ይህን ያውቁ ኖሯል ?

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ኤዲ » Thu Mar 30, 2006 10:17 pm

ጥሩና አስተማሪ መድረክ በመክፈትህ እያመሰገንኩ ለዛሬ:

- ማንኛውም size ያለውን ወረቀት እኩል ቢያጥፉት ከ8 ጊዜ በላይ ለማጠፍ አይቻልም
- በአለም ላይ ትልቁ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሚገኘው በቫቲካን ሳይሆን በአፍሪካ በኮትዲቯር ያሞሱክሮ ከተማ እንደሆነ ያውቃሉ
- ከአዛርባይጃን እና አፍጋኒስታን በስተቀር የተቀሩት ስማቸው በ A የሚጀምሩ ነጻ አገሮች የመጨረሻ ፊደላቸው A እንደሆነ አስተውለዋል
- 7ቱ አህጉራት በእንግሊዝኛ ሲጻፉ የመጃመሪያና የመጨረሻ ፊደላቸው ተመሳሳይ ነው
ኤዲ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Sat Feb 07, 2004 7:22 am

Postby ሚሚlove » Sat Apr 01, 2006 2:44 pm

ማህቡብ ጥሩ ነገር ነው እያስነበብከን ያለህው እና ቀጥልበት

እስኪ ካነበብኩት ጀባ ልበላችሁ . . . .

* ላምና በግ ጠጉርና ቁርበት ለብሶ ከመርኖሩሽማና ግምጃ ከለበሰው ውስጥ ገብተው በቅቤና በጨው ታፍኖ መኖር አይሻላቸውምን:: ዶሮስ ይህ ኮስኳሳ ሽቀናም ጠጉር ምን ይሆናታል ድልህና ቅቤ አጥግቤ በሞቀ ውሀ አጥቤ ከሚሞቀው ቦታ ብከታት አይሻላትምን::


* አሳስ በውሀ ውስጥ መኖሩ ምን እጠቀም ብሎ ነው እንደኔስ ቢሆን ከብርድ ስፍራ መኖር እጅግ ያሳዝነኛልና አጥቤ እንዲሞቀው ከእሳት ዳር ባደርኩት ነበር:; በወደደው ልክ ጨውና ቅባት ኑግም አጠግበው ነበር::

መልካም ምሽት ይሁንላችሁ ቀንም ለሆነ እንዲሁ መልካም ቀን ይሁንላችሁ::
ሚሚlove
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
Location: Ethiopia

Postby ቁም ነገር2 » Sat Apr 01, 2006 3:02 pm

ኤዲ wrote:ጥሩና አስተማሪ መድረክ በመክፈትህ እያመሰገንኩ ለዛሬ:
- 7ቱ አህጉራት በእንግሊዝኛ ሲጻፉ የመጃመሪያና የመጨረሻ ፊደላቸው ተመሳሳይ ነው


Africa
Asia
N. America
S.America
Austrialia
Antartica
Europe
respect yourself and others will respect you
ቁም ነገር2
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 451
Joined: Wed Sep 07, 2005 7:24 am
Location: ethiopia

Postby manche » Sun Apr 02, 2006 12:15 am

ማህቡብ ምስጋናዬን ከመቀመጫዬ ብደግ ብዬ ለማድረስ እወዳለሁ....እስቲ ለዛሬ ስለ አፕሪል ፉል ያገኘሁትን ላካፍል::
t is widely proclaimed that April Fool's day originated in France in 1562, or thereabouts, when Pope Gregory replaced the Julian calender with the Gregorian calender in the Julian calender month of April. The day of introduction of the Gregorian calender was made the first day of January. Some people hadn't heard about the change in the date, so they continued to celebrate the New Year's Day, but it being 1st April. So, others called them "April fools." The fact is that Pope Gregory XIII ordered Thursday 4 October 1582 to be the last day of the Julian calendar. The next day was Friday 15 October. April Fool's Day is an April Fool's tale.
manche
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 98
Joined: Tue Nov 04, 2003 4:52 pm

Postby ማህቡብ » Sun Apr 02, 2006 9:57 am

የቀጠለ.......
ከ1914 አመተ ምህረት የሰለጠነው ምጣኔ ሃብት ቴክኖሎጅ ያፈራው መርዝ ጋዝ ታንክ,እሳት የሚተፋ መሳሪያና እንደዘመኑም አጠራር ውሃ መትረየስ ነው ጦርነቱን የተዋጋው :: በጦር ግንባር የዋለ አንድ ፈረንሳዊ ወታደር በዘመተ ባመቱ ለቤተሰቡ በጻፈው ደብዳቤ እንዳመለከተው,ውጊያው ወታደር ከወታደር ሳይሆን ወታደር ከመሳሪያ ነበር :: ጠላትን ማጥፋት እንደዚህ ወታደር ትዝብት የመርዝ ጋዝ ሩምታ ጥቂት መትረየስ ነበር ያስፈለገው በዚህ ወቅት አካባቢ ነበር የኌላ ኌላ የጦርነቱን ሂደት እና ባህሪ የለወጡት አውሮፕላኖች ብቅ ያሉት ጦርነት,ውጊያ,ፍጅቱ እስካበቃ 10 ሚሊዮን ሠራዊት ነበር ያለቀው :: በ1870 እና በ1871 መካከል በዘመተው በፍራንኮ ፕሮሲያ ጦርነት150 ሽህ ሠው ብቻ ያለቀባት አውሮፓ ጉድዋ ወደ ኌላው ላይ ሊጠና ያን ያህል ሬሳ ስታነሳ የመጀመሪያዋ ነበር :: እልቂት ፍጅቱ ጉልበታቸውን ያዳከማቸው መንግስታት ቅሬታ ያደረበት ህዝባቸው መሪዎቹና አለቆቹ በየጦር ግንባሩ በመዋደቅ ላይ እንዳሉ ክንድ እንዲያነሳባቸው ገፋፍተዋል ::

በሠሜን አየርላንድ ሪፐብሊካኑ ወገን በ1916 አመተ ምህረት በአውሮፓዊያኑ ባአል ስቅለት ሰሞን በብሪታኒያ ላይ ክንዱን ሲያነሳ የጠበቀው አልነበረም,የመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ህዝብ ሎረንሶፍ አረቢያ ይባል በነበረው እንግሊዛዊ ሰላይ አማካኝነት ተባብሮ በቱርክ መንግስት ስልጣን ላይ ሲነሳ የሰሜን አየርላንድሪፐብሊካዊያን ብሪታኒያ በምትመራው መስተዳድር ላይ የወሰዱት እርምጃ አስተጋብኦቱ አስገምግሞ አላለፈም ነበር :: የሩሲያ ዛርኒኮላስ ዳግማዊ በወርሃ ህዳር 1917 አመተ ምህረት በገዛ ፈቃዱ ከዙፋን በወረደ በጥቂት ወራት ውስጥ ሌኒን አጅቦ የተነሳው ቦልሽቢክ የሥልጣን እርካብ ተቆናጠጦ የአለምን የፖለቲካ ሂደት መልክና ባህሪ የተለየ መንገድ አስይዞታል ::

===========ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Sun Apr 09, 2006 7:37 am

የቀጠለ....
የደራ የኮራ ዘመንዋ በዘመነ ለውጥ ሰይፍ አንገቱን እስከተቀላ መላው አለምን ላቢዮትና ላቢዮተኛነት ታስብ ታስተምር የነበረችውም ሶቭየት ህብረት ሪዮቱንና ፕርፓጋንዳውን ገና አንገቱን ማቅናት በጀመረው መገናኛ ብዙሀን አማካኝነት የለየለት መሳሪያ አድርጋዋለች:: የሶቭየት ህብረት አጉራ ዘልለነት መሰየም ጥሮ ግሮ በግንባሩ ወዝ የሚተዳደረውን ሰፊውን ህዝብ አርቃና እረግጣ ያስተዳደረችበት ስርአት የምእተ አመቱ መለያ ባህሪ ሊሆን የበቃውን ኮምኒስት ፋሽስት ወታደራዊ ወግ ነው የቀፈቀፈው :: የጥቅምቱ አቢዮት እንግሊዛዊው ታሪክ ተመራማሪ ኤሪክ ሆብስቦም እንደታዘበው ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ አሳምሮ የተደራጀ እንቅስቃሴ ነው የወለደው ሆብሶምም አክሎ እንዳለው ከእስልምናው ሀይማኖት መስፋፋት ወዲህ የኮምኒስቱን የመሰለ ሰደድ አልታየም :: በምእተ አመቱ አጋማሽ ከመላው አለም ህዝብ መካከል ሲሶው በኮምኒስቱ ስርአት ሥር ነበር ያም ሆኖ ሶቭየት ህብረት ገና ጥላ ያላጠላችበትንና እስከዚያም ድረስ በቁጥጥርዋ ሥር ያላደረገችውን የአውሮፓ ክፍል ለመያዝ አብዝታ ነበር የሻቀረችው ስጋት,ጭንቀት,ፍርሃትና ምን ይበጅ ::

ከ1945 አመተ ምህረት ወዲህ ሶቭየት ህብረትን መፎካከር በየአጋጣሚው መሻኮት ብቻ ሳይሆን እላፊ እንዳትሄድ አርቃ የያዘችው ዩኤስ አሜሪካ ጉድ ከታየበት 1917 አመተ ምህረት ጀምራ የአለምን ፖለቲካ መድረክ እንደናኘችበት መሆንዋ አሌ አይባልም :: ጀርመናዊው ታሪክ ተመራማሪ ኤቨርሃትየክም እንዳየው በሩሲያ ጣቢያዎችና በዩኤስ አሜሪካም የጦርነቱ ተካፋይ መሆን አስባብ ነበር በምእተ አመቱ አጋማሽ ገደማ መላውን አለም መቆራቆሻ ሜዳቸው ለማድረግ የበቁት የሁለቱ ሃያላን መንግስታት ኮከብ የበረቀው ::

========ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Apr 11, 2006 6:00 am

የቀጠለ.......
የዩኤስ አሜሪካ በመጀመሪያው የአለም ጦርነት መዝመት ለድል ያበቃ የጦር መሳሪያ ከማከሉም በላይ የአውሮፓ መንግስታት ሰራዊት እንዲጎለብትና ዲፕሎማሲውም ሞራለ ቢስ እንዳይሆን በጅትዋል :: ያም ነው ዛሬም ጭምር የምናየው የዩኤስ አሜሪካ የውጭ ፖለቲካ መርሆ,ዩኤስ አሜሪካ ጦርነቱ እስከተዘመተ ድረስ በ1912 አመተምህረት እንዳደረገችው ህግና ሥርአት ይከበር ዘንድ ባህር ሃይልዋን
ወደ ኒካራግዋ ከመላክ ያም በሆነ በሁለተኛው አለም እንደታየው የፓናማን ቦይ ከመክፈት በስተቀር ከጉዋሮዋ እርቃ አታውቅም :: 1917 ያን ያን እንዳየ ሁሉ ብሪታኒያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርዋ በአርሰር ጆ ቦልፈር ሥም ቦልፈር ዲክሌሬሽን ብላ በጠራችው አዋጅ አማካኝነት አይሁዳዊያን በምድረ ፈልስጤም ሃገር እንዲኖራቸው ለማድረግ ቃል ስትገባም ታዝብዋል ::

===== ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Apr 11, 2006 6:10 am

የቀጠለ........
እርግጥ ሃገረ እስራኤል ሁለተኛው የአለም ጦርነት ተዘምቶ እስካበቃና 6ሚሊዮን ይሁዳዊ የእሳት እራት ሆኖ እስከተሰዋ እስከ 1948 አልተወለደችም ነበር የመጀመሪያው የአለም ጦርነት የጦርነቶች ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል ተብሎ የታሰበው ታላቁ ጦርነት በወርሃ ህዳር 1918 ሲያከትም የነበረው ማእከላዊ ሃይል ነባሩ ሥልጣን የእንቡዋይ ካብ ሆኖ ሽብር ብጥብጥ ሥርአት አልባነት እንቅልቅብ አቢዮት ነው በየሃገሩ እንደ እንጉዳይ የፈላው::

የኦቶማን ዘውደ መንግስት የነበረው የአረብ ምድር ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ ተቀራመቱት በሃብስበርግ መስተዳድር ሥር የኦስትሪያ,የቡልጋሪያ,የችኮዝሎቫኪያ,
የፖላንድ የዩጎዝላቪያ ህዝብ ነጻነቱን ፍለጋ እንደየመልክአ ምድሩ አቀማመጥና እንደየባህሉም አወቃቀር ተሰበጣጥርዋል ::

=======ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Apr 11, 2006 6:27 am

የቀጠለ.......
እድሜ አላገኙም እንጅ አብዮተኞች ባዛሪያ ከምትባለው የጀርመን ክፍለሐገር ውስጥ የሶቭየትን የመሰለ ሪፖብሊክ ለመቆርቆር ሞክረው ነበር:: ንጉስ ቢልሀልም ዳግማዊ የገጠመ ገጥሞት ዙፋኑን ሲለቅ ጀርመን የተኩስ ማቆሚያ ስምምነት ተፈራርማ ህዳር 11 ቀን መድፍና መትረየስ ልሳኑ ተዘጋ የመጀመሪያው የአለም ጦርነትም ተዛመ ::

========ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Apr 11, 2006 6:36 am

የቀጠለ.......
ለሌሎች ይገዛ የነበረ ህዝብ ለነጻነቱ ትግል እንዲነሳ የገፋፉት አሜሪካዊው ፕሬዝዳንት ሉድሮ ዊልሶን በወርሃ ነሃሴ 1919 በርሳይ ላይ ለተፈረመው ውል ያበቃውን ድርድር ምሰሶ ማገርና ትት ነበር ያበቁት,ይሁንና ተጉዋዳኝ መንግስታት ሩሲያ,ኢጣሊያ,ፈረንሳይ,በልጅግ,ጃፓንና ብሪታኒያ በርሳይ ላይ የተፈራረሙት ውል ሃጢያት በደሉን ሁሉ በጀርመን ላይ የከመረው ልክ የሌለው የደም ዋጋ የጠየቀ ከመሆኑ የተነሳ ነገር በማለዘብ ፈንታ ጀርመናዊውን የባሰ አቆላጭቶና ጥርስ አስነክሶ በመጀመሪያው የአለም ጦርነት የዘመተውን ሃምሳ አለቃ አዶልፍ ሂትለር ለበቀል እንዲነሳ ምክኒያት ነው የሆነው ::

======ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

የቀጠለ......

Postby ማህቡብ » Wed Apr 12, 2006 5:47 pm

የቀጠለ........
ለቁም ነገር አልበቃም እንጅ የህዝብና የሃገረ ድሪቶ እንዲደረቱ መንገድ የጠረገው መልክና ባህሪ ያስያዘው የብሄር ብሄረሰቦች መከፋፈል ከጉያ የገባ ሰው የሆነባቸው ክፍላተ ሀገር በመንግስትነት እንዲመሰረቱ ፈር የቀደደው የአለም መንግስታት ማህበር በርሳይድ ላይ የተደረገው ውል ውጤት ነበር ማለት ይቻላል :: የኌላ ኌላ 1990ዎቹ አመታት የክሮሽያ የቦስኒያና የኮሶፎን አልባኒያ ዝርያ አናክሶ በሚያጣባ አጉል ብሄራዊ ስሜት ከሴርቢያ ጋር አባልትዋቸዋል, ሌላው ቀርቶ በርሳይድ ላይ የታደሙት የመንግስታት መሪዎች እንክዋ እርቀ ሰላም ይወርድ ዘንድ የቆነጠቡት ውል እስከናካቴው ጀርመን ሊለቅ መቻሉን በሙሉ ልብ የተቀበሉት መሆናቸው ሲበዛ ነበር ያጠራጠረው :: ቢሆን ኖሮ ከ20 አመት በኌላ ሃገር ምድር ያረሰው ሁለተኛው የአለም ጦርነት ውስጥ ውስጡን ሲንተከተክ እንደኖረ እሳተ ጎመር ባልኖጋ ነበር ::

=======ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Thu Apr 13, 2006 6:08 am

የቀጠለ.........
ውነት ታሪክ ሆኖ ለነበር ቦታ ሲለቅ በነበር ሊዘከር ብቻ ሳይሆን ባለ ሊወሳ,በይመጣል ሊነሳ ነው የጊዜ ኡደት ሂደት በመሆኑ አዲስ ለምንለው መጭውን አመላክቶ ነው የሚሄደው እንደሰማነው በምእተ አመቱ የመጀመሪያ አስርት የተደረገና የሆነው እንደተጠቀሰው ሆኖ,የቀረውን የታሪክ አሻራ ደግሞ እንደሚከተለው ይታያል :: ''ከዘመናችን ዘመን ከጊዜያችን ጊዜ ከወቅታችን ወቅት '' ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው....... 19ኛው ምእተ አመት ሲብት የእንግሊዝ ንጉሰ ነገስት ግዛት ድንበር ክልሉ ሥር ጥምጥሙ ውል እስከዚህ የሚባል አልነበረም እንዲያውም ጸሃይ ይጥለቅበት ይባል የነበረው የእንግሊዝ ንጉሰ ነገስት መንግስት አንድ ልብ,አንድ እራስ,አንድ ቁዋንቁዋ,አንድ የፖለቲካ መርህ ነበረው ነው የሚባለው ሳንክቢምርበርት በታዘበው እንደሚለው 19ኛው ምእተ አመት ከመባቱ ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አፈንግጦ በንግስት ቪክቶሪያ መንግስት ላይ የተነሳውና ቦር በሚል ሥም መጠሪያ የሚታወቀው ደች ባላገር የቀሰቀሰው አመጽ ነበር ያም ሆኖ ድል የመንግስት ቀኙ ለንግስቲቱ የሚውል መሆኑን የተጠራጠረ አልነበረም::

=========ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Mon Apr 17, 2006 6:09 am

የቀጠለ........
ይሁንና የትራንስባልና የኦሬንጅ ፍሪ ስቴት እስከተያዙ ድረስ የድል ፍንጭ ያልታየ መሆኑ ነበር ክፋቱ,እንዲያውም መላልሶ ጥቃት የደረሰበት የብሪታኒያ ጦር ሙሉ ድል እስካየ ድረስ ሁለት አመት ከሰባት ወር መዋደቅ ግድ ነበረበት :: ከኔዘርላንድ የፈለሰውና ቦር የሚል ሥም መጠሪያ የወጣለት የደች ዝርያ እጁን እስከሰጠ ድረስ የጀርመን መንግስት ድጋፍ አይለየኝም የሚል እምነት ነበረው ሆኖም መሪው ፓን ክሩገር እርዳታ ፍለጋ ጀርመንን በጎበኘበት የዘመኑ የጀርመን ንጉስ ተቀብሎ ማስተናገድ ቀርቶ ሊያነጋግረው እንኩዋን አልፈቀደም ከዚህም የተነሳ ነበር በንግስት ቪክቶሪያ መንግስት አምጾ የተነሳው ቦር ህዝብ እና መሪዎቹ ብሪታኒያ ባለችውና በፈለገችው አይነት ተስማምተው እጅ መስጠት ግድ የሆነባቸው :: ጦርነትና ፖለቲካ የቅርብና የሩቅ ጎረቤት በማናከስ ደም በማቃባት ላይ ሳለ ነበር አሜሪካዊው ኦልቢር ራይት ከስም ከሰሜን ካርላይና ፌደራል ግዛት ከአሼዋ ኮረብታ ተወንጭፎ ለ12 ሴኮንድ በአየር የሰፈፈው ለዚያች 12 ሴከንድ ኦልቢርና ወንድሙ የአራት አመት ምንድስና በብዙ ሽህ የሚቆጠር ቁጭ ብድግ እምርታና እንጣጥ ሞክረዋል ኤሬሽን ኤራ ተብሎ ለሚታወቀው አውደ ዘመን አዲስ ምእራፍ የከፈተው ከሼራና ከመቃ የተዋደደ አውላንዶ በአየር ያሰፈፈው ምንድስናቸው ሙከራ ጥረታቸውን ከዚያን ወዲህ በየጊዜው የተዘመተውን ጦርነት መልክና ባህሪውን ለውጦ ሠማይ ሃዋውን ወለል አድርጎ ነው የከፈተው :: የሁለቱ ወንድማማቾች አነሳስ አስተሳሰብ የተውት ንድፍና ሥዕላ ሥእል ዛሬም ጭምር እንዳመራመረ እንዳፈላሰፈ አለ ::

==========ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby የዘመኑ አፄ » Mon Apr 17, 2006 4:32 pm

ማህቡብ መቼም ለምታበረክተው አስተዋፆ ከፍ ያለ ምስጋና ነው የመቀርበው:: በጣም ጥሩ ስራ ነው እየሰራህ ያለህው::

የምታቀርባቸው ፅሁፎችም በጣም ጠቃሚ ስለሁን ምናልባት የአማርኛው ዊኪፒድያ ላይ ብትሳተፍ መልካም ይመስለኛል:: የአማርኛው ዊኪፒድያ በጣም ጠቃሚ የዕውቅት ምንጭ ሲሆን በአሁን ሰዐት ግን ከፍ ያለ ተሳትፎ ያስፈልገዋል::

ሁሉም ያቅሙን ቢተባበር ከፍ ያል ደረጃ መድረስ ይቻላል::
http://am.wikipedia.org
url=http://www.usersigs.com]Image[/url]
የዘመኑ አፄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 204
Joined: Wed Jan 19, 2005 3:40 pm
Location: fiji

Postby ማህቡብ » Wed Apr 19, 2006 6:31 am

የቀጠለ........
በመጀመሪያዎቹ አስር የ20ኛው መቶ ክለ ዘመን ከገበሬ ቤተሰብ አብራክ የሚከፈለው ሄነሪፉድ አውቶሞቢል ሰርትዋል እንግሊዞች ምካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ተዝቆ የማያልቅ የነዳጅ ምንጭ አግኝተዋል :: ዜግሞንድ ፍሮይድና አልበርታይንሽታይን እንደቅደም ተከታላቸው ሳይኮሎጅ እንበል የሥነ-ልቦናና የፊዚክስ ምርምር ፍልስፍናቸውን መልክና ቅርጽ አስይዘውታል :: ኦልቪልራይት ለእምርት ያህል እድሜ በአየር ሲሰፍፍ ሄንሪፉድ አውቶሞቢል ሲሰራ ሂሳብና ሥነ-ፍጥረት ተመራራማሪዎች ፍልስፍና ጥበባቸውን ከዘመን አስቀድመው ሲመሩት ከህንድ ውቅያኖስ በኩል የመጣው የብሪታኒያ ኢጣሊያ ከያዘችው የሶማሊያ ምድር ውስጥ ወፍፊው ሙላ የሚል ስም ቅጽል በወጣለት በሙሀመድ አብደላ ላይ ዘምተዋል, መህዲ መሲህ በሉኝ ይል የነበረው ሙሀመድ ቢን አብደላ ከላይ ከጌታ ሥልጣን ተሰጥቶኛል የሚል ዕምነት ነበረው :: ከኢትዮጵያ አስር ሽህ ሰራዊት ነበር ብሪታኒያ የወሰደችውን እርምጃ ደግፎ የወጣው,ገና ከስሙ ባልወጣለት በታማ ቁጭብርት አውድማ እና የመላውን አለም ኢኮኖሚ ቁዋያ ያገኘው የጤፍ ቁረና ባስመሰለው የምጣኔ ሀብት ውድቀት መሀል ሽብልቅ የገባው ተከታዩ ዘመን 1920 ጊዜ ሰፍሮም ሆነ አመት ቆጥሮ ካልተደረሰበት መልካም ተምኔት ጋር ነበር እንደ ንጋት ኮከብ የበረቀው :: ዘመኑ ለአለም ፖለቲካ መድረክ ገና እንግዳ የነበረችው ዩኤስ አሜሪካ የባለቀችበት ቻንስህንድበግ በአውሮፕላን አትላንቲክን ያቁዋረጠበት,የአክሲዎኑ ገበያ እንዳፍላ ፍቅር መቆሚያ መቀመጫ የነሳበት ነበር :: ያዛኝ አፈጻጸም ያሳዛኝ ሽፈቱ አስተጋብኦ ዛሬም ጭምር ቢያስገመግም ንዳዶቱ ቢያስረቀርቅ አቅዋቅዋም,አሰላለፉ,አገባብ አወጣጡ ምናልባት ከዘመናችን እሚመሳሰል ከመሆኑ የተነሳ ነው የዘመኑ ሥርዎ ንቃት ተመሳሳይነት አለው ማለት ብዙ የሚዳዳው ::

========ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests