይህ ሰአሊ (Artist) ለሀያኛው ክፍለ-ዘመን በርካታ ያሳሳል ዘይቤዎች የተጫወተው ሚና ታላቅ ነበር::በ1912 "A Nude descending a Staircase" የተሰኘ ስእሉን በ Kubism & Futurism ያሳሳል ጥበብ ባቀረበ ጊዜ ትልቅ የባህል ነውጥ አራማጅ እስከመሰኘት የደረሰ ሲሆን: በቀጣዩም አመት Ready-Mades ተብሎ በተሰኘው የራሱ መንገድ ካረጀ ባይስክል አውላልቆ በሌላ መልክ በመገጣጠም የሰራውን ስራ ለማሳየት በቃ:: ይሄ የእርሱ የሆነ ግኝት(ስነ-ጥበባዊ መንገድ እስከ ክፍለ-ዘመኑ ማብቂያና ዛሬም ቢሆን ትልቅ የሰአሊያን መገልገያ ስልት የሆነ ነው::
የዚህን ሰው ሌላ አስተዋጾ የሚያጎሉልን እንደ Dadaism, Surealism, Pop_Art ና የመሳሰሉት የስነ-ጥበብ መንገዶች ወይም isms የእርሱን ተፈላሳፊነት:ተመራማሪነትና ስር ነቀል ለውጥ ፈላጊነት በግልጽ በማሳየት ነው::
የእርሱ መታወቂያ ሆኖ ከተገኘች ለምናልባቱ አንድ ታዋቂ አሽሙር አዘል ስእሉ እዚህ ጋ ብትጠቀስ አይከፋም::ይህች ሰእሉ የታዋቂውን ጣሊያናዊ ሰአሊ ሊዎናርዶ ዳቬንቺ ሞናሊዛ ባለጺማም አድርጎ ያቀረበባት ነበረች::በዚያም በግርድፉ ሊታይለት የሚሆነው ነገር ከ 4ና500 አመታት በላይ ሲያገለግል የቆየውን Realism እንዲሁም አካዳሚክ የሆነ ያሳሳል ስልት በሌላ መተካት ለውጥ ፈላጊ እንደነበረ ነው::
እንግዲህ የነበረው ተሰልችቶ አዲስ እንዲፈጠር ማሪያም ማሪያም ለሚል የጥበብ ሰው እስከዚህም ድረስ ተሂዶ እጅ እጅ ባዩን ዘልማድ ማሄስና ማንቋሰስ ከመብትም በላይ ጠቢብነት እንዲመስል ያደረገ ይሄ dadaist የክፍለ-ዘመኑ ምርጥ ከመሰኘት ምን ያጉድለዋል?
በነገራችን ላይ Dadaism ማለት እንደ Nihilism ሲተረጎም
በአማርኛችን ይመችና ይጥም የመሰለኝ አዛማጅ ትርጉም "አፈንጋጭ' ወይም 'ጸረ-ዘልማድ' የሚል ነው::ጥሟችሁ ይሆን??
በወዳጅነት እንቀጥል::
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

Postby ማህቡብ » Sun Feb 05, 2006 10:02 am

ያንድ ሠው ልብ ካቆመ ሞተ ማለት ነው ? በካናዳ የዊኒቴ ህክምና ማእከል ውስጥ እንደ አውሮፓውዊያን አቆጣጠር ጥር 19 1997 አመተምህረት ሚስስ ጆን ጆባን የምትባል የ20 አመት ኮረዳ ልብዋ መምታት ካቆመ ከ3 ሳአታት ከ32 ደቂቃ በህዋላ 26 የሳይንስ ጠቢባንን የሚያጠቃልል የህክምና ቡድን ቪክቶኒያን ዳያለስስ የሚባል ዘዴ በመጠቀም ከላይ እንደጠቀስኩት ለ3 ሰአታት ከ32 ደቂቃ ቆሞ የነበረውን ልብዋን እንደገና ሊያንቀሳቅሱት እና ህይዎትዋን ሊመልሱላት ችለዋል ::


ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby Monica**** » Sun Feb 05, 2006 10:09 am

ለቤቱ ባለቤት የኔ ቁምነገረኛ ማህቡብዬና
ለተሳታፊዎቹ በሙሉ ስላምታዬ ይድረሳችሁ!!!
በጣም ደስ የሚል ትምህርት ነው የምትስጡን እንደውም የተወዳጁ የጳውሎስ ኞኞ አስደናቂ ታሪኮችን አስታወስኝ!!!
በርቱ ለማለት ነው የገባሁት :wink:
አክባሪያችሁ
ሞኒካ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

እስቲ ፍቅርን እንይ

Postby ቡናማ » Tue Feb 07, 2006 5:06 pm

ውድ የዚህ አምድ ወዳጆች
እንደምን ከረማችሁ?

የኮካ ኮላ ካምፓኒ ፋንታ የተባለውን ተወዳጅ መጠጥ Fantasy ከሚለው የእንግሊዘኛ ቃል ቆርጦ በማውጣት እንደሰየመው በቅርቡ ሰማሁ::ላስተውሎት ከጠቀመ ብዬ ነው ያነሳሁት::
ዛሬ ከተጨዋወትን ስለ ፍቅር ቢሆንስ ብዬ ነው የመጣሁ::
ፍቅር በግሪክኛና በላቲንኛ የተለያየ አተናተን አለው::መጠሪያዎቹም Philia, eros, agape, storge and xenia ይባላሉ::እነርሱንም ለመተንተን ያህል;

Agape;(በግሪክኛ s'agapo ማለት I love you የሚል ትርጓሜ ይሰጣል)
እናም ይሄ የፍቅር ቃል እውነተኛን,ፍጹማዊ የሆነን እንደመለኮታዊ ያለውን አይነት ፍቅር ይወክላል::ይሄው አገላለጽ ለላቲንኛው Caritas በይዘቱ ሲቀርብ በጥቅል መሰኛ እንደ Love of a soul ይታወቃል::
Eros (erota በግሪክኛ being in Love እንደማለት)
ይህ በስጋዊ መፈላለግ ላይ የተመሰረተና በተመሳሳይ ምኞት የታጨቀን(ሽፍደታዊ) ፍቅር ይወክላል::

Philia-ይህ ፍጹም የሆነንና የጤናማ ጓደኝነት ቅርርብን ለመጥራት ሲሆን ያም ቤተሰባዊ,ማህበራዊ ና መሰል የሆነን በእኩልነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተን ፍቅር የሚያወሳ ነው::

Storge-በዘመናዊው ግሪክኛ አወሳሰድ እንደ በፍቅር መጠመድ አልያም መማረክን ለመግለጽ ያገለግላል::

Xenia-ይህም እንክብካቤን የተሞላ ፍቅር መስጠት እንደማለትን ሲገልፅ አንድን ፍፅምና የተሞላ በእንግዳና ተቀባዩ መሀል የሚፈጠረን መንፈሳዊ ህብረት(አብሮነት),በጎነትን ይጠቅሳል::በጎን ነገር ለሌላው በማድረግ የሚገኝን የምስጋና ብልፅግና መጥሪያነት ያገለግላል::
እንደ John Alan Lee's "Love styles" ደግሞ ፍቅር እንዲህን መሳይ ጥቅል ትንታኔ አለው::

Eros (romantic love)- a passionate physical love based on physical appearance and beauty.

Ludus (game playing)- love is played as a game; love is playful; often involves little or no commitment and thrives on "Conquests".

Storge (companionate love)- an affectionate love that slowly develops, based on similarity and friendship.

Pragma (pragmatic love)- inclination to select a partner based on practical and rational criteria where both benefit from the partnership.

Mania (possessive love)- highly emotional love; unstable; the stereotype of romantic love; its characterstics include jealousy and conflict.

Agape (altruistic love)- selfless altruistic love; spritual

በነገራችን ላይ እንደ Susan S. Hendrick የተሰኙ የሳይኮሎጂ ፕሮፈሰር ግኝት ከታየ ወንዶች በተለይ ወደ ludic/ludius/ ና manic/mania/ የፍቅር አይነት ሲያዘነብሉ ሴቶች ደግሞ ወደ storgic/storge/ ና pragmatic/pragma/
ያመዝናሉ::
ወይ ፍቅር አያ አያልቅበት...
እንዳነጋገረ የነበረ,ያለና የሚኖር ታላቁ የሰው ልጆች የእውቀት ገበታ
ወዳጆች እኔ በኛው ባገሪኛው እወዳችኌለሁ በማለት ለዛሬ
ጣጣዬን በዚሁ ጨረስኩኝ::
በወዳጅነት እንቀጥል::
ቡናማ
Last edited by ቡናማ on Thu Feb 23, 2006 12:46 pm, edited 1 time in total.
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

Postby BRUKYIRGA » Wed Feb 08, 2006 3:55 am

Image
BRUKYIRGA
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 218
Joined: Sat Nov 26, 2005 12:36 am
Location: minnesota/usa

Postby BRUKYIRGA » Wed Feb 08, 2006 6:59 am

ገንዘብ ካለ .........
ይህ ፎቶ የተወሰደው የተባበሩት አረብ ኢማራት ነው በዛ በረሀ ላይ የበረዶ መንሸራተቻ ካምቦሎጆ ገንዘብ ካለ አረብ አገርም በረዶ አለ እንበል ይሆን Image
Image
Image
Image
Image
BRUKYIRGA
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 218
Joined: Sat Nov 26, 2005 12:36 am
Location: minnesota/usa

Postby BRUKYIRGA » Wed Feb 08, 2006 7:13 am

ወዳጅ ማህቡብ
ሰላም ሳልልህ ሩምህ በመግባቴ ይቅርታ
ከላይ ፖስት ያረኩት ምን ያህል እንደሚጠቅም እንጃ እኔን ግን አስገርሞኛል በዛም ላይ ያገኘውን የወረወረ .............
ይህን ፎቶ ለመለጠፍ (እንዴት እንደሆን) ቀብራራው ለወጭባራው ያስተማረበት ጽሁፍ እኔንም አስተምሮኛልና
ቀብራራው ምስጋናዬ ይድረስህ
ቸር ይግጠመን
BRUKYIRGA
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 218
Joined: Sat Nov 26, 2005 12:36 am
Location: minnesota/usa

Postby ማህቡብ » Thu Feb 09, 2006 7:09 am

ወንድሜ:- BRUKYIRGA ሠላም ባለህበት, በእውነቱ በጣም ትምህርታዊ ነገር ስለሆነ ሌላ ካለህ ቤቱ ቤትህ ነው ::

*** ለራስ ምታት ለሆድ ቁርጠት ለቁርጥማት መቸም አልፎ አልፎ ባመመንና በጎረበጠን ቁጥር የተለያዩ የህክምና እንክብሎችን መዋጥ የተለመደ ተግባር ነው :: የእንክብሎች መዋጥ ከተነሳ ዘንድ በጊዱራ ዚምባቡዌ ሲ ኤች ኤ ኬልነር ስለተባለ አንድ ሠው አንድ ወሬ ላካፍላችሁ, ይህ ሠው ለያዘው የጣፊያ በሽታ ቀዶ ጥገና ከተደረገለት በህዋላ ለ15 አመታት ከ1967 እስከ 1982 አመተምህረት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ባለው ጊዜ ውስጥ ለበሽታው ይጠቅማሉ 386 ሺህ 436 የህክምና እንክብሎችን እንዲውጥ ተደርጉዋል :: እንደው ጉድ እኮ ነው ::

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ቡናማ » Fri Feb 10, 2006 1:29 pm

ሰላም ወዳጆች
በአማርኛ የስነ ግጥም ስልት ውስጥ በመደበኛ ግጥምነት,ባለስድስት ቀለማማና የተዋጡ 4 ሀረጎች ያሉዋት አንዲት ታሪከኛ ግጥም አለች::
ግጥሚቱ እህች ናት::

አዳም በበደለ መድሀኒአለም ክሶ
ዋለ ቀራኒዮ ከለሜዳ ለብሶ::

ሚስጥረ ጥበቡዋ የተሰነቀው ለምሳሌ በመጀመሪያው ሀረግ "አዳም በበደለ..." የአዳም ጥፋቱ; "መድሀኒአለም ክሶ" ሲል ደግሞ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ለበደላችን ቤዛነት እንደሰው ስጋ ለብሶ ወደ ምድር መምጣቱንና ለእኛም ያደረጋቸውን ታምራት ሁሉ ሲያሳስበን;
"ዋለ ቀራኒዮ..." ስለሰው ልጅ በደል ራሱን ለመከራና ስቃይ አሳልፎ የሰጠበትን ወክሎ; "ከለሜዳ ለብሶ" በሚለው ደግሞ "የእኛን ሀጢያት እርሱ ለበሰ,ለበደላችንም እጥበት በከለሜዳ ደም የመሰለ ልብስ ተጎናፅፎ ከመስቀል ላይ ዋለ" የሚለውን እውነታ በስሜታችን ውስጥ ያገዝፈዋል::

ድንቅ አይደለችም ታዲያ?

በወዳጅነት ያስቀጥለን::
ቡናማ
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

Postby ማህቡብ » Sun Feb 12, 2006 9:53 am

*** የኢኮኖሚ ውጥረት አለማችንን አፋጥዋት በሚገኝበት በአሁኑ ጊዜ የሥራ አጡ ቁጥር ከፍ እያለ በመሄድ ላይ ነው የሚለውን ወሬ የተለያዩ የዜና ምንጮች በየጊዜው ያሰማሉ ከሚሊዮን በላይ, ግማሽ ሚሊዮን, በመቶ ሺ, በሺ የሚቆጠር በሥራ አጥነት ይጎሳቀላሉ በሚባልበት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1973 አመተ ምህረት 6ሚሊዮን 6መቶሺ ህዝብ በሚገኝባት ስዊዘርላንድ የሥራ አጡ ቁጥር የሚያስገርመው 81 ሠው ብቻ ነበር ::

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ሚሚlove » Tue Feb 14, 2006 10:49 am

ስላም ለናንተ ይሁን. . . . .

* በጠፈር ላይ መነጋገር አይቻልም:: ምክንያቱም የድምፅ ሞገድ ተሸክሚ የሚጓዝ ሚድየም ባለመኖሩ ነው::
* ሁሉም ፕላኒቶች የሚዞሩት ከምዕራብ ወደ ምስራቅ ነው:: ቨነስ ግን በተቃራኒ አቅጣጫ ከምስራቅ ወድ ምዕራብ ትዞራለች (ልክ እንደ ሰአት)
* ለሊት በእንቅልፍ ላይ ሆነን ቁመታችን 8 ሚ.ሜ ይጨምራል:: ጠዋት ስንነሳ ግን ወድ ቦታው ይመለሳል::
* አንጎላችን አንዳችም ስሜት (ሴላሴቪን) ከሌለው በስለት ቢቆረጥ እንኳን አይሰማንም::

ለዛሬ ይችን ታክል ካልኩ በሌላ ጊዜ እስክንገናኝ ቸር ሰንብቱ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 2 guests