ይህን ያውቁ ኖሯል ?

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ማህቡብ » Wed Apr 19, 2006 2:43 pm

የቀጠለ.........
የጦርነቶች ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል ሲባል የነበርው ታላቁ የአለም የመጀመሪያው የአለም ጦርነት አውሮፓን መልክና ባህሪ እንደነሳ የነባሩንም ሥራት ደብዛ አጥፍቶ ነው ያለፈው ከታላቁ ጦርነት ወዲህ የታየው ሰላምና ጸጥታ እምብዛም የሚያወላዳ አልነበረም :: የኮምኒስቶችና የፋሽስቶች በየሃገሩ የሥልጣን እርካብ መቆናጠጥ ማገገም ይዛ የነበረችውን አውሮፓ ችቸርሶ እንዳትሽር ጥላ ነው የሆነባት 1922 ፋሽስቱ በኒቶ ሞሶሎኒ በሃገረ ኢጣሊያ በትረ መንግስት ሲጨብጥ በምድረ ሩሲያ በሌኒን መሪነት የተነሱት ኮምኒስቶች ቀደም አድርገው ሥልጣን ይዘዋል:: ዩኤስ አሜሪካ ባንድ በኩል ከታላቁ ጦርነት አውድማ በመራቅዋ በሌላው ደግሞ ለፍልሚያው ዘግይታ በመድረስዋ እምብዛም አልተጎዳችም,ስለሆነም ከጦርነቱ በህዋላ ማገገም ማንሰራራቱ ጊዜ አልወሰደባትም,ይሁንና እንደነበረው ሰላም ሁሉ 1920ዎቹ አመታት አካባቢ የታየው እድገትና ብልጽግና ጽኑ መሰረት ያልያዘ መሆኑ ነው ትልቁ ችግር,የዘመኑ መልካም ተምኔት የዘመኑ ፍዳ ተጽቢት ወሰን ድካውን ስቶ ትርጉም የታጣለት ሥር ነቀል ሃሴት ነው የወጣው ::

ከ1920 እስከ 1930አመተምህረት አስሩ አመት አውዱን ሲገጥም በድህረ ጦርነቱ የነበረው እፎይታም ሆነ ወፍ አጥጋቢ ጭንቀት ሃገር ምድር የገለበው የጥፋት ማእበል አጥፊ አይኑ ገና ያልጠፋ የታሃም በስተሁዋላ የሚመጣ መሆኑን አሳይቶ ነበር ያለፈው,ሃሴትና ፍሠሃ በታየበት በዚያ ዘመን ኒዎርክና ፓሪስ የገባ የወጣ ጣምን ይዞ ጎራ ያለው እንግዳ ተቀባይ አስተናጋጅ ስማሪያዋት ወጥትዋቸው ነበር :: የ19ኛው ምእተ አመት ሥራት የእምቡዋይ ካብ መሆን ኪነት ኪነጥበቡን የረባ ያጣንለት በሆነ በዚያ በተውሶ ቁዋንቁዋ ያለባበሱን ፈሊጥ ፋሽን እንበለውና መሽቀርቀሩን ሥነ-ጽሁፉንና የኑሮውን ወግ በዘመናዊነት ጃኖ አዲስ ፍልስፍና ለማስያዝ ሰበብ ሆኖታል::

=======ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Thu Apr 20, 2006 6:36 am

የቀጠለ.........
የጊዜው እንቅስቃሴ አዲስ ወግ አዲስ ደንብ እስኪድትለት ትንፋሹን መዋጥ የተሳነው መስልዋል,የአየር ላንዱ ተወላጅ ጀምስ ጆይስና የስፓኙ ፒካሶ የቁዋንቁዋውን ሂደት የኪነቱን ጅረት ጎርፍ አወራረድ ያልነበረ ጠባይ እንግዳ ባህሪ ካስያዙት ከያኒያን መካከል የመጀመሪያዎቹ ነበሩ :: ይሁንና የተደረገው ጥረት የተደከመው ድካም ሁሉ ወዲያው ተቀባይነት አላገኘም ነብይ በሃገሩ አይከበር እንዲሉ የሁዋላ ሁዋላ ሥምና ዝና ያተረፈውና ዩሊሲስ የሚል ስም መጠሪያ የሰጠው መጽሃፉ ከሃገር ውጭ ከወገኑ እርቆ በ1922 አመተምህረት በሃገረ ፈረንሳይ ላይ ነበር አስቀድሞ የታተመለት ይሁንና ይህ ቀደም ብለው በነበሩት አመታት የጨረሰው መጽሃፉ ለዘመኑ ህብረተሰብ አመለካከትና ሞራል የማይጥም ምንባብ የያዘ ከመሆኑ የተነሳ ውቅያኖስ ተሻግሮ ዩኤስ አሜሪካ እስኪገባ ቢያንስ የ12 አመት እድሜ መግፋት ግድ ነበር የሆነበት ::

ምናልባት ደንብና ሥራት ይሳበር ዘንድ ከተደረገው ጥረትና ትግሉ ሁሉ ዩኤስ አሜሪካ የአልኮል ሽያጭ በህግ እንዲታገድ ያወጣችው ደንብ 1920 በባተ በ16ኛው ቀን መላ ሃገሪቱ የተፈተነችበት ህግ ያስከተለው መዘዝ ትዝታው የላቀ ሳይሆን አይቀርም 13 አመት የተሰራበት ያ ህግ እስከተሻረ ጋዜጠኛው ኤስ ኤች ኤም መንኮን እንደታዘበው ያደረሰው ድቀትና መከራ በ1664 እና በ1665 አመተምህረት መካከል እንደ ሰደድ እሳት ለንደንን የገለበው መቅሰፍት ዘብላክ ፕሌግ ወይንም በ1618 እና በ1648 አመተምህረት መካከል የአውሮፓ መንግስታት ደም የተቃቡበት የ30 አመት ጦርነት ከታየበት ፍዳ የከፋ ነበር::

=======ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Sun Apr 23, 2006 6:12 am

የቀጠለ..........
ዘመን ያመጣው ያለባበስ ፈሊጥ እስከ ቁርጭምጭሚትያለብስ የነበረውን ቀሚስ እስከ ጉልበት መዳረሻ ቅምጥል የጸጉሩን መሰራት እንደዚያው እቅጭ ነው ያደረገው :: የሴቲትዋ የእግር ሹራብ ሰውነትዋን የቆዳዋን ቀለም መስልዋል ወንድየው ይታበልበት የነበረውን ጺምና ሪዝ መላጨቱን የዘመኑ አመጣጥ ፈሊጥ አድርጎታል :: በፊተኛው ዘመን መርጣ እንዳትመረጥ እድል ተነፍጋ የነበረችው ነጭ አሜሪካዊት ድምጽ የመስጠት መብት አግኝታለች,በዚያው አመት በ1920 መሆኑ ነው በወርሃ ሚያዝያ ነበር የጎሳና የነገድ ድሪቶ መደረቱን ሞያ ብሎት የነበረው የአለም መንግስታት ማህበር,ፍልስጤን በብሪታኒያ ሶሪያ በፈረንሳይ የአደራ ጥበቃ አስተዳደር ሥር እንዲውል የተወሰነው :: ኪነት ኪነጥበቡ የአለባበስ ፈሊጥ,ሥነ ጽሁፉና የኑሮ ዘይቤው በዘመን ለውጥ ጥላ ሥር ዘመናዊ መሆን ጀምሮ ሳለ,ቱርክ ትገዛት የነበረችው ሶሪያ ነጻነትዋን አውጃ አሚር ፈይሰልን አነገሰች በወሩ የቱርክ ምክር ቤት በድምጽ ብልጫ ሱልጣን መሄመት 6ኛውን በትረ ሥልጣን ነጥቆ አገሪቱ በሙስጠፋ ከማል መሪነት ዘመናዊ የሥልጣኔ ጎዳናዋን ጀመረች ::

በሃገረ አሜሪካ ከኒው ኦርሊንስ ፌደራል ግዛት የተነሳውና ጃዝ እየተባለ የሚጠራው የሙዚቃ ስልት መላ ሃገሪቱን የስሜት ምርኮኛ አድርጎ አውሮፓን ሲያስገብር ውሎ አላደረም ::ቀደም ሲል ሎይ አርምስትሮንግን በስተሁዋላም ዲዩን ኤሊንግተንን የመሳሰሉ ዝነኞች ከአለምና ከአለምም ህብረተሰብ ያስተዋወቀው ከጥቁር አሜሪካዊው ውሳጣዊ ስሜትና ሃሊያ የፈለቀው ጃዝ ሙዚቃ ነበር ::

=======ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Mon Apr 24, 2006 7:26 am

የቀጠለ........
የዘመኑ የዩኤስ አሜሪካ ከተሞች,መዝናኛ ቦታዎች አዳራሾችና አውራ መንገዶች ጭምር ጃዝ ሙዚቃ ነበር የእለት ጉርሳቸው,ይሁንና የዘመኑ ጥቁር አሜሪካዊያን ባለሙያዎች የሙዚቃቸውን ያህል ተቀባይነት ያልነበራቸው መሆኑ ነው የሚያሳዝነው,ከኔ በላይ ከንቱ የሚል አጉን አስተሳሰብ እኩይ አመለካከት እንግልጋብ እብሪት ያደረበትና ኩክለክስ ክላን እየተባለ የሚጠራው ለነጩ ህብረተሰብ የበላይነት ጥብቅና የቆመው የሃኬተኞች ማህበር ጥቁሩን ህብረተሰብ እና ደቡቡን የዩኤስ አሜሪካ ክፍል መቅሰፍት ሆኖበት ሌት እንቅልፍ ቀን እረፍት አልነበረውም :: እርግጥ አሜሪካዊው የሙዚቃ ታሪክ ተከታታይ ፊልስካፕ እንደተመለከተው,ጃዝ ሙዚቃ በሃገረ አሜሪካ ሆነም በምድረ አውሮፓ አፍቃሪ ተከታይ የማግኘት እክል አልነበረበትም ይሁንና ፊልስካፕ እንደታዘበው ጥቁር አሜሪካዊውን ሙዚቀኛ ሃገር ወገኑ የበለጠ ቢረዳ ቢገነዘበውም አውሮጳዊው ላቅ ያለ ክብር የሰጠው መሆኑ ነበረ ሚዛን ያጋደለ ያስመሰለው ::

ምናልባት ከዚህ ሁሉ ይልቅ ቀደም ባለው ዘመን በተለይም በ1919 አመተምህረት በሃገረ ፈረንሳይ በርሳይ ላይ ጀርመንና ተጉዋዳኝ መንግስታት ያደረጉት ውል ጽድቁ በተግባር እንዲተረጎም እና ዩኤስ አሜሪካም የአለም መንግስታት አባል ሃገር እንድትሆን የተጣረው ጥረት ሳይሳካ መቅረቱ የበለጠ ሚዛን የሚደፋ ሳይሆን አልቀረም:: ለውሉ ዋስና ጠበቃ ከነበሩት እርእሳነ ብሄርና መራሂያነ መንግስታት አብረው የታደሙትና በወቅቱም ባደረባቸው የልብ ድካም ሳቢያ ጤና የከዳቸው አሜሪካዊው ፕሬዝዳንት ዊድሮ ዊልሶን የለፉለትንና የለፉበትን ውል ሳይደግፉት መቅረታቸው የጊዜውን ሁኔታ ክፉኛ ነው ያወናከበው ::

=======ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Apr 25, 2006 11:26 am

የቀጠለ.........
ወዴትም ወሰዱት ወዴት ፓሪስ ፈረንሳይ የጊዜው የአውሮፓ ህኔታን ዝንባሌ መለኪያ ወደሮ መሆን ሲበዛ ነው የሚከብደው እንደዚሁም ሁሉ ተጉዋዳኝ መንግስታት እና ጀርመን ጦርነቱ ይቆም ዘንድ በሃገረ ፈረንሳይ በርሳይ ላይ ያደረጉት ውል በ1920ዎቹ አመታት በየሀገሩ የታየውን ጥላቻና መናጨት አስወግዶ የፖለቲካውንና የማህበራዊውን ቀውስ ልክ ማስገባት አልሆነለትም :: ሩሲያ በ1922 አመተምህረት ሶቪየትህብረትን በቆረቆረች በሁለተኛው አመትዋ መሪዋን ሌኒን አጥታለች,እድል ገጥሞት በተራው በትረ መንግስት የያዘው ጆሴፍ ስታሊን በሩሲያ ዛሮችና ነገስታቶች ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የፍዳ እረመጥ በሃገሬው አናት ላይ ሲነሰንስ የሁለት አመት እድሜ እንኳን አልወሰደበትም ::

========ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Apr 25, 2006 11:36 am

የቀጠለ......
መልካም መራመድ ይዛ የነበረችው ብሪታኒያ ገንዘብዋ ፓውንድ ስተርሊንግ መሰረተ ዝምድናው ከብር መሆኑ ቀርቶ የመጀመሪያው የአለም ጦርነት ከመዘመቱ በፊት እንደነበረው ከቀርቅ ይሆን ዘንድ ያደረገችው ውሳኔ ያልተጠበቀ የስራ ማቆም አድማና ሽብር አስነስቶ ማትኣኔ ሃብትዋን አጉል ነው ያደረገው :: በጀርመን ላይ ጥርስዋን ነክሳ በቀል ታበቅል የነበረችው ፈረንሳይ እንደ እሳተ ገሞራ እንዳትኖጋ ሲበዛ ነበር ያሳሰባት :: እንደሌላው ሁሉ ድህረ ጦርነቱ የቫይመር መንግስት በጦርነቱ ሳቢያ የተጣለበት 33 ሽህ ሚሊዮን ዶላር ጉማ አልበቃህ ያለው ይመስል የመትረየስ ውካታ የመድፍ ድምታ አፍዝዞት ህሊናውን እንደ መሳት ብሎ በብዙ ሽህ ሰራዊት መልሶ ከህብረተሰቡ መቀላቀሉ አባይን በጭልፋ ነበር የሆነበት ::

=======ይቀጥላል

ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Apr 25, 2006 2:29 pm

የቀጠለ.......
ከቀኝም ከግራም ተቃውሞ ያነሳው የቫይመር ሪፓብሊክ አልበጀውም እንጅ እዳውን ሊከፍል ችግሩን ሊወጣ በገፍ ነበር ብር ያሳታመው,ያም ሆኖ 1927 አመተምህረት ሲብት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ መቅኖ አልነበረውም,ጊዜን ጊዜ ገፍቶት 1930 አመተምህረት ሲጠባ የጀርመን ህዝብ ድቀት መከራው ጭንቀት ብሶቱ ልክ ጠፍቶለት ለአዶልፍ ሂትለር ሥልጣን መያዝ አይነተኛ ምክኒያት ነው የሆነው ::

ከታላቅ አክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ዓምቼ » Fri Sep 29, 2006 9:52 pm

ይህንን ድህረ ገጽ ሳገላብጥ አግኝቼው በውነቱ ተዝናንቼበታለሁ ተምሬበታለሁም ሆኖም ግን የመጨረሻው የተቋጨ አይመስለኝም እስቲ የቤቱ ባለቤት ትረካውን ቢቀጥል በታዳሚ ስም እማጸናለሁ ::
ዓምቼ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Thu Sep 28, 2006 10:11 am

መማማር ተገቢ ነው

Postby እሪኩም » Sun Feb 11, 2007 6:22 pm

ሠላም ማህቡብ!

ጥሩ እና አስተማሪ አምድህን ጥለህ ዬት ጠፋህ ጃል? ብቅ ብለህ ቀጥልበት እኛም ከማወቅ እና ከመገንዘብ ወደ ኍላ አንልም::
http://www.ekho.com/What_We_Know.htm

መማማር ተገቢ ነው -- የዕውቀት አድማስን ያሰፋልና!
እሪኩም
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

የዓለም ዋና ዋና አን(ም)ባገነን መሪዎች

Postby እሪኩም » Sun Feb 11, 2007 6:55 pm

ሠላም ለሁሉም!

ከዛሬው የዓለም ዜና ያገኘሁትን ላካፍላችሁ::

By ANI
Sunday February 11, 05:56 PM
Washington, Feb 11 (ANI): Pakistan President General Pervez Musharraf has for the third consecutive year been featured in the Parade magazine's list of world's worst dictators.

He has been placed at the 15th place this year. Last year he was at no 17.

At number one place is (1) Omar al-Bashir of Sudan followed by (2) Kim Jong-Il of North Korea, (3) Sayyid Ali Khamenei of Iran.

The others on the list are
4. Hu Jintao of China,
5. King Abdullah of Saudi Arabia,
6. Than Shwe of Burma,
7. Robert Mugabe of Zimbabwe,
8. Islam Karimov of Uzbekistan,
9. Muammar al-Qaddafi of Libya,
10. Bashar al-Assad of Syria,
11. Teodoro Obiang Nguema of Equatorial Guinea and 12. King Mswati III of Swaziland.

13. Isayas of Afewerki of Eritrea,
14. Choummaly Sayasone of Laos.
16. Meles Zenawi of Ethiopia,
17. Hosni Mubarak of Egypt and
18. Paul Biya of Cameroon also feature in the list.

Surprisingly, Russian President Vladimir Putin has also been included in the list of the world's worst dictators.

Elsewhere, former Cuban President and US's bete-noire Fidel Castro has not been included in the list this time, reports the Daily Times. (ANI)

ምንጭ:
http://in.news.yahoo.com/070211/139/6bzuh.html

መልካም ጊዜ
እሪኩም
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

ይቺ ናት ጨዋታ

Postby እሪኩም » Fri Feb 16, 2007 8:51 am

ሠላም ለሁሉም!

Image
አይታችሁ ፍረዱ----:-)

ይቺ ናት ጨዋታ
እሪኩም
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Postby ማህቡብ » Tue Mar 20, 2007 6:24 am

ሠላም ጤና ይስጥልኝ!!

በቀን ከስንት ወዳጅ ዘመድ ወይንም ባለጉዳይ ጋር ሠላምታ ይለዋወጣሉ? ወይንም ይጨባበጣሉ? ተብለው ቢጠየቁ የሚሰጡት መልስ ይህን ያክል አሳሳቢ አይደለም እና ይተውት:: ከቤትዎ ሲወጡ,መንገድ ላይ,ለቡና ጎራ ሲሉ,ቢሮ ሲደርሱ የጨበጧቸው እጆች ሳይቆጠሩ በአንድ በተወሰነ ወቅት እንበል እርስዎም በዕንግድነት ከሄዱበት አገር እንግዶች ሲቀበሉ ስንት ሰዎች ይጨብጣሉ?

በዚህ እረገድ በ1858 ተወልደው በ1919 የሞቱት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት አንደኛ ናቼው ሩዝቬልት የፈረንጆችን እንቁጣጣሽ ጃንዋሪ 1 1970 ምክኒያት በማድረግ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኜው ቤተመንግስት በተከናወነው ሥነ ሥርአት ላይ የተገኙ 8513 ሰዎችን አንድ በአንድ እየጨበጡ መልካም ምኞታቼውን ገልጸዋል:: እንደው ጉድ እኮ ነው
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby Good ሰው » Tue Mar 20, 2007 2:24 pm

ማህቡብ wrote:
በዚህ እረገድ በ1858 ተወልደው በ1919 የሞቱት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት አንደኛ ናቼው ሩዝቬልት የፈረንጆችን እንቁጣጣሽ ጃንዋሪ 1 1970 ምክኒያት በማድረግ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኜው ቤተመንግስት በተከናወነው ሥነ ሥርአት ላይ የተገኙ 8513 ሰዎችን አንድ በአንድ እየጨበጡ መልካም ምኞታቼውን ገልጸዋል:: እንደው ጉድ እኮ ነው


ተጉድም ጉድ! በጣም ይገርማልኝ; ግን ቆየኝማ? ፕረዝዴንት ቲዎዶር ሩዝቤልት የሞቱትኝ ባ1919 ተሆነ እንዴት ሁኖ ነው ካ51 አመት ቦሀላ ባ1970 ያን ያህል ሰው አንድባንድ የጨበጡትኝ? አልተረዳኝምና ነው;
;መልካሙ;
Good ሰው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 79
Joined: Thu Feb 22, 2007 6:52 pm
Location: Ethiopia

Postby ማህቡብ » Tue Mar 20, 2007 2:51 pm

ሠላም መልካሙ ሠው!! ይህን ግዝፈት ያለው ስህተት አይተህ ባለማለፍህ ወፈር ያለ ምስጋናየ ይድረስህ መቼም ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት እንዲሉ 1970 በ 1907 ተብሎ ይታረም :: የሥራ ዘመናቼው ከ1901 እስከ1909 ነበር

ከታላቅ አክብሮት እና ምስጋና ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ዋናው » Tue Mar 20, 2007 11:52 pm

ሠላም ማህቡብ
የብሕር አድባር ውስጠ-ቀለምህን ታድምቅልህ እያልኩኝ እቺን
ሸላይ መጣጥፍ ምናልባት ለመጣፍ ችላ 'ሚያስብል ስሜትን'ኳን ቢኖርህ እኛን በጉጕት የምንጠብቅ አንባቢያኖችህን አስበን::

እንቁለጨለጫለንና........


ከበዛ ማድነቅ ጋር

ዋናው_________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest

cron