ጠቅላላ እውቀት 1

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ጠቅላላ እውቀት 1

Postby አኒታ » Sun Jan 29, 2006 8:07 pm

ሰላም ለመላው..!
ሀሳብ መለዋወጥ..እውቀትን መማማር.. ብዙ ጥሩ ነገር ያስጨብጣልና..ከምናበነበው.. ከምናየው ጥሩ ነው..ጥሩ ነገርን ያስጨብጣል ለሌላው ብለን የምናስበውን.. በጨዋ አማርኛ ታስነብቡን ዘንድ እጋብዛለሁ::
እስቲ እኔ ካነበብኳት እነሆ..
ሰለሞን ሹምዬ መኮንን.. በአሁኑ ሰአት የ "'ሻይ ቡና"' ኢቲቪ ፕሮግራም የሚታወቀውን አዘጋጅ ነው ድንቅ...ስራዎቹን ላስነብባችሁ..!! .. ይህን ሰው በ ኢቲቪ ብቅ ማለት የጀመረው.. በ ሻይ ቡና ፕሮግራሙ ቢሆንም ግን ከ 1972-1988 ዕ.ም ድረስ የጻፋቸውን ግጥሞች ለህትመት ያበቃው ህዳር 1988 እትም በሆነው.. ሚስጥር በሚል ርእስ ውስጥ የሚገኘውን ሥነ-ግጥም የመጀመሪያ ገጣሚ ነው::
ይህ የግጥም መጽሀፍ ባለ 121 ገጽ ሲሆን... እጅግ ማራኪና.. አስደሳች.. አዝናኝ የሆኑ ብስል ግጥሞች ይገኙበታል.. ይህ ድንቅ ስራው በ 1972-88 ድረስ ካሰባሰባቸው ስራዎች አውጣጥቶ በ አንድ ርእስ ቢያስነብብም: ይህ ድንቅ ሰው አሁን በ ኢቲቪ ላይ እስከታየበት ጊዜ ድረስም ይሁን አሁን የሰራቸውን ምግባሮች የሚያውቅ ውሱን ይመስለኛል:: እንግዲህ ዋርካ የሚመጡት ሆነ ይህን አምድ የሚያነቡት ሌሎችም እንዲሁ ከምታውቁትና .. ለሌላው ትምህርት ይሰጣል .. ይጠቅማል የምትሉትን ሁሉ እንድታካፍሉን እየጋበዝኩ.. ከሰለሞን ሹምዬ ስራዎች 2 ልጋብዛችሁ!
ይህን ለ እናቱ ወ/ሮ ገበያነሽ ወርቅነህ 121 ገጽ በመጀመሪያ እንደ መግቢያ የጻፈው ነው..
እዚህ ምድር ሳልደመር
ከሰው ልጅ ሆኘ ሳልቆጠር
በበቀልኩት ማህጸንሽ
ህያው ባረገኝ እስትንፋስሽ
ከአለም በፊት አለሜ ነሽ
የኔ ወዳጅ ገበያ ነሽ::
ለ እናትነትሽ መታሰቢያ
ብእር ልሳኔን መጀመሪያ
ላንቺ ያለው ልጅነቴ
እነሆ በፍቅር አክብሮቴ
የመጀመሪያ በረከቴ::

ሰ.ሹ. 1988
ይሄንንና በጣም ከምወደው.. አንዱ
""ለሁሉም ጊዜ አለው""
ሐቅን ይዘው ቢጋተሩ
ባሰት ገመድ ከታሰሩ
ዚዜ ደርሶ እስኪላቀቅ
መቃጠል ነው ነዶ ማለቅ
የማይሆን ሆኖ መሆን ያለበት
የፍትህ ሚዛን ሲሰራ አቀበት
ከልክ ሳያልፍ በጊዜ ወቅቱ
ቀን እስኪሞላ ይሻል ትግስቱ::

ሰለሞን ሹምዬ
ገጽ 26 ሐምሌ 1980
እና ሌሎች ብዙ ድንቅ ስራዎች...
:idea: እንግዲህ ዳሞት(ዋኖስ):ጆሲ1:ሳምቻው:ሸግዬ:ሌሎች ድንቅ ግጥም ጸሀፊዎችም.. ከዚህ በኋላ ድንቅ ስራዎቻችሁን በመጽሀፍት መደብር.. አቅርባችሁ ለመሸመት ያብቃን ዘንድ ምኞቴ ነው::
እንግዲህ ቢጠቅምም ባይጠምም ይህችን ታክል አስነብቤያለሁ ከዚህ በተረፈ ደግሞ እናንተ ለ እውቀት እንዲሆን እና ሌሎችን ያስተምራል የምትሉትንች እንድትጨምሩ እጋብዛለሁ:: የሚያቁትን ማካፈል መልካም ተግባር ነው!!
እስኪ ከኔ ስንኞች 1.. ለፈገግታ.. :lol:
እኔ ሰው አክባሪ
የማውቃትን ተናጋሪ
ማልወድ ክፉ መካሪ
ባልሆነ ሸክላ ተሰባሪ
በሽክናው ሙሉ :wink: ቺርስ በቅራሪ! :oops: :lol: :lol:
አክባሪያችሁ
አኒታ ቦኒታ 8)
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Postby Jossy1 » Mon Jan 30, 2006 6:08 am

አኒታ ገጣሚን እና ግጥምን ያነሳ ብእርሽ ይባረክ እያልኩኝ ያስነበብሽንን ሁለት የሰለሞን ሹምዬ ግጥምን በተለይ ይሄኛውን ወድጄለታለሁ

እዚህ ምድር ሳልደመር
ከሰው ልጅ ሆኘ ሳልቆጠር
በበቀልኩት ማህጸንሽ
ህያው ባረገኝ እስትንፋስሽ
ከአለም በፊት አለሜ ነሽ
ባንቺ ግጥም ውስጥ ያነበብኩት አክባሪነትሽን የማውቀው ሲሆን ጠላውን ሳንቀምስ በቅራሪ ቺርስ ብትዪን ቅር አይለንም ብለሽ ነው?

ገጣሚን ካነሳሽ በኔ ልብ ውስጥ የአንበሳ ድርሻ ያላቸው ገጣሚያን ደበበ ሰይፉ (በሞት የተለየን) እና ሰለሞን ደሬሳ (ካገኘሽው ዘበት እልፊቱን አንብቢ) ናቸው::

ሰለሞን ደሬሳ ግጥሙን ሳይሆን የህይወቱን ፍልስፍናና አኗኗሩን የምወድለት ገጣሚ ነው::

ከማስታውሰው የደበበ ሰይፉ ግጥም ውስጥ

'.'....ጊዜ በረርክ በረርክ
ጊዜ በረርክ በረርክ
ግና ምን አተረፍክ
ሞትን አላሸነፍክ...." የሚለው የማልረሳው ሲሆን

ሎሬት ፀጋዬ ደግሞም

''.... የማይነጋ ህልም ሳልም
የማይድን ህመም ሳክም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የሰው ህይወት ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም....''

የምትለው ልቤ ላይ ቀርታለች
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby ቁም ነገር2 » Mon Jan 30, 2006 7:36 am

አኒታዬ የቡቱቱ ገበያ እንዴት ይዞሻል:: የሄ የሻይ ብና አቅራቢው ሁል ጊዜ ሳየው መንግስት ቤት ያለውን ግምገማ ያስታውሰኛል 'ሂስ አቅርብ ...እንደዚህ መናገር ክልክል ነው አካሄድ ምናም' የሚሉት የመለስ ጭፍራዎች ቋንቋ ትዝ ይለኛል::
ቁም ነገር2
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 451
Joined: Wed Sep 07, 2005 7:24 am
Location: ethiopia

ስላም

Postby አኒታ » Mon Jan 30, 2006 9:31 pm

ሰላም ለመላው
ጆሲ1 በጣም አመሰግናለሁ..ሰለመጣህም.. ሰለምስጋናውና.. ለጠቆምከኝ መጽሀፍቶች..መቼም እንደ እናንተ ባልሆንም ለዋርካ ሰው የሚሆን መጣጥፍ ለማቅረብ አላንስም አይደል? :lol: :lol: ግን የ እናንተ ሁሉ በመጽሀፍ እንደ ቅርስ ሊቀመጥ የሚገባ ግሩም ስራ ነው.. ::
ለማንኛውም ሌላም የምንማማርባቸው ልናውቃቸው የሚገባውን ይዤ ብቅ እላለሁ..!!
ቁምነገሬ.. የኔ ቁምነገረኛ.. ብቅ እያልክ አስተያየትህን ቁምነገር ቦታዎች የምትሰጥ/ጪ ሰው እጅግ የማከብርሽ/ህ.. ሰላም.. ሰውዬው ማንነት ሳይናገር አብዛኛው አንደበቱ.. እንደ እሳቸው የሚመስለው እኔም ጠርጥሬዋለሁ.. ለዚህም ነው "" ኢቲቪ ፕሮግራም የሚታወቀውን አዘጋጅ ነው "" ብዬ በ ደፈናው ሰለ ፕሮግራሙ የተናገርኩት.. ብዙም የማይስብ ፕሮግራም ቢሆንም ግን ጥሩ የሥነ-ግጥም ስራዎች ነበሩት.. በርግጥ..ኢቲቪን የመመልከቱን ፍላጎት ሰለሌለኝም እና የሱን ፕሮግራም ተከታትዬው ባላቅም.. መጽሀፉን አንብቤው ማንነቱን ሌሎች ብነግር ሰለገረማቸው ነው ለዚህ አምድ ያበቃሁት..በብዛት ሰለ ማንነቱ የሚያቅ የለም.. ለዚህ ነው.. ሰለ ንግግሩ ባላቅም.. ግን ጥሩ ስራ ነበረው..!! የዛሬውን አያድርገውና :lol: :lol:
ሰላም ያገናኘን ደግሞ.. ሌላም ይንገረን ከሚያቀው..>>
አክባሪ እህታችሁ
አኒታ
ቺርስ በቅራሪ!(ቡቅሪ)
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels

Postby ሳምቻው » Mon Jan 30, 2006 11:39 pm

b]
አኒታ wrote:
እኔ ሰው አክባሪ
የማውቃትን ተናጋሪ


የኔ ጨዋ -የኔ ዘረ ብዙ
ጠላሽ የቀጠነው-ቅራሪ የሆነው
ቤትሽ የእግዛብሄር - አላፊ'አግዳሚው ነው .....


ተያዝሽ !

ያንቺን ቤት በምን በምን እንዳገኘሁት ታውቂያለሽ በየደጁ እያረፍኩ ውሀ ሲጠማኝ :: ሥጠይቅ :: ስጠጣ ::ደግሞ ሳዘግም :: ሲደክመኝ በየታዛው ጥላ ስር እንደገና ሳርፍ :: በኅላ አጸዱ ከሚያምር ከአንድ ትልቅ ግቢ ጋር ደረስኩ :: የሰው ቤት ያስፈራል አይደል :: ይሄኛው ግን ቅልልልልልልልል አለብኝ :: የትልቅ ሰው ጊቢ እንደሆነ ያስታውቅ ነበር ::

እና ጠምቶኝ ነበርና ዘቦቹን ውሀ እንዲሰጡኝ ጠየኳቸው :: የተሰጠኝ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ ? የ ዶሮ አይን የመሰለ ቅራሪ ......ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ታዲያ ይሄ የማን ቤት ሊሆን ይችላል ? አኒት-ቦኒትዬ ! ያንቺን ያንቺን እጅ ይላል ---እሺ ::

እና ቤትሽ ምችት ብሎኛል :: ኮት ያደረግሽውን ግጥም ወድጄልሻለሁ :: በተለይ ያንቺው ልብ ይሰርቃል :: ሆደ ሰፊ እና ደግ ስለሆንሽ እንደፈለገን እንሆንበታለን ቤትሽን እንግዲህ ::እኔ ቴብል ላይ እግር መዘርጋት እወዳለሁ አንቺስ ? መሽቷል :: ሞልቷል :: የሚለን የለም :: i feel at home ! በተማመን

ጆሲ ያንተም ኮቴሽኖች ፖወር ፉል ናቸው ::

አኒት በይ እንዳትጠፊብኝ :: ቤት ያፈራውን ቅራሪ እየኮመኮምን ሰመሩን በዚያ እናዘግማለን በኮሌክሽን ኖውሌጅ :: ቬሰር ያ ?
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby አኒታ » Tue Jan 31, 2006 12:25 am

ያንቺን ቤት በምን በምን እንዳገኘሁት ታውቂያለሽ በየደጁ እያረፍኩ ውሀ ሲጠማኝ :: ሥጠይቅ :: ስጠጣ ::ደግሞ ሳዘግም :: ሲደክመኝ በየታዛው ጥላ ስር እንደገና ሳርፍ :: በኅላ አጸዱ ከሚያምር ከአንድ ትልቅ ግቢ ጋር ደረስኩ :: የሰው ቤት ያስፈራል አይደል :: ይሄኛው ግን ቅልልልልልልልል አለብኝ :: የትልቅ ሰው ጊቢ እንደሆነ ያስታውቅ ነበር ::
---------------------
ኖርር ብያለሁ ታላቁ እንግዳዬ..
እኔው የቀለስኩት ቤት ነው አዎ... ቤት ለንቦሳ ብለው ይግቡ.. ከልካይ በሌለበት.. እውቀት በሞላበት...
:lol: :lol: እንዴት ነህ>> ቅራሪ ልጨምር..? ቅምጥጧል መሰለኝ.. ጨጓራህን እንዳይነካህ :lol:
አክባሪህ
አኒታ
አኒታ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 704
Joined: Sat May 29, 2004 10:03 am
Location: City of angels


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest