ይህን ያውቁ ኖሯል ?

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

አሚ

Postby ሳምሶን13 » Wed Feb 15, 2006 1:42 pm

Image
ሳምሶን13
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Wed Sep 15, 2004 3:48 pm
Location: sudan

Postby ማህቡብ » Thu Feb 23, 2006 8:52 am

***የካቲት 6 1984 እንደ ኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር በሞት የተለየው ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ አለም መዝገበ በጋዜጠኝነት ሞያው ሲሰራ ገና የ22 አመት ወጣት ነበር በዚህ ሞያው በራዲዮ ኢትዮጵያ,በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን,በጀርመን ድምጽ ራዲዮ እና በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የሎንዶን ዘጋቢ ሆኖ ሰርትዋል :: እንደገናም አለም መዝገበ ሎንዶን እየታተመ የሚወጣው ኒው አፍሪካ የተባለ መጽሄት ዋና አዘጋጅ በመሆን አለማቀፋዊ ጋዜጠኝነቱን ያረጋገጠ ታታሪ ሰራተኛ ነበር ::

አለም መዝገበ ለሰው ልጆች እኩልነትና ለፍትህ ሕይዎቱን የሰጠና የታገለም ጋዜጠኛ ነበር,በዚህም ምክኒያት የ1953ቱን የነጀኔራል መንግስቱ ንዋይን መፈንቅለ መንግስት ሙከራ በመደገፍ በጊዜው የነበረው ስራት አለቀ ደቀቀ ብሎ የነውጥ ትርጉሙ በማይታወቅበት በዚያ በጨለማ ዘመን በራዲዮ ለህዝብ ያበሰረ ቆራጥ ጋዜጠኛ ነው ::


ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ሚሚlove » Thu Feb 23, 2006 11:08 am

ውድ ማህበሩ ጥሩ ነገር ነው ያስነበብከን እስኪ አትጥፋ

* ቀንድ አውጣ ያለማቋረጥ ከ 3-4 አመት ማንቀላፋት ይችላል::
* ከሰው ከጦጣ ከዝንጀሮ በቀር ሌሎች እንስሳት ቀለማትን መለየት አይችሉም ሁሉም ቀለም ጥቁር ወይም ነጭ መስሎ ነው ይታያቸዋል
* በሰጎን እንቁላል አንዱ ቢጠበስ ለስምንት ሰው ቁርስ ይሆናል

አይገርምም እስኪ ሌላ ሳገኝ ብቅ እላለሁ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ቡናማ » Thu Feb 23, 2006 1:01 pm

ውድ ወዳጆች እንደምን ከረማችሁ?
ዩኔስኮ የኛን ሀገር ድንቁን ላሊበላ 8ኛው የአለም ድንቅ እንዳለው ታውቁ የለ?ለዛሬው ጥቂት በዚያ ረገድ ያሉ አንድምታዎችን ያጎላ የመሰለኝን ይዤ መጥቻለሁ::

Lalibela is a city in the Amhara ethnic division, or kilil, of Ethiopia. It lies within the former province of Wollo. It is located at 2,500 meters above sea level at 12.04* N 39.04* E and has a population of 8,484 according to the 1994 census. Lalibela is one of modern Ethiopia's holiest cities, second only to Aksum, and is a center of pilgrimage for much of the country. Unlike Aksum, the population of Lalibela is very nearly 100% Ethiopian Orthodox Christian.

This rural town is known around the world for its monolithic churches, which were built during the reign of Saint Lalibela (a member of the Zagwe Dynasty) who ruled the Ethiopia in the 13th century. There are 11 churches, assembled in three groups:

The Northern Group: Bete Medhane Alem, home to the Lalibela Cross and believed to be the largest monolithic church in the world, probably a copy of St Mary of Zion in Aksum. It is linked to Bete Maryam (possibly the oldest of the churches), Bete Golgotha (known for its arts and said to contain the tomb of King Lalibela), the Selassie Chapel and the Tomb of Adam.

The Western Group: Bete Giyorgis, said to be the most finely executed and best preserved church.

The Eastern Group: Bete Amanuel (possibly the former royal chapel), Bete Merkorios (which may be a former prison), Bete Abba Libanos and Bete Gabriel-Rufael (possibly a former royal palace), linked to a holy bakery.

Farther afield lie the monastery of Ashetan Maryam and Yimrehane Kristos church (possibly eleventh century, built in the Aksumite fashion but within a cave).

Contrary to certain spurious myths, the great rock-hewn churches of Lalibela were not built with the help of the Knights Templar; rather, they were produced solely by medieval Ethiopian civilization. (This is testified to by the presence of many architectural decorations and styles similar to those of the ancient Ethiopian capital city of Aksum.)

በወዳጅነት እንቀጥል
ቡናማ
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

Postby ማህቡብ » Sat Mar 04, 2006 3:51 pm

***የሠሜን ምስራቅ አፍሪካ ህዝቦች የተጻፈ ታሪክ ከዛሬ ወደ ኌላ እስከ ጥንቱ ፈርኦናዊው የግብጻዊያን ዘመን ድረስ ቢያንስ 4800 አመታት ይደርሳል :: በሰሜን የቀይ ባህር ወደብ ሱዋኪን ጀምሮ በደቡብ ምስራቅ በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ እስከ ጉአርዶፋይ ጫፍ ድረስ የሚገኘውን የአፍሪካ ቀንድ የጠረፍ ቀበሌ ጥንታዊው ግብጻዊያን በወል ስያሜ ''የፑንት የቅመማቅመምና ያአማልክት አገር , የአገሩን ህዝብ ደግሞ ''ሀበሻ'' ብለው ይጠሩት ነበር ::

በጥንቱ የግብጽ ስእላዊ ሃይሮግላፊክስ ጽሁፍና ታሪክ ታዋቂ ምሁር ፕሮፌሰር ጆን ዶሬስ እንደሚሉት በአፍሪካ ቀንድ ኢትዮጵያዊያንን በሚመለከት ''ሀበሻ'' የሚለው ስያሜ ታሪካዊ አመጣጡ ምናልባትም ከዚህ ከጥንቱ ፑንታዊያን ሥም ሊሆን ይችላል ::

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ቀበሌው » Sun Mar 05, 2006 4:54 pm

እናመሰግናለን ማህበቡ ቆንጆ አርዕስት ነው:
እስኪ እኔም ካነበብኩት አንድ ሁለት ልበላችሁ:-

ከእንሰሳት መካከል መካከል "ቁራ" ብቻ መራራ ስጋ እንዳለው ያውቃሉ:
አረንጛዴ ደም ያለው ነፍሳትስ እንዳለ ያውቃሉ?አወ ስሙን ለጊዜው ባላገኘውም የጉንዳን ዘር የሆነ ባለ ስድስት እግር ደሙ ከማናቸውም ፍጥረታት ልዩ ነው:

መልካም ጊዜ
that is good
ቀበሌው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 43
Joined: Mon Feb 09, 2004 4:29 pm
Location: ethiopia

Postby ማህቡብ » Sat Mar 18, 2006 9:39 am

***ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው:: እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 1880 አመተ ምህርት ከአፍሪካ ክፍለ አለም የሚበልጠው በአፍሪካዊያን እጅ ሆኖ,ገብቶ የሞከረው ከፍቶ ያየው አልነበረም ይሁንና ከ22 አመት በኌላ በ1920 አመተ ምህረት አምስት የአውሮፓ መንግስታትና አንድ ግለሰብ ከክፍለ አለሚቱ የሚበልጠውን ተከፋፍለው 30 ቅኝ ግዛቶችንና በአደራ የሚጠበቁ ሃገሮች 10 ሚሊዮን አጻፍ ምእራፍ ወረዳና 110 ሚሊዮን ግራ የተጋባ ህዝብ ተቀራምተዋል ::

አፍሪካን በቅኝ ገዥነት ለመቃረጥ የነበረውን ጥድፊያ እንግሊዛዊው የቅኝ ግዛቶች ጉዳይ ተመልካች ሚስተር ሎድ ደርቤ የዝበት,ጀርመናዊው መራሂ መንግስት ልኡል ቢስማርክ የቅኝ አገዛዝ አዙሪት ፈረንሳይው ጠቅላይ ሚኒስተር ጆርጅ ሰሪክ ከማያውቁት የሚያደርስ የመሰናክል ሩጫ ብለው እስኪቆላጩበት ነበር የአውሮፓን መንግስታት መሪዎችና የፖለቲካ አለቆች ፋታ የነሳቸው :: በዘመኑ ይነገድ የነበረው የባሪያ ንግድ ያስከተለውን ድቀት ይፋ ያወጣውና በ1873 ያረፈው የሚሲዮናዊው የዴቪድ ሊቨንግስተን ሞት ይመስላል የሽቅድምድሙ የቅርጫው መንስኤ ::

========ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

ቀጥልበት

Postby እሪኩም » Sun Mar 19, 2006 10:41 am

ቆንጆ ነው - ቀጥልበት

**********እሪኩም**********
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby ድራኮላ7 » Sun Mar 19, 2006 11:45 am

ሌሎቹ እንስሳት ቀለም እንደማይለዩ እንዴት ሊታወቅ ይችላል ? ወይስ በእነሱ አይን አይተውት ነው ቅቅቅቅቅቅ
ድራኮላ7
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 116
Joined: Wed May 25, 2005 10:19 pm
Location: ethiopia

Postby ማህቡብ » Mon Mar 20, 2006 6:20 am

የቀጠለ......
ሊቪንግስተን አለምና የአለም ህብረተሰብ በንግድ በክርስትና ትምህርትና በስልጣኔ አፍሪካን ይዋጅ ዘንድ ያቀረበው አቤቱታ ሰለጠነ የሚባለውን አለም ህሊና ለመጎነጥ የታሰበ ሳይሆን አልቀረም :: ከሆነ በየምክኒያቱ መጣጣም የተሳናቸው አውሮፓዊያን ቅኝ ገዥዎች ነበሩ ሊቪንግስተን ላቀረበው አቤቱታ መልስ የሰጡት ሄንሪስታሊንን የመሳሰሉ ጋዜጠኞች, ፒየድ ብራዛን የመሳሰሉ ባህር ገማሾች,ፍሬድሪድ ለጋድን የመሳሰሉ ወታደሮች,ካርስፔተርሰን የመሳሰሉ መምህራን,ሲስል ሮድሰን የመሰሉ ወርቅና አልማዝ አዳኞች ነበሩ ስምሪት የወጡት:: በየደኑ በየጨቀጨቁና በየበረሃው አዲስ ግዛት,አዲስ መንግስት መቆርቆሩ ከወጭ በስተቀር የረባ የማይገኝበት የመሰላቸው የአውሮፓ መንግስታት ወደ መጀመሪያው ላይ የእሽቅድምድም ቅርጫውን እንደዘበት ለማየት ሞክረው ነበረ::

ዘመኑ ምጣኔ ሃብቱ አይሆኑ የሆነበት ከእጅ ወደ አፍ እንክዋን ማለት ያዳገተበት ከመሆኑ የተነሳ ጨለማው አለም ትባል የነበረችው አፍሪካ ተዝቆ የማያልቅ ሃብት ግምጃ ቤት መሆንዋን ልብ አላሉትም :: ያም ሆኖ ቅኝ ገዥነት የመሰየም ትኩሳት ተገብ ያገዘው ሰደድ እሳት ያህል መላ አውሮፓን ሲገልብና በሳቢያው ቅኝ ገዥ መሆኑ ብሄራዊ ኩራት ሲያመጣ ውሎ አላደረም :: አፍሪካንና ሌሎችንም በቅኝ ገዥነት ለመቃረጥ የተጀመረው አሽቅድምድም እያደር በጋመ ሚሲዮናዊው ዴቪድ ሊቪንግስተን ያለም መንግስታት በንግድ በክርስትናና በስልጣኔ አፍሪካን ይዋጁ ዘንድ ያቀረበው አቤቱታ በጉልበት ጭምር ድል አድርጎ መያዝን ጋሻ ጃግሬ አስከትሎ የነበረውን ፍልስፍና ለውጦታል ::

የዘመኑ መለያ ምልክት ውሃ መትረየስ እንጅ የክርስትና ትምርትና ስልጣኔ አልነበረም በዚህ ሁሉ መሃል ነበር ወደ መነሻችን ላይ አንድ ግለሰብ ብለን ያለፍነው የበልጅጉን ንጉስ ዳግማዊ ሊዎፖልድ የአውሮፓን መንግስታት አይንና ናጫ መሆን መሳሪያ አድርጎ ኮንጎን የግል ንብረቱ ያደረገው ::

========ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Sun Mar 26, 2006 9:35 am

የቀጠለ.....
ብዙ እርቀን ሳንሄድ የዛሬ ዘጠና አመት ሊዎ ፖልድ ዳግማዊ ወደ ኮንጎ የላካቸው እንደራሴዎች 10 ሚሊዮን አፍሪካዊ ነው የፈጁት :: በሠው ቁስል እንጨት ስደድበት አይነት ያልቆረቆረው ጆሮ ዳባ ሲለው,ያደረና ያጎበደደ ንጉሱና እንደራሴዎቹ የሰሩትን ግፍ የፈጸሙትንም በደል በተቻለው ሁሉ ለመደባበቅ ብዙ ነው የጣረው :: ታሪኩ የስስት የምዝብርና የጭካኔ ታሪክ መሆኑን መደበቅ አልተቻለም,እርድጥ ዩኤስ አሜሪካ ብሪታኒያና ሌሎችም የአውሮፓ መንግስታት ንጉስ ሊዩ ፖናልድና ጋሻ ጃግሬዎቹ በ1900 እና 1908 መካከል ኮንጎ ውስጥ የሰሩትን ግፍ አጥላልተው ንቀውታል :: ይሁንና እነዚህ ዳግማዊ ሊዮፖልድን በማብጠልጠል ላይ የነበሩት መንግስታት እልፍ ብለው እዚያው አፍሪካ ውስጥ በየ ሀገሩ ተመሳሳይ በደል የበደሉ ያላነሰም ግፍ የፈጸሙም መሆናቸው ነው ክፋቱ:: ከኮንጎ ወንዝ በስተ መራብና በስተሰሜን የሚገኙትን ሀገሮች የያዘችው ፈረንሳይ,አንጎላን የገዛችው ፖርቱጋልና ካሜሮንን የጨመደደችው በየነበሩበት አንጡራ የሃገሪቱን ሃብት ወስደው ጉልበቱን በዝብዘው ባኮርባጅ ገርፈው ሴቶቻቸውንም ደፍረው ቁም ስቃይ ነው ያበሉት:: ሃገር ምድሩን መቀማቱን ያስመረረውና ሄረሮ እየተባለ የሚጠራው የደቡብ ምእራብ አፍሪካ የዛሬይቱ ናሚቢያ ህዝብ በ1904 አመተ ምህረት አምጾ ቢነሳ ቅኝ ገዥይቱ ጀርመን ዘር ማንዘር የሚመነጥር ሠራዊት አዝምታበት ከ800 ሽህ ሄረሮ መካከል 20 ሽህ ብቻ ነው የተረፈው ::

19ነኛውን መእተ አመት ሊሰናበት ደጅ መጥናት ከያዘው ከ20ኛው መቶ ክፍለዘመን የሚለየው ድንበር ክልል ወሰን አለ ቢባል,ድንበር ክልል ወሰኑ በመጀመሪያው የአለም ጦርነት የዘመተው ወታደር መከላከያ ይሆነው ዘንድ የቀደደውን ቦይ,የመድፍ ጥይት የቆፈረውን ጉድጉዋድ ፈሰስ ይዞ ነው የሚወርደው :: ይሁንና ጊዜ ባሼለበና ዘመንም ባለፈ ቁጥር እንዳውሮፓ ዳር ድንበር ሁሉ ያም ላይነስጋ ቀርቶ ላይነህሊና እንኩዋ መሰወር ይዝዋል :: ደም እንደ ጎርፍ የፈሰሰባቸው አጥንት እንደ ዱቄት የተከሰከሰባቸው አካባቢዎች ዛሬ ሳር ቁጥቁዋጦ ዛፍና ለምለም ለብሰው,የሠው ልጅ እንደ ጭድ ከብት የታረደባቸው አይመስሉም:: የፍራንደርስ አሮንቃና ምስራቁ የፈረንሳይ ክፍል እንደተራበ ዘንዶ ፍንዳውን ጊዜ የትላንቱን ወርቅ አለም የሰለቀጠው እለት ነበረ :: የሠው ልጅ በሁለት እግሩ ቆሞ መሄድ ከጀመረ አንስቶ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ እግዚኦ ያሰኘ የድቀትና የጥርስ ማፍዋጨት ዘመን ነው የተወለደው :: ከእቶን እሳት የከፋ የጦር መሳሪያ የብሄር ብሄረሰቦች ጥላቻ የፋሽስቶች, እንቅስቃሴ,የኮምኒስቶች አብዮት የ20ኛው ምእተ አመት መቅሰፍት ከመጀመሪያው የአለም ጦርነት ምናልባት በጦርነቱ አስባብ እንደ ሠደድ እሳት ነው የተዛመተው ::

============ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ARERU » Mon Mar 27, 2006 1:47 am

ሰላም አምዱ ስለሳበኝ ገባ አልኩ::
1. በአለም ላይ በባልና ሚስት ፍች በአንደኛ ደረጃነት የሚጠሩት ሶማሌወች ናቸው
2. ብቸኛዋና እረጅም እድሜ እራስዋን በራስዋ የገዛች ሀገር ማን እንደሆነች ያቃሉ ኢትዮጵያ ናት::
ለዛሬ ይሄን ስተት ካለ ይታረምልኝ ሌላውን በሌላ ጊዜ
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

Postby ሚሚlove » Tue Mar 28, 2006 6:05 am

ሰላም ቤቶች እስኪ እኔም አንድ ልበል . . . . .

* በሰው እጅግ የተገደሉት የቀድሞው የእስራኤል ጠ/ሚኒስተር ራቢን የለየላቸው አጫሽ ነበሩ:: ራቢን በቀን በአማካይ 60 ያህል ሲጋራዎችን ያጨሱ እንደነበር ይነገራል::

* የቀድሞው የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን ሳክስፎን የሚጫወቱ ብቸኛው ፕሬዘዳንት ናቸው:: በተጨማሪም በስልጣን ዘመናቸው በግቢያቸው ውስጥ በርካት ሴቶችን በመስየም ክሊንተንን የሚስተካከላቸው አልተገኘም::

አክባሪያችሁ
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ማህቡብ » Wed Mar 29, 2006 7:16 am

የቀጠለ......
ትክ ብሎ ላየው ቆም ብሎ ላጤነው ረቂቅ ሚስጥረ ስውር ከሚባለው ኪነት እስከ ሴቶች መብትና ነጻነት ከዩኤስ አሜሪካ ሀያል መንግስት ለመቆነጥ ቃት እስከ ቅኝ ግዛቶች ሃርነት ፍለጋ መነሳት ያለፉት መቶ አመታት መለያ ምልክት ነው ማለት ይቻላል :: አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ዎልተር እንፕመን እናት ሃገሩ ዩኤስ አሜሪካ ለመጀመሪያው የአለም ጦርነት በዘመተች በሳምንቱ እንደአውሮፓዊያኑ ዘመን አቆጣጠር ሚያዝያ 1917 አመተ ምህረት መሆኑ ነው እንደታዘበው የወደፊት ኑሮዋችን በአብዮትና በአብዮተኞች አለም ነው የሚሆነው :: የዛሬ ሁለት አመት ያለፈው ፈረንሳዊው የታሪክ ሰው ፍራንስዋ ፉሬ እንዳለው የትላንቱ አለም የሚባልበት እምብዛም እሩቅ አይደለም ጊዜና ዘመኑ እርቆ ደብዛው የወቅት ትቢያ የሆነው የዛሬው ትውልድ ትርጉም ያጣለት መሆኑ ነው ትልቁ ችግር::

19ኛው ምዕተ አመት ማብቂያ አካባቢ ድረስ ለነበረው ክፍለ ዘመን ሠላምና ጸጥታ መረጋጋትና ብልጽግና ዋቢ የነበረው አሮጌ ትውልድና አሮጌው ሥርአት 267 አመት ተተክሎ የኖረውን የቻይና ማንቹ ሥርዎ መንግስት በሱንያግሳን መሪነት የተነሳው ኮሚታንግ ከነቀለ ከ1911 አመተ ምህረት ወዲህ መቅኖ አላገኘም :: የቻይናው ማንቹ ሥርዎ መንግስት በፈረሰ ባመቱ ነበር ቱርክን ከደቡብ ምስራቅ አውሮፓ የመነገለውና ከ1300 አመት ጀምሮ አንሰራፍቶ የኖርው የኦቶማን ንገሰ ነገስት መንግስት እንኩቶ የሚሆንበት ዘመን መቃረቡን ታበሰረው :: በ19ኛው ምዕተ አመት የታየው የኢንዱስትሪ እድገትና የጥበቡም መሰልጠን ተጥሎበት የነበረው ጽኑ እምነትም ሆነ መልካም ተምኔት ለምንም አትበገር ትመስል የነበረችው መርከብ ታይታኒክ በድንግል ጉዞዋ እንደነበረች ከበረዶ ጎራ ጋር ተላትማ ካሳፈረቻቸው መንገደኞች መካከል 1513ቱ በ1912 አመተ ምህረት ህይዎቱን ያጣ ለት ነበር ጉድፍ የጣለበት :: ይሁንና ይህ ሁሉ በ1914 አመተምህረት በኖጋውና የጦርነቶች ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል ተብሎ ከታሰበው ከመጀመሪያው የአለም ጦርነት የሚነጻጸር አብሮም ሚዛን የሚመዝን አልሆነም ::

የኦስትሪያ መስፍን የፍራንስ ሳርግዳንድ ሰራይቮ ላይ በሰው እጅ ህይዎቱን ማጣት መዘዝ ማስከተሉና በሳቢያውም በየአቅጣጫው የጦርነት አዋጅ መታወጁ በዘመኑ የነበሩት ነገስታትና መሳፍንት የስልጣኑ አደላደልና የጦር ሃይሉ ሚዛን የተልባ ስፍር የሚሆንበት ወቅት ቀኑ መድረሱን አብስሮ ነው ያለፈው :: ተስፋ ትጽቢቱ አልያዘ አልሰመረም እንጅ ያችን ቀን በሳቅ በፈገግታ ወዳጅ ጉዋደኛውን, እህት ወንድሙን, እናት አባቱን, ሚስቱንና የከንፈር ወዳጁን ተሰናብቶ ለዘመቻው የወጣው ወታደር ገድሎና ተጋድሎ ወድቆና ተዋድቆ ለአውሮፓዊያኑ ባህል ልደት ተመልሶ ቤቤቱ የሚውል መስሎት ነበረ ::

=========ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ሚሚlove » Thu Mar 30, 2006 4:23 pm

ማህቡብ ቀጥልበት ጥሩ ነገር ነው እያስነበብከን ያለህው::
እኔም ያነበብኩትን እንዲህ አቅርቤዋለሁ::

* የነብር ቁርበት ከበርት ቢሰቀል ፍየ.ሎች ይፈገደጋሉ:: ብርቱም ንጉስ በተነሳ ጊዜ መናፍቃን ይታወካሉ:: የጎመን ዘር ቢዘሩት ሰናፍጭ አይሆንም:: ሰውንም አንት ባርያ ብለው ቢሰድቡት ያዳም ልጅ ሙሆኑን አይተውም::

* ፍቅር ቢያረጅ ቅርፊት ይሆናል:: ወይም ይይዛል:; ምነው ቢሉ ተቀርፎ ቢእውድቅ ከመልካም ከታላቅ ወንዝ ከለመለመ ብትደርስ ተጠንቀቅ ከዚያ የሚመጣው ብዙ ነውና::

* መልካም ቆንጆ አመንዝራ ሴት ካለችበት ቤት አትግባ በከንቱ እንዳትሞት::

(ከዘነበ ኢትዮጵያ መፅሀፍ ጨዋታ 1995)
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests