ይህን ያውቁ ኖሯል ?

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ማህቡብ » Mon Mar 19, 2012 8:43 am

VOA የአማርኛው የሬዲዮ ፕሮግራም በፈረንጆቹ የቀመር አቆጣጠር ነሀሴ 1982 ላይ ነበር የተቋቋመው:: ፕሮግራሙን በአዘጋጅነት እና በመሪነት የጀመረው አቶ ንጉሴ መንገሻ ወይንም ሁሉም በሚያውቀው ስሙ ታምራት ጌታሁን ሲሆን ታዲያ በዚያን ጊዜ አብሮት ስራውን የጀመረው ታምሩ አምቦ ወይንም ሱራፌል ፋንታየ ነበር:: በተጠቀሰው ቀን ከጧቱ ሁለት ሳአት ላይ የሙከራ ወይንም የልምምድ ስርጭቱን ሲጄምር መስከረም 26 1982 ደግሞ መደበኛ ፕሮግራሙን ጄመረ::

ከሳምንት በኋላ አሸናፊ አበጄ እና ዩሀንስ ሐይለ እየሱስ ነብሱን ይማረው ሲከተሉ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ደግሞ ይህይስ ውሂብ እና አዳነች ፍሰሃዬ ተቀላቀሉ:: ሚካል በይሳ ምክትል አዘጋጅ ሆና ጸራ ነበር እንዲሁም ወርቃፈራሁ ከበደ ፕሬስ ውስጥ የሰራ ሲሆን የውቀት ማእበል ውስጥ ነበር የሚዘፈቀው የሆነ ነገር ስትጠይቀው ማንኛውንም ታሪክ ከነ ቀኑ ነበር የሚነግርህ:: ሁለት አመት ዘግይታ ወደ ቪኦኤ የመጣችው ትዝታ በላቸው ስትሆን የሂግፓሬድ ፕሮግራም ከይህይስ ውሂብ ጋር ታቀርብ ነበር:: ከዛ በኋላ አዲሱ አበበ ሰለሞን ክፍሌ ወዘተረፈ ብቅ ብቅ ያሉበት ጊዜ ነበር::
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue May 15, 2012 3:23 pm

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው

የአልጄሪያዉ ጠቅላይ ሚንስትር አሕመድ ኦያሒድ «የአረብ አብዮት ተብዬዉ» አሉ ባለፈዉ ሳምንት ኢራቅን ከቅኝ ተገዢዎች እጅ የጣለ፥ ሊቢያን ያጠፋ፥ ሱዳንን ለሁለት የከፈለ፥ ግብፅን ያዳከመ ወረርሺኝ ነዉ።» ቀጠሉ።ሶሪያስ? ወረፋ እየጠበቀች ነዉ-እንበል ይሆንአስራ-አራት ወራት ያስቆጠረዉ ግጭት-ዉዝግብ፣ የተቃዉሞ ሠልፍ-ዉግዘት ግመትን ከድክመቱ ከማፈራረቁ ባለፍ ለሶሪያ በርግጥ አዲስ አይደለም።የግጭት ዉዝግቡን ግመት ሥጋት ከድክመቱ፣ ምናልባትም ከመቆሙ ተስፋ የቀየጠዉ የኮፊ አናን የሰላም ሐሳብ ለወር በመለመዱ-እንግዳ አይደለም።ምርጫ ግን ምርጫን ከስም ባለፍ ለማታዉቀዉቀዉ ሐገር ከስም ባለፍ ማስተዋወቁ ቢያጠራጥርም አዲስ ነበር።ሰኞ ምርጫ ነበር።ማክሰኞ-የኮአናን አስጊ ማስጠንቀቂያ።የሰላም ተስፋ የፈነጠቀዉ የአናን ዕቅድ-ገቢር የሆነበት አንደኛ ወር ሐሙስ ሲዘከር ሽብር።ሶሪያ።ፖለቲካዊ ቀዉሳ መነሻ፥ ምክያንት እንድምታዉ መድራሽን ነዉ ላፍታ አብራችሁን ቆዩ።


ሶሪያዊዉ ፈላስፋ፣ የሥነ-ማሕበረሰብ አጥኚ፣ የታሪክ ምሑርና የአረብ ብሔረተኛ ዘኪ አል-አርሱዚ ለተማሪ ተከታዮቻቸዉ ያስጠኑት ፖለቲካዊ ፍልስፍና አረብ የባሕል፣ ሐይማኖቱን ልዩነት፣ የታሪክ፣ የጎሳ ዳራዉን ብዙነት የአሰፋፈሩን ርቀት አቻችሎ በአረብነቱ ብቻ አንድነቱን እንዲጠብቅ፣ የጋራ ጥቅሙን እንዲያስከብር እንጂ ኋላ የሆነዉ እንዲሆን አስበዉ ነበር ማለት ሲበዛ ከባድ ነዉ።

ክርስቲያኑ ሚካኤል ኢፍላቅ፣ ከሙስሊሙ ሳላሕ አል-ዲን አል-ቢተር ጋር ከሚንስቶቹ ከሐይማኖት አጥባቂዎቹ ጋር በ1947 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎሮጎሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) የአረብ ሶሻሊሲት በአዝ ፓርቲን የመሠረቱት አረብነታቸዉን መሠረት፣ የአርሱዚን ፍልስፍና መመሪያ አድርገዉ እንጂ በጎሳ-ሐይማኖት አንድ ሆነዉ አልነበረም።

አርሱዚ በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ ከሁለት ሳምንት በሕዋላ አንድ መቶ አስራ-ሰወተኛ አመት ልደታቸዉን ባከበሩ ነበር ።ፍልስፍናቸዉ በተለይ በ1943 The Genius of Arabic in its Toung በሚል ርዕሥ ባሳተሙት መፅሐቸዉ የተነተኑት የአረብ ብሔረተኝነት በእነ-ኢፍላቅ መሪነት በፖለቲካ ፓርቲነት ከተደራጀ ባለፈዉ ወር ስልሳ-አምስተኛ አመቱን ደፈነ።

የአርሱዚን ልደት፣ የእነ-ኢፍላቅ ፓርቲ የተመሠረተበት ዕለት ለሶሪያዎች በተለይም በአርሱዚ ፍልስፍና ሥም፣ በበአዝ ፓርቲ ሽፋን ለሚገዙት ለደማስቆ መሪዎች የትልቅ ድግስ-ፌስታ በሆነ ነበር።የአረብን ብሔረተኝነት በሚሰብከዉ ፍልስፍና አፍላቂ አንድ-መቶ አስራ-ሰወስተኛ ልደት ዋዜማ፣ የአረብን ብሔረተኝነት በሚያራምደዉ ፖርቲ ስልሳ አምስተኛ አመት ማግስት የደማስቆ ገዢዎች ሥጦታ የብዙዉ አረብ አይደለም የአንዲቷ ሶሪያ ክፍፍል መርዶ፥ የዉጊያ ዛቻ እና ፉከራ ነበር።


ግድያ


«ከታጠቁ፥ ሁከትና ትርምስን ከሚያቀጣትሉ አሸባሪዎች ጋር፥ ከዉጪ ሐይላት ጋር ተመሳጥረዉ በገዛ ሐገራቸዉና ሕዝባቸዉ ላይ ከሚያሴሩ ሐይላት ጋር እርቅ የለም።»

ፕሬዝዳት በሽር አል-አሰድ።ምርጫ ቨጠሩበት ዕለት ዋዜማ።


የተቃዋሚዎቻቸዉ አፀፋም፥ የሶሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰኘዉ ስብስብ ቃል አቀባይ ሎዋይ ሳፊ እንዳሉት የመጠፋፋት ዉግዘት ነበር።«በጣም አሳፋሪ ነዉ።ገሚስ ሐገሪቱ በጦርነት ተዘፍቃ፥ ጦር ሐይሉ ከተሞችን በቦምብ እየደበደበ ሰዉ እንዴት ምርጫ ይደረጋል።»

ባለፈዉ የካቲት በተሻሻለዉ ሕገ-መንግሥት መሠረት በተደረገዉ ምርጫ ከ1966 ጀምሮ ሥልጣን ላይ የሚገኘዉን የባዕዝ ፓርቲን የሚቃወሙ ጥቂት የፖለቲካ ማሕበራት ተሳትፈዋል።ሁለት መቶ ሐምሳ መቀመጫዎች ላሉት ምክር ቤት የተደረገዉ ምርጫና መርሑ አነሰም በዛ በሶሪያ የአርባ ስድስት ዘመን ታሪክ አዲስ ክስተትነቱ በርግጥ አለነጋገረም። ምርጫዉ የሕዝብ ጥያቄ፥ የዋነኛ ተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ ለማፈን ፥ የዉጪዉን ዓለም ግፊት ለማደናገር ያለመ የመሆኑን ያክል፥ የምርጫዉ ሒደት አስራ-አራት ወራት ባስቆጠረዉ ግጭት-ዉጊያ መጀቦኑ እንጂ ያዲስ-አሮጌነቱ ድቀት።

ምርጫዉ የደማስቆ ገዢዎች እንዳለሙት የገጠማቸዉን ተቃዉሞ-ገፊት ማፈን እንደማይችል፥ ወይም ባደባባይ እንዳሉት የተሐድሶ ለዉጥ መሠረት እንደማይሆን ለብዙዎች ገና ሲታቀድ ግልፅ ነበር።ተፋላሚ ሐይላት፥ የዉጪ ደጋፊዎችም የቀድሞዉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ የኮፊ አናን የሠላም ዕቅድ የደገፉትም የማፈን-ማደናገሩ ሙከራ፥ የአስራ-አራት ወራቱ ዉጊያ ለዉጤት እንደባይበቃ ሥለተረዱት ነዉ-ነበር ተስፋ እምነቱ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተፋላሚዎችን የተኩስ አቁም ዉል ገቢራዊነት ለመከታተል ታዛቢ ቡድን ማሠፈሩ በጎ ተስፋ-እምነቱን የሚያጠናቅር ነበር።

የታዛቢ ቡድን ቃል አቀባይ ኒራጅ ሲንጌሕ እንዳሉትም የቡድናቸዉ አላማ-ምግባር ተስፋ ሰጪነቱን ጠቋሚ ነበር።

«የእኛ ተልኮ እዚሕ (ያለዉ) ግጭት በሙሉ ቅርፅና በሁሉም ወገን መቆሙን በማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ነዉ።በተጨባጭ የሚደረገዉን በመከታተልና በመዘገብ ሒደት ላይ ነን።የቡድኑ አባላት ብዛት አስካሁን ድረስ ሰባ ነዉ።ከነዚሕ መካካል ሰላሳ-ዘጠኙ ወታደራዊ ታዛቢዎች ሲሆኑ የተቀሩት ሰላማዊ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ናቸዉ።»

በሶሪያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የታዛቢዎች ቡድን ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ሮበርት ሙድ ወደ ዳራዕ የተጓዙት ቃል አቀባይ ኒራጅ ሲንጌሕ የሰማነዉን ባሉ በሳልስቱ ነበር።ኖርዌያ-ዊዉ ጄኔራል አስራ-አንድ ባልደረቦቻቸዉን አስከትለዉ በሶሪያ መንግሥት ወታደሮች ታጅበዉ ደራዕ ከተማ ሲቃረቡ ጄኔራሉና ባልደረቦቻቸዉ የተሳፈሩባቸዉን መኪኖችን የሚመሩት መኪኖች በፈንጅ ጋዩ።

የታዛቢዉ ቡድን ባልደረቦች የደረሰባቸዉ ጉዳት የለም።እነሱት ያጀቡት አስር የሶሪያ ወታደሮች ግን ቆስለዋል።ገሚሶቹ ክፉኛ ተጎድተዋል።ዋና ሸምጋይ ኮፊ አናን በጄኔራል ሙድና በባልደረቦቻቸዉ ላይ የተቃጣዉን ጥቃት አልሰሙም፥ የሶሪያን የምርጫ ሒደት አልተከታተሉም ማለት አይቻልም። ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ግን የታዛቢዉን ቡድን ያገጠመዉን አደጋ ግን አልጠቀሱም።
ስደት
ሥለምርጫዉ ሒደት በጎ መጥፎነት ያሉት የለም።ባለፉት ሰላሳ ቀናት እንደተለመደዉ ዲፕሎማሲያዊ ወግ የሰላም ተስፋ የሚያጭር አልነበረም።የሥጋት ማስጠንቀቂያ እንጂ።

«ሐገሪቱ ወደ ሙሉ የርስ በርስ ጦርነት ትገባለች የሚል ሥጋት አለ።የዚሕ እንድምታ ደግሞ አስፈሪ ነዉ።ይሕ እንዲሆን ልንፈቅድ አንችልም።ወታደራዊ እንቅስቃሴዉ በሆነ ደረጃ ቀንሷል።ግጭቱን ለማስቆም የተደረገዉ ሥምምነት ግን በተደጋጋሚ እየተጣሰ ነዉ።የግጭቱ መጠንና ስምምነቱን የማወኩ ደረጃ ተቀባይነት የለዉም።»

ተቀባይነት የለዉም። ግን ቀጥሏል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለዉ በሶሪያዉ ግጭት ዉጊያ ከዘጠኝ ሺሕ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ቆስለዋል።አሜሪካ መራሹ ጦር ኢራቅን ከወረረበት ከሁለት ሺሕ ሰወስት ሚዚያ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በርካታ የኢራቅ ስደተኞችን በማስተናገድ ሶሪያን የሚወዳደር ሐገር አልነበረም።

ወረራ፥ ጦርነት ሽብር ከሐገሩ ካሰደደዉ አራት ሚሊዮን ያክል ኢራቃዊ ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ለሚበልጠዉ መጠለያ የሰጠችዉ ሶሪያ እንጂ የኢራቅን ሕዝብ ከአምባገነኖች ነፃ ለማዉጣት፥ ለማበልፀግና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማስረፅ ጦር አዘመትን ያሉት ሐያላን አልነበሩም።ሶሪያ የተጠለሉት ኢራቃዉያን ወደ ሐገራቸዉ ተመለሰዉ ሳያበቁ አስተናጋጆቻቸዉ ራሳቸዉ ይሰደዱ ገቡ።

ዛሬ በብዙ መቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሶሪያዉን የቱርክ፥ ዮርዳኖና የኢራቅን ድንበሮች እያጨናነቁ ነዉ።ባለፈዉ ሳምንት ለሶሪያ እንዳዲስ የታየዉ ምርጫ የአዲስ አረጌነቱ እንዴትነት፥ የዓለም አቀፉ ድርጅት ታዛቢዎች ተልዕኮ እስከየትነት፥ የአናን ማስጠንቀቂያ ምክንያት ምንነት ሲያነጋግር-ደማስቆ ተሸበረች።


ቦምብ።የሰዉ ልጅ ጥንታዊ ስልጣኔ መሠረቲ፥ የሐይክሶሶቿ ጥንስሰ፥ የዑመያዶች መናገሻይቱ፥ የአይቡዶች መናኸሪያ፥ የመምሉኮች መግዢያቱ፥ ዉብ ከተማ እንደገና በደም በሰዉ ደም ጨቀየች።ሐሙስ።

ፋርሶች፥ አረቦች፥ አባሲዶች፥ቱርኮች፥ፈረንሳዮች፥ አይሁዶች እገነቡ ያፈረሷት፥ እየገደሉ ነግሰዉ፥ እየተገደሉ የወደቁባት ጥንታዊት ከተማ በነዋሪዎችዋ አካል-አስከሬን ጎደፈች።በቋሚዎቿ ዋይታ ጩኸት ደፈረሰች።ዲማሽቅ።

የሰዉ ልጅ ያለማቋረጥ ለረጅም ጊዜ ከነረባቸዉ አካባቢዎች የመጀሪያዋ ትልቅ ከተማ ካለፈዉ ታሕሳስ ጀምሮ በቦምብ ስትሸበር የሐሙሱ ስድስተኛዋ ነዉ።የሐሙሱ ግን ባንዴ ሁለት ቦምብ ያደረሰዉ ጥፋትም ከቀዳሚዎቹ ሁሉ ከባድ ነበር።ወደ ሥልሳ ያሕል ሰዎች ገድሏል።ከአራት መቶ በላይ አቁስሏል።ግን ለምን-ደግሞስ ማነዉ።ብዙዎች ብዙ ጊዜ ጠይቀዉታል።ብዙዎች እንደመሰላቸዉ መልሰዉታል።

መመለስ ከነበረባቸዉ ዋንኞቹ የሶሪያ መንግሥትና ተቃዋሚዎቹ አንዱ ሌላዉን ለመወንጂያነት ከመጠቀም ባለፍ ትክክለኛዉን መልስ አልሰጡትም።የደማስቆ ገዢዎች ከዚሕ ቀደም እንደሚሉት ሁሉ የሐሙሱን የቦምብ ጥቃትም ሶሪያን ለማጥፋት በሚሹት «በፅዮናዉያንና በአሜሪካዉያን የሚደገፉ» ያላቸዉን የመንግሥት ተቃዋሚዎች ወንጅሏል።

የመንግሥት ጦር የሚወጉ ታጣቂዎችንና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን የያዘዉ የሶሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰኘዉ ስብስብ የበላይ ቡርሐን ጋሊዩን ባንፃሩ መንግሥትን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

«ይሕ የቦምብ ጥቃት በደረሰበት ወቅት የነበሩ ሒደቶችን ማጤን ያሻል።ጥቃቱ የተፈፀመዉ በአናን የሠላም እቅድ መሠረት ሥርዓቱ ከባድ የጦር መሳሪያዎቹንና ጦሩን ከየከተሞቹ እንዲያስወጣ ግፊት በሚደረግበት ወቅት ነዉ።በእኛ እምነት ይሕ ግፊትና ጥቃቱ በቅጡ የተያያዙ ናቸዉ።»

ደማስቆ ስትሸበር እዚያዉ የነበሩት የሊባኖስ ጡረተኛ ጄኔራል ሐሺም ጀባር የሶሪያ ተፋላሚ ሐይላት የሚወነጃጀሉበትን ሰበብ ምክንያት አይቀበሉትም።

«ሶሪያ ዉስጥ ያለዉ እዉነተኛ ሥጋት የተለመደዉን አይነት ዉጊያ የሚያደርጉት አማፂያን (የሶሪያ ነፃ ጦር ይባል ወይም ሌላ) ያደርሱታል የሚባለዉ አይደለም።ዋነኛዉ ፍርሐት ይሕን መሠሉ የቦምብ ወይም የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት ነዉ።የሶሪያ መንግሥት ሐገሪቱን መቆጣጠር ያቃተዉ መስሎ መታየት አይፈልግም።እነሱ ደማስቆ እንደወትሮዉ ሰላም መሆኗን ሙሉ በሙሉ እንደሚቆጣጠሯት ማሳየት ነዉ የሚሹት።ሥለዚሕ መንግሥት ከእንዲሕ አይነቱ ጥቃት ሥለማይጠቀም የመንግሥት እጅ አለበት ብዬ አላስብም።»


በሽር አል-አሰድ ከደማስቆ ሲዝቱ፥ ተቃዋሚዎቻጨዉን ሲወነጅሉ፥ ቡርሐን ጋሊዩኒ ከኢስታንቡል፥ ኮሎኔል ሪያድ አል-አሰድ ከተደበቁበት ይፎክራሉ።ኮፊ አናን ከዤኔቭ ድርድር ዉይይት ሲሉ የቀጠር፥ የሪያድ ነገስታት፥ የአንካራ መሪዎች የደማስቆ ገዢዎችን ለማስጥፋት ይዝታሉ።ዋሽግተኖች ደማስቆን ሲያወግዙ ሞስኮዎች የደማስቆ ተቃዋሚዎችን ይተቻሉ።

አንዳቸዉም ግን የሶሪያ ሕዝብን መከራ-ሰቆቃ ያባሰዉን ያሁኑንም ሆነ የእስካሁኑን የሽብር ጥቃት ያደረሰዉን ወገን ማንነት አልጠቆሙም።የዓለም አቀፉ የታዛቢ ቡድን አባል ጀርመናዊዉ ሐገን ፔንከርት ግን አል-ቃኢዳን ይጠረጥራሉ።

«በተከታታይ የደረሱት የአጥፍቶ ጠፊዎች የቦምብ ጥቃቶች ይዘት አል-አቃኢዳ በሆነ ደረጃ ቢሆን የተሳተፈባቸዉ ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ያመለክታሉ።» የፔንከርትን ሐሳብ የተጋሩ ብዙዎች ናቸዉ። የብሪታንያዉ ማሰራጪያ ጣቢያ ባለፈዉ ቅዳሜ እንደዘገበዉ ግን አደጋዉን ያደረሰዉ አል-ኑስራ የተሰኘ አዲስ ፅንፈኛ ቡድን ነዉ።


ሽብር


«ባለፈዉ መግለጫችን ሥርዓቱ በብዙ የሶሪያ አዉራጃዎች በቤተሰቦች፥ በሴቶች፥ በሕፃናትና በአዛዉንቶች ላይ የፈፀመዉ ግድያ እንደምንበቀል ቃል ገብተን ነበር።እነሆ አሁን ቃላችንን ገቢር አደረግን» ይላል-ቢቢሲ የጠቀሰዉ የቡድኑ የቪዲዮ መግለጫ።የእልቂት አዋጅ።

ጄኔራል ሐፊዝ አል-አሰድ የመሯቸዉ የጦር መኮንኖች በአዝ-ፓርቲ ሽፋን በ1966 የደማስቆ ቤተ-መንግሥት ከተቆጣጠሩ ወዲሕ በ1940ዎቹ የአረብ-አንድነት፥ ብሔረተኝነት የተሰበከባት፥ በ1950ዎቹ ገቢራዊነቱ የተሞከረባት ሐገር-አናሳዎቹን አል-አዊት ሐራጥቃ አገዛዝ ነዉ የሰፈነባት።

በ1970ዎቹ ማብቂያ አገዛዙን በመቃዉም ብቅ ያለዉን የአብዛሐዉ የሱኒ እምነት ተከታይን አመፅ አገዛዙ ባፍታ ነበር የደፈለቀዉ።የኩርዶችን ጥያቄም እንዲሁ።ያም ሆኖ-አመፅ ተቃዉሞዉም ሆነ አፀፋዉ ያሁኑን ያክል ሕዝብ የሚፈጅ፥ የሚያሸብር ምናልባትም የጥንታዊቱን ሐገር አንድነት ከጥያቄ የጨመረ ነበር ማለት ያጠራጥራል።

የአልጄሪያዉ ጠቅላይ ሚንስትር አሕመድ ኦያሒድ «የአረብ አብዮት» ተብዬዉ አሉ ባለፈዉ ሳምንት ኢራቅን ከቅኝ ተገዢዎች እጅ የጣለ፥ ሊቢያን ያጠፋ፥ ሱዳንን ለሁለት የከፈለ፥ ግብፅን ያዳከመ አደገኛ ወረርሺኝ ነዉ።» እያሉ ቀጠሉ።ሶሪያስ? ወረፋ እየጠበቀች ነዉ-እንበል ይሆን።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Sep 11, 2012 7:59 am

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው

ነሐሴ አስራ-አራት ሩቅ አሳቢዉ ቅርብ አደሩ።ጠቅላይ ሚንስት መለስ ዜናዊ አረፉ።በአስራ-ሰወስተኛዉ ቀን ተቀበሩ።ነሐሴ-ሃያ ሰባት።መለስ ኮንትራት ካሉት የአምስት አመት ዘመነ-ሥልጣን ቀሪዉን የሚፈፅሙት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ናቸዉ።

በሁለት ሺሕ አራት በስተመጨረሻዉ ዛሬ-ከአዲስ አበባና ከናይሮቢ የሰማነዉ የእስረኞች መለቀቅ፥ የይቅርታ፥ድርድር ዜና የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሒደት የመቀየሩ ተስፋ መሆን አለመሆኑ ነገ-አንድ በሚለዉ አዲስ ዓመት ሒደት የሚታይ ነዉ።ዜናዉ ግን ከእስራት፥ ዉንጀላ፥ ከግጭት፥ ቁርቁስ፥ ከታታላቅ ኢትዮጵያዉያን ሞት ሌላ ምንም ወይም በጣም ጥቂት በጎ ነገር ለተሰማበት ለነገዉ አሮጌ ዓመት በርግጥ የምሥራች ብጤ ነዉ።የሁለት ሺሕ አራት የኢትዮጵያ አበይት ክንዉኖች ደግሞ የዛሬ ርዕሳችን።ላፍታ አብራችሁን ቆዩ።


የቀድሞዉ የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጥቅምት።ጠቅላይ ሚንስትሩ የጋዜጠኝነትና የአሸባሪነትን ልዩነት፥ የነጭና የጥቁር ደም ቀለምን አንድነት፥ ለተነተኑበት ማብራሪያ ምክንያትና ከሆነዉ አንዱ ሁለት የሲዊድን ጋዜጠኞች ያለ ሕጋዊ ፍቃድ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ መያዛቸዉ ነበር።

ዛሬ ካዲስ አበባ እንደተሰማዉ እኒያ ሁለት ጋዜጠኞች ይቅርታ ተደርጎላቸዋል።ከሁለቱ ጋዜጠኞች ጋርም አንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ የሚሆኑ እስረኞች በይቅር ይለቀቃሉ::


የዛሬዉ አሮጌ ዓመት ሁለት ሺሕ አራት ሊብት ሁለት ወር ሲቀረዉ ሰኔ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግን)፥ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦብነግ)፥ የግንቦት ሰባት ለለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲን ከአል-ቃኢዳና አሸባብ ጋር ደብሎ በአሸባሪነት ፈረጃቸዉ።

ሐምሌ ግም ሲል ኋላ የተዘጋዉ የአዉራምባ ጋዜጣ አዘጋጅ ዉብሸት ታዬና አሁን በመዘጋትና አለመዘጋት መሐል የተንጠለጠለዉ የፍትሕ ጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ በሁለት ቀን ልዩነት ታስረዉ በአሸሪነት ተከሰሱ።ሁለቱ ጋዜጠኞች ኋላ የበርካታ ዓመታት እስራትና የገንዘብ መቀጮ ተበይኖባቸዋል።ወንጀሉ ያዉ አሸባሪነት ነዉ።

ወዲያዉ ሲዊድናዊ ፎቶ ግራፍ አንሺ ጆን ፔርሰንና ዘጋቢ ማርቲን ሺብዬ ከኦብነግ ታጣቂዎች ጋር ሆነዉ ከሶማሊያ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠዉ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸዉ ተሰማ።ታሕሳስ ላይ ከአሸባሪዎች ጋር በማበር ወንጀል እያንዳዳቸዉ አስራ-አንድ አመት እስራት ተበየነባቸዉ።

የሁለቱ የዉጪ ጋዜጠኞች መታሰር የኢትዮጵያዉያኑን ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የመታሰር፥ መወንጀል፥ መሰደድን ዜና በጀቦነበት በሁለት ሺሕ አራት ዋዜማ የተቃዋሚዎቹ የኦሮሞ ፌደራሊስትና የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ አባላት አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ኦልባና ሌሌሳ ታሰሩ።ከዕለታት በሕዋላ አርቲስት ደበበ እሸቱም ወሕኒ ተወረወረ።ወንጀላቸዉ፥ መንግሥት እንደሚለዉ የአሸባሪ ድርጅት አባላት ወይም ተባባሪዎች ናቸዉ።

ያም ሆኖ ያዉ ያመት ግብር፥ ወግ፥ ባሕል ነዉና ሐበሻ ከአዲስ አበባ እስከ ሳንሆዜ አዲስ ዓመት አለ።ሁለት ሺሕ አራት።ከበጎ ተስፋ፥ ከጥሩ ምኞት፥ ከመልካም ፀሎት ጋር እዮሐ አበባዬ።

ኢዮአበባዬዉ፥ ተዘፍኖ፥ ምኞት ተስፋዉ ተነግሮ፥ ፀሎት ምልጃዉ ሳያበቃ የተቃዋሚዉ የለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ አንዱአለም አራጌና ታዋቂዉ የፖለቲከ ሐያሲና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በርካታ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ታሰሩ።

ሁለት ሺሕ አራት ገና አራተኛ ቀኑ ነበር።ዓለም አቀፉ የሠብአዊና የመብት ተሟጋች ድርጅቶች በኢትዮጵያ መንግሥት እርምጃ ላይ ዉግዘት፥ተቃዉሟቸዉን ያዥጎደጉዱት ያዙ።ተቃዋሚ ፖለቲከኞችም እንዲሁ።ደበበን ከመፍታት በስተቀር የሰማቸዉ ግን አልነበረም።

እንዲያዉም ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጥቅምት ላይ ለምክር ቤታቸዉ በሰጡት ማብራሪያ የመንግሥታቸዉን እርምጃ ተገቢነት አረጋገጡ።

ትናንት በርግጥ ዛሬ አይደለም።ዛሬ ከናይሮቢ የድርድር ጅምር ተዘግቧል።የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ከወነጀለዉ ሁለቱን ጋዜጠኞች አስርጎ አስገብቷል፥ ጋዜጠኞቹ በተያዙበት ወቅት አምስት ታጣቂዎቹ ተገድለዉበታል፥ ካለዉ ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር ኦብነግ ጋር ናይሮቢ ዉስጥ ሥለ ድርድር ለመደራደር አንድ ሁለት ማለቱ ተረጋግጧል።የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ።የኦብነግ የዉጪ ግንኙነት የኢትዮጵያ ጉዳይ ሐላፊ አቶ ሐሰን አብዱላሒ የሰጡት ምክንያት ለየት ይላል።ግን ድርድሩ እዉነት ነዉ።

ነገ-ሌላ ቀን ነዉ።ጊዜዉ ይሮጣል።ሁለት ሺሕ አራት በሲዊድን ጋዜጠኞች ብይን፥ በእነ አንዱዓለም አራጌ የፍርድ ቤት ዉጣዉረድ ታሕሳስን አሰናብቶ ጥርን ሲቀበል፥ አዲስ አበባ አስራ-ስምተኛዉን የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ለማስተናገድ ሽር ጉድ ማለት ጀምራ ነበር።ከወደ ሰሜን ግን መርዶ ተሰማ።ጥር ዘጠኝ።

አርታ ዓሌ የተሰኘዉን የአፋር መስተዳድር ይገበኙ ከነበሩ አዉሮጳዉያን መካከል አምስቱ በታጣቂዎች ተገደሉ።ሌሎች ታገቱ።የታገቱት ከብዙ ዉጣ ዉረድ፥ ከወራት በሕዋላ ተለቀቁ።የአጋች-ታጋቾቹ ድራማ ግን የኢትዮጵያና የኤርትራን የቆየ የቂም ቁርሾ ቁስል ሳያመረቅዝ አልተዘጋም ነበር።

ኢትዮጵያ ሐገር ጎብኚዎቹን ያገቱትንና ሌሎችንም የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሐይላት ታስታጥቃለች፥ ፥ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤን ለማሸበር አሲራ ነበር ያለቻትን ኤርትራን ለመቅጣት ጦር አዝምታ የኤርትራን ወታደራዊ ተቋማት ደበደበች።


አቶ ሽመልስ ከማል የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ።መጋቢት ነበር።ጥር በተደረገዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ አንድ ያለዉ ትልቅ ጉባኤ በሁለት ሺሕ አራት አዲስ አበባን በጉባኤ አንበሻብሿታል።አስራ-ሰወስተኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ፥ የዓለም የምጣኔ ሐብት ጉባኤ፥ የኢጋድ ጉባኤ፥ የሱዳኖች ጉዳይ ጉባኤ፥ የሶማሊያ ጉዳይ ጉባኤ እና ሰኔ እንደገና የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ።

የሰኔዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ለኢትዮጵያ የመጥፎ ምልኪ አማጭ መስሏል።ሐምሌ ሁለት ሺሕ ሰወስት የተጀመረዉ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሐይማኖታዊ ጥያቄ እስከ መጋቢት የዉይይት ድርድር መልክና ባሕሪ አልተለየዉም ነበር።የሙስሊሞቹ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቡበከር አሕመድ።መጋቢት።

ድርድሩ በጠብ ተቀይሮ መጀሪያ አሳሳ አርሲ ዉስጥ ሕይወት አጠፋ።አዲስ አበባ ሰኔ ላይ ለሁለተኛዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ስትሰዘጋጅ ደግሞ የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪዎች የአወሊያ መስጊድን ወርረዉ በርካታ ሙስሊሞችን ደበደቡ፥ አሰሩ፥ አጋዙም።መንግሥት የሰጠዉ ምክንያት ያዉ አሸባሪ የሚል ነዉ።ከራሱ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ይደራደሩ የነበሩት የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትም ተለቃቅመዉ ታሰሩ።

የሰኔዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ሰኞ ሊጀመር አርብ ማታ የኢትዮጵያ ወታደሮች መስጊድ ለመዉረር ከመዝመታቸዉ በፊት አርብ ቀን ላይ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት አንዱዓለም አራጌና እስክንድር ነጋን ጨምሮ በአሸባሪነት በተወነጀሉት ሃያ አራት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ላይ ከሰባት አመት እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ ቅጣት በየነ።

ታደሰ እንግዳዉ።ይሕ ዘገባ በአዲስ አበባ ለዶቼ ቬለዉ ዘገቢ ለታደሰ እንግዳዉ የመጨረሻዉም ሆነ። ቀልጣፋዉ፥ ፈጣኑ፥ በሳሉ ጋዜጠኛ እሁድ በመኪና አደጋ ሞተ።ሰላሳ-ዘጠኝ አመቱ ነበር::


የሞት ነገር ከተነሳ፥ ታዋቂዉ ደራሲ፥ ጋዜጠኛና ሐያሲ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር የሞተዉ ዘንድሮ ነዉ። የካቲት።ሥነ-ፅሑፍ አድናቂ፥ አክባሪዉ በሥብሐት ሞት ሲያዝን ሲተክዝ የኢትዮጵያ መንግሥት ሥኳር ለማምረት በሚል ለሸንኮራ ተክል የከለለዉ ሰፋፊ ግዛት ከአፋር አርብቶ አደሮች፥ እስከ ዋልድባ ገዳም መነኮሳት መጉዳቱ የቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ ተባብሶ ቀጥሎ ነበር።

የዋልድባ ገዳም የወደፊት እጣ ፈንታ ሲያከራክር ከሃያ ዓመት በላይ የተከፋፈሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የሐይማኖት አባቶች ከመወጋገዝ ወደ ድርድር ያዘነበሉት ዘንድሮ ነበር።ሲያትል ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በስማ በለዉ የተጀመረዉ ድርድር የካቲት አጋማሽ ወደ ፊትለፊት ዉይይት ከፍ ብሎ ነበር።


ንግስት ሠልፉ።የድርድሩ መቀጠል አለመቀጠል ሲያነጋግር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳዉሎስ ፓትሪያርክ ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በትንሽ ቀናት ሕመም አረፉ።ሰባ ስድስት አመታቸዉ ነበር።ቀብራቸዉ።ነሐሴም ተጋመሰ።የሞት ነገር ካነሳን እዉቁ የሥ’ነ-ሥዕል ጠቢብ የዓለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ የሞቱትም ዘንድሮ ነዉ። ሚያዚያ።ሰማንያ ዓመታቸዉ ነበር።

እሳቸዉ ደግሞ አመቱ መባቻ ላይ እንዳሉት በርግጥ ሩቅ አስበዉ፥ አልመዉም ነበር።

ነሐሴ አስራ-አራት ሩቅ አሳቢዉ ቅርብ አደሩ።ጠቅላይ ሚንስት መለስ ዜናዊ አረፉ።በአስራ-ሰወስተኛዉ ቀን ተቀበሩ።ነሐሴ-ሃያ ሰባት።መለስ ኮንትራት ካሉት የአምስት አመት ዘመነ-ሥልጣን ቀሪዉን የሚፈፅሙት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ናቸዉ።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ዋኖስ » Sat Sep 15, 2012 3:36 pm

እሕ! ቀሪዉ ታሪክ! ማን እሄን አወቀ?
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ማህቡብ » Tue Oct 30, 2012 8:37 am

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው::

ማን፥ ምንም አለ ምን፥አሜሪካ አለምን ትመራለች እንጂ አለምን የምትመራዉን ሐገር መሪ የሚመርጠዉ አሜሪካዊ ያዉም መምረጥ የሚችለዉ ሁለት መቶ አርባ ሚሊዮኑ ሕዝብ ብቻ ነዉ።

አሜሪካኖች ትናንትና ዛሬ ምናልባትም ነገ ከተፈጥሮ ቁጣ ጋር ይታገላሉ።በመጪዉ ሳምንት የነገን ዕለት ደግሞ የአራት ዓመት መሪያቸዉን ይመርጣሉ።ድምፅ የሚሰጠዉ 240 ሚሊዮን ሕዝብ ነዉ።ሥልጣኑን የሚይዘዉ አንድ ሰዉ።ያ አንድ ሰዉ በአራት ዓመታት ዉስጥ የሚያደርግ፥ የሚያቅድ የሚወስነዉ የድፍን ዓለምን አብዛኛ ፖለቲካዊ፥ምጣኔ ሐብታዊ እዉነት፥ሒደትንም መዘወሩ ሐቅ ነዉ።የዚያችን የዓለም መሪ ሐገር፥የመሪነት ሥልጣን ለመያዝ ሁለት ጠንካሮች እየተፎካከሩ ነዉ።ኦባማና ሮምኒ።ተመራጩ ዓለምን የመዘወሩ ሐቅ ምክንያታችን፥ የምርጫ ዘመቻቸዉ ሒደት መነሻ፥ የሁለቱ ጠንካሮች ማንነትና የዉጪ መርሕ መድረሻችን ነዉ::
ባለፈዉ መስከረም ማብቂያ ቬኑዙዌላ ዉስጥ በተደረገዉ ምርጫ ለአራተኛ ዘመነ-ሥልጣን ያሸነፉት የሐገሪቱ ፕሬዝዳት ሁጎ ራፋኤል ሻቬዝ በምርጫ ዘመቻቸዉ መሐል «አሜሪካዊ ብሆን ኖሮ የምመርጠዉ ኦባማን ነበር» አሉ።ከአራት ዓመት በፊት የያኔዉን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዳብሊዉ ቡሽን በሰይጣን መስለዉ፥ ቡሽ የቆሙበትን ሥፍራ ድኝ፥ ድኝ ይሸታል ያሉት ሻቬዝ ለዋሽግተን መሪዎች «የአፍንጫ ስር መዥገር» አይነት ናቸዉ።አክራሪ ኮሚንስት።

ፕሬዝዳት ኦባማም ለኮሚንስቶቹ ከብዙዎቹ የአሜሪካ መሪዎች ብዙ የተለየ አቋም አላቸዉ ማለት ያሳስታል።ያም ሆኖ የደቡብ አሜሪካ ኮሚንስቶች አባት የሚባሉት አንጋፋዉ የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ ወይም ሥልጣናቸዉን የወረሱት ታናሽ ወንድማቸዉ ራዑል ካስትሮ ቢጠየቁ ኦባማን እንደሚደግፉ መገመት አያሳስትም።

የዩናይትድ ስቴትስ የዉጪ በጣሙን የንግድ ግንኙነት ከቻይና ይልቅ ደቡብ አሜሪካ ላይ ማተኮር አለበት ያሉት ግን ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አይደሉም።የሪፐብሊካኑ እጩ ተቀናቃኛቸዉ አገረ-ገዢ ሚት ሮምኒ እንጂ።

«ንግዳችንን እናሳድጋለን።ንግዱ በየዓመቱ በአስራ-ሁለት ከመቶ ያድጋል።በየአምስት አመቱ ደግሞ በእጥፍ ያድጋል።ከዚሕ የተሻለ ማድረግ እንችላለን።በተለይ ከደቡብ አሜሪካ ጋር።ደቡብ አሜሪካ ለኛ ያለዉን ምቹ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ አልተጠቀምንበትም።እንደ እዉነቱ ከሆነ የደቡብ አሜሪካ ምጣኔ ሐብት ከቻይና ምንም አይተናነስም።ቻይና ላይ ብቻ ነዉ ያተኮር ነዉ።»

እርግጥ ነዉ ሮምኒ፥ የፕሬዝዳት ባራክ ኦባማን የንግድ መርሕ ከቻይና ጋር «አለቅጥ የተጣበቀ ነዉ» እያሉ በተደጋጋሚ መተቸታቸዉን አጣትለዉታል።በተለይ ቱጃሩ ፖለቲከኛ እንደ ነጋዴ ኩባንዮቻቸዉን ቻይና እና ከቻይና ጋር እያሰሩ፥ እንደ እጩ ፕሬዝዳት አሜሪካ ከቻይና ጋር ያላትን ግንኙነትን መቀነስ አለባት ማለታቸዉ ለፕሬዝዳት ኦባማ የመልስ ምት ጥሩ ዱላ ብጤ ነዉ-የሆነዉ።

«አገረ ገዢ ሮምኒ በቻይና አንፃር ጠንካራ መሆን አለብን ሲሉ፥ ቻይና ዉስጥ በግንባር ቀደምትነት በሚሰሩ ኩባንዮች ላይ መወረታቸዉን እንዳትዘነጉት።በአሁኑ ጊዜ እንኳን ለቻይና የቃኚ መሳሪያዎችን በሚያመርቱ ኩባንዮች ላይ ገንዘባቸዉን እያፈሰሱ ነዉ።አገረ-ገዢ ሆይ! በቻይና ላይ ጠንካራ መሆን አለብን ለማለት የመጨረሻዉ ሰዉ በሆኑ ነበር።»

የቻይና የምጣኔ ሐብት፥ የቴክኖሎጂ፥ የዲፕሎማሲና የወታደራዊ ጡንጫ ፈጣን እድገት ያቺን የቢሊዮኖች ሐገር ወደፊት የት እንደሚያደርሳት ከመላምት ባለፍ አሁን በትክክል መተንበይ አይቻልም።በቀዝቃዛዉ ጦርነት ወቅት አሜሪካ፥ እና ሶቬት ሕብረትን ቀርቶ ጃፓንና ምዕራብ አዉሮጶችን በሩቅ ርቀት ታማትር የነበረችዉ ቻይና አሁን በብዙዉ መስክ ብዙዎቹን ቀድማለች።ዩናይትድ ስቴትስን ግን አሁንም ገና እየተከተለች ነዉ።

ሮምኒ ከቻይና ጋር እየነገዱ፥ ቻይና ላይ ጠንከር፥ ጨከን ማለት አለብን የማለታቸዉ ሚስጥር ምናልባት የቤጂንጎችን ሁለንታናዊ ሩጪ መግታት ይገባናል ማለት ሊሆን ይችላል።

«ቻይና ሸሪካችን ልትሆን ትችላለች።ይሕ ማለት ግን እኛ ላይ እንዳሻቸዉ ይፈንጩ፥ ሥራችንን ያለ አግባብ ይስረቁን ማለት አይደለም።»

በዚሕም ይሁን በሌላ ምክንያት የቻይናዉ ፕሬዝዳት ሁ ጂንታኦ እንደ ሁጎ ሻቬዝ ቢጠየቁ እንደ ዲፕሎማሲዉ ወግ ካለበሉ በስተቀር ከሻቬዝ የተለየ መልስ የሚጠብቅ የለም።ለነገሩ ሁ እራሳቸዉ ሥልጣን ለማስረከብ የአስር ዓመት ፕሬዝዳንታዊ ጠረጴዛቸዉን እየወለወሉ ነዉ።

የአሜሪካኖቹ ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች የዩናይትድ ስቴትስ ቀንደኛ ጠላት ሥለሚባሉት ሥለ ኢራን እና ሥለ ሶሪያ መንግሥታት የሚከተሉት መርሕ ተመሳሳይ ነዉ።ኢራን፥-ፕሬዝዳት ኦባማ ከሰወስት ዓመት በላይ ያሉትን ደገሙት።«እኔ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት እስከ ሆንኩ ድረስ ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሊኖራት አይችልም።»

ሮምኒ ደግሞ ሥልጣን ከያዙ ኦባማ በዘመነ-ሥልጣናቸዉ ያደረጉትን ወደፊት እንደሚያደርጉት ቀጠሉ።«ሥለ ኢራን ያለን ተልዕኮ ምን እንደሆነ መገንዘብ በጣም ጠቃሚ ነዉ፥ ይሕ ደግሞ ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይኖራት በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ መከልከል ነዉ።»

እንደ ቻይና፥ እንደ አሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ሁሉ ዘንድሮ ዘመነ-ሥልጣናቸዉ የሚያበቃዉ የኢራኑ ፕሬዝዳት ማሕሙድ አሕመዲኒጃድ ወይም ጠንካራዉ ክርናቸዉ በአሜሪካና በተባባሪዎችዋ መንግሥታት በሚደገፉት አማፂያን ዉጊያ የዛለዉ የሶሪያዉ ፕሬዝዳንት በሽር ሐፊዝ አል-አሰድ እንደ ሻቬዝ ቢጠየቁ የሚመልሱትን መገመት ከባድ ነዉ።

የኦባማም ሆነ፥ የሮምኒ አቋም ግን ለሁለቱ የአሜሪካ ቀንደኛ ጠላቶች «ያዉ በገሌ» የሚያሰኝ አይነት ነዉ።«ያደረግነዉ ምንድነዉ፥-አሳድ መወገድ አለባቸዉ በማለት ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብን አስተባበርን። በዚያ መንግሥት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል አስተባብረናል።እንዲነጠሉ አድርገናል።ሰብአዊ ርዳታ ሰጥተናል።ተቃዋሚዎቹ እንዲደራጁ እየረዳን ነዉ።በተለይ ፍላጎታችን ሶሪያ ዉስጥ ያሉ ለዘብተኞች መደራጀታቸዉን ማረጋገጥ ነዉ።»
ከየባለቤቶቻቸዉ ጋርሮምኒ፥-«ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንዲኖር አንፈልግም።ከወታደራዊ ግጭት መዘፈቅ አንፈልግም።የጦር መሳሪያዎቻቸዉ ከማይሆኑ ወገኖች እጅ እንዳይገባ ማረጋገጥ አለብን።እነዚሕ መሳሪያዎች ኋላ እኛን ለመጉዳት ሊዉሉ ይችላሉ።----»

እያሉ ፕሬዝዳት ኦባማን ለመተካት የሚፎካከሩት የሪፐብሊካኖቹ እጩ ኦባማ እስካሁን ያሉ፥ ያደረጉትን እንደሚደግሙት አረጋገጡ።የፍልስጤሞቹን የዘመን-ዘመናት የነፃነት ትግል፥ምኞት ገቢር ለማድረግ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ሥልጣን በያዙ ሰሞን ብዙ ብለዉ፥ ጥቂት ሞክረዉ ነበር።ያደረጉት ግን ምንም የለም።

ፕሬዝዳት ማሕሙድ አባስ ከሁለቱ እጩዎች የሚደግፉትን ቢጠየቁ-ምርጫቸዉን በትክክል ማወቅ ይከብድ ይሆናል።በልማዱ፥ እስራኤል እንደ ሐገር ከተመሰረተች ጀምሮ የተፈራረቁት የአሜሪካ መሪዎች ከተጨባጩ እዉነት፥ ከገጠጠዉ ሐቅ፥ ምናልባት ከራሳቸዉም ዉስጣዊ ፖለቲካዊ እምነት ይልቅ ብዙ የሚያስጨንቃናቸዉ ሥልጣን የሚይዙበት፥ ወይም የያዙትን ሥልጣን እንደያዙ የሚቀጥሉበት ሥልት ነዉ።

ብዙዎቹ መሪዎች እስራኤል ያደረገችዉን ሁሉ ብታደረግ ከእስራኤል ጎን መቆማቸዉን የሚገልጡት፥ የፍልስጤሞችን ይሁን የሌሎች ሕዝቦችን የመብት ጥያቄ የሚደፈልቁት፥ ወይም ሸንግለዉ የሚያልፉት ከጠንካራዉ እና ከሐብታሙ የአሜሪካ አይሁድ ማሕበረሰብ የሚደርባቸዉን ቅጣት ጠንቅቀዉ ሥለሚያዉቁት ነዉ።

አነሰም በዛ በእስራኤልን ላይ ጠንከር ያለ አቋም የሚይዙት ወይም ማብቂያ የሌለዉ የፍልስጤሞችና የእስራኤል ድርድር እንዲቀጥል እስራኤሎችን ለመገሰፅ አቅም የሚያገኙት በሁለተኛ ዘመነ-ሥልጣናቸዉ ወቅት ነዉ።ምክንያት፥- ለሰወስተኛ ዘመነ-ሥልጣን ስለማይወዳደሩ ያን በድምፁ፥ በሐብቱ፥በሚቆጣጠረዉ መገናኛ ዘዴ፥ ወይም በደጋፊዎቹ አማካይነት የሚቀጣቸዉን ማሕበረሰብ አይፈሩትምና።

በዚሕ ምክንያት ወይም ከማያቁት «መላዕክ----»አይነት ሆኖ፥ አባስ ምናልባት ከሮምኒ ይልቅ ኦባማን ይደግፉ ይሆናል።ሁለቱን እጩዎች ብዙ ያሳሰበ፥ ብዙ ያናገረዉ ግን አሜሪካ ለእስራኤል የምትሰጠዉ ድጋፍ እንጂ የፍልስጤሞች የዘመነ-ዘመናት የነፃነት ጥያቄ፥ የሰብአዊነት ክብር ከቁብ የሚገባ አይደለም።

«እስራኤል እዉነተኛ ጓደኛችን ናት።በአካባቢዉ ታላቅዋ ተባባሪያችን ናት።እስራኤል ከተጠቃች አሜሪካ ከእስራኤል ጎን ትሰለፋለች።ይሕን በፕሬዝዳትነት ዘመነ-ሥልጣኔ በሙሉ ግልፅ አድርጌያለሁ።»

ሮምኒም ሌላ አላሉም።«የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳት ስሆን ከእስራኤል ጋር እንቆማለን።እስራኤል ከተጠቃች ደግሞ ድጋፋችንን ያገኛሉ።ዲፕሎማሲያዊ፥ ባሕላዊ ድጋፍ ብቻ አይደለም።ወታደራዊም ጭምር እንጂ።»

እስራኤል ዘመን የማይሽራት የአሜሪካ ልዩ ወዳጅ ናት።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እንደ ሻቬዝ ቢጠየቁ ማንን ይሉ ይሆን? የኦባማንና የኔታንያሁን የእስካሁን ግንኙነት የሚያዉቅ፥-መልሱን ለማወቅ ሁለቴ ማሰብ አያሻዉም።ማን፥ ምንም አለ ምን፥አሜሪካ አለምን ትመራለች እንጂ አለምን የምትመራዉን ሐገር መሪ የሚመርጠዉ አሜሪካዊ ያዉም መምረጥ የሚችለዉ ሁለት መቶ አርባ ሚሊዮኑ ሕዝብ ብቻ ነዉ።

የሕዝቡን ፖለቲካዊ ትርታ የሚከታተሉት የአሜሪካ መገናኛ ዘዴዎች የእስካሁን ዘገባ ግን አገረ-ገዢ ሮምኒን ሳያናድድ አልቀረም።«አርዕስተ ዜናዎች፥- ኦባማ በኮርን ፍሌክስ ተከበዋል፥ ሮምኒ የሚበሉት ከሐብታሞች ጋር ነዉ»

እዉነቱ ግን ከዚሕ ብዙም የራቀ አይደለም።ሁለቱ የአንድ ሐገር ዜግነት፥ የፖለቲካ ዝንባሌ፥ አቀራረባቸዉ እንጂ የተቃራኒ ቤተ-ተሰብ፥ የተራራቀ መደብ፥ የሩቅ ለሩቅ ዘመን ዉጤቶች ናቸዉ።ትንሹ፥ ክልሱ ባራክ ሁሴይን ኦባማ በ1962 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎሮጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ነዉ) ለአንድ ዓመት ልደቱ አንድ ሻሚ ሊበራለት ቀናት ሲሰላለት፥ የአስራ-ስድስት አመቱ ጎረምሳ ፖለቲካን አንድ-ሁለት ማለት ጀመረ።የአዉቶሞቢል ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ አባቱ ለሚችጋን አስተዳዳሪነት ሲወዳደሩ ዘመቻዉን ያስተባብር ነበር።ዊላርድ ሚት ሮምኒ።

ፍጥጫ
በዚያ ዘመቻ አባቱ አሸነፉ።ሐርቫርድ ዩኒቨርስቲ ለመግባት ሐብቱም፥ችሎታዉም አላነሰዉም።ፖለቲካን ለጊዜዉ ገሸሽ አድርጎ ሞርሞን የተሰኘዉ ሐይማኖታዊ ሐራጥቃ አስተምሕሮትን እንዳጠበቀ በ1975 በሕግ የዶክትሬት፥ በንግድ አስተዳደር ደግሞ ማስተርስ ዲግሪ ይዞ በሁለት ዲግሪ ተመረቀ።

ከኬንያዊዉ ጥቁር አባት የተወለደዉ፥ ያለ አባት ያደገዉ ወጣት የቱጃሩ ልጅ ከገባበት ዩኒቨርስቲ ለመግባት፥ ሐብት ንብረቱ የእናቱ ፅናት፥ የአያቶቹ ድጋፍ፥ የራሱ ጥረት፥ ብቻ ነበር።ግን ገባ።ልክ እንደ ሮምኒ ግን ከሮምኒ በተሻለ ዉጤት በሕግ በዶክተርነት ተመረቀ።1991።

ከእንግዲሕ ሁለቱም አንቱ ናቸዉ።ሮምኒ ከዩኒቨርስቲ እንደ ወጡ ንግዱን ተቀላቅለዉ በሚሊዮን እና ሚሊዮን ዶላር ሲያሰሉ።ወጣቱ ኦባማ የዩኒቨርስቲ አስተማሪ ሆኑ።

ሮምኒ ዳግም ወደ ፖለቲካዉ የዞሩት በ1994 ነበር።ለምክር ቤት እንደራሴነት ተወዳድረዉ ተሸነፉ።በስድስተኛዉ አመት ኦባማ ልክ እንደ ሮምኒ ለምክር ቤት እንደራሴነት ተወዳድረዉ ልክ እንደ ሮምኒ ተሸነፉ።ሮምኒ ሽንፈታቸዉን ለስምንት ዓመት ያሕል አስታመዉ ለማሳቹሴትስ አገረ-ገዢነት ተወዳድሩ።አሸነፉ።ሁለት ሺሕ ሁለት።በሁለተኛዉ አመት ኦባማ ለሴናተርነት ተወዳድረዉ አሸነፉ።ሁለት ሺሕ አራት።በአራተኛዉ ዓመት በተደረገዉ ምርጫ የዲሞክራቲኩ ፓርቲ ወክለዉ አርባ-አራተኛዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳት ሆኑ።
መራጩ


«ለእረጅም ጊዜ ያንቀላፋሁት በመጀሪያዉ ክርክር ወቅት ነበር።»

አሉ በቀደም።ብዙ ባልተመቸ እድገት፥ ሥራ፥ ትምሕርት ኑሯቸዉ መሐል ብዙ ቢያንቀላፉ ኖሮ-ብዙ ላንቀላፉበት ዕለትና ሥፍራ ባልደረሱ ነበር።ኦባማ ከአራት አመት በፊት ያሉትን ያክል በርግጥ አልሰሩም።የወደፊቲም ከኦባማ ወይስ ከሮምኒ ላሁኑ አለየም።የአሜሪካ ሕዝብ ሳምንት ማክሰኞ እስኪወስን ዓለም መጠበቅ አለበት::
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Nov 27, 2012 3:02 pm

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው
አታካቹ፥ አሳዛኙ የእልቂት ፍጅት ዑደት አንድ ምዕራፍ ዘለለ። ከተለመደዉ፥ አሰልቺ ዲፕሎማሲ ልመና ተማፅኖ በሕዋላ የተለመደዉ ጦርነት፥ በተለመደዉ ተኩስ አቁም-መተካቱ ታወጀ። ሮብ።አሰልቺ፥ አስጊዉ ዉዝግብ ግን ቀጥሏል።ምናልባት እስከሚቀጥለዉ ጦርነት-እና እልቂት

ጋዛዎች የቀበሩ ወገኖቻቸዉን በትክክል ቆጥረዉ ሳያበቁ፣ ሐዘን-እራሮታቸዉን እንዳመቁ፣ በፍርስራሽ፣ ትቢያ ክምር እንደታመቁ በተስፋ ፈነደቁ።ቴል አቪቮች የቁስለኞቻቸዉን ጉዳት እንዴትነት በዝርዝር ሳያዉቁ፣ በማስጠንቀቂያ ደወል የደነገጡበትን ጊዜ እንደቆጠሩ፣ በመደፈራቸዉ እልሕ እንደተንተከተኩ በእፎይታ ፈገጉ።ሮብ።የጋዛ-የእየሩሳሌሞ መሪዎች የለኮሱት፣የዓለም ፖለቲከኛ ዲፕሎማቶችን ያራወጡበት ጦርነት ቆመ።ዘላቂ ሰላም ግን የለም።ፍልስጤም-አይሁድ ቂም-በቀሉን አይረሳም።ደሞ በተቃራኒዉ ተስፋ አይቆርጥም።እና ተኩስ ቆመ ሲባሉ ፍልስጤሞች ቦረቁ፣ አይሁዶችም ፈገጉ።የቅርቡ ጦርነት ምክንያት ዉጤቱ መነሻ፥ የእልቂት ፍጅቱ አሳዛኝ፥ አሰልቺ ዑደት መድረሻችን ነዉ ላፍታ አብራችሑኝ ቆዩ።

ባለፈዉ ሳምንት ማክሰኞ፥-ቴል አቪቭ የማስጠንቀቂያዉ ደወል-አጓራ።«ሙዚቃ እያዳመጥኩ ነበር።ድንገት ሰዎች ሲሩጡ አየሁ።ወዲያዉ የፖሊስ መኪና ከፊት ለፊቴ ቆመ።እና ፖሊሶቹ እንድንከለል ነገሩን።አጠገቤ ስድስት ሰዎች ነበሩ።በጣም ፈርተዋል።ከአስር ደቂቃ በሕዋላ ግን ጉዞዬን ቀጠልኩ።ሁሉም ጉዞዉን ቀጠለ።»

የቴል አቪቩ ነዋሪ፥-ዳን ዮኤል።የአብዛኞቹ የጋዛ ነዋሪዎች የዕለት-ከዕለት ሙዚቃ እገዳ-ከበባ የወለደዉ የፍዳ-መከራ ሐዘን እንጉርጎሮ ከሆነ ዓመታት ተቆጠሩ።ጋዛ የተዋጊ ጄቶች ስግግምግምታ፥ የቦምብ ሚሳዬል ፍንዳታ ሲሞዘቅባት» ደግሞ ሐዘን እንጉርጉሮዉ በጣር-ጩኸት፥ በስቃይ-ሰቆቃ ዋይታ-ተለወጠ።

ጋዛ-ሕፃኑም ተገደለ

የጋዛ ሕዝብ ይሕ የተገደሉ ወገኖቹን የሚቀብረዉ ሕዝብ በስቃይ ሰቆቃ እና ድብደባ ለመኖር ተገድዷል።ሁሉም እምነትና ምግባራቸዉ ሊከበርላቸዉ በተገባ ነበር።»

የጋዛዉ ነዋሪ።በማግስቱ ሮብ፥-ተኩስ ቆመ ተባለ።ጋዛ፥-ደስታ፥ተኩስ አቁሙ ግን ለሁሴይን አብድ እንደ ብዙ የጋዛ ነዋሪዎች ሁሉ ተስፋን-ከስጋት የቀየጠ ነዉ።«ዘላቂ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እንፈልጋለን።ከሁሉም ወገን ዋስትና እንፈልጋለን።ካጭር ጊዜ መረጋጋት በኋላ በወር ዉስጥ ችግሩ ዳግም እንዲባባስ አንፈልግም።»

አሽኬሎን፥ ቴላቪቮች ላፍታ እፎይይ አሉ።ግን እሳቸዉ እንደሚሉት እፎታዉ በጥርጣሬ የታጀለ፥ ዛቻም ያመቀ ነዉ
እንደሚመስለኝ ይሕ ስምምነት ዋጋ የለዉም።ከልብ ካልተከበረ ከወራት በሕዋላ እንደገና ሮኬት ይተኮስብናል።እና ዳግም እንሰቃያለን።እነሱን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የእግረኛ ጦር ጥቃት አስፈላጊ ነዉ
እስራኤልና ሐማስ፥ እስራኤልና ፍልስጤሞች፥ እስራኤልና ሒዝቦላሕ፥ እስራኤልና ሊባኖስ፥ እስራኤልና ሶሪያ፥ እስራኤልና ግብፅ እና እስራኤልና ድፍን አረብ ሲዋጉ ተኩስ ሲያቆሙ፥ ሲደራደሩ ሲጋጩ ያሁኑ የመጀመሪያቸዉ እንዳልሆነ ሁሉ የመጨረሻቸዉም ይሆናል ብሎ የሚጠብቅ የለም
ከዘንድሮዉ በፊት እንደ ድሮዉ ሁሉ በሁለት ሺሕ ስምንት ማብቂያ (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ጋዛ ነድዳ-ወድማ፥ የደቡባዊ እስራኤል ከተሞች በሮኬት ተጎጫጭፈዉ ነበር።ሰበቡ ያዉ እንደ ድሮ-ዘንድሮዉ ሁሉ እንደተመልካቹ ተቃራኒ ነዉ።

ጋዛ ነብስ አዳኞችም ተመቱ ግን እንዲሕ ተጀመረ።የፍልስጤሙ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሐማስና እስራኤል በግብፅ ሸምጋይነት ሰኔ-አስራ ዘጠኝ ሁለት ሺሕ ስምንት ተኩስ ለማቆም ተስማሙ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደዘገበዉ ከሰኔ ሐያ-እስከ ሃያ ስድስት በነበረዉ ጊዜ የእስራኤል ጦር ስድስቴ፥ ከሐማስ ጋር ግንኙነት የሌላቸዉ» የተባሉ የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች ደግሞ ሰወስት ጊዜ ለንቋሳዉን የተኩስ አቁም ስምምነት ጥሰዋል።

ሐይ» ያላቸዉ አልነበረም።ከነበረም አልሰሙትም።ሕዳር አራት 2008 እስራኤል የሐማስ መተላለፊያ ምሽግ ያለችዉን ለማጥፋት የሐማስ ይዞታቸዉን ደበደበች።ወዲያዉ የእስራኤል እግረኛ ጦር፥ ታንኮችና ቡልደዞሮች ጋዛን ይመነቃቅሩት ያዙ።ታሕሳስ አስራ-ሰባት የእስራኤል ጦር አንድ የአርባ ዓመት ፍልስጤማዊ ገደለ።በማግስቱ ሐማስ ተኩስ አቁሙ መፍረሱን አወጀ።በዘጠነኛዉ ቀን ጦርነት ተባለ።ታሕሳስ ሃያ-ሰባት።ያኔ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ኤሁድ ኦልሜርት ነበሩ።

ዘንድሮ፥ቤንያሚን ኔታንያሁ ናቸዉ።ኔታንያሁ በቀደም እንዳሉት ሐገራቸዉ የጋዛን ሕዝብ የምትጎዳ፥ የምታጠቃበት ምክንያት የላትም።ሐማስን እንጂ
እኛ ከጋዛ ሕዝብ ምንም ነገር የለንም።የሚያሳስበን ሐማስ ነዉ።እስራኤልን በሮኬት የሚደበድበዉ አሸባሪ ቡድን ነዉ-የሚያሳስበን።የዘመቻችን ምክንያትም ይሕ ብቻ ነዉ።»

ታሕሳስ-ሁለት ሺሕ ስምን በተጀመረዉ ጦርነት ግን ከአንድ ሺሕ አንድ መቶ ስልሳ-ስድስት እስከ አንድ ሺሕ አራት መቶ አስራ-ሰባት የሚደርስ የጋዛ ነዋሪ ተገድሏል።ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ንብረት ወድሟል።ከአምስት መቶ በላይ መኖሪያ ቤቶች ተደምስሰዋል።ወትሮም እስራኤል በጣለችዉ እገዳ ፍዳዉን የሚያዉ ፍልስጤማዊ ከሰማንያ ከመቶ የሚበልጠዉ ተመፅዋች ሆኗል።

እስራኤል አስር ወታደሮችና ሰወስት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዉባታል።የደቡባዊ እስራኤል ከተሞች በጦርነቱ የመጀመሪያ ሳምንት ብቻ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ያሕል ገቢ አጥተዋል።ተምሕር ቤቶች ተዘግተዉ፥ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ተሰርዘዉ ከርመዋል።በሰወስተኛ ሳምንቱ ግን ጦርነቱ ቆመ ተባለ።እስራኤል «አሸባሪ» ካለችዉ ሐማስ ጋር ተኩስ ለማቆም ተስማማች።ጥር ሃያ-አንድ ሁለት ሺሕ ዘጠኝ።አይሁድ ፍልስጤም ተስፋ አይቆርጠም።የሰላም ተስፋ።

ተስፋዉ ግን ከዘንድሮ አልዘለቀም። ፍልስጤም-አይሁድ ቂም በቀሉን አይረሳም።ጋዛዎች የወደመ ቤት፥ መስሪያ ቤት፥ ሕንፃ፥ መጠለያቸዉን ጠግነዉ ሳያበቁ-ሌላ ጦርነት።የተጀመረበት ሰበብ-ምክንያት እንደሁሌዉ እንደየባለ ጉዳዩ ተቃራኒ ነዉ።

ብቻ ሕዳር አስራ-አራት፥-እስራኤል የሐማስን የጦር መሪ አሕመድ ጃቢሪንና ሌሎች ሰወስት ሰዎችን ገደለች።የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች ሮኬቶች ከጋዛ ወደ ደቡባዊ እስራኤል ይወነጨፉ ያዙ።ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዛቱ
ማንኛዉም ሐገር ከተሞቹና ሰላማዊ ሰዎቹ በሮኬት ሲጠቁ አይታገስም።እስራኤልም እንዲሕ አይነቱን ጥቃት አትታገስም።»
የጋዛዎች የእልቂት ስቃይ-ሰቆቃ እቶን ዳግም ተበረገደ። የአሽኬሎን፥ የቴል አቪቮች የሥጋት-መሸማቀቂያ በር እንደገና ተከፈተ።ከፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እስከ መሐመድ ሙርሲይ፥ ከዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሒላሪ ክሊንተን፥ እስከ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቬለ፥ ከልዩ መልዕክተኛ ቶኒ ብሌር እስከ ዋና ፀሐፊ ፓን ጊሙን ያሉ የዓለም መሪ-ዲፕሎማቶች ቀዳሚዎቻቸዉ በየጊዜዉ እንዳደረጉት፥ እነሱ በቅጡ እንለመዱት እንደገና ይባትሉ ገቡ።

ቴል አቪቭ መንገደኞች ተጎዱ
አሰልቺ ልመና ተማፅኗቸዉን እንደገና ደገሙት።ፓን ጊ ሙን።የነገ-ሳምንት ማክሰኞ
መልዕክቴ ግልፅ ነዉ።ሁሉም ወገኖች ተኩስ ማቆም አለባቸዉ።ሁኔታዉን ማባባስ መላዉን አካባቢ ከአደጋ ይዶሏል
የዓለም ትልቁ ዲፕሎማት «አደጋ» ያሉትን በርግጥ አላብራሩትም።ሠላም ማለታቸዉ ከሆነ ግን ጥያቄ ይጭራል።እስራኤልና ፍልስጤሞች በርግጥ ሰላም ናቸዉ።ሶሪያ ሠላም ነች።ኢራቅ፥ ሊባኖስ፥ ኢራን፥ ሊቢያ---ሌሎቹስ? የሚል ጥያቄ
ግን ሌሎች መሪ-ዲፕሎማቶችም ሌላ አላሉም።በአካባቢዉ ቀድመዉ ከደረሱት ዲፕሎማቶች አንዱ፥-የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቬለም ደገሙት
እስራኤል የራስዋን ዜጎችዋንና ሐገሯን የመከላከል ሙሉ መብት አላት።(አሁን) በጣም አስፈላጊዉ ነገር ግጭቱ እንዳይባባስ ማድረግ ነዉ
ጋዛዎች ሙቶቻቸዉን እየቀበሩ-ሲቆጥሩ፥ አንድ መቶ አምስት ሰላማዊ ሰዎች፥ ሐምሳ-አምስት ታጣቂዎች አሉ።የቆሰለ-ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ።ከእስራኤሎች አራት ተገደሉ፥ ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ ቆሰሉ።የተጠፋዉ ሐብት ንብረት መጠን እስካሁን በዉል አልተሰላም።

የጦርነቱ ዓላማ ግን የእስራኤሉ መከላከያ ሚንስትር ኤሁድ ባራክ እንዳሉት ሙሉ በሙሉ ግቡን መትቷል

ዓላማችን ሙሉ በሙሉ ግቡን መትቷል።ሐማስና እስላማዊ ጂሐድ ቆጥቋጭ ዱላ ቀምሰዋል። የሐማስ የጦር መሪ ጃብሪ እና ሌሎች በርካታ አሸባሪዎች፥ አዛዦችና ተባባሪዎች ተገድለዋል።ባጠቃላይ ከአንድ መቶ ሠላሳ በላይ ተገድለዋል።ከዘጠኝ መቶ በላይ ቆስለዋል።»

ስማቸዉን የሸሸጉት የሐማስ አባልም ጦርነቱ በድል ተጠናቀቀ አሉ
ቴል አቪቭ፤አዉቶቡስም «ይሕ ጥሩ ነገር ነዉ።ፍልስጤሞች ድል አስመዝግበዋል።መጀመሪያ አይዶችን በደንብ ደብድበዋል።አሁን ደግሞ ተኩስ እንዲቆም አድርገዋል።»

እና አታካቹ፥ አሳዛኙ የእልቂት ፍጅት ዑደት አንድ ምዕራፍ ዘለለ። ከተለመደዉ፥ አሰልቺ ዲፕሎማሲ ልመና ተማፅኖ በሕዋላ የተለመደዉ ጦርነት፥ በተለመደዉ ተኩስ አቁም-መተካቱ ታወጀ። ሮብ።አሰልቺ፥ አስጊዉ ዉዝግብ ግን ቀጥሏል።ምናልባት እስከሚቀጥለዉ ጦርነት-እና እልቂት።ለዛሬዉ ይብቃን።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Dec 11, 2012 7:44 am

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው::

የወጣቶቹን ቀና ጥሪ፥ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ገንቢ ትችት፥ የባለሙያዎችን ጠቃሚ ምክር፥ የሕዝብን ሰላማዊ ጥያቄ ለማድመጥ፥ ሰልፈኛዉ እንዳለዉ ያሉ አልመሰሉም።ወይም አልፈለጉም።ጠሪ፥ ተቺ፥ መካሪ፥ ጠያቂዎችን ለማጣጣል ግን በርግጥ አሉ።ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ።

ብዙም፥-አንድም ናቸዉ።

ወጣቶቹ

የሕግ ባለሙያዎቹ


«ገዢዉ ፓርቲ ሕገ-መንግሥቱን አያከብርም»


ከሕገ-መንግሥቱ የአንዱን አንቀፅ ቁጥር ያነገበዉ ሕዝብ ደግሞ ጠየቀ።እሳቸዉ የወጣቶችን ቀና ጥሪ፣ የባለሙያዎችን ጠቃሚ ምክር፣ የፖለቲከኞን ገንቢ ትችት የሕዝብን ሰላማዊ ጥያቄ ለማድመጥ ሰልፈኛዉ እንዳለዉ ያሉ አይመስልም።ወይም አልፈለጉም።ግን አለሁ-አሉ።ተናገሩም።

«ከሕገ-መንግሥቱ በሕዋላ---- ሕዝባችን በሥርዓቱ በጣም ረክቷል።»


ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማርያም ደሰላኝ።

ዛሬ የዓለም የሰብአዊ መብት ቀን ነዉ።ባለፈዉ ቅዳሜ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት የፀደቀበት አስራ-ስምተኛ አመም።አጋጣሚዉ መነሻ፥የተቃርኖዉ ምክንያት ማጣቃሻ ፖለቲካዉ እንድምታዉ መድረሻችን ነዉ ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።እሳቸዉ እና እነሱ ምናልባትም የአያት-ይሕ ቢቀር የአባትና ልጅ የእድሜ ክፍተት የሚያለያያቸዉ የሩቅ ለሩቅ ዘመን ዉልዶች ናቸዉ።እሳቸዉ በእግረ-ሰፊ ሱሪ፣ በታኮ ትልቅ ጫማ በሚዘነጥበት፣ ዘመን ወጣትነትን የተሰናበቱ፣ ዶክተርነትን የጨበጡ፣ የኮሚኒስት-ካፒታሊስ ፖለቲካዉ ፍልስፍና በናኘበት ዘመን ፖለቲካን የተቀየጡ ናቸዉ።ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ።

«ኢሕአዴግ ለሕዝብ ፍላጎት ደንታ የማይሰጥ ድርጅት ነው፡፡በሕገ-መንግሥቱ የተረጋገጡትንና በአንቀጽ 29፣ 30: 31፣ እና 38 የተዘረዘሩትን መብቶች አፍኖል፡፡ገዢው ፓርቲ ሕገ-መንግሥቱን አያከብርም።፡» እያሉ ፃፉ በቀደም።


ከእነሱ አብዛኞቹ ሃያዎቹን ያልጨረሱ ተማሪ ወይም ስራን ከጥቂት አመታት በላይ የማያዉቁ ወጣቶች ናቸዉ።የፌስ-ቡክ፣ የቲዉተር ዘመን ዉልዶች።አንጋፋዉ ፖለቲከኛ እንደሚያዉቁት በወረቀት ሲፅፉ፥ ወጣቶቹ እንደዘመኑ ፊሊጥ በአምደ-መረብ ዘመቱ።«ሕገ-መንግሥቱ ይከበር።» እያሉ

ሰወስተኞቹ በእድሜም በሙያም፣ ከሁለቱም አይገጥሙም።ወይም የሚገጥሙ አይመስሉም። በአዛዉንቱ ምሁር ፖለቲከኛ እና በወጣቶቹ መካካል ያለዉን የዘመን ክፍተት ለማገኛኘት ግን የጎልማሳነት እድሚያቸዉ፥ እዉቀት ሙያቸዉ ጥሩ ድልድይ ያስመስላቸዋል።

በፖለቲካዉ ርዕዮት እንደ ወጣቶቹ ገለልተኛ ሆነዉ ከሽማግሌዉ ይርቃሉ።ሁለቱም የሕግ አዋቂዎች ናቸዉ።አንደኛዉ ዶክተር መሐሪ ታከለ።


ሁለተኛዉ አቶ ተማም አባቡልጋ።በአሸባሪነት የተከሰሱት የሙስሊም መሪዎችና ተባባሪዎቻቸዉ ጠበቃ ናቸዉ።

እና እድሜ፥ እዉቀት፥ የፖለቲካ ዝንባሌ የሚያራርቃቸዉ ሰወስቱም ወገኖች የኢትዮጵ ሕገ-መንግሥት ከመከበሩ ይልቅ በመጣሱ አንድ እዉነት አንድ-ሆኑ።

ካለፈዉ ዓመት ጥር ጀምሮ መንግሥት በሐይማኖታዊ ጉዳያችን ጣልቃ ገብቷል በማለት ሲፈቀድላቸዉ ከራሱ ከመንግሥት ጋር የተደራደሩት፥ ሲከለከሉ፥ በየመሳጂዱ የጮኹት ሙስሊሞች ጥያቄም ደጋግመዉ እንዳስታወቁት አንድ ነዉ።ሕገ-መንግሥቱ ይከበር።

ሙስሊሙን ወክለዉ ከመንግሥት ጋር ሲደራደሩ ከነበሩትና ከተወካቻቸዉ ጋር ከታደሙት ሃያ-ዘጠኙ ባለፈዉ ሐምሌ ታስረዉ፥ በአሸባሪነት ተወንጅለዋል።

የሙስሊሞቹ ተወካዮች ከታሰሩ፥ በአሸባሪነት ከተከሰሱ፥ ከአዲስ አበባ-እስከ ሐርቡ፥ ከደሴ እስከ አርሲ በየመስጂዱ የተሰበሰቡ ሙስሊሞች በፀጥታ አስከባሪዎች ባደባባይ እየተደበደቡ፥ ከታሰሩ፥ ከተጋዙ፥ መንግሥት ምርጫ ያለዉ ምርጫ ከተደረገም በሕዋላ ጥያቄ-ተቃዉሞዉ አላባራም።1997 የተማሪዎች ተቃዉሞ ሕገ-መንግሥቱ የፀደቀበት አስራ-ስምተኛ ዓመት ከመታሰቡ ካንድ ቀን በፊት አንዋር መስጊድ የታደመዉ ሙስሊም፥ የሐማኖት ነፃነትን የሚጠይቀዉን የሕገ-መንግሥቱን አንቀፅ-ሃያ ሰባትን አንግቦ በሰወስት የፈረጅናቸዉን ወገኖችን አስተያየት ተጋራ።ሕግ አክባሪ-አስከባሪ መንግሥት የለም ወይ እያለም ጠየቀ።ዘመረም።

እሳቸዉ የወጣቶቹን ቀና ጥሪ፥ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ገንቢ ትችት፥ የባለሙያዎችን ጠቃሚ ምክር፥ የሕዝብን ሰላማዊ ጥያቄ ለማድመጥ፥ ሰልፈኛዉ እንዳለዉ ያሉ አልመሰሉም።ወይም አልፈለጉም።ለሳቸዉ ለመንግሥታቸዉ፥ ለሐገር ሕዝባቸዉ የሚጠቀም ነዉን ለማድማጥ የሌሉት ወይም ያልፈለጉት፥ ጠሪ፥ ተቺ፥ መካሪ፥ ጠያቂዎችን ለማጣጣል ግን በርግጥ አሉ።ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ።

«እንደሚመስለኝ ይሕ የአናሳዎች ድምፅ ነዉ።የአብዛኞቹ ሙስሊሞች ድምፅ አይመስልም።የአብዛኞቹ ጥያቄ የአስተዳደር ሥርዓት እንዲኖራቸዉ ነበር።የራሳቸዉ የአስተዳደር ሥርዓት ሥርዓት።መንግሥት ከሐይማኖታዊ አስተዳደራቸዉ ጋር ምንም ግንኙነት የለዉም።»

ዶክተር መሐሪ እንደሚሉት ሕግ-ወይም ሕገ መንግሥት ሲወጣ በሥልጣን ላይ ያለ ሥርዓትን ግለሰብን፥ ወይም ቡድንን ብቻ አስቦ፥ ወይም መሠረት አድርጎ መሆን የለበትም።


ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የሚመሩት የሕገ-መንግሥት አፅዳቂ ምክር ቤት ሕዳር ሃያ-ዘጠኝ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሰባት የኢትዮጵያ ፌደራላዊት፣ ዴምክራሲያዊት ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥትን ሲያፀድቅ የያኔዎቹን ፖለቲከኞች፥ የሕግ አዋዊቂዎችና ተንታኖችን እኩል አስደስቶ ነበር ማለት በርግጥ ስሕተት ነዉ።

ጠ/ሚ ሐይለማርያም

ይሁንና ዶክተር መሐሪ እንደሚሉት ሕገ-መንግሥቱ እስከዚያ ዘመን ድረስ የነበሩ የኢትዮጵያዊያንን መሠረታዊ የፍትሕ ጥያቄዎች ለመመለስ ሕገ-መንግሥቱ ጥሩ ሰነድ ነዉ።

ጥሩዉ ሰነድ ለያኔዎቹ ሕፃናትና ወጣቶች፥ ለወደፊቱ ትዉልድም የተሻለ ፍትሕ፥ ነፃነት፥ እኩልነት የሰፈናባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ይበጃል፥ ያስችላል የሚል እምነት ነበር።ባለፉት አስራ-ስምት አመታት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የገዢዉን ፓርቲ መስመር ተከትለዉ ከሚንስርነት እስከ ፕሬዝዳትነት ደርሰዉ፥ ከገዢዉ ፓርቲ ተነጥለዉ እንደ ግል ፖለቲከኛ ከምር ቤት እንደራሴነት ወደ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪነት ተለዉጠዋል።

በዚሁ ዘመን በሕገ-መንግሥቱ የተደነገገዉን መብት በመጠቀም ለመደራጀትና ለማደራጀት የሞከሩ በርካታ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፥ የሙያና የሠረተኛ ማሕበራት ተወካዮች፥ ለፍርድ ቤት ነፃነት የተሟገቱ ዳኞች ሳይቀሩ አንድም ታስረዋል፥ አለያም ተሰደዋል ወይም ከስራ ተወግደዋል።በምርጫ የተወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፥ ለተቃዉሞ ያንገራገሩ ወጣቶች፥ መንግሥትን ለመተቸት የሞከሩ ጋዜጠኞች «ሕገ-መንግሥቱን ለመናድ» በሚል ወንጀል ታስረዋል።ተቀጥተዋል።ተሰደዋል።ተቋማት ተዘግተዋል።ማሕበራት ተበትነዋል።

እዚሕ ቦን ይማር የነበረ ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪቃዊ ባልጀራዉ የኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከጎርጎሮሳዉያኑ በሰባት ወይም በስምንት አመት እንደሚያንስ ይነግረዋል።«እኸ» አለ አሉ ደቡብ አፍሪቃዊዉ «ኢትዮጵያዉያን፥ እየሱስ ክርስቶስ መወለዱን የሰሙት ከስምት ዓመት በኋላ ነዉ-ማለት ነዉ?» ብሎ ኢትዮጵያዊ ባልንጀራዉን ጠየቀዉ።ወይም አሾፈበት።

ዩናይትድ ስቴትስ አል-ቃኢዳን በአሸባሪነት የፈረጀችዉ በ1991 ነበር።በ1994 ኒዮርክና ዋሽግተን አል-ቃኢዳ እንዳዘመታቸዉ በሚታመን ወጣቶች ከተመቱ በሕዋላ ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ አብዛኛዉ ዓለም ያን ድርጅት በአሸባሪነት ፈርጆታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት አል-ቃኢዳን እና አሸባብን በአሸባሪነት ለመፈረጅ አንድም ደቡብ አፍሪቃዊዉ ተማሪ እንዳሾፈዉ ከተቀረዉ ዓለም በሕዋላ ስምንት ዓመት መጠበቅ፥ አለያም ሁለቱን አሸባሪ ድርጅቶች የኦነግ፥ የኦብነግ እና የግንቦት ሰባት መናጆ የሚያደርግበትን አጋጣሚ መፈለግ ነበረበት።

በ2001 በወጣዉ የፀረ-ሽብር ሕግ መሠረት፥አምስቱ ድርጅቶች ሐምሌ ሁለት ሺሕ ሰወስት በአሸባሪነት ተፈረጅዋል።ከዚያ በሕዋላ የመብት ተሟጋቾች እንደሚሉት ከርዮት-እስከ እስክንድር ያሉ ጋዜጠኞችን፥ ከኦልባና እስከ አንዱ ዓለም፥ ያሉ ፖለቲከኞች፥ ከመስሊም መሪዎች እስከ ሚንስትር ባለቤት ያሉ ተሟጋቾችን ለማሰርና በአሸባሪነት ለመወነጀል ብዙዎች እንደሚሉት ሕገ-መንግሥቱን የሚቃረነዉ የፀረ-ሽብር አዋጅ አልፋ-ወኦሜጋ ሆነ።ሺዎች ታስረዋል።ተከሰዋል።ተፈርዶባቸዋልም።ዶክተር ነጋሶ ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ግን እሰረኛ የለም ባይ ናቸዉ።«እስር ቤት ዉስጥ የሚማቅቁ ፖለቲከኞች የሉም።ቁጥር-አንድ።እስር ቤት ዉስጥ የሚማቅቁ ሌሎች የፖለቲካ አቀንቃኞች የሉም።በመርሐችንና በአዕምሯችን በጣም ግልፅ ነን።የሐገሪቱን ሕግ የሚጥስ ማንኛዉም ሰዉ፥ ፖለቲከኛ ይሁን የመንግሥት አካል ሁሉም ከሕግ በታች ናቸዉ።»

የሕገ-መንግሥት አስራ-ስምንተኛ ዓመት ሲዘከርም ይሕን መሰሉ ተቃርኖ መደመጡ ነዉ-የወደፊቱም ከእስካሁኑ የበለጠ የማስጋቱ ነዉ-ፍራት ጭንቀቱ።ዶክተር መሐሪ ፍራቱን ለማስወገድ አብነት የሚሉት አላቸዉ።ሰሚ ይኖር
ይሆን? ካለ ሲሆን ለማየት-መስማት ያብቃን።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Mon Dec 17, 2012 2:26 pm

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው::

ውለታ የማታውቅ ሀገር !!

ከሃገር ቤት የተጻፈ ደብዳቤ::

ያ የኮሜዴ አውራ እብድ ተብሎ ጎዳና ላይ ቆሼ ይለቅማል:: እርሱን ያፈራው ሕብረተሰብ የወደቀን ቀና ከማድረግ እንዳይቃና ይተጋል:: ስለዚህ ሕብረተሰቡ እንደ ድመት የራሱን ልጆች ይበላል እየውልህ ዎዳጄ ! የተመለከትኩትን የታዘብኩትን እና ያስተዋልኩትን እንደ ወረደ ላጫውትህ::

ያ እውቁ የጥበብ ሰው ያ የኮሜዲ የጭውውት አውራ ያ ጥበብን የተቀባው ባለትልቅ ተሰጥኦ ሰው ያ ከሥነ-ጥበብ ተሻግሮ የአዕዋፋትን ዝማሬ ሚስጥር የነፋስን ሿሿታ የበር የመስኮትን ሲጥሲጥታ ሳይቀር በጥበብ ሥራው አክሎ የሚከውንልን ተዋናኝ "ልመንህ ታደሠ" ከፒያሳ ወረድ ብሎ ከሚገኘው ቢስ መብራት አካባቢ ላይ እንደማንም ቆሼ ሲለቅም ተመለከትኩት::

ልመንህን ያየ እኔን አንተን አየ እኔን አንተን ያየ ሕብረተሰቡን አዬ ሕብረተሰቡን ያየ ተቝማትን አየ ነው እያልኩ ያለሁት ዎዳጄ:: ያ የጥበብ አውራ ልመንህ ታደሠ ሰውነቱ ከርፍቶ የማይቀይራትን ጥቁር ሰማያዊ ወይንም ጥቁር ሱፍ በውሃ ሰማያዊ ሼሚዝ አጥልቆ የተጨራመጠች ልሙጥ ጥቁር ቆዳ ጫማ ተጫምቶ እንደባይንደር የመሳሰሉ የተጨረማመቱ ቡጭቅጫቂ ወረቀቶችን ይዞ የሥነ-ሥዕል ንድፍ እንደሚሰራ ጄማሪ ሰአሊ ከአደባባይ ሆኖ ድምም ፍዝዝ ይላል:: በጄርባው ባነገተው ጥቁር ቦርሳ ወይንም ኮሮጆ አንዳንድ ነገሮችን ሼክፏል ልመንህ ታደሰ ተርቦም ሊሆን ይችላል ማን ያውቃል? ለጠቅ አድርጎ ደግሞ ከቢስ መብራት ሳይርቅ አቀርቅሮ ራመድ ራመድ ይልና ወዲያው ቆሽ ነገር ይለቅማል ከመሬት:: ከዚያም ቀረብ ብሎ ከደማሚው ከሚያናጥበው ሠው ጋራ ከራሱ ጋር ብቻ ከሚያወራ ሠው አናዳች ውል የሌለው ነገር ያወራል ብዙዎች የዕድሜ አቻዎቹና የእድሜ ታናናሾቹ እያፌዙበት ያልፋሉ:: ባደባባይ ላይቭ እየተወንክ ነው.... ልመንህ አለባቸው ተካ ይጠራሐል አትሄድም ቶሎ ልመንህ ኑሮ ጠረረብህ ከዋሽንግተን ዲሲ ተንደርድረህ ፒያሳ ጎዳና እና ሌላም ሌላም በጆሮየ ያደመጥኩት ከሕብረተሰቡ የተበረከተለት አቀባበል ነው::

ይቀጥላል........
Last edited by ማህቡብ on Tue Jan 15, 2013 3:02 pm, edited 2 times in total.
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Mon Dec 17, 2012 3:11 pm

የቀጠለ....
የጎዳና ተዳዳሪዎች ብቻ በፍቅር ሲቀበሉት አስተውያለሁ ሊንከባከቡት ይሞክራሉ ግን ደግሞ እሱ አይመቻቸውም:: እብዱ ልመንህ ፊቱን ወደ ፒያሳ አዙሮ ተንቀሳቀሰ እንደብዙ ወጭ ወራጅ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊት እኔም በለበጣ ከንፈሬን እየመጠጥኩ ተዘባበትኩበት እንደ ብዙ አሽከርካሪዎች እኔም ገልመጥ አድርጌው የስላቅ ፈገግታ አሳይቸ የእርምጃየን ማርሽ ጨምሬ ወደ መርካቶ እብስ ለማለት ፈልጌ ነበረ:: ግን አልቻልኩም መጽሃፍ ቅዱስ ያለው የሳምራዊት ታሪክ ትውስ አለኝ አንዳጭ የጥፋተኝነት ስሜት ጭምድድ አድርጎ ያዘኝ አይምሰልህ ዎዳጄ ልመንህን እኔ በግል አልበደልኩትም በአካልም አላውቀውም በተናጠል ያስቀየምኩት አንዳችም ነገር የለም
በቅርቡ አበደ ብለው ከአሜሪካን ሃገር አውጥተው ዲፖርት አደረጉት ነው የሚባለው በተወለደበት ሕብረተሰብ ውስጥ አምጥተው ሕዝቡ ውስጥእስኪደፉት እስኪጥሉት ድረስ እንደዚህ ገጽ ለገጽ ባካል አይቸው አግኝቸውም አላውቅ በቲቪ እስክሪን እና በሲዲዎች ብቻ የምመለከተው እና የማደንቀው ብርቅየ አርቲስት ነበረ ነበር ልበል እንግዲህ ጎዳና ላይ ጣልነው አይደለ::

እኔና እሱ በትውልድም በደረጃም ዱባ እና ቅል የምንባል ነን የትናየት ይርቀኛል መሰለህ ኢሀድግ ከበረሃ ወደ አዲስ አበባ በገባ እና መንበረ ሥልጣኑን በተቆናጠጠበት ጊዜ የነበረውን አስፈሪ የጭንቅ ወቅት የበቅሎ ቤቶች ፍንዳታ በልጅ አይናችን ያየነው የሼጎሌው ፍንዳታ እና እልቂት በየቤታችን ጣራ በስቶ የሚመጣውን ጥይት እና የመትረየስ እሩምታ የፈጠረብንን የፍርሃት አባዜ በጥበብ ስራቸው ያረሳሱን ከነበሩስ የጥበብ ሰዎች አንዱና ዋናው ልመንህ ታደሠ ነበረ ካለባቸው ተካ ጋራ ተጣምሮ ማለት ነው:: እንደማስታውሰው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የመቶ ሃያ ፕሮግራም አሁን እሁድ መዝናኛ በሚል ተቀይሯል ሲጄመር ለዝግጅቱ አስኳል ተደርገው እሚጠበቁት አርቲስቶች ልመንህ ታደሰ እና አለባቸው ተካ ዋናዎቹ ነበሩ ::

ዛሬ አለባቸው ተካ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ካለፈ ሰነባበተ ልመንህ ታደሰ ደግሞ አብዷል ተብሎ የወለደ ያፈራ ሕብረተሰብ ጥሎ አይጥልም ተብሎ ከአሜሪካን ሃገር ወደ አዲስ አበባ ፒያሳ አራት ኪሎ ጎዳና ከደጅ ተደፍቷል ተጥሏል ነው እያልኩ ያለሁት:: ግን እኮ የወለደ ያፈራ ሕብረተሰብ አይጥልም የሚባለው አባብል ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ አይመስለኝም ምናልባትም ወላጅ እናት አትጥልም ይሆናል እንደ ሕብረተሰብ ግን ጥሎ የማይጥልህ ወይ በሥጋ የምትዋለደው ቤተሰብ ካጤገብሕ ሊኖር ይገባል አሊያ በጎሳ በሃማኖትበኑሮ መደብ ዎይንም በፖለቲካ ሪዮት የምትጓደን ቡድን ሊኖርህ እና ያም ቡድን በማህበረ ፖለቲካው ጥሩ ቦታ ሊኖረው ግድ ይላል::

አለበለዚያ ከዚያ ውጭ ከሆንክ እንደ ልመንህ ታደሰ ልቀህ የታየህለት ተግተህ የሰራህለት ቍንቕውን የተቀኘህለት ባህሉን ያዳበርክለት ኪነቱን ያጎላህለት እና የሕብረተሰብ አገልግሎት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል የሰጠኸው ሕዝብ የግለሰብ እና የማሕበራዊ ተቓማት ስብስብ ውይ ብሎ ከንፈሩን እንደ ጡጦ መጥጦ ዋ እንደሱ እንዳትሆን እያለ ለራሱና ለቤተሰቡ መማሪያ ያደርግሃል እንጅ ላንተ ምንም አይፈይድልህም::
ይቀጥላል....
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby እንሰት » Mon Dec 17, 2012 11:00 pm

ታንክ ዩ ለማለት ነው:: የአምድህ አንባቢ ነኝ::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ማህቡብ » Tue Dec 18, 2012 6:39 am

ወንድሜ እንሰት እኔም ምስጋናውን ተቀብያለሁ ከታላቅ ምስጋናን አክብሮት ጋር::

የቀጠለ.....

ምክኒያቱም የኛ ህብረተሰብ በጣም ትንሽ ልጅ ነው አሁን ያለው ኢትዮጵያዊ ስብስብ ይህን የምልህ አንድ ልመንህ ታደሰን ብቻ ዋቢ አድርጌ እንዳይመስልህ በርካታ ለሕብረተሰቡ አገልግሎት የሠጡ ሰዎችን ከሰፈሬ ካካባቢየ ልጠራልህ እችላለሁ ዳሩ ግን አንተ እነሱን በጉልህ አታውቃቸውም እኔ ጻሃፊው እና የአካባቢው ሰዎች ብቻ ነን የምናውቃቸው:: አንተና በዙሪያህ ያሉ ሰዎች የምታውቍቸው እኔ የማላውቃቸው ለሕብረተሰቡ ብዙ የሰሩ ሰዎች እንደሚኖሩ እገምታለሁ ስለዚህ በጋር በምናውቃቸው ሰዎች ብቻ እንጨዋወት ካልከኝ ደግሞ "አንሙትን" ታውቀው የለ ? ምነው አንሙት ያ አጭሩ ? ባለዋሽንቱ የጊሼ አባይ ኪነት ቡድን ጥበበኛ አዎ እንዴት እሱን ታጣዋለህ ? ውለታ መብላት ነው የሚሆንብህ ከድምጻዊያን ይሁኔ በላይ እና ሰማኸኝ በለው ጋራ "አንቱየዋ እነሱ እኮ ልጆች ናቸው ይጫወቱ በጊዜያቸው" ሲል በሙዚቃ ድራማ ላይ የሚያቀነቅነው ባለዋሽንቱ እረኛ::

እየውልህ ከጥቂት አመታት በፊትእሱም በኑሮ ደህይቶ እና ተደብቶ ሼራተን ሆቴል ፊትለፊት ላስቲካ እና ሼራ ዘርግቶ ተቀምጦ ነበረ ታዲያ ነነስ ያሉ አበው እና እመዎ ዳቦ እና ጣሳ ውሐ ሲሰጡት በሱ የጥበብ በረከት ሲዝናና እና ሲጨፍር የነበረው ሕብረተሰብ እና የማህበረ ፖለቲካው ሊቃውንት በማርሰዲስ መኪና ፍስስ እያሉ ወደ ሼራተን ሆቴል ሲገቡ የለበጣ ፈገግታቸውን እያሳዩት በበላይነት መንፈሰ እየተኮፈሱበት ያልፉ ነበረ:: አብረውት ከልጅነት እስከ ውቀት የተጠበቡት ጥበበኞች ዝናና ገንዘብ ባፈሱበት በዚያ ወቅት እንኳ ለሱ ጠብ ያደረጉለት ነገር አልነበረም:: በመጨረሻ እራሱን እየገዛ እየተነቃቃ ሲመጣ ግን በንዲህ አድርጌለት ነበር እምቢ አለኝ እንጅ ላደርግለት አስቤ ነበር ነበር ቅብርጢሶ እያሉ ሞራል በሚያንሳቸው አንዳዳ መጽሔቶች ሞራላቸውን ሊያነቃቁ ሞከሩ::

እሺ ዎዳጄ ደግሞ በሌላ ሠው ታሪክ ልሰልልህ:: ደራሲ እና ተርጓሚን ሐሩን ምናሴን አውጉቸው ተረፈን ታውቀዋለህ ? እሱም እንዲሁ አበደ ተብሎ ካደባባይ ወድቆ የሱን ማበድ ሳይሆን የኛን የማሕበረሰቡን ማበድን እና ሞራል ማጣት ጋሐድ አውጥቶብን ነበረ:: አንድ ሠው በማሀበረሰብ አገልግሎት ዘመኑ እንደሸልኮራ ምጥጥ አድርገን ተጠቅመን እንደማንኛውም አንዳች የሕይዎት ውጣውረድ ሲገጥመው ግን ምጣጭ ነው ገለባ ብለን አደባባይ እንጥለዋለን ምንም ውለታ እና ባለዕዳነት እንኳን አይሰማንም እኔ እና አንተ ሕብረተሰቡ ዎዳጄ::

ጻሃፊና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሙሉ ታፈሰን እንዲሁ ከትውስታ ትጥለዋለህ ብየ አልጠራጠርም ዎዳጄ ይኸው ያን የመሰለ ጻሃፊ የሕይዎት ውጣውረዱ ላይ የኛን ምሳር ማብዛት ጨምረንበት አደባባይ ከወረወርነው አመታት አለፈን:: እዚህ ጊወርጊስ አደባባይ ላይ ተቀምጦ ዘዎትር ይታዘበናል ትላንት ቤቱ እየተመላለሱ ተልካሻ የጥበብ ሥራቸውን እንዲያደምቅላቸው አድርገው ስማቸውን የገነቡ የጥበብ ነጋዴዎች ሁሉ ዛሬ በመኪና ሰላም ነህ "ሰሌ" እያሉ ያልፉታል:: እነሱ ጥበቡን ስለሼጡ አተረፉ እሱ ነጋዴ ባለመሆኑ አበደ ተባለ አለቀ በቃ :: የሰለሞንን ብዕር ያልተጋራ እና ትሩፋቱን ያልተጠቀመበት ያንን ጊዜው የኪነት ሰዎች እና የማስታወቂያ ባለሙያዎች የሉም ለማለት እደፍራለሁ ካለኝ መረጃ ማለት ነው:: ግን ዛሬ እነሱ የነሱ የገንዘብ ተጠቃሚዎችም ሆኑ እኛ የጥበብ በረከቱን ያጣጣምን የሕብረተሰቡ አባሎች በርሱ የጎዳና ሕይዎት የኛን የበላይነት እያሳየን ምንም ሳንፈይድ ባለዕዳነታችን ሳይሰማን እንደ ከብት በሃያአነደኛው ክፍለዘመን የጦጣ ኑሮ እንኖራለን::

ይቀጥላል.......
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Dec 18, 2012 7:52 am

የቀጠለ..........

ዎዳጄ ! ከቀድሞዎቹ ሰለባዎች ዋቢ ከፈለግክ ደግሞ ድምጻዎቷ ባለክራር ሜሪ አርምዴ ታማ ቤቷን ዘግታ ስትቀመጥ የገጠማትን ወደ ኋላ ሄደህ አስታውስ ሰሞኑን ደግሞ በመረዋዋ ተርገብጋቢ ድምጽዋ "እንቁጣጣሽ እንቁጣጣሽ እና ትዝታን በፖስታ ልኬልሃለሁ መልሱን በቶሎ እጠብቃለሁ" እያለች የምታዜመው ዘሪሁን ጌታሁን ታማ... ሃኪም ወደ ውጭ ሃገር ሄደሽ ካልታከምሽ በሕይዎት የምትቆይው ለ አንድ አመት ብቻ ነው ብሏት ቤቷን ዘግታ ተቀምጣለች:: በቃ ዘጠኝ ሞት ቢመጣ አንዱን ግባ በለው አይነት ነው የሷ ቆይታ::

ዎዳጄ! አንተን ማስቸገር እንዳይሆንብኝ እንጅ ብዙዎች በርካታ የታዋቂ ሰዎች ታሪክን እያነሳሁ ባወጋህ እንዴት በውወደድኩ ግን ስንቱን አንስተን በማውራት ስንቱን የሕብረተሰብ አባላት አስቀይመን እንችለዋለን:: ያ የጥበብ አውራ ልመንህ ታደሰ እምር እምር እያለ በመራመድ የሚለክፉትን ፍንዳታዎች እና የሚያሽሟጥጡትን ሽማግሌ ግንባታዎች የመልስ ምት እየሰጠ በአንድ ብር ምጽዋት እየሰጡ ሊያልፉት የሚሞክሩትን ቁን ሰዎች ሁለት ብር የመልስ ምት እየሰጠ ገንዘቡን እየበተነ ያልፋል እኔም ጻሃፊው እከተላለሁ ጂል ታዛቢ ሆኘ:: ሲኒማ ኢምፓየር ላይ አንድ ሰው አስቆሙትና እጁን ይዘው ልመንህ ምነው እንደዚህ እራስህን ጣልክ አሉት? አዘንታ በሚታይበት የፊት ገጽታ እሱ በባይንደር መሳይ የያዛቸውን ወረቀቶች እንዳይነጥቁት በመስጋት ይመስላል በአንድ እጁ ደረቱ ላይ ለጥፎ ""ለምን አትተውኝም እኔ ማናችሁንም አልፈልግም ተጣልቻችኋለሁ"" ሰውየው ሳቃቸው መጣ ሌሎች ብዙ ሰዎች ከበዋቸው ቆሙ:: ልመንህ ተቆጣ እጁን አስለቅቆ የአራት ኪሎን መንገድ ያዘ:: አስፋልት ዳር ለነበሩት የጎዳና ተዳዳሪዎች የያዘውን አንድ ብር ሳንቲም እንዳለ ለገሳቸው እና እየሳቀ ከራሱ ጋር ነጎደ::

ይህ እየሆነ ያለው ተመሳሳይ ክንፎች ያላቸው ዎፎች በጋር ይበራሉ በሚል ብሒል ለመረዳዳት በተሰባሰቡ የሙያ ማህበራት ባሉበት ሃገር ነው:: የደራሲያን ማህበር, የሴት ደራሲያን ማህበር, የኮሜዲያን ማህበር, የሙዚቃ ማህበር የተውኔት ደራሲያን ማህበር, የፊልም ባለሙያዎች ማህበር,የፕሮዲዩሰሮች ማህበር...ይኸ ማህበር ባሉበት ሃገር ነው::

አየህ ዎዳጄ አበሻ አበሻ ነው!! ግለሰብ ሆነ ሕብረተሰብ ተቍም ሆነ ዲያስፖራ በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ በዚህ ረገድ የሚፈይደው በጎ ነገር የለም:: በቅርቡ ከአሜሪካን ሃገር ለእረፍት የመጣ ጕደኛየ ቴዎድሮስ ታደሰን በአንድ ቅዝቅዝ ያለ የሃበሻ ሬስቶራንት ውስጥ ሲዘፍን እንደተመለከተው በኩራት ነግሮኝ እዚህ እዚህ እንደ ታአር የምናያቸው ድምጻዊያን እዚያ በአንድ ቢራ በቅርብ እንመለከታቸዋለን አለኝ::

ልመንህ ታደሰን ጨምሮ አሜሪካ ሁላችንንም እኩል አድርጋናለች ይህንንም ለእከሌ ድምጻዊ ድሮ እኮ አገርቤት እንደ ብርቅ ነበር የማይህ እዚህ ግን እንደ ዋዛ አየሁህ ብየ ነግሬዋለሁ በማለት ስለብርቅየወቻችን ምንምነት ሲነግረኝ በርሱ ሥነ-ልቦና ላይ ስላለፈው ጠባሳ ምንም አልተጨነቀም ነበረ:: በአንጻሩ ሌሎች ሃገራት ታዋቂ ሰዎቻቸውን ላራያነት ሚና ሕብረተሰቡ ውስጥ ስለሚያጫዉቷቸው ለታዋቂ ሰዎቻቸው እንክብካቢያቸው የላቀ ነው:: ከነዚ ታዋቂ ሰዎች ጄርባ ባህላቸው, ቋንቋቸው,እሴታቸውና ባንዲራቸው መኖሩን ለደቂቃ አይዘነጉትም:: እንግሊዛዊያን ሼክስፒር,ቻርልስ ዲንከስም ሆነ እግር ኳስ ተጫዋቹ ቤካም እና ሮኒ ጄርባ ታላቋ እንግሊዝ መኖሯን ጠንቅቀው ያውቃሉ::

በተለይ በዚህ በሃያአንደኛው ክፍለዘመን እና ለታዋቂ ሰዎቻቸው እንክብካቤ ያደርጋሉ የሰዎቻቸውንም አያያዝ ያውቃሉ በእንግሊዝ ሃገር ውስጥ ለጥበብ ሰዎቻቸው ለጻሃፊዎቻቸው ለጋዜጠኞቻቸው እና ለሕብረተሰቡ ምርምር የሚያደርጉ ሰዎች በኑሮ ውጣውረድ ውስጥ ሰጥመው ለሕብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት እንዳይገቱ 'አርትረዝደንት" የተባለ ተቋማዊ አገልግሎት አላቸው ሲታመሙ ያሳክሟቸዋል ሲቸገሩ መፍትሄ ያመላክቷቸዋል:: ይህ አይነቱ የአገልግሎት ተቋም በለጋሽ ግለሰብ በድርጅቶች እና በመንግስታዊ ድጎማ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በሥራው እቅድ አቅርቦት የሚያገኝ ጥበበኛ እንደተፈቀደለት ጊዚያት ለሁለት ሳምንት ለወራት ለአንድ አመት እና ለሁለት አመት ለኑሩ የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ በተቋሙ ቀርቦለት የጥበብ ሱባኤ ይገባል ማለት ነው እቅዱን ተግባራዊ ሊያደርግ::

አየህ ወዳጄ አርትረዚደንት የተባሉ ተቋማት ጥበብን የማዋለድ ሥራ ይሰራሉ የዚህ ጸሃፊም ጓደኛ የሶስት ወር አገልግሎቱን ተግባራዊ ማድረግ ተስኖት የነበረውን ጥበባዊ ክህሎቱን ባህል ተሻግሮ ወጥቷል:: ወደ እንግሊዝ የመብረሪያውን አየር ቲኬት የምግብ እና የመኝታ አገልግሎቱን የቀን ተቀን የኪስ ገንዘ ሰጥተው ነበር በውስጡ የታመቀውን ጥበብ ያዋለዱት:: አስትውለህ ከተመለስክ ደቡብ አፍሪካ እና ቡርኪኖፋሶን በመሳሰሉት ሃገራት ትልልቅ ፋውንዴሽን አሉ:: ለሕብረተሰባቸው አገልግሎት የሰጡ ሰዎች የለት እክል ሲገጥማቸው ሊያቃኗቸው እሚተጉበት እዚህ የእኛ ሃገር ኢትዮጵያዊ ግን ምንም እንኳ ሦስጥ ሽህ አመት እንደ ሃገር የመቆም ታሪክ ቢኖራትም ምንም እንኳ የቀደምት ስልጣኔ ባለቤቶች ብንሆንም እንደ አንድ ሕብረተሰብ ገና በቅጡ አላደግንም ገና ህጻን:: በየዘርፉ ያገለገሉ አራያ ሰዎቻችን የሕይዎት ውጣውረድ ሲገጥማቸው ቀና ልናደርጋቸው ከመጣር ይልቅ ቁልቁል ገደል ልንከታቸው እንረባረባለን::

ይቀጥላል.......
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Dec 18, 2012 8:09 am

የቀጠለ............

ታመው ከማሳከም ይልቅ ሞተው እናለቅስላቸዋለን እንደ ልመንህ ታደሰ ያሉትን ወደ ሆስፒታል ወስደን ወደ ጤናቸው እና የመረጋጋት ሕይዎት ከመመለስና ብሄራዊ ክብራችንን ከመጠበቅ ይልቅ በጎዳና ከንፈር እንመጥላቸዋለን::

አየህ ዎዳጄ ! መፍሄው እዚሁ ጉያችን ሥር አለ የአይምሮ ህክምና የሚሰጥባቸው ሆስፒታሎች አሉ ለዘርፉ እስፔሺያሊስት ሃኪሞች አሉ መድሃኒቶችም አሉ::ነገር ግን ይንን አቀናጅቶ በእንደዚህ ያለ ሁኔታ አገልግሎት የሚሰጥ በሃገራችን ተቋም የለንም እናም ያላደገ ሕብረተሰብ ነን ያልኩት ለዚህ ነው::ያላደገ ሕብረተሰብ ያደጉ ሕብረተሰቦችን እንደ ድመት ካለማወቅ ወልዶ ይበላቸዋል ስለዚህ ውጤቱ አንችም ዜሮ እኔም ዜሮ አንተም ዜሮ እሱም ዜሮ ሁላችንም ዜሮ ሆንን::

ዎዳጄ ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ኮሜዴ ልመንህ ታደሰ በአደባባይ ብቻውን ሲጋልብ በርቀት ይታየኛል ለሱ የሰጠነውን ማህበራዊ ምላሽ የተመለከተችው ጥሪ በአገልግሎት ጥምህን ያጋር ይመስልሃል ? ይልቅ ይነግድብሃል ዎዳጄ!!


ቼር ያሰማን
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ሾተል » Sat Dec 22, 2012 2:19 pm

ሰላም ማህቡብ

በአርቲስት ልመንህ ታደሰ ዙርያና ተዛማጅ ነጥቦች ዙርያ ጽፈህ ያስነበብከንን ወድጄልሀለሁ::ጥሩ ግንዛቤ....ጥሩ እይታ ነው::

ተዳፈረኝ አትበልና ትዝብትህና ወቀሳህ ምንም የማይወጣለት ሲሆን ለዛ ልትመሰገን ይገባሀል ነገር ግን አንተ እንደ አንድ ዜጋ ልመንህ እንደዛ ታሞና ተቆሳቁሎ አይተኸው ስታበቃና ሁኔታውን እንዲሁም የቀን ውሎውን እየተከታተልክ ስታጠና ከቆየኽ በሁዋላ ለጥናትህ የሚሆኑ ማቴሪያሎችን ከሰበሰብክ በሁዋላ ለልመንህ ምንም ሳታደርግለት ወደ ጽሁፉ አቀናኽ ወይስ እንደ አንድ ህሊና እንዳለውና እንደ አንድ የዜጋ አላፊነት ምን አደረክለት?

ምቼም ያደረግክለት ነገር ካለ ሌላውም እንዲማር እስቲ ማንም እንደጉራ ሊቆጥርብህ የሚችል ስለማይኖር በግልህ ለልመንህ ካየኸው ጊዜ ጀምሮ ያደረክለትን ንገረን::

በርታ

ሾተል ነን..........
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ማህቡብ » Tue Dec 25, 2012 2:41 pm

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው::

ፀረ-አዉሮፕላን ሚሳዬል ቢኖረን ኖሮ» አሉ ጄኔራሉ-አሶስየትድ ፕረስ ለተሰኘዉ ዜና ወኪል ዘጋቢ ባለፈዉ ሳምንት።«ይሕን ሥርዓት ባንድ ወር ዉስጥ እናስወግደዋለን።» ፀረ-አዉሮፕላን መሳሪያዉ ካልተገኘ ደግሞ ፥ ቀጠሉ የሐምሳ አምስት አመቱ ጄኔራል «ሰወስት ወር»


የደፈጣ ተዋጊዎቹ አዛዥ ጄኔራል ሳሊም ኢድሪስ እና ስደተኛዉ ጋዜጠኛ ማሊክ አብድሕ ሲጠብ ለየግላቸዉ ሥልጣን፣ ሐገራቸዉ ለመኖር፣መሥራት-ጉጉት ስኬት፣ ሲሰፋ ብዙዎች ብዙ ጊዜ እንደሚሉት ለሶሪያዎች፣ መብት፣ ነፃነት መከበር ፍላጎት-ግብ፥ የአሰድ ሥራዓትን መወገድ እኩል ይፈልጉታል።ይታገላሉም።ብሪታንያዉያኑ፥ጄኔራል ቲም ክሮስና ሚንስትር አላስተር በርት በየግላቸዉ ምናልባት ለመሾም-መሸለም፣አማፂያኑን እንደምትረዳ ሐገር ሹማምንት በጋራ የአሰድን መወገድ ይሹታል።አራቱ-እኩል ከሚፈልጉት እንደርሳለን የሚሉበት ሥልት፣ጊዜ፣ ሥለ ወደፊቷ ሶሪያ ያላቸዉ ዕምነት ዝግጅት ግን ይቃረናል።የአራቶቹ አንድነት፣ ተቃርኖ ሥለ አንዲሲቱ ሶሪያ፥ ሶሪያዎችም የዓለም ዘዋሪዎችም አድም-ተቃራኒም አቋም የመያዛቸ ነፀብራቅ መሆኑ ያሰጋል።እንደገና ሶሪያ እያልን እንደገና አንድም-ተቃርኖዉን ላፍታ እንቃኝ።

ሐልፋያ-ሶሪያ። ትናንት።አማፂያን እና ደጋፊዎቻቸዉ እንዳስታወቁት የመንግሥት የጦር አዉሮፕላኖች በጣሉት ቦምብ አንድ ዳቦ ቤት አጠገብ ተሰብስበዉ የነበሩ ዘጠና ሰዎች ተገደሉ።የቆሰለዉ በመቶ ይቆጠራል።የሶሪያ መንግሥት መገናኛ ዘዴዎች ባንፃሩ እንደዘገቡት አደጋዉን የጣሉት እነሱ «አሸባሪ» የሚሏቸዉ አማፂያን ናቸዉ።በዚያም ብሎ በዚሕ ሌላ ቦምብ፥ ሌላ እልቂት፥ ሌላ ጥፋት፥ እና ለቀሪዎች የሰቆቃ ጩኸት።

የጦርነቱ ጥፋት-አሌፖ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአረብ ሊግ ልዩ መልዕክተኛ ላሕዳር ብራሒሚ ከፕሬዝዳት በሽር አል-አሰድ ጋር ዳግም ተነጋገሩ።ደማስቆ-ትናንት።የልዩ መልዕክተኛዉ መልዕክት፥ የዉይይቱ ዝር ዝር ይዘት፥ ሒደት ዉጤቱ በግልፅ አልተነገረም።ጥቅል ዓላማዉ ግን ባለፉት ሃያ-ሰወስት ወራት ከካይሮ፥ ከብራስልስ፥ ከኒዮርክ ደማስቆ እየደረሱ ከተመለሱት የአረብ ሊግ፥ የአዉሮጳ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኞች ካሉት የተለየ አይደለም።ለሶሪያ-ሰላም የሶሪያ ተፋላሚዎች ማስታረቅ።

እስካሁን የዉጊያዉ ግመት፥ የሕዝቡ እልቂት ፍጅት፥ስደት-እንግልት ንረት እንጂ የሰላም ተስፋ ጨርሶ የለም።ልዩ መልዕክተኛ ብራሒሚ ደማስቆ ከመግባታቸዉ ጥቂት ቀደም ብሎ ትናንትናዉኑ የሶሪያዉ ማስታወቂያ ሚንስትር የመንግሥታቸዉን የተለመደ መልዕክት ባስተርጓሚ አስተላለፉ።

«ለእኒያ ድርድርን እንቢኝ ላሉት የፖለቲካ ሐይላት አጠቃላይ ምክር አለኝ።ጊዜዉ እየከነፈ ነዉ።ለፖለቲካዊ መፍትሔ ፈጥናችሁ ተንቀሳቀሱ።መንግሥትን እና ፕሬዝዳንቱን አስወግዶ፥ ርዕሠ ከተማይቱን ለመቆጣጠር የሚደረገዉን ይሕን ወታደራዊ ዘመቻ እርሱት።ይሕ ነዉ-የኔ ምክር።»

ጄኔራል ሳሊም ኢድሪስ ለማስታወቂያ ሚንስትሩ ማስጠንቀቂያ የሰጡት መልስ ሥለመኖር አለመኖሩ ላሁኑ የታወቀ ነገር የለም።የቀድሞዉ የሶሪያ ወታደራዊ ኮሌጅ የኤሌክትሮኒክስ መምሕር ሰላሳ ዓመት ያገለገሉትን፥ የጄኔራልነት ማዕረግ የለጠፉበትን ጦር ከድተዉ አማፂያኑን ከተቀላቀሉ ታሕሳስ አምስተኛ ወራቸዉ ነዉ።

አንድ መቶ ሃያ-ሺሕ ተዋጊዎች እንዳሉት የሚታመነዉ የአማፂያን ቡድናት ጦር ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሆነዉ ባለፈዉ ወር ተሰይመዋል።«ፀረ-አዉሮፕላን ሚሳዬል ቢኖረን ኖሮ» አሉ ጄኔራሉ-አሶስየትድ ፕረስ ለተሰኘዉ ዜና ወኪል ዘጋቢ ባለፈዉ ሳምንት።«ይሕን ሥርዓት ባንድ ወር ዉስጥ እናስወግደዋለን።»የጦርነቱ ጥፋት-ደማስቆ ፀረ-አዉሮፕላን መሳሪያዉ ካልተገኘ ደግሞ ፥ ቀጠሉ የሐምሳ አምስት አመቱ ጄኔራል «ሰወስት ወር» አሉ ፍርጥም ብለዉ።ጄኔራሉን «አዲስ መጤ» የሚላቸዉ የአማፂ ቡድናት መሪዎች ግን የእሳቸዉን አዛዥነት አልተቀበሉትም።አማፂያኑ በሚንቀሳቀሱበት በተለይም በሰሜን-ምዕራብ ኢድሊቢ አዉራጃ ያሉ የሐገር ሽማግሌዎና የጎሳ ታጣቂ መሪዎችም በጄኔራሉም ሆነ በጄኔራሉ አለቆች የሚታዘዘዉን ተዋጊ ሐይል አይፈቅዱትም።

ጄኔራሉ ራሳቸዉ የሚያዙት ጦር ወደ ሚቆጣጠራቸዉ አካባቢዎች የሚገቡ የሚወጡት በጥምጣም፥ ኮፊታ፥ በአልባሌ ልብስ ማንነታቸዉን ደብቀዉ ነዉ።የማደሪያ ወይም የዕዝ ጣቢያቸዉን «የመንግሥትን ሰላዮች ፍራቻ ባንድ ሌሊት ሁለቴ ወይም ሰወስቴ ለመቀየር እገደዳለሁ» ይላሉ።

ጄኔራሉ የአማፂያኑን ሐይል በቅጡ አላስተባበሩም። የሚታዘዛቸዉ ጦር በሚቆጣጠረዉ አካባቢ ሕዝብ እንኳን በቂ ድጋፍ የለዉም።ተዋጊዎቻቸዉን ለማስተባበርና ለመምረት መንቀሳቀስ አይችሉም። የመሸጉበት ቱርክ፥ የሚደግፏቸዉ የዓረብና የምዕራባዉያን መንግሥታት ለጦራቸዉ እሳቸዉ የሚመኙትን የጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ታማኝነቱን አላገኙም።በዚሕ መሐል ነዉ፥- ጄኔራሉ የአሰድን ስርዓት ሲፈጥን-በወር፥ ሲዘገይ በሰወስት ወር አስወግዳለሁ የሚሉት።

ጄኔራሉ እንዳቀዱት፥ የበላይ-የበታቾቻዉ እንደሚተመኙት፥ ደጋፊዎቻቸዉ እንደፈለጉት የአሰድ ሥርዓት ቢወገድ አስወጋጆቹ ሶሪያን የሚመሩበት ሥልት-ዝግጅታቸዉን ሊያስታዉቁ ቀርቶ ሐገር ለመምራት የማቀድ-መዘጋጀቱን አስፈላጊነት እንኳን በግልፅ አላስታወቁም።ይሕ ነዉ እንደ ብዙ የሶሪያዊዉያን ሁሉ የሶሪያዊዉ ጋዜጠኛ ሥጋት፥ ይሕ ነዉ-እንደ ብዙዉ የዉጪ የጦር ባለሙያ ሁሉ የብሪታንያዉ ጄኔራል ትችት መሠረት።

እና ምናልባት ሶሪያ ዳግማዊት ኢራቅ፥ አፍቃኒስታን ወይም ሊቢያ የመሆንዋ ጥፋት ምልክት።

ያ-አሜሪካዊዉ ወፈፌ ወጣት ሃያ-ሕፃን ተማሪዎችን ከስድስት አስተማሪዎቻቸዉ ጋር የመረሸኑ አስደንጋጭ ክስተት ዛሬም በአስረኛ ቀኑ የትልቂቱ ሐገር ትልቅ ሕዝብ ትልቅ ርዕስ፣ ለተቀረዉ አብዛኛ ዓለም የብዙ ጥያቄ፣ የትዝብት ግራሞት ሰበብ እንደሆነ ነዉ።

እርግጥ ነዉ አሜሪካ ከልዕለ-ሐያልነቱ መንበር ብቻዋን ተደላድላ የመቀመጧ ሚስጥር ከሐብቷ ግዝፈት፣ ከእዉቀት፣ ብልሐቷ፧ርቅቀት ይበልጥ ከጦር መሳሪያዋ አይነትና ብዛት የሚተረተር ሐቅ መሆኑ አንድ ሁለት አላሰኘም።የጦር መሳሪዋ እንደ መርሕ፣ ጥቅሟ ሁሉ የተቃርኖ እርምጃ ጉዞዋ መሠረትነቱ ለዜጎችዋም፣ ለታዛቢ፣ ከጃይ ተከታዮቿም እንግዳ አይደለም።


የዓለም ድሐ፣ በሽተኛ፣ ረሐብተኞችን የመርዳት ለጋስነቷ፣ የመሳሪያዋን የማጥፋት አቅም በማሳደጓ ጥፋት የሚጣፋባት፣ ለተበዳዮች መብት ነፃነት የመሟገቷ ሰናይ፥ ብዙ አጥፊ ጦር መሳሪያ ብዙ ከማምረቷ ሐቅ፣ ለጨቋኞች ሳይቀር ከመሸጥ ማስታጠቋ እኩይ ጋር የሚቃረንበት፣ ለዓለም ሠላም የመሟገቷ ጥሩ፥ ብዙ አጥፊ መሳሪያ በታጠቀ ጦሯ ብዙ ከማስጥፋቷ መጥፎ ጋር መላተሙ የሁሌም እንጂ የትናንት ወይም የዛሬ ብቻ እዉነት ብአይደለም።


የዜጎቿን ደሕንነት ለማስጠበቅ የገንዘብ፣ የዲፕሎማሲ ከሁሉም በላይ የጦር ጉልበቷን በድፍን ዓለም ለማዝመት የማታመነታዉ ትልቅ ሐገር፥ ሕዝቧን ብዙ በማስታጠቅ፣ ብዙ በማስገደልም ዓለምን የመምራቷ-ሐቅም ድንቅ ተቃርኖ ነዉ።የበቀደሙ ግድያ የፈጠረዉ ንዝረት፣ ድንጋጤ፣ ሐዘን ሲሰከንም፣ የዚያች ሐገር ነባር የእኩይ ሰናይ ቅይጥ ታሪክ ቁንፅል እዉነት ከመሆን አያልፍም።ያም ሆኖ ንዝረት ድንጋጤዉ የዋሽግተን መሪዎችን ሳይቀር እንባ አራጭቷል።የዋሽግተኖች የዉስጥ ጉድ-ድንጋጤ ሶሪያን አላስረሳቸዉም።የፕሬዝዳት በሽር አል-አሰድን መንግሥት ይደግፋሉ ያሏቸዉን የሊባኖድ ፖለቲከኛ ባሸባሪነት ፈረጁ።

«ይሕ (እርምጃ) እኛ ባለን ግንዛቤ እና የአሰድ ደጋፊዎች አጎራባች ሐገራትን ማወክ እንዳይችሉ ለማድረግ ባለን ቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ ነዉ።»

የዩናይትድ ስቴትሷ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ቪክቶሪያ ነላንድ-ባለፈዉ ሰኞ።

ዋሽግተኖች በቀድሞዉ የሊባኖስ ሚንስትር ሚሼል ሳመሐ ላይ የወሰዱት እርምጃ የሶሪያ አማፂ መሪ ጄኔራል ሳሊም ኢድሪስንም ሆነ ስደተኛዉን ጋዜጠኛ ማሊክ አብዴሕን ባያስደስት እንኳን የሚያስከፋ አይደለም።ለሶሪያና ለአካባቢዋ ሠላም የሚተክረዉ መኖር-አለመኖሩ ግን በርግጥ ግልፅ አይደለም።

በዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት የስለላ ጉዳይ ኮሚቴ መሪ እንደራሴ ማይክ ሮጀርስን ብዙ ያስጨነቀዉ ግን ከሶሪያ ሰላም ይልቅ በሶሪያ ምሥቅልቅል መሐል የሐገሪቱ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ከማን እጅ ይወድቅ ይሆን የሚለዉ ነዉ።

«የኬሚካል ጦር መሳሪያዎቹ እንደተከማቹባቸዉ የምናዉቃቸዉ አንዳድ አካባቢዎች ከመንግሥት ሐይላት ቁጥጥር እየወጡ ነዉ።ከዚሕም በተጨማሪ የመደበኛ መሳሪያቸዉ ረቂቅነትም በጣም ያሳስበናል።በአብዛኛዉ ከሩሲያ መንግሥት የተገኙት እነዚሕ መሳሪያዎች በጣም ብዙ ናቸዉ።እንዲሕ ዓይነት የሥርዓት ለዉጥ ሲደረግ ለረጅም ጊዜ የፀጥታ ክፍተት እንደሚፈጠር እናዉቃለን።በዚሕ ክፍተት ደግሞ እነዚያ የጦር መሳሪዎች መጥፎ ነገር ከሚያደርጉ ወገኖች እጅ እንዳይገቡ ያሰጋል።»

የአሰድን ሥርዓት ለመዋጋት አንዳድ ዘገቦች እንደሚጠቁሙት የሰባ ዘጠኝ ሐገራት ዜጎች ዘምተዋል።የየጎጡን ተዋጊ ቁጥር የቆጠረዉ የለም።ጄኔራል ሳሊም ደማስቆን ዳግም የሚረግጡበትን ቀን ከማስላት ዉጪ ለቁጥር የሚታክተዉን ታጣቂም ሆነ አስጊዉን ጦር መሳሪያ የሚቆጣጠሩበት አቅም፥ ፍላጎት ሐሳቡም ያላቸዉ አይመስልም።

የብሪታንያዉ የመካካለኛዉ ምሥራቅና የሰሜን አፍሪቃ ጉዳይ ምክትል የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አላስተር በርትን እንደሚሉት በተለይ የኬሚካል ጦር መሳሪያዉ ከማይሆኑ ሰዎች እጅ ገብቶ አካባቢዉን እንዳያፋጅ ፈጣን እርምጃ ሥለሚወሰድበት ሥልት መንግሥታቸዉ ይመለከታቸዋል ከሚላቸዉ መንግሥታት ጋር እየተናገረ ነዉ።

የሶሪያ አማፂያን ዕቅድ አልባ-ዕቅድ፥ የዋሽግተን፥ ለንደን ፖለቲከኞች የመጨረሻ ሰዓት ጥድፊያ፥ ሩጫ፥ ብሪታንያዊዉን ጄኔራል ቲም ክሮስን ሳያሰገርም አልቀረም።የፕሬዝዳት ሳዳም ሁሴን መንግሥት በተወገደ ማግስት ኢራቅ ዘምተዉ የነበሩት ጄኔራል ሥርዓትን ለማስወገድ ብቻ ያለመ ዉጊያ፥ጦርነት የሚያስከትለዉን ጥፋት ከትምሕር ቤት፥ ከፊልም ወይም ከቴሌቪዥን ሳይሆን ኢራቅ ኖረዉበት፥ ምስቅልቅሉን ለማስወገድ ሰርተዉበትም፥ አልሳካ ብሏቸዉም ያዉቁታል።

«ምዕራቡ ይሕን የሶሪያን ጉዳይ በተገቢዉ መንገድ ይዞታል ብዬ አላስብም» አሉ ጄኔራሉ ከትናንት በስቲያ።«አሰድን ለማዉገዝ፥ ለማግለልና ኢሰብአዊ ለማድረግ በጣም ተጣድፈናል።አሁን መዘዙን እያየን ነዉ።» አከሉ።ብሪታንያ የሚኖረዉ ሶሪያዊ ጋዜጠኛ የማሊክ አብዴሕ ሥጋት ደግሞ የኬሚካዊ ጦር መሳሪያ ይዞታ ብቻ አይደለም።ሶሪያ ሥርዓተ አልበኝነት ይሰፍንባታል የሚለዉ ጭንቀት ጭምር እንጂ።

«ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት ከሌለ» ይላል ጋዜጠኛዉ ዩናይትድ ስቴትስ፥ ብሪታንያም ሆነች መላዉ ምዕራባዊ ዓለም የሚፈይዱት ነገር የለም።የአሰድ ሥርዓት ሲወገድ ጦሩ ከተበተነ ሶሪያ ቢያንስ ለአምስት አመት ካሁኑ ይበልጥ ትመሰቃቀላለች።» እያለ ቀጠለ ጋዜጠኛዉ።

የበሽር አል-አሰድ ሥርዓትን መወገድ እኩል የሚደግፉት የሶሪያ አማፂ መሪ፥ ጋዜጠኛ፥ የአማፂያኑ ደጋፊ ሐገራት ፖለቲከኞች እና የጦር ባለሙያዎች፥ በተቃርኖ ሐሳብ ሲፋጩ፥ የደማስቆ መንግሥት ደጋፊ የምትባለዉ ኢራን «የሰላም ዕቅድ» ያለችዉን ሐሳብ ሰንዝራ ነበር።የምዕራባዉያኑ የማዕቀብ ዱላ ከሶሪያ እኩል የሚደቁሳት ኢራን አቀረበች የተባለዉ ባለሥድስት ነጥብ የሰላም ሐሳብ የዓለም ዘዋሪዎችን ትኩረት ሊስብ ቀርቶ ለመገናኛ ዘዴዎቻቸዉ የዜናነት ሚዛን እንኳን የሚደፋ አልነበረም።አማጺያኑ እንደ ቴሕራን ሁሉ የደማስቆዎች ደጋፊ የሚባሉት የሞስኮ ባለሥልጣናት የሚሉ የሚያደርጉትን ግን ወቃሽ፣ ተቺዎቻቸዉ፥ መገናኛ ዘዴዎቻቸዉም ጭምር እንደ ቴሕራኖች ሊዘጉት አይችሉም። የቴሕራኖች ዕቅድ-መኖሩ ሳይነገር፣ በወደቀ በአራተኛዉ ቀን የሩሲያዉ ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቱን ከሞስኮ ተናገሩ።ሐሙስ።

«ሩሲያ የበሽር አል-አሰድ ሥርዓት ሕልዉና አያስጨንቃትም።ይሕ ቤተ-ሰብ ለላለፉት አርባ ዓመታት በሥልጣን ላይ መቆየቱን እናዉቃለን።ለዉጥ እንደሚያስፈልግ አያጠያይቅም።የዛሬዎቹ ተቃዋሚዎች ሥልጣን የሚይዙ ከሆነ፥ የዛሬዎቹ የመንግሥት መሪዎች በተገላቢጦሹ ተቃዋሚ ሆነዉ
ጦርነቱ እንዲቀጥል አንፈልግም።ሩሲያ በዚያ አካባቢ ጥቅም ስለሌላት ጥቅሟን ለማስከበር የሚያሳስባት ነገር የለም።ሐገሪቱንና አካባቢዉን ከጥፋት ለማዳን ግን ለችግሩ ትክክለኛ መፍትሔ እንዲገኝ እንሻለን።የሩሲያ አቋም ተፋላሚ ሐይላት የራሳቸዉን ፀጥታና ደሕንነት ለማስከበር፥ በመንግሥታዊ አስተዳደር ለመጋራትና ሐላፊነትን ለመዉሰድ እንዲስማሙ ማድረግ ነዉ።የዚሕ ተቃራኒዉ አይደለም።በጦርነት የሚመጣ የሥርአት ለዉጥ ለሶሪያ ሕዝብም ለመላዉ አካባቢዉም ዉጤታማ ሊሆን አይችልም።»

ፑቲን መንግሥታቸዉን የሚያሰጋዉ የሶሪያዉ ፕሬዝዳንት የበሽር አል-አሰድ ሕልዉና ሳይሆን የሶሪያ እና የአካባቢዉ ሠላምና ደሕንነት ነዉ ማለታቸዉን አንዳድ የፖለቲካ ተንታኞች ሩሲያ ከቀድሞ አቋሟ የማፈግፈጓ ማረጋገጪያ አድርገዉ ተርጉመዉታል።


የድሕረ-ዚያድ ባሬዋን ሶማሊያ፣ የድሕረ ታሊባኗን አፍቃኒስታን፣ የድሕረ-ሳዳሟን ኢራቅ፣ የድሕረ ቃዛፊዋን ሊቢያን እልቂት፣ ፍጅት፣ ዉድመት ጥፋት ያየ-የሰማ ግን የሶሪያ የወደፊት እጣ አያሰጋዉም ማለት በርግጥ ጅልነት ነዉ።በእስካሁኑ ጦርነት ብቻ በትንሽ ግምት ከአርባ ሺሕ በላይ ሕዝብ አልቋል።ከመቶ ሺሕ በላይ ቆስሏል።ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጥ ተሰዷል።አራት ሚሊዮን ተፈናቅሏል።አማፂያን ዛሬ እንዳስታወቁት አንድ የመንግሥት የጦር አዉሮፕላን ጥለዋል።እና ጦርነቱ ቀጥሏል።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests