ይህን ያውቁ ኖሯል ?

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ማህቡብ » Sun Dec 27, 2009 3:06 pm

ሰላም ውድ ማህቡብ የ 2009 አመት መውጫን የአዲሱን አመት መባቻን አስመልክተህ የአለምን ውሎ - ክራሞት በብእርህ አስዳደስከን :: ድንቅ ግምጋሜ ነው :: እዚህ ከመጣሁ አይቀር ካነበብኩት አንድ ላካፍላችሁ


መልከጻዲቅ ወንድሜ ሠላም ባለህበት:- ዛሬም አዝናኝ እና ትምህርታዊ የሆኑ መጣጥፎችህን ማንበብ ደስ ይለኛል:: በርግጥም ልክ እንደ ሮክፌለርን እርባና አይኖራቸውም እየተባሉ ያደጉ ያለማችን ታዋቂ ሰዎች ብዙ ናቸው እሚያስገርመው የእንዴትነቱ ሳይሆን የጥረታቸው ሚስጥር እንጅ:: ቸር እንሰንብት

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Mon Dec 28, 2009 8:02 am

መማክርት ሳይጠሩ ጠበብት ሳያስፈልጉ ዘመነ ጋብቻቸውን ወርቃማ ሊያደርጉ የበቁ አረጋውያንና አረጋውያት አሉ አይደለም ዎይ ? የአርባና የሀምሳ አመት ባልና ሚስት ሆነው የብር የወርቅ ኢዮቤልዩ አክብረው የተገኙ አሉ
አይደለም ዎይ ? ተብሎ ይጠየቃል ::

እነዚህን ነጥቦች ጠለቅ ብለን ስንመረምራቸው እውነቱ የሁዋላ የሁዋላ ይገለጽልናል እንጅ ለጊዜው በጥያቄዎቹ መደነጋገራችን አይቀርም :: እውነት እኮ ነው ! መጽሀፍ ሳያነቡ በእውቀት ሳይጠበቡ መማክርት ሳያሻቸው ሊቃውንት ሳያስፈልጋቸው ተጋብተው የኖሩ አብረው የሼበቱ አሉ አይደሉም ዎይ ? ታዲያ የምክሩ የዝክሩ የሰነዱ የጥራዙ ጥቅም ከየት ላይ ነው ? ብለን በነገሩ ላይ በብርቱ ሳንጠያየቅበት አንቀርም ::

አዎን ሳያቁ በጥበብ ሳይረቁ ለንባብ ለምክር ሳይጨነቁ እመ -ቤት አበ -ቤት ሆነው የልጅ ልጅ አይተው ለሁለት ጸጉር በቅተው ለግዜው አዛውንትነት ምስክር ሆነው የኖሩ አሉ :: ይህን በምንፈትሽበት ወቅት አንድ በምሳሌነቱ የማይናቅ ሌላ ነጥብ ማንሳቱንም አንጠላውም ::

ይህውም ስለ አንድ ህንጻ ቤት ነው :: የጥበብ እጅ ሙያተኛ ሳይገባበት የማሀንዲስ ጥበብ ሳይጨመርበት ንድፍ ቅያስ ሳይታከልበት የታነጸ ቤት በስንት ጥናትና እውቀት መከራ አይተው ከሰሩት ቤት እኩል የእድሜ ባለጸጋ መሆኑን አይተናል ::

ያ ጥበብ በጎደላችው የእነጻ ተግባር ምን እንደሆነ ባላወቁ ሰዎች የተገነባው ቤት እንደ እምቡዋይ ካብ እለቱን አልፈረሰም :: እንዲያውም ከጥበበኞች ማለፊያ ስራ እኩል ሼምግሉዋል :: "ሽምግልና " ብለን በጥልቅ ስንፈትሽ ግን አንዳንድ ጥያቄዎች ይደቀኑብናል :: ሽምግልናው በወዙ ነው ያለው ወይንስ ቆርፍዶ ? ተጭማዶና ተጭራምቶ መቸም እንዳማሩ ማርጀት ባይኖር እንኩዋ ወላልቆና ተጎሳቁሎ መገኘት የሽምግልና ወግ መሆን የለበትም ::

ታዲያ ያ የጥበበኞችን እጅ ሊያገኝ ሳይበቃ የተገነባው ህንጻ የሽምግልናው መልክ ምን ይመስል ይሆን ? እንደዛ የአዋቂ ጥበብ እንደዳሰሳቸው እንደዚያ የጥበበኞች ብልሀት እንዳልተለያቸው ህንጻዎች መሰረቱ ጸንቶ በነበረበት ረግቶ "አዛውንት " ተብሉዋል ? ወይንስ መሰረቱ እየተናጋ ግድግዳው ከአመት አመት እየነቃቃ በአሼዋና ኖራ ብርታት ብቻ የግዱን እየተንገዳገደ የቆመ ነው ? ቀጥ ብሎ እንዳማረበት የሼመገለ ወይንስ ተንጋዶ የጃጀ ?
እንግዲህ የህንጻውን ጉዳይ ከጋብቻው ጋር አዛምደን ስንመለከተው መሰል ጥያቄዎችን ለራሳችን አቅርበን አእምሯችን እንዲቸገር እንሻለን ቁም ነገሩ አብሮ መሼበት መበልተት የሚለው ላይ አይደለም :: መጀመሪያ እንደ ጸሀይ ሞቆ እንደ ጨረቃ ደምቆ የነበረው ፍቅር እንደ ክረምት ሳይቆፈንን እንደ ዛገ ብረት ሳይዘጉን አብሮ ሼምግሉዋል ዎይ ? በየወራቱ በየአመቱ በአረጋዊያን ምእላድ እየተጠጋገነ እንደ ነዳይ ድሪቶ እየተጣጣፈ ለአዛውንትነት በቅቱዋል ? እንግዲህ የአብሮ መሼበት ባልና ሚስት ሆኖ የዘመን መቁጠርና የአመታት መቀመር ትርጉዋሜው ሰፋ ያለ መሆኑን እንገነዘባለን ::

ልጅ ያለ አባት ይቅርብኝ ዎይ ? ህጻናቱ ያለ እናት ይደጉ ዎይ የለፋሁበትን ትዳር ትቸ ልውጣ ዎይ ? እምነቴስ ? ሀይማኖቴስ ? በሚሉትና በመሳሰሉት ልዩ ልዩ ምክኒያቶች ባልና ሚስት አብረው ያረጃሉ :: ዘመናቸውን ትቆጥራሉ ለብር ለወርቅ ኢዮቤልዩ ይደርሳሉ እዚህ ላይ እንግዲህመንፈሳዊ ውህደት በአካላዊ አንድነት ደርጅቶ በፍቅርታስሮና ተተብትቦ የተገኘበትን አዝማሚያ አይጠቁመንም
ምናልባት ስለ ልጅና ስለተለፋበት ቤት በማሰባቸው ስሜታዊ ብስለት ሊኖራቸው ይችላል :: ልብ የገዙ አእምሮ ያላቸው ይሆናሉ :: በአካልና በመንፈስ ግን የበለጸጉ አይደሉም :: በውህደትና አንድነትም የጠነከሩ አይደሉም :: አንድ አካል አንድ አምሳል ሊያደርጋቸው የበቅው ወሲባዊ ግንኝ Uነት በፍቅር መሳሪያነት እውን ሊሆን የቻለበት ሁኔታ አይታየንምና !

ታዲያ እነዚህ ሰዎች አብረው ቢያረጁ የጠቀሙት ማንን ነው ? ልጆቻቸውን ብቻ ሊሆን ነው :: ወይንም የላእላይ ስሜታቸውን በሀብትና ንብረት አስጊጠው ውስጥ ውስጡን ተቆራምደውና ደህይተው የሚኖሩ ናቸው ማለት ነው ቤቱን አዋቅሮ ያለ ክፍካፍ እንዳስቀረው ሰው ሊቆጠሩም ይችላሉ ::

ጋብቻና ፍቅር ምክር ያስፈልጋቸዋልን ? ለሚለው ጥያቄ መልሱን በመጠኑ ያገኘን ይመስላል :: የስነ ጋብቻ መማክርትና የስነ ልቦና ሊቃውንት የተመራመሩ የብእር አለቆች የማህበራዊ ጉዳይ ፈታሾችና ተንታኞች የሚጽፉትና የሚመክሩት ባልና ሚስት በትዳራቸው ጸንተው በውህደታቸው ረግተው እንዲኖሩ ነው :: የተፈጥሮ ህግ በሆነውና ለውህደት ጽድቅ መረጋገጫነቱ በተመሰከረበት በወሲባዊ ግንኙነት ታርቀው ህይዎታቸው ከወንዝ ዳር እንደበቀለች ተክል እንድትለመልም ነው :: በፍቅር አልባ ጉድኝት ሳቢያ ድረ ወጥነት እንዳይነግስ ጎጆ እንዳይፈርስ ጋብቻ እንዳይረክስ ነው :: ለዚህ ነው የምክርና መማክርት አስፈላጊነት ::

ሠው በትዳሩ የተደሰተ በጋብቻው የተደላደለ ካልሆነ በቀር ምርታማነቱ ያዘቀዘቀ ይሆናል :: ስለዚህ የሙያው በሰሎች ሰው አደብ የገዛ በስነ ስራትና ስነ ምግባር የተገዛ በስሜቱ የበሰለና የሰከነ በውህደቱ የደነደነ ይሆን ዘንድ ያስተምራሉ ይመክራሉ :: እንደተዋደደ እንዲያረጅ እንዳማረበት እንዲሼመግል የተቻላቸውን ያደርጋሉ ወረቀቶችን ለጥራዝ ያበቃሉ ሰነዶችን አደባባይ ያወጣሉ ከሀሳብ አፍልቀው ከልብ አመንጭተው ይጽፋሉ :: ድርሳናት መርምረው ህብረተሰብ አዋይተው ግለሰብ አነጋግረው በቀለም ያስጌጣሉ ::
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby መልከጻዲቅ » Sun Jan 03, 2010 2:07 am

ወርሀ ሰኔ 1945 ዐ. ም ለህትመት የበቃው የአዕምሮ ጋዜጣ ከዚህ የሚከተለውን ማስታወቂያ ባምዱ ላይ አስፍሮ ነበር::

ማስታወቂያ

ከሁሉም የኮኛክ ፋብሪካ የበለጠው ከግሪክ አገር የባርቤሬሶ ነው:: ባርቤሬሶ ከቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት እጅ ያሰናጂ ፍቃድ የተቀበለ ነው:: ( ቢዝነስ ላይሰንስ እንደምንድነው ማለት ነው) ተታላችሁ ክልስ እንዳትገዙ አደራ:: ክልስ ( ፍቃድ የሌለው.. ፌክ ፕሮዳክት...):: ይህን በካፕሱሉ ያለውን መርምሩ:: ይህ ምልክት በካፕስሉ የሌለበት ኮኛክ "" ኮኛክ ክልሱ "" ነው::

የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታህሳስ 17 1935 ዐ.ም እትም ለአምደኞቹ ይሄንን ማስታወቂያ አስነበበ::

አምቦ ጠበልና ንፋስ ለመለወጥ የምታስቡ ክቡራኖች ነጻነት ክብሬ በሚባለው ሆቴላችን እንግዶችን በትህትናና በፍቅር እንቀበላለን:: አምቦ ከመውረዳችሁም በፊት አዲስ አበባ ፍልውሀ ግቢ ባለው ቡና ቤታችን አሽከር ልካችሁ የክፍል ቤቶችን ማዕረግ ልታስጠይቁ ትችላላችሁ::
አዘጋጂዎች:: ካብትህ ይመር አደራና ገብረ መስቀል ዋስይሁን::
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby መልከጻዲቅ » Sun Feb 14, 2010 1:24 am

ከጳውሎስ ኖኞ ትዝታዎች

ጥያቄ:- ከእድገት በህብረት ዘማች

ከወሊሶ ወደ ቡኢ ስንዘምት አንዲት ቅል ይዤ ነበር የመጣሁት:: ታዲያልህ ይሀውልህ ይቺ ቅል መጋቢት 1 ቀን ተሰበረችብኝ:: አሁን ውሀ የምይዝበት ኮዳ የለኝም:: ባለፈው እትምህ ላይ ልመና አብዝታችኌል ብለህ ወቅሰሀን ነበር:: በርግጥ ሌላውን ማስቸገር ይቀፋል:: ግን ምን ይሻላል ትላለህ?

የጳውሎስ መልስ:- ለዚህ የሚሻለው መፍትሄ ከዚያው ሌላ ቅል መፈለግ ነው::

ጥያቄ :- ስሙ አቶ ጳውሎስ በወላምኛ ጽፌ የላኩትን ለምንድነው ያላወጡት? አስተርጔሚ አጡ? ወይስ ንቀት ነው?

የጳውሎስ መልስ:- ሳትረሳው በመጠየቅህ አመሰግናለሁ:: አቶ ቤዛ ሊተረጉሙልኝ ቃል ከገቡልኝ በኌላ በየቀኑ እስከ አሁን ድረስ እንደለመንኴቸው አለሁ:: እምቢ ላይሉኝ እኔም ሌላ እንዳልፈልግ አሁን መጣሁ እተረጉምልሀለሁ እያሉኝ ቀጠሮ የሚያፈርሱ በመሆናቸው ብቻ ቆየብህ:: ያስቀመጥኩትም ከሌላዎቹ ሁሉ ለይቼ ለብቻው ነው:: ሌላ የምልህ ነገር ግን ይሄ ንቀት ነው ምንትስ የምትለውን ተወኝ:: ምናልባትም ላይወጣ ይችላል::
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ማህቡብ » Tue May 18, 2010 3:49 pm

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው::

መስከረም -ሁለት ሺሕ (ዘመኑ በሙሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ ) የያኔዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳት ቢል ክሊንተን ከኩባዉ መሪ ፊደል ካስትሮ ጋር ድንገት ሳያስቡት ያዉም ለቅፅበት ያደረጉት ወራት በዘለቀ -የትችት፣ ወቀሳ ማዕበል የሚገፋ «ተዓምር» ነበር -የሆነዉ።ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማም ከትችት ወቀሳ አያመልጡ ይሆናል።ሰሞኑን ያሉት መደረጉን -የጀመሩት ዳር መዝለቁን በያኙም በርግጥ ጊዜ -ና ሁነት ነዉ።ከአይዘናወር -እስከ ቡሽ ከነበሩት አስር -ቀዳሚዎቻቸዉ ሥሕተት የመማራቸዉ ብስለት፤ የደደረዉን ዉልግድ -ለማረቅ -የመድፈራቸዉ ጀግንነት ያስደንቅ ይሆናል።ተዓምር ግን አይደለም።ሐቅ እንጂ።ሐቁ መድረሻችን፣ የሐቫና ዋሽንግተን ግንኙነት ዳራ -ጉልሕ፥ የአሜሪካ እዉነት ስስ -አብነታችን፣ የአሜሪካኖች ጉባኤ መነሻችን ነዉ -ላፍታ አብራችሁን ቆዩ።
ፊደል ካስትሮ የመሯቸዉ አማፂዎች በ 1959 ሐቫናን -እስኪቆጣጠሩ ድረስ እንደዘበት አይተዋቸዉ የነበሩት የዋሽንግተን መሪዎች ዳግመኛ -አልተዘናጉም።ዋሽንግተኞች በነካስትሮ፣ በነቼ -ጉቤራ ርዕዮት፣ገድል -ድል ልቡ የሸፈተዉ የደቡብ አሜሪካ ወጣት ኮሚንስት ቺሊ ላይ በሕዝብ ምርጫ ሥልጣን ሲይዝ በጄኔራል አጉስቶ ፒኖሼ አስጨፈጨፉት።

የኒካራጓ ሶሻሊስቶችን በኮንትራ አማፂያን ለማስደፍለቅ አሜሪካዉያንን ካገቱት ከቴሕራን እስላማዊ አብዮተኞች ጋር እስከመዋዋል ደርሰዋል።ጥቅምት 1983 ቤርናርድ ኮርድ የመሯቸዉ የግሪናዳ ኮሚንስቶች -የጠቅላይ ሚንስትር ማዉሪሲ ቢሾፕን መንግሥት አስወግደዉ ትንሺቱን ሐገር ተቆጣጠሩ።ሳምንት ግን አልቆዩም።

የዩናይትድ ስቴትስና የተባባሪዎቿ ጦር ግሪናዳን ወርሮ -ከስልጣን አስወገዳቸዉ።አስፈጠማቸዉም። ለረጅም ጊዜ የዋሽንግተን ታማኝ የነበሩት የፓናማዉ ገዢ ጄኔራል ማኑኤል ኑርኤጋ በ 1980ዎቹ ማብቂያ ዉልፊጥ ቢሉ -የአሜሪካ ጦር ማንቁርታቸዉን ይዞ -ወሕኒ ወረወራቸዉ።ዩናይትድ ስቴትስ ሲሻት ጦሯን -እያዘመተች፣ ሲፈልጋት የቦጎታ መንግሥትን እየረዳች፤ የኮሎምቢያ ጫካዎችን መደብደብ ማስደብደቧ የአደንዛዥ እፅ -ተክል ዝዉዉርን ከማጥፋት ይልቅ የኮሚንስቶችን እንቅስቃሴ ለመግታት በርግጥ በእጅጉ ጠቅሟታል።

ሶቬት ሕብረት በተፈረካከሰች፣ አለም ኮሚንዝምን እርም ባለበት በ 1999 የቬኑዙዌላ ሕዝብ የመረጣቸዉ ሁጎ ራፋኤል ሻቬዝ ፍሪያስ ዳግማዊ ካስትሮ -መሆናቸዉ ለትልቂቱ ሐገር ትላልቅ መሪዎች ትልቅ ራስ ምታት ነዉ -የሆነዉ።ፕሬዝዳት ቢል ክሊንተን የሻቬዚን መርሕ -አላማ ቢያዉቁቱም ወደ ኒዮርክ ያቀኑት ሻቬዝ የትልቅ -ሐገራቸዉ ያፍንጫ -ሥር መዥገር መሆን -አለመሆናቸዉን ሳይወስኑ ነበር።


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአመአቱ ጉባኤ ያለዉ -የመሪዎች ጉባኤ ለክሊንተን የመጨረሻዉ፤ ለሻቬዝ የመጀመሪያቸዉ፣ ለካስትሮ ምናልባት አርባኛቸዉ ነበር።።የአለም መሪዎች ከምሳ -እረፍት ወደ ጉባኤዉ አዳራሽ እየተመሙ ነዉ።ክሊተን እያወጉ -ሲያዘግሙ፣ ካስትሮ ቀደም፣ ሻቬዝ ከተል ብለዉ ደረሱባቸዉ።ካስትሮ -እጃቸዉን ዘረጉ።ክሊንተንም።ተጨባበጡ።የኒዮርክ ተዓምር።መስከረም -ስድት ሁለት ሺሕ።

ተዓምሩ ለሰላም ጥሩ ጀምር በሆነ -ነበር።ሥልጣናቸዉን ለማስረከብ የአራት ወር እድሜ የቀራቸዉ ክሊንተን በጅምሩ ሊቀጥሉ ቀርቶ የጅምሩን ጥሩ -መጥፎነት ለማስተንተን እንኳን በርግጥ ጊዜ አልነበራቸዉም።«በቃ -ድንገት ሆነ» ብለዉ -አለፉት።

ለሌላዉ ግን አይዘናወር ከካስትሮዋ ኩባ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ካቋረጡበት ከ 1960 ጀምሮ፣ በካስትሮዋ ኩባ ሰበብ ሰወስተኛዉን የአለም፤ የመጀመሪያዉን የኑክሌር ጦርነት ለመግጠም የቆረጡት፣ ካስትሮን ለማስወገድ የቤይ ኦፍ ፒግ ተዋጊዎችን ያዘመቱት፤ ማዕቀብ የጣሉት፣ ካስትሮን ለማስገድል ስድስት መቶ -ሰላሳ ስምንት ጊዜ የወሰኑት የስምንት ቀዳሚዎቻቸዉን ዉግዘት ክሊንተን አረከሱት ነበር -ፍቺዉ።በዘጠነኛ አመቱ በቀደም ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ አሜሪካዊ -ኩባዉያን ኩባን እንዳይጎበኙ፥ለወዳጅ ዘመዳቸዉ ገንዘብ እንዳይልኩ፣የሚደነግገዉን ደንብ ማላላታቸዉ -በአክራሪ አሜሪካዉያን ዘንድ ብዙ ያስወቅስ -ያስተቻቸዉ ይሆናል።

አላማዉ ግን ቃል አቀባይ ሮበርት ጊብስ እንዳሉት ዲሞክራሲ፥ ሰብአዊ መብትን መደገፍ ነዉ።
ድምፅ
«ሁላችንም ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የምንመኘዉ ለዜጎችዋ በሙሉ የሰብአዊ መብት፥የፖለቲካ እና የምጣኔ ሐብት ነፃነት መሠረት የሆኑት የዲሞክራሲያዊ እሴቶች የሰፈኑባት ኩባ እንድትኖር ነዉ።ፕሬዝዳንት ኦባማ ዛሬ የወሰዱት እርምጃ ይሕን አላማ ከግብ ለማድረስ ይረዳል ብለዉ -ያምናሉ።»

በክሊንተንን ድንገተኛ ጅምር ላይ የተሰነዘረዉ ጠንካራ ትችት የጅምሩን ጥሩ መጥፎነት ለማስተንተ ብቃቱ፤ ፍላጎቱ፤ ብስለቱም ላልነበራቸዉ ለፕሬዝዳት ጆርጅ ቡሽ አጓጉል መርሕ ጠንካራ መሸፈኛ ነበር -የሆነዉ።የቡሽ መስተዳድር በሐቫና እና በካራካስ፣ መሪዎች ላይ ሲዝቱ፤ ብራዚልን ከሜክሲኮ ሲያላትሙ፣ ቦሊቪያ ላይ «ሳልሳዊ ካስትሮ» ስልጣን ያዙ።ኢቮ ሞራሌስ።

የቡሽ መስተዳድር የኩባ፤ በቬኑዝዌላ እና የቮልቪያ ገዢዎችን ለማዳከም ኮሎምቢያን የመሳሰሉ ታማኞቹን ሲያስተባብር፥ በ 1980ዎቹ የሬጋን መስተዳድር ሊያጠፋቸዉ ሲባትል ከቅሌት የተነከረባቸዉ ዳንኤል ኦርቴጋ ዳግም የኒካራጉዋ መሪ ሆኑ።«አራተኛዉ ካስትሮ።» ኦርቴጋ « ...ኦባማ ተጠያቂ አደሉም»
ኦርቴጋ ባለፈዉ ቅዳሜ ፖርት ኦፍ ስፔን ለተሰየመዉ የአሜሪካ ሐገራት ጉባኤ ባደረጉት ንግግር የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ያሉት ሥርዓት በደቡብ አሜሪካ ሕዝብ ላይ ፈፀመ ያሉትን በደል -ሲዘረዝሩ -ሁለት አብነት ጠቅሰዉ ነበር።የሬጋን መስተዳድር በኒካራጓ -፣የኬኔዲ በ 1961 ቤይ ኦፍ ፒግስ በተባለዉ ዉጊያ በኩባ ሕዝቦች ላይ ፈፀሙ ያሉትን ግፍ።ኦባማን ግን ለዚሕ ግፍ አይጠየቁም ነዉ -ያሉት -ኦርቴጋ።

«የሰወስት ወር ሕፃን እያለሁ ለተሰራዉ» መለሱ -ኦባማ «እኔን ተጠያቂ ባለማድረጋ
ቸዉ» አመሰግናለሁ።የሰወስት ወር ሕፃን -አይደለም ጨርሶ ከመወለዳቸዉ በፊት ጀምሮ የፀናዉን የኩባና የዩናይትድ ስቴትስን የጠላትነት ግንኙነት መለወጡ እራሳቸዉ ኦባማ እንዳሉት ከባድ፥ጊዜ የሚጠይቅም ነዉ።
ድምፅ
«ዩናይትድ ስቴትስ ከኩባ ጋር አዲስ ግንኙነት እንዲጀመር ትሻለች።ዘመናት ያስቆጠረዉን አለመተማመን ለማስወገድ ብዙ ርቀት መጓዝን እንደሚጠይቅ አዉቃለሁ።ይሁንና ካዲሱ ዕለት ለመድረስ መሠረታዊ የሆኑ እርምጃቸዉን መዉሰድ እንደምንችል አዉቃለሁ።»

የቡሽ መስተዳድር በ 2006 የተመረጡትን የቺሊ ፕሬዝዳት የወዝሮ ቬሮኒካ ሚሼላ ባችቤት የሪያን ግራ ዘመም መንግሥትን ለማዳከም ከፔሩና ከአርጀቲና ጋር ለማናቆር ሲባትል ከቺሊዋ መሪ ጋር ፆታም የፖለቲካ መርሕም የሚጋሩት ወይዘሮ ክርስቲና ኤሊዛበት ፈርዲናንዴስ ኪርቺነር የቦኒስ አይሪስን ቤተ -መንግሥት ተቆጣጠሩት።የቡሽ ባለሥልጣናት ክሪችኒር -እንዳይመረጡ ፥ለምርጫ ዘመቻቸዉ ከቬኑዝዌላዉ ፕሬዝዳት ሁጎ ሻቬዝ አንድ ሚሊዮን ዶላር ተቀብለዋል በማለት እስከመወንጀል ደርሰዉ -ነበር። ራኡል ካስትሮ « ... እንደራደር»
የአርጀቲና ሕዝብ ዋሽግተኖችን ሰማቸዉ -ታዘባቸዉ።ሴትዮዋን ይበልጥ ወደዳቸዉ መረጣቸዉም።ኦባማን ኦርቴጋ -ለአልወነጀሏቸዉም፥ፕሬዝዳት ጆርጅ ቡሽን ዳቢሎስ በማለት ይሳደቡ የነበሩት ሁጎ ሻቬዝ ለኦባማ መፀሐፍ ነዉ -ያበረከቱላቸዉ።በቡሽ መስተዳድር አቂመዉ የነበሩት ከቦልቪያ እስከ አርጀንቲና፥ ከብራዚል እስከ ቺሊ ያሉት ሐገራት መሪዎችም በታላቅ አክብሮት ነዉ -የተቀበሏቸዉ።ራኡል ካስትሮ ደግሞ የሁሉንም አሉት -እንደራደር።
ድምፅ
«ለዩናይትድ ስቴትስ እናገራለሁ።በሁሉም ጉዳይ ለመደራደር ዝግጁ ነን።ሥለ ሰብአዊ መብት፥ሥለ ፕረስ ነፃነት፥ሥለ ፖለቲካ እስረኞች -እዉነት እላችኋለሁ -ሥለሁሉም።ድርድሩ ግን በእኩለት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት።ሉአላዊነታችን መቼም ቢሆን ሊያጠራጥር አይገባም።»

ይሕ አይነቱ ምላሽ ኦባማ የክሊተንን ደመነሳዊ -ጅምር በበሳል -መርሕ ለመተካት -ለመጣራቸዉ፤እስከ ክሊንተን የዘለቀዉን ጅምላ ስሕተት በነጠረ -እዉነት ለማረም -ለመሞከራቸዉ፣ የቡሽን የስምንት አመት የጥፋት ጉዞ ቀና ፈር ለማስያዛቸዉ ጥሩ እማኝ ነዉ።ይሕ ቢቀር ሰባ -ከመቶ የሚበልጠዉ አሜሪካዊ ሐገሩ ኩባን ከመሳሰሉ ጎረቤቶቿ ጋር መልካም ግንኙነት እንድትመሰርት ይፈልጋል።ኦባማ ሌላ አላደረጉም። የመራጣቸዉን ሕዝብ ፍላጎት ማስፀም እንጂ።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue May 18, 2010 4:06 pm

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው ::

አንድ ነገር እርግጥ ነዉ።ኢትዮጵያ ዉስጥ የፊታችን እሁድ ምርጫ አለ።ሌላም ነገር እርግጥ ነዉ።
የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ከዛሬ የደረሱት እንደ ዲሞክራሲዉ ወግ እየተከራከሩ፣ እንደ አዉቶክራሲዉ ልምድ ሕይወት፣ አካል እያስጠፉ፣እንደ አዋቂ እየተወያዩ፣ እንደ እንጭጭ እየተተራረቡ፣እንደ ጨዋ ኢትዮጵያዊ በክብር-አንቱ ቅፅል እየተጠራሩ፣እንደ ዋልጌ-እተወራረፉ ነዉ።ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዉን እስከ እሁድና እሁድ የሚገጥማቸዉን፣ የከዕሁድ በሕላ ፖለቲካዊ ጉዟቸዉን ማወቅ አይቻልም።ማወቅ አይደለም መገመት የሚችል ካለ እሱ በርግጥ ነብይ አከል ነዉ።መጠየቅ ግን ማን ገዶን።እርግጠኛዉን ሁነት እያነሳን የማይታወቀዉን ላፍታ አብረን እንጠይቅ።

ኢትዮጵያና ኢጣሊያ ዉጫሌ ላይ የተፈራረሙት ዉል የአማርኛና የኢጣላያንኛዉ ትርጉም አስራሰባተኛዉ አንቀፁ ላይ እንደሚቃረን ለንጉሠ-ነገሥት ዳግማዊ ሚኒሊክ የተነገራቸዉ ግንቦት ነበር አሉ።1881።ደገኛዉ ኢትዮጵያዊ የግቦትን ወር ከዚያ በፊትም ሆነ በሕዋላ እንደ መጥፎ ወቅት ነዉ-የሚያየዉ።ግንቦት ሞቃት ነዉ።አይታረስበትም።ቢሰረግበት ፍቅር ትዳር አይጠናበትም።ሞፈር፣ ቀንበር፣ ድግር-ቢቆረጥ ቢጠረብበት-ቶሎ ይሰነጣቃል።

ግን ወሩ ምን አደረገ።አጉል እምነት እንጂ።የዉጫሌዉስ ዉል ምን ይወጣለታል።ብቻ ትርጉሙ መዛባቱ መዘዙ ጦርነት ማስከተሉ እንጂ ክፋቱ።የዚያ ዉል መዘዘኛ አንቀፅ ትርጉም በታወቀ በሃያኛዉ አመት ልጅ እያሱ የአያታቸዉ የዳግማዊ ምኒልክ አልጋወራሽ ሆነዉ ተሾሙ።ግንቦት ነበር ወሩ።በኢትዮጵያ የብዙ መቶ አመታት ታሪክ የመጀመሪያዉ ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር መጀመሪያ ነበር።አምልኮ እንኳን ቢሆን ግንቦት ለትዮጵያ ጥሩ እንጂ መጥፎ ወር የሚባልበት ምን ምክንያት አለ።

እንዲያዉም የቀድሞዉ
ምርጫ-1997 የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፕሬዝዳንት ያሁኑ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ሊቀመንበር ኢንጂነር ሐይሉ ሻዉል ባለፈዉ አመት ግንቦት እንዳሉት በተለይ የ1997ቱ ግንቦት ለኢትዮጵያ የድንቅ ሁነት አብነት ነዉ።

ኢንጂነር ሐይሉ የሰማነዉን ሲሉ-ኢትዮጵያዊዉ የ1997ቱን ምርጫ አራተኛ አመት እየዘከረ የዘንድሮዉን አመት አሻግሮ እያማተረ ነበር።የደገኛዉ ኢትዮጵያዊ ልምድም ግንቦት አይሰረግበትም አይልም-ፍቅር ትዳሩ ዳር አይዘልቅበትም-እንጂ።ግንቦትን ልጅ እያሱ ለአልጋወራሽነት ተሾሙበት እንጂ አልነገሱበትም።

ኢትዮጵያዊዉ ከዚያ በፊትና በሕላ ብዙም የማዉቀዉን የሠላማዊ የስልጣን ሽግግርን ተስፋ አደረገበት እንጂ በገቢር አላየበትም።ደርግ ከሕልፈቱ በሕዋላ ብዙዎች እንደሚሉት የኢትዮጵያ ድቀት ምክንያት፥ የኢትዮጵያዉያን ዉድቀት፥ የጦርነት-እልቂት ፍጅት ሰበብ ከነበረ-የዉጫሌዉ ዉል በተፈረመ በመቶኛ አመቱ ሌላ ተስፋ ነበር።1981-ግንቦት።መፈንቅለ መንግሥት።ተሞከረ እንጂ አልተሳካም።

በሁለተኛ አመቱም ሌላ ሁነት ነበር።የደርግ-ሥርዓት ዉድቀት።እንደገና ግንቦት።1983።እንደገና ተስፋ ቃልም ጭምር።-የሠላም፥ የዲሞክራሲ፥ የነፃነት የብልፅግና ቃል-ተስፋ።ዳር መዝለቁ ግን አጠራጣሪ አነጋጋሪም ነዉ።በሰባተኛ አመቱ እንደገና ሌላ ጦርነት።እንደገና ግንቦት።1997 ከተስፋዉ ቅጭት ጋር-የዉጪዉ አለም-ኋላ ቀር፥ ብዙ የማያዉቅ መሐይም፥ የሠላም-ዲሞክራሲ ልምድ የሌለዉ የሚለዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ትልቅ ነገር አሳይቷል።ጨዋ-ታጋሽ፥ አዋቂነቱን አሳይቷል።

በነገሥታት-አምባገነኖች መገዛት መረገጥን እንጂ መሪዎቹን መርጦ መሾምን ያልለመደዉ፣ ችግር ችጋርን እንጂ ድሎት ምቾትን ብዙ የማያወቀዉ፣ ጦርነት-ግጭትን እንጂ ሰላም-መረጋጋትን ብዙ የማያወቀዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመሪዎቹ እና ሊመሩት ከሚመኙት ፖለቲከኞቹ ቀድሞ መብሰሉን በርግጥ ያኔ አስመስክሯል።ኢንጂነር ሐይሉ ከዋናዎቹ ምሥክሮች-አንዱ ናቸዉ።

ዘንድሮም ግንቦት ነዉ።ዘንድሮም ምርጫ አለ።-እሁድ።የሚሆነዉ ግን አሁን አናዉቅም።የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የሚሉትን የሚያደርጉ ጀግኖች፣ የማያደርጉትን የማይሉ ብልሆች፣የሕዝብ ፍላጎት አክባሪ-ቅኖች፥ የሐገር ጥቅም፣ተቆርቋሪ አርቆ አሳቢዎች መሆናቸዉን አስመሰክረዉ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያዉያን የድሕረ-እሁድ ጉዞን በጎ-መጥፎነት ለመገመት ዛሬና አስከዛሬን መጠበቅ ባላስፈለገ ነበር።አለመሆኑ ነዉ-ሥጋቱ።

ያ ሕዝብ ሥለወደፊቱ ቀርቶ ሥለዛሬ ኑሮዉ፥ የሚያዉቀዉ የፖለቲከኞቹን ብያኔ ጠባቂነቱን ከዚሕ ካለፈም አለማወቁን ማወቁ ነዉ መሆኑ ነዉ ድቀቱ።የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ-መድረክ ባጭሩ ጥምረት ከፍተኛ ባለሥልጣንና ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ መሪ ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉ ከቅድመ ሁኔታ ጋር ተስፋ አላቸዉ።

ገዢዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር -ኢሕአዴግ ምርጫዉን እንደ ዲሞክራሲዉ ወግ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆን ከብዙ ጊዜ በላይ ብዙ ብሏል።የተቀዋሚ ፓርቲ መሪዎች ግን የገዢዉን ፓርቲ ቃል-አያምኑትም።ከዚሁ ጋር የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪዎች እንደ ዲሞክራሲዉ ሥርዓት አስር ጊዜ በአስር ጉዳዮች ላይ ተከራክረዋል።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ስርርር » Fri May 21, 2010 10:00 pm

:D ይህንን ቤት እንዴት እስከዛሬ አላየሁትም? ምህቡብ ጥሩ ነው:: እንዲህ ቆየት ያሉ ቁምነገሮችን ማንበብ.... የኔም ሆቢ ነው:: መልከ-ፀዴቅም በርታ:: በርቱልን....ማለፍያ!!!

ማህቡብ ከላይ ያስነበብከን ፅሁፍ ይችኛዋን ክፍል ውድድ ነው ያደረግህዋት::
ዘንድሮም ግንቦት ነዉ።ዘንድሮም ምርጫ አለ። -እሁድ።የሚሆነዉ ግን አሁን አናዉቅም።የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የሚሉትን የሚያደርጉ ጀግኖች፣ የማያደርጉትን የማይሉ ብልሆች፣የሕዝብ ፍላጎት አክባሪ -ቅኖች፥ የሐገር ጥቅም፣ተቆርቋሪ አርቆ አሳቢዎች መሆናቸዉን አስመሰክረዉ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያዉያን የድሕረ -እሁድ ጉዞን በጎ -መጥፎነት ለመገመት ዛሬና አስከዛሬን መጠበቅ ባላስፈለገ ነበር።አለመሆኑ ነዉ -ሥጋቱ።

ያ ሕዝብ ሥለወደፊቱ ቀርቶ ሥለዛሬ ኑሮዉ፥ የሚያዉቀዉ የፖለቲከኞቹን ብያኔ ጠባቂነቱን ከዚሕ ካለፈም አለማወቁን ማወቁ ነዉ መሆኑ ነዉ ድቀቱ።የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ -መድረክ ባጭሩ ጥምረት ከፍተኛ ባለሥልጣንና ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ መሪ ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉ ከቅድመ ሁኔታ ጋር ተስፋ አላቸዉ።

ገዢዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር -ኢሕአዴግ ምርጫዉን እንደ ዲሞክራሲዉ ወግ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆን ከብዙ ጊዜ በላይ ብዙ ብሏል።የተቀዋሚ ፓርቲ መሪዎች ግን የገዢዉን ፓርቲ ቃል -አያምኑትም።ከዚሁ ጋር የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪዎች እንደ ዲሞክራሲዉ ሥርዓት አስር ጊዜ በአስር ጉዳዮች ላይ ተከራክረዋል።
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby በይሉል » Tue May 25, 2010 6:51 am

ዳጋፉፍ wrote: .........................................................................................


ሰላም ዳጋፋፍ

የስታሊን ጥቅስ በጽሁፍህ ስር ይነበባል.የዚህን ጥቅስ ምንጩን ብታካፍለኝ ደስ የለኛል. ከሰላምታ ጋር...በይሉል
*The hardest thing about any political campain is how to win without proving that you are unworthy of winning!! E.stevenson

*Even if you win the rat race,you are still a rat!!!
በይሉል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1075
Joined: Thu Sep 16, 2004 9:30 pm
Location: Beylul-60km North of Assab.

Postby መልከጻዲቅ » Sat Jun 19, 2010 6:37 pm

አበረታች አይጥፋ :D የቤቱ ባለቤትም አንዳንዴ ብቅ ይበሉ. 8)

ከጋሽ ጳውሎስ ትዝታዎች ያነበብኩትን ላካፍላችሁ::

ጠያቂ:- ባብዛኛው ሀገሮች እንደምሰማው አንድ ሰው በወንጀል ተከሶ ለምሳሌ ሁለት አመት ቢፈረድበት ሌሊቱ ጭምር ይታሰብለትና ለሁለት አመት የነበረው ፍርድ ባንድ አመት ይጣጣለታል:: በኛ ሀገርስ ይሄ ህግ ለምን ተግባራዊ አይሆንም?
የጳውሎስ መልስ:-እንደው በፈጠረህ ይሄ ህግ የት ሀገር ነው ያለው?

ጠያቂ :- ሎተሪ አዟሪ ነኝ:: በማዞርበት ጊዜ ቡዙዎቹ ይሄን ቁመት ይዘህ እንዴት ታዞራለህ እያሉ ሞራሌን እየገደሉት ነው:: እባክህን ለነዚህ ልናገር ባዮች ወይም የወሬ ቌቶች ምክርህን ስጥልኝ::
የጳውሎስ መልስ:- ሎተሪ ለማዞር አጭር ብቻ ነው እንዴ የተመረጠው? ሰዎቼ እባካችሁ ቀውላላ አትበሉኝ ይላልና ምናለ ዝም ብላችሁ ብትገዙ..? አፍ እላፊ ምን ያስፈልጋል? ወይም አንገዛም በሉ:: ቢያጥር ደሞ ድውይ ለማለት ነው??

ጥያቄ:- የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት እርስት ክፍል ስትገባ እንደ ባለጸጋ ቤት አንድ ትልቅ ውሻ አለ:: ታዲያ ባለጉዳይ የሚገባው እባካችሁን ውሻውን ያዙልን እየተባለ ነው:: ነገሩ ውሸት ይመስል እንደሆነ አንድ ቀን ብቅ በልና እየው :: ግን የወንድምነቴን ልምከርህ...ከመምጣትህ በፊት " ያዙልኝ" ብለህ መደወሉ አይከፋም::
የጳውሎስ መልስ:- ታዲያስ ማዘጋጃ ቤት..ለዚህ ምን ትላላችሁ?

ስርርር wrote::D ይህንን ቤት እንዴት እስከዛሬ አላየሁትም? ምህቡብ ጥሩ ነው:: እንዲህ ቆየት ያሉ ቁምነገሮችን ማንበብ.... የኔም ሆቢ ነው:: መልከ-ፀዴቅም በርታ:: በርቱልን....ማለፍያ!!!

ማህቡብ ከላይ ያስነበብከን ፅሁፍ ይችኛዋን ክፍል ውድድ ነው ያደረግህዋት::
ዘንድሮም ግንቦት ነዉ።ዘንድሮም ምርጫ አለ። -እሁድ።የሚሆነዉ ግን አሁን አናዉቅም።የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የሚሉትን የሚያደርጉ ጀግኖች፣ የማያደርጉትን የማይሉ ብልሆች፣የሕዝብ ፍላጎት አክባሪ -ቅኖች፥ የሐገር ጥቅም፣ተቆርቋሪ አርቆ አሳቢዎች መሆናቸዉን አስመሰክረዉ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያዉያን የድሕረ -እሁድ ጉዞን በጎ -መጥፎነት ለመገመት ዛሬና አስከዛሬን መጠበቅ ባላስፈለገ ነበር።አለመሆኑ ነዉ -ሥጋቱ።

ያ ሕዝብ ሥለወደፊቱ ቀርቶ ሥለዛሬ ኑሮዉ፥ የሚያዉቀዉ የፖለቲከኞቹን ብያኔ ጠባቂነቱን ከዚሕ ካለፈም አለማወቁን ማወቁ ነዉ መሆኑ ነዉ ድቀቱ።የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ -መድረክ ባጭሩ ጥምረት ከፍተኛ ባለሥልጣንና ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ መሪ ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉ ከቅድመ ሁኔታ ጋር ተስፋ አላቸዉ።

ገዢዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር -ኢሕአዴግ ምርጫዉን እንደ ዲሞክራሲዉ ወግ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆን ከብዙ ጊዜ በላይ ብዙ ብሏል።የተቀዋሚ ፓርቲ መሪዎች ግን የገዢዉን ፓርቲ ቃል -አያምኑትም።ከዚሁ ጋር የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪዎች እንደ ዲሞክራሲዉ ሥርዓት አስር ጊዜ በአስር ጉዳዮች ላይ ተከራክረዋል።
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ማህቡብ » Wed Jun 30, 2010 4:55 pm

ሠላም ጤና ይስጥልኝ !


"ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው"

የ«እርሻ መሬት ቅርምት» ና ሳዑዲ አረቢያ

በቅርቡ ግን የሳዑዲ አረቢያ ገበሬዎች ለንጉስ አብዱላሕ «ብሔራዊ» ያሉትን የሰብል ምርት አበረከቱ።የተመረተዉ ግን ሳዑዲ አልነበረም።ኢትዮጵያ እንጂ

ሳዑዲ አረቢያ ከአለም ሐብታም ሐገራት አንዷ ናት።በነዳጅ ዘይት ሐብት የበለፀገችዉ ሐገር በድሆቹ ሐገራት የእርሻ መሬት ለማግኘት በሚደረገዉ አለም አቀፍ ዉድድርም ከግባር ቀደሞቹ ሐገራት አንዷ ሆናለች።«የመሬት ቅርምት» በሚባለዉና አንዳዶች «አዲሱ ቅኝ አገዛዝ» እያሉ የሚተቹት ሥልትም በሳዑዲ አረቢያ እይታ ለወደፊት ኑሮ አስተማማ መሠረት መጣል ነዉ።በነዳጅ ዘይት ሐብት ከአለም የመጀመሪያዉን ሥፍራ የያዘችዉ ሐገር የሌሎች ሐገራትን መሬት በመግዛት በራሷ ግዛት ማድረግ የማትችለዉን ኢንዱስትሪ እያስፋፋች ነዉ።

የ«አረብ -ሳዑዲ የእርሻ ባንክ» እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ 1962 ሲመሠረት ለሳዑዲ ታሪካዊ ክስተት ነበር።የዉሐ እጥረት ያለበት በረሐይቱ ሐገር በዚሕ ተቋም አማካይነት አብዛኛዉን የምግብ አቅርቦት የሚሸፍን የራሷን የእርሻ መስክ ለመገንባት ነበር -አለማዉ።ከፍተኛ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግለት ሰብል ከራስ ምድር፥በራስ ጥረት የተገኘ ምርት ተብሎም አስፈንድቆም ነበር።ወዲያዉ ግን ዘላቂ እንደማይሆን ተረጋገጠ።
«የግብርናዉ መስክ አዳዲሶቹን ብሔራዊና አለም አቀፋዊ ፈተናዎች መቋቋም አለበት።በመጀመሪያ እየሰፋ የመጣዉ የአለም አቀፍ ንግድ ሥርዓት ነፃነት፥እና ሁለተኛ ደግሞ እተባባሰ ያለዉ የከርሰ ምድር ዉሐ እጥረት»

ይላሉ -የሳዑዲ አረቢያዉ የግብርና ሚንስትር ደ ኤታ አብደላሕ አል -ቁባይድ።ገበያዉ አለም ንግድ ይበልጥ መክፈቱና የከርሰ ምድር ዉሐ እጥረት ከፍተኛ ድጎማ የሚደረግለትን የሐገር ዉስጡን ምርት ዋጋ አስወድዶ፥በስምት አመቱ አስቆመዉ።

በቅርቡ ግን የሳዑዲ አረቢያ ገበሬዎች ለንጉስ አብዱላሕ «ብሔራዊ» ያሉትን የሰብል ምርት አበረከቱ።የተመረተዉ ግን ሳዑዲ አልነበረም።ኢትዮጵያ እንጂ።ስጦታዉ ዘገቢዉ ኤል ካኦዉቲት እንደሚለዉ የዉጪ ሐገር መሬት በመያዙ ሒደት የመንግሥት ተሳትፎ መኖሩን ጠቋሚ ነዉ።ሚንስትር ደ ኤታዉም የሚሉት አለ።

«በእኛ እምነት በዉጪ ሐገር ለግብርናዉ መስክ የሚዉለዉ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት የምግብ አቅርቦታችን ማረጋገጪያ ነዉ።እንደ ብዙዎቹ የአለም ሐገራት ሁሉ ሳዑዲ አረቢያ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት እንዲኖራት ትፈልጋለች።»

ሚንስትር ደኤታ አል -ቁባይድ በእርሻዉ መስክ በዉጪ ሐገራት የሚወርቱ ባለሐብቶችን የሚያማክር፥ የሚረዳና የሚያበረታታና ፍቃድ የሚሰጠዉ የሚንስትሮች ኮሚቴ አባልም ናቸዉ።ኮሚቴዉ ስምንት መቶ ሚሊዮን ዶላር ተመድቦለታል።ስዑዲ አረቢያዊዉ የምጣኔ ሐብት አዋቂ መሐመድ አልቁናይቢ ግን የመንግሥታቸዉን አቋም አይቀበሉትም።

«በዉጪ ሐገር የሚደረግ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት በዚያ (በታላሚዉን ) ሐገር የአስመጪ ሕግ የሚመራ ነዉ።እዚያ ምግብ ፍላጎት ካለ እሕሉ በተመረተበት ሐገር መቅረት አለበት።ከዚሕ በተጨማሪ (ሥራዉ ) የዚያ ሐገር ፖለቲካዊ ሁኔታ ጥገኛ ነዉ።»

እንደ ኢትዮጵያ፥ ሱዳን የመሳሰሉት በግብርናዉ መስክ መዋዕለ ንዋይ የሚፈስባቸዉ ሐገራት ተደጋጋሚ የምግብ እጥረት ያለባቸዉ ናቸዉ።በነዚሕ ሐገራት እሕል አምርቶ ወደ ሳዑዲ አረቢያ መዉሰድ ኢኮኖሚስት አል ቁናይቢ እንደሚሉት የሳዑዲ አረቢያን መልካም ስም የሚጣፋ ነዉ።እንዲሕ አይነቱ የመከራከሪያ ሐሳብ በሚንስትር ደ ኤታ አል -ቁባይድ ዘንድ ተቀባይነት የለዉም።

«ይሕ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት አለም አቀፍ ምርታማነትን የማሳደግ አለማም አለዉ።ለግብራናዉ መስክ ሥራ በሚደረገዉ የጋራ ስምምነትም በርግጥም ታላሚዎቹ (የባለመሬቶቹ ) ሐገራት ብሔራዊ ምርታቸዉን እንዲያሳድጉ እድል የሚፈጥር ነዉ።ሳዑዲ አረቢያ በነዚሕ ሐገራት ከምታመርተዉ እሕል የተወሰነዉ እዚያዉ ነዉ የሚሸጠዉ።»

የኢራቁ የምጣኔ ሐብት አዋቂ መሐመድ አል ዶኦላይሚ የዉጪ ሐገራት የእርሻ መሬትን በመኮናተር የሚደረገዉን የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት በጥቅሉ ይተቻሉ።በተናጥል ግን ከቻይና የሳዑዲ ይሻላል ባይ ናቸዉ።
«ቻይና መሬቱን ብቻ አይደለም የምትገዛዉ።ለማምረት የሚያስፈልገዉን የሰዉ ሐይልም ይዛ ነዉ የምትገባዉ።የሳዑዲ አረቢያ የተለየ ነዉ።በባለ መሬቶቹ ሐገራት የስራ እድል ይፈጥራል።ይሕ አንድ ጥሩ ጥቅም ሊሆን ይችላል።ከዚሕ በተጨማሪ የሐገራቱ ብሔራዊ የምግብ ምርት ይጨምራል።»
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Wed Jun 30, 2010 5:12 pm

"ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው"


ኩባዎች እንደ ዉብ ደሴታቸዉ-ያደንቋታል።-እንደ ቆንጆ-ጠንካራ ልጃገረድ መፍለቂያ ግዛታቸዉ ያወድሷቷል።ኹዋንታናሞ።ኹዋንታላሜራ-እያሉ።ከትልቅ ግዙፍ፥ አይበገሬ ጎረቤታቸዉ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ይወዛገቡባታል።ከ1903 (ዘመኑ በሙሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ጀምሮ የሚቆጣጠሯት ግን አሜሪካኖች ናቸዉ።የኩባ፥ የሔይቲና የሌሎች የካረቢክ አካባቢ ሐገራት ሥደተኞች ሲሰፍሩባት-አሜሪካኖችን ካሜሪካኖች፥ አሜሪካኖች ካካቢዉ ሐገራት ጋርም ብዙ አወዛግባ ነበር።ተጠርጣሪ አሸባሪዎች ከታሰሩባት ወዲሕ ደግሞ አለምን ታከራክር ይዛለች።በቅርቡ ደግሞ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማን ቃል-አባይ አደረገች።ይሕ ነዉ የዛሬ ጉዳያችን።አብራችሁን ቆዩ።


ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ-ጥር 20 2009።ቃለ መሐላ ፈፀሙ።ዋይት ሐዉስ ገቡ።በሁለተኛዉ ቀን-የመጀመሪያ ትልቅ ዉሳኔያቸዉን አስታወቁ።ጥር-ሃያ ሁለት።

«እንደ ፕሬዝዳት በዩናይትድ ስቴትስ ሕገ-መንግሥትና ሕጎች በተሰጠኝ ሐላፊነት መሠረት፥ ባሁኑ ወቅት በመከላከያ ሚንስቴር አማካይነት ዃንታናሞ ማቆያ ማዕከል በሚገኙት (በታሰሩት) ግለሰቦች ላይ ሊደርስ የሚችለዉን አግባብ ያልሆነ በደል ለማስቀረት፥ ከሐገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም፥ ከዉጪ መርሕ እና ከዩናይትድ ስቴትስ የፍትሕ-ሥርዓት ጋር በተጣጣመ መልኩ የኩዋንታናሞን ማቆያ ማዕከል እንዲዘጋ ከዚሕ በታች ያለዉን አዋጅ አፅድቄያለሁ።የመዝጋቱ ሒደቱ ካሁን ጀምሮ ኹዋንታናሞ አንድ አመት ባልበለጠ ጊዜ ዉስጥ ይዘጋል።»

የፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ እቅድ ትዕዛዝ ከተሰማ ባለፈዉ ሮብ አመት ደፈነ።ማቆያ ጣቢያዉ ግን የወትሮዉ ነዉ።በፈለጉት ጊዜ ወደ ፈለጉት መሔድ፥መብረር የሚችሉ ወፎች ይዘምሩበታል። ወታደሮች በጥብቅ ይቆጣጠሩታል።ተጠርጣሪ አሸባሪዎችም ያዉ ከሁለት ሺሕ ሁለት ጀምሮ እንደነበረዉ አንድም ይፀልዩ፥ አለያም ይመረመሩበታል።

ባለፈዉ የኢትዮጵያዉያን ክረምት ማዕከሉን እንዲጎበኙ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የፈቀደላቸዉ ጋዜጠኞች በድምፅ ከቀደት-ጥቂቱ ይንኑ ከመመስከር ባለፍ-አዲስ ነገር ብዙ አልነበረም::


የኹዋንታኖሞ-የባሕረ-ሠላጤ ወይም ወሽመጥ።በ1494 አገር አሳሽ ክርስቶፎር ኮሎምቦስ መሕለቁን በአካባቢዉ ሲጥል ፖርቶ ግራንዴ፥ አላዉ።ታላቁ ወደብ እንደማለት።የአካባቢዉ ነባር ነዋሪዎች (ታይኒዎች ነዉ የሚባሉት) የወደፊት ቅኝ ገዢዎቻቸዉ ለግዛታቸዉ የሰጡትን አዲስ ስም አልተቀበሉትም።እኒያ አሳ አስጋሪዎች በሰየሙት ፀኑ ኹዋንታናሞ እንዳሉት።

የስጳኞች አገር አሳሽ፥ ቅኝ ገዢዎች፥ ከአካባቢዉ ነዋሪዎች ጋር፥ኩባዎች ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ሲወዛገቡባት፥አሳ አጥማጆች፥ መርከበኞች፥ ነጋዴዎች፥ ወታደሮች፥ስደተኞች ሲፈራረቁባት ዘመነ-ዘመናት አስቆጥራለች። ዛሬም ያቺ የባሕር በር-አሜሪካዊ ጓንታናሞ፥ ጂታሞ ሲላት፥ ኩባዊዉ ኹዋንታናሞ እያለ በኔነት ካሜሪካዊዉ ጋር ይወዛገብባታል።

ዩናይትድ ስቴትስ በ2002 ባብዛኛዉ አፍቃኒስታንና ፓኪስታን ዉስጥ የተማረኩ ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን እዚያች ደሴት ማሰሩን የመረጠችዉ በሐገሪቱና በአለም አቀፍ ሕግ ደንቦች መሰረት የተጠርጣሪዎቹ ይዞታ ሊያስነሳ የሚችለዉን ጥያቄና ክርክር ለማስወገድ ነበር።በወቅቱ በስልጣን ላይ የነበረዉ የፕሬዝዳንት ቡሽ መስተዳድር ባለሥልጣናት እንደሚሉት ተጠርጣሪዎቹ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ሐገራት ከሌላ ሐገር ወይም ሐገራት ጋር በገጠሙት ጦርነት የተማረኩ ሳይሆኑ ከየቦታዉ የተጠረቃወሙ አሸባሪ ወሮበሎች ናቸዉ።

በዚሕም ምክንያት የጦር ምርከኞች ይዞታን የሚደነግገዉ የጄኔቫዉ ሕግም ሆነ፥የእስረኞችን የሰብአዊ መብት ይዞታን መጠበቅ የሚያስገድደዉ የራስዋ የአሜሪካ ሕግ ለኹዋንታናሞ እስረኞች ሊያገልግል አይችልም ባዮች ነበሩ።የቡሽ መስተዳድር እርምጃ፥ በተለይ ደግሞ ሚስጥር ለማዉጣት በሚል በተጠርጣሪዎቹ ላይ የተፈፀመዉ ግፍ የዲሞክራሲያዊቱን ሐገር፥ሥም ክፉኛ አግዱፏል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ እንዳስታወቁት ተጠርጣሪዎቹ ሚስጥር እንዲያወጡ በሚል በኤሌክትሪክ እየተንጨረጨሩ፥ ዉሐ ዉስጥ እየተደፈቁ፥ እንቅልፍ እየተከለከሉ፥ ርቀነ-ገላቸዉን እንዲቆሙ-እንዲቀመጡ ተገድደዋል።እድሜያቸዉ ለአካለ-መጠኝ ያልደረሱ ተጠርጣሪዎች ሳይቀሩ የዚሕ ግፍ ሰለባ መሆናቸዉ ከመብት ተሟጋቾች አልፎ፥ የአለም ፖለቲከኞ
ዕቅድ-ዉል ሳተች መነጋገሪያ ርዕሥም ነበር።

በፕሬዝዳት ቡሽ መስተዳድር ላይ የሚሰነዘረዉ ወቀሳ ትችት ባየለበት በዚያ ዘመን ቡሽን ለመተካት ይፎካከሩ የነበሩት እጩዎች በተለይም የዲሞክራትክ ፓርቲዎቹ እጩዎች ያን የሐገራቸዉ ክብር፥ ማዕረግ፥ ስም-በጎ ዝና ያጎደፈዉን እስር ቤት እንዘጋለን የማይሉበት ምክንያት አልነበራቸዉም።

ኦባም በምርጫ ዘመቻቸዉ ወቅት አደርገዋለሁ ያሉትን ለማለት ሥልጣን ከያዙ በሕዋላ ሁለት ቀን አልፈጀባቸዉም።አሉት።

«ኹዋንታናሞ አንድ አመት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ይዘጋል።»

የኦባማ ቃል-ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፥ ለፍትሕ ተቆርቋሪዎች፥ ለአንዳድ ፖለቲከኞችም በርግጥ የምስራች ነበር።እዚያ እስር ቤት ለነበሩት ተጠርጣሪዎች ደግሞ ታላቅ ጉጉት።እስረኞቹን ከሚጠብቁት የአሜሪካ ወታደሮች አንዱ ያኔ ያስተዋለዉም ይሕንኑ ነበር።

«በጣም ተደስተዉ ነበር።ታዉቃለሕ።ከዚሕ ለመሔድ በጣም ተዘጋጅተዉ ነበር።ኹዋንታናሞን ለመልቀቅ ጓጉተዉ ነበር።ከዚያ ጊዜ በሕዋላ ግን ብዙ ወራት አለፉ።እና አሁን ነገሮች ሁሉ እሳቸዉ (ኦባማ) ሥልጣን ከመያዛቸዉ በፊት እንደነበሩት ናቸዉ-የሚል አስተሳሰብ ነዉ-ያላቸዉ።»

ኦባማ ሥልጣን በያዙ-ቃል በገቡበት ወቅት 240 ተጠርጣሪ አሸባሪዎች ኹዋንታናሞ ማቆያ ጣቢያ እንደተያዙ ነበር።የኦባማ ቃል-ዉል መሳቱ ባለፈዉ ሮብ ሲመሰከር ሁለት መቶ ያሕል እስረኞች እዚያዉ ናቸዉ።

ባንድ አመት ዉስጥ ወደየሐገራቸዉ ወይም ወደ ሰወስተኛ ሐገር የተላኩት እስረኞች አርባ ብቻ ናቸዉ ማለት ነዉ።ተጠርታሪዎቹ ወደየትዉልድ ሐገራቸዉ ቢላኩ በሰብአዊ መብት ረገጭነታቸዉ የሚታወቁት፥ አምባገነን የየሐገሩ መንግሥታት የተጠርጣሪዎቹን ይበልጥ ያሰቃዩ፥ ይበድሏቸዋል የሚል ትልቅ ሥጋት ነበር።

ተጠርጣሪዎቹ ከአምባገነን ገዢዎቹ በደል ካመለጡ ምናልባት አሸባሪዎችን ይቀላቀሉ ይሆናል-የሚለዉም ጥርጣሬም የጎላ ነበር።ሥጋት ጥርጣሬዉን ለማቃለል የተገኘዉ መፍትሔ ተጠርጣሪዎቹ ራስዋ ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ወደተለያዩ ሐገራት እንዲላኩ፥ እና በመደበኛ ፍርድ ቤት መዳኘት የሚገባቸዉም በየሚሔዱበት ሐገራት ይዳኙ የሚል ነበር።

የፕሬዝዳት ቡሽ መስተዳድር ያንን ማቆያ ጣቢያዉን እንዲዘጋ ግፊት ከሚያደርጉት ሐገራት አብዛኞቹ የአዉሮጳ ሐገራት ነበሩ።ተጠርጣሪዎቹን ለመቀበል ዝግጁነታቸዉን የገለጡ የአዉሮጳ ሐገራትም ነበሩ።የኦባማ መስተዳድር ማቆያ ጣቢያዉን ለመዝጋት ሲወስን ግን ብዙዎቹ ቅሌን ጨርቄን ይሉ ገቡ።ከነዚሕ አንዷ ጀርመን ናት።

ዩናይትድ ስቴትስ ራስዋ ለአዉሮጶች ይሁን ለሌሎች ጥሩ ምሳሌ መሆን አለመቻሏ ነዉ-እንቆቅልሹ።የተወሰኑ እስረኞቹ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ይዛወሩ የሚለዉን ሐሳብ የፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ መስተዳድር ተቃዋሚ የሪፐብሊካኖች ፓርቲ አይቀበለዉም።ከራሳቸዉ ከኦባማ ፓርቲ ከዲሞክራቶቹ ባለሥልጣናት መካካል ሴናተር ጂም ዌብን የመሳሰሉት ሐሳቡን አለመቀበላቸዉ ነዉ-ግራዉ።

«ማድረግ አለብን።ኹዋንታናሞን በተገቢዉ ጊዜ መዝጋት ይገባናል።መዝጋት የሚገባን ግን ሰዎችን ወደዚሕ (ወደ ዩናይትድ ስቴትስ) በማዛወር አይደለም።»

የፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ የአመት-እቅድ ቃል ዉሉን ስቷል። ግን ፕሬዝዳንቱ ባቋማቸዉ እንደፀኑ ነዉ።መስተዳድራቸዉ ከእስረኞቹ መካካል አንድ መቶ ያሕሉን ኢሊኖይ ግዛት ወደሚገኘዉና ጥብቅ ቁጥጥር ወደሚደረግበት እስር ቤት ለማዛወር ማቀዱን ባለፈዉ ታሕሳስ አስታዉቋል።

ተጠርጣሪዎቹን ወደ ኢሊኖይ የማዛወሩ እቅድ-ሥልት አነጋግሮ ሳያበቃ የመን የከረመዉ ናይጄሪያዊዉ ወጣት የአሜሪካን የመንገደኞች አዉሮፕላን ለማጋየት ሲመክር መያዙ ነገሩን እቅድ ሥልቱን ሁሉ ቅራ ቀኝ ያላጋዉ ይዟል።እስካሁን ድረስ ኹዋንታናሞ ከሚገኙት ሁለት መቶ ያሕል ተጠርታሪዎች ዘጠናዉ የየመን ዜጎች ናቸዉ።ይሕ ነዉ-ምስቅልቅሉ።የፕሬዝዳት ኦባማ ቃል አቀባይ ሮበርት ጊብስ በቅርቡ እንዳሉት ግን ኹዋንታናሞን የመዝጋቱ እቅድ ይዘግይ እንጂ አይታጠፍም።የመኖችን ግን፣-

«ማቆያ ሥፍራዉ ከዚሕ ቀደም በገባነዉ ቃል መሠረት ይዘጋል። ተጨማሪ (እስረኞችን) ወደየመን ማስተላለፉ ግን ባሁኑ ጊዜ ጥሩ ሐሳብ አይደለም።»


ኹዋንታናሞ-ዛሬም እንደ ጥንቱ፥ ታከራክር-ታወዛግባላች ቃል-እቅድ ታሳጥፍ ወይም ታራዝማለች።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby መልከጻዲቅ » Sat Jul 17, 2010 8:38 pm

የጳውሎስ ትዝታዎች

ጥያቄ:- ሚያዚያ 7 ቀን ሁለተኛ አመቷን ለምታከብረው ለቢፍታዊት መንገሻ እንኴን አደረሰሽ በላት..አዋሳ ለሚገኘው ለህጻን ነብዩ ፍስሀ ደግሞ አንተ ረባሽ.. አንተ ረባሽ...ቤተ ሰቦችህን ከምትረብሽ ጥጦ አስገዝተህ ዝመት እኔ ግን በጣም ደህና ነኝ ብለህ ለናፈኮአቸው ህጻናት ባንተ በኩል መለክቴን አስተላልፍልኝ::

የጳውሎስ መልስ:- ወይ አያነቡ ወይ አይሰሙ በምን ቌንቌ ልንገርልህ?

ጥያቄ:- በኢትዮጵያ ውስጥ በሽታ የሚያመጡትን እንደ አይጥና ዝንብ የመሳሰሉትን ህዝቡ የስምንት ቀን ዘመቻ አድርጎ ቢያጠፋቸው መልካም አይመስልህም?

የጳውሎስ መልስ: አዝማች ከተገኘ ሀሳቡ መልካም ነው::

ጥያቄ: እንጀራ የሚጋግርልን አጥተን ተቸግረናልና ባስቸኴይ ፈልገህ ብትልክልን ጥሩ ነው የማሾም ችግር ስላለበን ቢቻል ይዘህልን እንድትመጣ...

የጳውሎስ መልስ:- ካንድ ስውር ምንጭ እንደሰማሁት በቅርብ ቀን ማሾውን ሳታገኙ አትቀሩም...የዘመታችሁት በቅርብ ጊዜ ሆነ እንጂ አሁን ሁሉም ያላችሁት ይላካል...ሴት ዘማቾች እስከዛው ይጋግሩ::
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ማህቡብ » Sat Sep 11, 2010 11:22 am

ሰላም ለቤቱ ወንድሜ መልከጻዲቅ ዛሬም እንደሁሌው ከታላቅ አክብሮትና ምስጋና ጋር እንኵን ለኢትዮጵያ አዲስ አመት 2003 በሰላም አደረሳችሁ !!

ከስኬት በርካታ ነገሮችን ማግኘት ቢቻልም ከወንድማዊ ፍቅር የሚገኘው መንፈሳዊ እሴት ግን ፍጹም ከሌላ ሊገኝ የማይችል ነው :: ምክኒያቱም የነቢያቱን ትንቢት የጠቢባኑን ምሳሌ የአዛውንቱን ተስፋ የሃያላኑን ጄግንነት የሊቃውንቱን ትምህርት የጌታን ምህረት የጠላትን ሽንፈት የነፍሳትን ጽናት የመሳፍንቱን ጉልበት በዚሁ የወንድማማችነት ፍቅር መዳፍ ውስጥ ተከማችቶ እናገኘዋለን ሠላምና ጤና የዘዎትር ሃብታችሁ ይሆን ዘንድ የዘዎትር ምኞቴ ነው :: እስካለን ለዓለም ሠላም ለሠው ልጅ ሁሉ ፍቅርን ለሁላችንም ጤናን ለሃገራችንም እድገትና ብልጽግና እመኛለሁ ::

የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ

የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ 1969 እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር የተቍቍመ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ አህጉር ከሚገኙት ታላልቅ ብሄራዊ ፓርኮች ውስጥ አንዱ ነው :: ፓርኩ ከባህር ወለል በላይ ከ1500 እስከ 4300 ሜትር ከፍታ መካከል የሚገኝ ሲሆን በጠቅላል ስፋቱ 2200 ካሬ ኪሎ ሜትር ነው :: ይህ ፓርክ ባብዛኛው ከፍተኛ የሆኑ ደጋማ ቦታዎችን የሚያጠቃልል በመሆኑ ቀዝቃዛነቱን አንዳንድ ጊዜ ከዜሮ በታች እስከ 15 % ሴንቲ ግሬድ የሚወርድ እና በመካከለኛ ቦታዎችም ሙቀቱ እስከ 26 % ሴንቲ ግረድ ይደርሳል :: እንደ አየር ንብረቱ ልዩነትም የተለያዩ የ እጽዋት አይነቶችም ማለትም ከደጋው የጥድ እና የኮሶ ዛፍ አንስቶ በመካከለኛው የአየር ንብረት የሚገኝ የዝግባና የቀረፋ ዛፎች በሚገኙበት ከመሆናቸውም በላይ ለአይን የሚማርኩ ለጌጥ እና ለውበት የሚያገለግሉ በተፈጥሮ በቀል የሆኑ የተለያዩ የእጽዋት ዝርያዎች የሚገኙበትና ከኢትዮጵያ በስተቀር በሌላው አለም የማይበቅል "ጅብራ' ተብሎ የሚጠራው የእጽዋት ዝርያም ሣኒቴ ተብሎ በሚጠራው በፓርኩ ምስራቃዊ ክልል ይገኛል በኢትዮጵያ በከፍታው ሁለተኛ የሆነው የቱሉ ጊንቱ ተራራም የሚገኘው በዚሁ ፓርክ ነው :: የፓርኩ ወሰንና ይዞታም በስተ ሰሜን ከጊሌ ተራራ ዲሾ አካባቢ ተነስቶ ወደ ደቡብ መዳረሻ ያሎ ድረስ ያለውን 70 ኪሎ ሜትር ሲይዝ በስተ ምስራቅ ከጎባ ከተማ ከፍ ብሎ ከሚገኘው ከሳኒቴ ከፍተኛ አምባ ቦታ ጄምሮ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ የኡደብ ወንዝ ሸለቆን አቍርጦ 50 ኪሎ ሜትር በመጓዝ የአዳባን ተራራማ ቦታዎች ይሸፍናል :: ይህ ፓርክ የቱሉ ይንቱን የባቱን የዋርጉንና የዋስማን ተራራማ ቦታዎች በመያዙ ከፍተኛ ማራኪነት ያለው ሲሆን የቀርቃሃና የዝግባ ደኖችን በመሸፈኑ የበለጠ ውበትን አክሎለታል ::

የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ በአፍሪካ ባቀማመጣቸውና በማራኪ ውበታቸው በስፋታቸው ከታወቁት ፓርኮች አንዱ መሆኑን የደጋ ቀበሌዎች ብሄራዊ ፓርኮች ውስጥም ትልቁ ነው :: ኢትዮጵያ ብቸኛ ባለሃብት ከሆነችባቸው የዱር አራዊትና አእዋፍ መገኛ ቦታ ነው :: የማያቋርጥ ጥቅም በመስጠትና የተፈጥሮን ችግር በማስተባበር ረገድ ከሚሰጠው ጠቀሜታ ሌላ በርካታ የየብስ እና የውሃ እንስሳቶች ይገኙበታል ከነዚህ ውስጥ አራት የአሳ ዝርያዎች ሁለቱ ከውጭ የመጡ ሲሆን ሁለቱ ዝርያዎች ደግሞ በውሃ ተፋሰስ ውስጥ የሚገኙ ናቸው በዚህ ፓርክ ውስጥ 14 የውሃ እና የየብስ እንስሳት ሲገኙ 11 በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ 3 ደግሞ ለምርምር አዲስ የሆኑ ናቸው :: እንዲሁም በኢትዮጵያ ብቻ የምትገኝ በቀቀን ፓሮት ወፍ ዝርያ አለች እስካሁን ድረስ በዚህ ፓርክ ውስጥ ከ 64 የሚበልጡ የጡት አጥቢ ዝርያዎች ሲኖሩ 13ቱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ለምሳሌ ኒያላ,ቀይ ቀበሮ,የምኒልክ ድኩላ ከ203 የሚያንሱ የአእዋፍ ዝርያዎች የተመዘገቡበት ሲሆን ሌላው በእናት ሆድ ውስጥ የሚፈለፈሉ የእባብ ዝርያዎች ከባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ ውጭ በሌላው አለም የማይገኙ ቀይ ቀበሮዎች እንዲሁም በይበልጥ ቀበሮዎቹ ለምግብነት የሚጠቀሙበት የፍልፈል ዘርም የመገኘው በዚሁ ፓርክ ውስጥ ነው :: ፓርኩ ማራኪ የሆኑ የመሬት ገጽታዎችን ከማካለሉም በላይ ቀዝቃዛ ሃይቆችንና ከ40 የማያንሱ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች የሚፈሱ በአሳ የተሞሉ ቀዝቃዛ ወንዞች አሉት :: በዚህ ፓርክ ውስጥ ከትናናሽ አራዊቶች እና ነፍሳት አንስቶ እስከ ታላልቅ አራዊቶች እንደ ነብር አንበሳ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዝሆንም የሚገኝበት እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ ጽህፈት ቤት ከአዲስ አበባ ውደ ጎባ በሚወስደው ቀጥታ መንገድ ከአዲስ አበባ 400 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም መንገድ የፓርኩን ሰሜናዊ ክፍል በማቍረጥ ወደ ጎባ ከዚያም የፓርኩን ምስራቃዊ ክፍል በማካለል ጎባን አልፎ ደሎ መድረሻ መንገድ ይደርሳል ::

ፓርኩ 400 ሜትር ከባህር ወለል በላይ በተመሰረተ በአለም በትልቅ ከፍታ ላይ የተሰራው የመኪና መንገድ በዚሁ ፓርክ ውስጥ ይገኛል :: በፓርኩ ውስጥ 33 ኪሎ ሜትር የመኪና መንገድ የተሰራ ስላለ ለጥበቃ እና ለጉብኝት ለሚመጡ ሁሉ አገልግሎት ይሰጣል ይህ ፓርክ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ በእግርና በፈረስ ከ 4 እስከ 6 ቀናት በላይ ጊዜ ይወስዳል :: ይህ ብሄራዊ ፓርክ ውስጡ ተፈጥሮ የለገሰው በመሆኑ በሃገሪቱ ብሄራዊ ኢኮኖሚ ግንባታ ካለው የተፈጥሮ አቀማመጥ የብርቅ አራዊትና የእጽዋት ክምችት የተሻለ እድል እንዲኖረው አድርጎታል::
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Thu Dec 30, 2010 10:50 am

አምደ መረብ አገልግሎት ሃያኛ አመቱ ሲዘከረ ዊኪሊክስ የተሰኘዉ አምደ መረብ ያፍረጠረጠዉ ሚስጥር የአለምን አመለካከት ቀይሮ-ዘመን በዘመን ሊቀየር አራት ቀን ቀረዉ።

መካከለኛዉ ምሥራቅ -ሰዉ የጊዜን ዑደት ማስላት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እንዳረጀበት ሠላም ፍቅር፥ ዉይይት-ድርድር እየተሰበከ፥ እየተነገረበት ሞት መከራ እንደታፈሰበት ሁለት ሺሕ አስርም ተወልዶ-አድጎ አረጀበት።ኢራቅ የጦርነት ፍፃሜ፥ ምርጫ እየታወጀ-እየተደረገባት ቦምብ-ዉዝግብ እንዳዋከባት፥ አፍቃኒስታን ፓኪስታን የአሸባሪዎች ሽንፈት እየተነገረባቸዉ እንደተሸበሩ የዘመን ዘመን ሊተካ ነዉ።አምደ መረብ አገልግሎት ሃያኛ አመቱ ሲዘከረ ዊኪሊክስ የተሰኘዉ አምደ መረብ ያፍረጠረጠዉ ሚስጥር የአለምን አመለካከት ቀይሮ-ዘመን በዘመን ሊቀየር አራት ቀን ቀረዉ። የጎርጎሮሳዉያኑ ሁለት ሺሕ አስርን አበይት መታወሻዎች ላፍታ ዘክረን-እንሸዉ።አብራችሁኝ ቆዩ።

አለም ለያኔዉ አዲስ አመት ቅበላ የተኮሰ-የለኮሰዉን የርችት-ችቦ አመድ-ክሳይ አፅድቶ ሳያበቃ የዱባይ ሰይማይ ከወገቡ የሚተፋዉ የርችት ብርሐን የፋርስ ባሕረ ሰላጤ ሕዋን ሲያጥለቀለቅ አየ።የምሕንድስና እዉቀት፣ የሥነ-ሕንፃ ጥበብ ምጥቀት ፣የገንዘብ ጉልበት ዱባይ ላይ-ጉድ አሰኘ።ጥር አራት።ቡርጅ ኸሊፋ ሕንፃ ተመረቀ።ከአለም አንደኛ ነዉ።ስምንት መቶ ሃያ-ስምንት ሜትር ይረዝማል።አንድ መቶ ስልሳ ፎቆች አሉት።አንድ.ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ፈሶበታል።አረብ-አጃኢብ፣ አለም በየቋንቋዉ ጉድ ብሎ ሳያበቃ-ተፈጥሮ ሄይቲ ላይ በፍጡሯ ጨቀነች።

«የሆነ ነገር ሕንጻዉን የመታዉ ነበር-የመሠለን።መሬት መንቀጥቀጥ መሆኑን ያወቅነዉ ሁሉም ከሆነ በሕዋላ ነዉ።»

የርዕሠ-ከተማ ፖርትኦፕረንሱ ነዋሪ።ጥር አስራ-ሁለት ከተማይቱ ሁሉም ተደፋባት።በቅፅበት ወደ አስከሬን፣ የአካል ቁርጥራጭ፣ የሕንፃ ፍርስራሽ፣ ክምርነት ተቀየረች።ደም ያቋረ ምድሯ፣ በቁስለኞች፣በቤት-የለሾች ተሞላ።ሁለት መቶ ሃያ ሺሕ ሕዝብ አለቀ።ከሞት የተረፈዉ የመከራዉን ልክ አሰላስሎ ሳያበቃ ከሌላ መከራ ገባ።ኮሌራ።ሁለት ሺሕ ሰዉ ገደለ።ጥቅምት የምርጫ ዉዝግብ ታከለበት።ጥቂት ሞቱ።

ዩናይትድ ስቴትስ፣ እስራኤልና ፍልስጤሞች በየአመት ወሩ እንደሚያደርጉት ሁሉ ሽምግልና ድርድር ሲሉ በግዙፍ ሕንፃዋ አለምን ጉድ ያሰቸዉ ዱባይ ፍልስጤማዊ እንግዳዋ በጉደኛ ጠላቶቻቸዉ ጉድ-ሆነዉ-ጉድ ሆነች።

የአክራሪዉ የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊ የሐማስ የጦር መሪ ማሕሙድ አል-ማብሑሕ ሆቴላቸዉ ዉስጥ ተገደሉ።ጥር ሃያ።ገዳዮች የእስራኤል የስለላ ድርጅት የሞሳድ አባላት መሆናቸዉን ፍልስጤሞች በይፋ የተቀረዉ አለም በሹክሹክታ ይናገሩ ገቡ።እስራኤል አላመነችም።የሟች ደም፣ የፍልስጤሞች ቁጣ፣የአረብ ኤሚሬቶች ዉርደት የገዳዮቹ ማንነት ከየባለጉዳዮቹ ባለፍ ሐያሉን አለም የሚጎረብጥ አልነበረም።
ገዳዮቹ የአዉሮጳና የሌሎች ምዕራባዊ ሐገራትን ፓስፖርት ይዘዉ መሆኑ ግን የብራስልስ፣ የለንደን፣ የፓሪስ፣ የበርሊን፣ የካምቤራ፣ የኦታዋን ፖለቲከኞች ያንጨረጭር ያዘ።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Thu Dec 30, 2010 11:01 am

«በግድያዉ የተካፈሉት ከአዉሮጳ ሕብረት ዜጎች የተሰረቀ የአዉሮጳ ሕብረትን መታወቂያና ክሬዲት ካርድ አጭበርብረዉ መጠቀማቸዉን አጥብቀን እናወግዛለን።»የአዉሮጳ ሕብረት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ካትሪን አሽተን።ብሪታንያና አዉስትሬሊያ የእስራኤል ዲፕሎማቶችን ከየሐገራቸዉ አባረዋል።

ኢራቅ የሰባት አመቱ የእልቂት ፍጅት ድግግሞሽ ቀዝቀዝ-ቀነስ ቢልባት ደም ለለመደ ቆሌዋ የቀድሞዉ ከፍተኛ ባለሥልጧናን ገበረችለት። በስልጣን ዘመናቸዉ ኩርዶችን በኬሚካል በማስገደል ወንጀል ሞት የተበየነባቸዉ አሊ ሐሰን አል-መጂድ ተሰቀሉ።

እንደ ፕሬዝዳትና እንደ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ባንድ አብረዉ የታሚል ታይገር ጠላቶቻቸዉን ድል ያደረጉት የሺሪላካ ባለሥልጣናት በእኩል ድል እኩል እንደፈነደቁ-በተቀበሉት አመት ትልቁን ስልጣን በምርጫ ለመያዝ ይሻሙ ገቡ።ተጣሉ።ጄኔራል ሳራታ ፎንሴካ እንደ ወታደር ያድርግ-አታድርግ መርሕን ሲቀምሩ ብልጣብልጡ ፖለቲከኛ ፕሬዝዳት ማሂንዳ ራጃፓካሳ ጄኔራሉን በወንጀል ሾኬ ጥለዉ በምርጫዉ ድል አድራጊነት አስጨፈሩ።

የበረዶዋ ሐገር ካናዳ የካናዳዋ ከተማ ቫንኩቨር የክረምት ኦሎምፒክን ለማስተናገድ በረዶ ቸግሯት ከሌላ ሥፍራ መለቃት፣በማቀዝቀዣ መስራት ግድ ነበረባት።እንዲያ ተጠባ-ተጨንቃ ያዘጋጀችዉ የበረዶ-ድግስ ፌስታዉን-በሐዘን ጭጋግ ጋረደባት።በጆርጂያዉ ስፖርተኛ ኖዳር ኩማሪታሺቪሊ ሲለማመድ ሞተ።ገደ ቢስ ድግስ።

በረዶ-የበረዶ ተጨዋች ሕይወትን የመቅጨቱ ሐዘን የበረዶ ስፖርተኞችን ልብ እንደሰበረዉ-ከአንታርክቲክ የበረዶ ግግር ላክሰምበርግን የሚያሕል የበረዶ ክምር ተደረሰመ።የሰሐራ በረሕይቱን አፍሪቃዊት ሐገር የኒጀርን ሙቀት ያጋማዉ ግን ፖለቲካዊ ሽኩቻ ነበር።የፕሬዝዳት ማማዱ ታንጃ መንግሥትን አሽቀንጥሮ ጣለዉ።

ታንጃ እንደ ወጣት የጦር መኮንን የተሳተፉበት መፈንቅለ መንግሥት አጉዞ አጉዞ ከኒያሚ ቤተ-መንግሥት በዶላቸዉ በአስራ-አንደኛ አመታቸዉ የጠሩት ምርጫ ዉጤት ጦራቸዉን አሳምፆ ከስልጣን አሽቀነጠሯቸዉ።የፕሮቶሪያ የሥልታዊ ጥናት ተቋም አስተንታኝ ኢሳይ ሱአሬ እንደሚሉት ታንጃ የእጃቸዉን ያገኙት።
«ታንጃ ሕገ-መንግሥቱን ለዉጠዋል።ምክር ቤቱን በትነዋል።የሕገ-መንግሥታዊዉ ፍርድ ቤት የተቃዋሚዎች ያቀረቡት ቅሬታ ተገቢ ነዉ ብሎ ሲበይን ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ፍርድ ቤቱን አገዱት።በመጨረሻ የምርጫ ኮሚሽኑ እቅዳቸዉን በመቃወሙ አገዱት።»

ትንሿ ወር ልትጠናቀቅ አንድ ቀን ቀራት።የካቲት።

ቺሌ በሃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተናወጠች።በሬክተር መመዘኛ ስምንት ነጥብ ስምንት የተለካዉ የመሬት መንቀጥቀጥና ጎርፍ ስምንት መቶ ሰዉ ገደለ።የቺሌ ሕዝብ ወገኑ ያለቀበትን ስድስተኛ ወር ሲዘክር ሰላሳ-ሰወስት የማዕደን ሠራተኞቹ በቁማቸዉ የመቀበራቸዉ መርዶ ደረሰዉ።ነሐሴ።
ጥቅምት አጋማሽ ግን የትም የማይሆነዉ ቺሌ ላይ ሆነ።ሰባት መቶ ሜትር ጥልቀት ጉርጓድ ዉስጥ ከሰባ-ቀን በላይ ከነሕወታቸዉ የተቀበሩት ማዕድን ቆፋሪዎች በሙሉ በሕወት ወጡ።ተአምር እና ፈንጠዝያ።

መጋቢት ዘጠኝ።ማዕከላዊ ናጄሪያ ጆስ በሚኖሩ ሙስሎሞችና ክርስቲያኖች መካካል በተነሳዉ ግጭት አራት መቶ ሰዉ ተገደለ።ግጭት ግድያዉ ዛሬም ቀጥሏል።

የኮሪያ ልሳነ-ምድር ላዲስ ፍጥጫ ንረት አዲስ ደም ፈሰሰለት።አንዲት የደቡብ ኮሪያ የጦር መርከብ ተመታ ሰጠመች።አርባ-ስድስት ባሕር ሐይሎች ተገደሉ።ለጥቃቱ ሰሜን ኮሪያን ተጠያቂ ያደረጉት ዩናይትድ ስቴትስና ደቡብ ኮሪያ ሲዝቱ ቆይተዉ ሐምሌ ላይ ሰፊ ወታደራዊ ልምምድ ጀመሩ።ከአንድ መቶ በሚበልጡ ተዋጊ አዉሮፕላኖች እና በሃያ ተዋጊ መርከቦች የተጠናከረዉ የጠላቶችዋ-ስምንት ሺሕ ጦር አፍንጫዋ ስር የሚያደርገዉ ልምምድ ለሰሜን ኮሪያ-አንድ የሐገሪቱ ባለሥልጣን እንዳስጠነቀቁት ነገር ፈፍለጋ ነዉ።
«ይሕ የዲሞክራቲክ ሕዝባዊት ሪፐብሊክ ኮሪያ ጠላቶች ለሚከተሉት የጠብ ጫሪነት መርሕ ተጨማሪ ማረጋገጪያ ነዉ።የኛ አቋም ደግሞ ግልፅ ነዉ።ዩናይትድ ስቴትስና ደቡብ ኮሪያ ለሚደርጉት ወታደራዊ ልምምድ ተጨባጭ አፀፋ እንሰጣለን።»

የሰሜን ኮሪያዉ መሪ ኪም ጆንግ ኢል ምናልባትም የኑክሌር ቦምብ የሚጎርስ ሚሳዬላቸዉን በደቡብ ጠላቶቻቸዉ ላይ እንዳስደገኑ ለልጃቸዉ የባለ አራት ኮኮብ ጄኔራልነት ማዕራግ ሰጡ።መስከረም ማብቂያ።ለሃያ-ስምንት አመቱ ወጣት ለኪም ጆንግ ኡን የተሰጠዉን ሹመት ሽልማት ታዛቢዎች የአልጋወራሽነት ዝግጅት ብለዉታል።

የሶል-ዋሽንግተን ወታደሮች እያሰለሱ ጫካ፥ ጋራ-ባሕሩን በቦምብ-መትረየስ እየቀጠቀጡ-የአመቱን የጉዞ ፍፃሜ ሲያሰሉ የሰሜን ኮሪያ ጦር ሌላ ጠንካራ የመድፍ ዱላዉን ደቡቧ ደሴት-ዬኦንፕዮን ላይ አሳረፈ።ሁለት ወታደሮችና ሁለት ሠላማዊ ሰዎች ገደለ።

የዋሽንግተን፥ ሶል ፒዮንግዮንግ አየር በዳግም ዉግዘት ዛቻ፥ በፉከራ የጦር ልምምድ እንደቀረና ሁለት ሺሕ አስር ተሸበለለ።መጋቢት ሃያ ዘጠኝ። ሞስኮ።ሁለት ሴት አጥፍቶ ጠፊዎች ሞስኮ ባቡር ጣቢያ ባፈነዱት ቦምብ-ሰላሳ ሰባት ሰዎች አጥፍተዉ ጠፉ።ፕሬዝዳት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ሞስኮቫይቶችን አፅናንተዉ ለብቀላ በዛምቱ በሳምንቱ፥ የዩናይትድ ስቴትስ አቻቸዉን ለማነጋገር ወደ ፕራግ-ቼክ ሪፐብሊክ ወረዱ።ሚያዚያ ስምንት ሁለቱ መሪዎች አዲሱ የስልታዊ ጦር መሳሪያዎች ቅነሳ ዉልን ፈረሙ።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests