ለስብሀት ገ/እዝጋብሄር ሀውልት እናቁምለት!!!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ለስብሀት ገ/እዝጋብሄር ሀውልት እናቁምለት!!!

Postby መንፈሳዊው » Tue Jan 31, 2006 7:28 am

ክቡራት እና ክቡራን
እንደሚታወቀው አገራችን ካፈራቻቸው ድንቅ የስነጽሁፍ እና ፍልስፍና ሰዎች መካከል ግንባር ቀደሙ ስብሐት ገ/እግዚያብሄር በቁልምጫ ስሙ ጠይሙ ልኡል ነው
የዚህን ብርቅዬ ሰው ስራዎች በተለያየ አጋጣሚ ስንቋደስ ስናደንቀው ኖረናል
ስብሀትን ልዩ ከሚያደጉት ስብእናዎቹ ዋነኛው ለስነወሲብ ያለው ምጡቅ አመለካከት ከርሱ ትውልድ ርቆ የሄደ ከመሆኑ የተነሳ ብዙሀን እንደባህል በራዥና ተራ ጋጠወጥ አድርገውት ሲያሳጡት ይስተዋላል:: ለነገሩ እንደስብሀት ያሉ ፊሎዞፈሮች በጊዝያቸው ሳይከበሩ የወደፊት ትውልድ ሲያከብራቸው ታይቶ ተመስክሯል:: ሶቅራጥስን እዚች ላይ በምሳሌ ማስቀመጥ ይቻላል::የስብሀት አድናቂዎች ምን ትላላቹ ለዚህ ምርጥ ዜጋ ሐውልት ብናቆምለት?
መንፈሳዊው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Sat Jan 21, 2006 11:50 pm

Postby Jossy1 » Tue Jan 31, 2006 10:30 am

ደጋፊህ ነኝ
ሀውልት ይቁምለት
መንገድ ይሰየምለት

ስብሀት በሚቀጥለው ትውልድ ድንቅ ፀሀፊነቱ ይበልጥ የሚረጋገጥለት ድንቅ ፀሀፊ ነው
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby የዘመኑ አፄ » Tue Jan 31, 2006 3:05 pm

እኔም አንዱ አድናቂው ነኝ:: የስነ ፅሁፍ ችሎታው ባይኖረኝም ከአንባቢነት አንፃር ለየት ያለ ተሠጥኦ እንዳለው ግን በሚገባ የተረጋገጠ ነው::
url=http://www.usersigs.com]Image[/url]
የዘመኑ አፄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 204
Joined: Wed Jan 19, 2005 3:40 pm
Location: fiji

Postby ሳምሶን13 » Tue Jan 31, 2006 5:42 pm

ማን ነው ስብሀት ገ በድርሰት ባጠራቀመው ገንዘብ እራሱ ይስራ አይ ስብሀት ምን ሆኖ ነው ግን :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ሳምሶን13
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Wed Sep 15, 2004 3:48 pm
Location: sudan

Postby እድላዊት » Tue Jan 31, 2006 7:21 pm

ሰላም ሰላም መቼም የጋሽ ስብሀት ስም ሲነሳ ጆሮዬ ነው የሚቆመው ጋሽስብሀትን ውድድድድድድ ነው የማረገው አብሶ ምኑን እንደምወደው ልንገራቹ በቃ ለዚ አለም ያለውን ትርጉም እና ሰዎች እሱን የሚያስቡት በጣም የተለያየ ነው
ጋሽ ስብሀትን ሳውቀው:-
በመንገድም በምንም ሳየው መጽሀፎቹን ብወድም ግን ትንሽ ያይምሮ ችግር ያለበት አርጌ አስብ ነበር አንድ ቀን ነበር ከጋሽ ስብሀት ጋር አንድ ጠረቤዛ ላይ የቀረብኩት
እናም በቃ በጣም ነጻ የሆነ እንደሆነ ባንድ ቀን ውስጥ ያለው የራሱ የሆነ አለም ገባኝ
ብዙ ሰአሊዎች የሚያመሹባት ቤት በቃ የጋሽ ስብሀትን ወዝ ያለው ቁም ነገር አዘል ጨዋታዎችን ስኮሞኩም የዋልኩባቸው ቀናቶች ብዙ ናቸው መቸም ጋሽ ስብሀትን ባካል የምታቁት ካዋቂዎች ይልቅ ከወጣት ጋር የመግባባት ችሎታው ልዩ ነው እና በኛ አገር ውስጥ ለሰው ሳይጨነቅና እንደፈለገ የሚኖር የራሱ አለም ያለው ማቴሪያል የማያጉዋጉዋው ፍጹም ሰው እለዋለው ባለቤቱም ጥሩዬ ነፍስዋን ይማራት ጥሩ ሰው ነበረች
ጋሽ ስብሀት ያወራልኝ ጆክ እስከዛሬ የሚያስቀኝ ነበረኝ እንዳላቀርባት ግን ይህ ብልግናን የማይለይ ህዝብ እንዳይባርቅብኝ ፈራው :)
በሉ ለጋሽ ስብሀት አይደለም ሀውልት መንገድ ምንም ብትሰሩ ካጠገባችው ነኝ ጋሽ ስብሀትዬ ውድድድድድድድድ ነው የማረግህ
አክባሪህ እድላዊት
hany
እድላዊት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 283
Joined: Sat Nov 27, 2004 12:49 pm
Location: united states

Postby መንፈሳዊው » Tue Jan 31, 2006 8:02 pm

አድናቆት ኪስ አይገባም ቶሎ ኪሳቹን ዳብሱ::
ፕላን አውተን ሀውልቱ እንዴት ና የት ሊሰራለት እንደሚችል እንወያይ::
መንፈሳዊው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Sat Jan 21, 2006 11:50 pm

Postby ቦብ ማርሊ » Tue Jan 31, 2006 9:00 pm

በጣም ደስ የሚል ሀሳብ ነው!!!!!!!!!!
ቦብ ማርሊ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Fri Dec 09, 2005 12:37 am
Location: DEJACH WUBE SEFER

Postby ካሳው » Tue Jan 31, 2006 10:02 pm

የሱዳን ዋርካወች መቸ ይሆን የሚበስሉት??

ሰላም
ካሳው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 91
Joined: Mon Nov 17, 2003 12:56 pm
Location: ethiopia

Postby Monica**** » Tue Jan 31, 2006 11:04 pm

ስላም
እኔ እንክዋን አቶ ስብሀትን ለጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅኩዋችው እዚህ ቅዳሜና እሁድ የሚተላለፍ የአማርኛ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ኢንተርቪው የተደረጉትን ነው::
መጽሀፋችውን አላነበብኩኝም!
ስውዬው ቀልደኛ ነገር ይመስላሉ......በቲቪም ጫት ምናምን እንድሚቅሙና እንደሚጠጡ ተናግረው ነበር::
የሆነ ሆኖ ስውየው ሞቱ ማለት ነው? ሀውልት እናቁምለት ስለተባለ ነው የጠየቅኩት ይሄንን ጥያቄ ወይስ እንደው ለመታስቢያ ያህል ነው?
ደሞ እንዳትሞልጩኝ :oops: :oops:
አክባሪያችሁ
ሞኒካ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby Jossy1 » Wed Feb 01, 2006 6:00 am

ሞኒካዬ

ምነው በደህና ነው ወይስ ሌላ ሰው ነው ይሄንን የፃፈው:: የሰይጣን ጆሮ አይስማ በይ:: ጋሽ ስብሀት ይኑርልን እንጂ!!!

መንፈሳዊ

በሉ ሁላችሁም ኪሳችሁን ዳብሱ:: ለስብሀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ

በነገራችን ላይ ለምን የስብሀት ክበብ የሚል አንድ thread አንከፍትም?????? ምን ታስባላችሁ:: የስብሀት አድናቂ የሚሰበሰብበትና በስብሀት የህይወት ፍልስፍና ዙሪያ ውይይት የምናደርግበት የተለየ ትሬድ ቢኖረን መልካም ነው::

እድላዊት

እውነትም እድለኛ ነሽ:: እኔም ከስብሀት ጋር አጠገብ ላጠገብ ቁጭ ብዬ ያወራሁትን ቀን የምረሳት አይደለችም:: ውስጤ ለስብሀት ቅን ተፈጥሮ ትልቅ ቦታ አላት:: አፈሩን ይቅለላትና ልጁንም በቅርብ አግኝቶ የማውራት እድሉን አግኝቻለሁ:: ተስፋ የሚጣልባት የጥበብ ሰው እየሆነች ነበር::
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby መንፈሳዊው » Wed Feb 01, 2006 7:26 am

ሞኒካ የ30 ደቂቃ ቁራጭ ፕሮግራም በማየት ስለስብሀት ልታውቂ አልጠብቅብሽም
አንችም ባጻጻፍሽ ስረዳ ገልጃጃ ነገር
ሳቶኝ አትቀሪም ሀውልት ለሞተ ሰው
ብቻ የሚመስልሽ
ጆሲና እድላዊት ከአቶ ስብሀት ጋር
ጊዜ ጊዜ አሳለፍን ብሎ አንጀባ መስራት ወቅታዊ አይደለም
ቶሎ ቶሎ በተግባር እንረባረብ
የስብሀት ክበብ ያልከው ተስማምቶኟል-----ክፈተውና እንየዋ
ሌሎች አድናቂ ነን በማለት ያካበዳቹም ቀረብ ቀረብ ማለትና የተግባር ሰው ሁኑ
መንፈሳዊው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Sat Jan 21, 2006 11:50 pm

ስለደራሲ ስብሀት ገብረእግዚአብሄር የቀረበ ብቸኛ ምላሽ

Postby ዲጎኔ » Wed Feb 01, 2006 8:26 am

ውድ ሞኒካ

ስለደራሲ ስብሀት ከተከተቡት ተአማኒ ጽሁፍ የአንችን ብቻ አየሁ እንደ ባህላችንም ሀውልት የሚሰራላቸው የሞቱ ሰዎች ሲሆኑ ጋሼ ስብሀት ህይወቱና ፍጻሜው የሙታን እንጂ የህያዋን ነገር ስለሌለበት ሀውልቱ ሌላውን ለማስጠንቀቅ ይሰራለት ካልተባለ በቀር::
ጋሼ ስብሀትን ገና ኩራዝ አሳታሚ ሲሰራ ጀምሮ በቅርብ አውቀዋለሁ ለእኔም ሆነ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ለምመኛቸው ደራሲያን ተምሳሌት መሆን የማይችል አሳዛኝ ፍጡር ነው::
ደራሲ ሰዎችን ለተሻለ ለውጥ የሚያበቃው እራሱም የተስተካከለ ህይወት ሲታይበት እንጂ በነዶ/ር አዲስ አለማይሁ በነዶ/ር ከበደ ሚካኤል የተገራውን ህዝብ ባህርይ በሚያፈርስ በዚህ ክፉ ዘመን ልቅ ዝሙትን የሚያበረታታን ሰው መምረጥ የጤና አይመስለኝም::

ለጋሼ ስብሀት የተመራ መጽሀፍን ግምገማ ለመወያየት ጠጋ ብሎ መወያየት የሚከለክል የአረቄ የሲጋራና የጫቱ ሽታ እጅግ ያንገፈግፋል:አሁን በጡረታ ዘመኑ ከጎልማሳ ከያኒያን እርጥባን ሲመጸወት ያየሁ ሲሆን የንስሐ ጊዜ አግኝቶ እንደመስተካከል የሌላም ነገር ሱሰኛ ሆኗል::

እንደባህላችን ሐውልት የሚሰራው ለሞተ ሰው ስለሆነ ስብሀት እንዲሻሻል መክረው ያልሰማቸው በጣም ጨዋ ለሆኑትና ስለኢትዮጵያ አንድነት ታሪክ ለጻፉት የአክሱም ሐውልት እንዲመለስ ብዙ ላስተባበሩት ለደራሲ በላይ ግደይ ሐውልት ቢሰራ የተሻለ መሆኑን አሰምርበታለሁ::
ዲጎኔ ሞረቴው ከዮፍታሄ ንጉሴ የብእር ፍሬ አምባ


Monica**** wrote:ስላም
እኔ እንክዋን አቶ ስብሀትን ለጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅኩዋችው እዚህ ቅዳሜና እሁድ የሚተላለፍ የአማርኛ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ኢንተርቪው የተደረጉትን ነው::
መጽሀፋችውን አላነበብኩኝም!
ስውዬው ቀልደኛ ነገር ይመስላሉ......በቲቪም ጫት ምናምን እንድሚቅሙና እንደሚጠጡ ተናግረው ነበር::
የሆነ ሆኖ ስውየው ሞቱ ማለት ነው? ሀውልት እናቁምለት ስለተባለ ነው የጠየቅኩት ይሄንን ጥያቄ ወይስ እንደው ለመታስቢያ ያህል ነው?
ደሞ እንዳትሞልጩኝ :oops: :oops:
አክባሪያችሁ
ሞኒካ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ትትና » Wed Feb 01, 2006 9:08 am

ወይጉድ ታዲያ በሂወት ላለ ሰው ነው ሀውልት እንስራ የምትሉት? እኔ ደሞ ያው ያርቲስ ነገር መሞት መሞት ሆኗል ብዮ ከምር በጣም እያዘንኩ ነበር የገባሁት!! ሆ! እስቲ እድሜያቸውን ያርዝመው ልበላ::

ቆይ ግን ጥያቄ አለኝ እንዳትቆጡኝ ደሞ! ጋሽ ስብሀት ሒሀዲግ ሆኑና ሰዉን አስቀየሙ የሚል ወሬ የት ነው የሰማሁት? ካልተባለ በህልሜ ይሆናል! አደራ እንዳትቆጡኝ ደሞ::

አክባሪያችሁ
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby እድላዊት » Wed Feb 01, 2006 3:22 pm

ሰላም ለሁላቹ ይሁን
ዲጎኔ ላንተ ትንሽ ልበልህ እስቲ ጋሽ ስብሀትን መውደድም መጥላትም መብትህ ነው ግን አንድ ልል የምፈልገው ላንተ ምን መሰለህ ጋሽ ስብሀት ማንንም መስሎ አይኖርም እራሱን ስብሀትን እንጂ ስለሰው አሉባልታ እና ስለሰው የማይጨነቅ የራሱ የሆነ አለም አለው ለሰዎች ሱሰኛ እና በአለባበሱም ዝቅ ብሎ ቢታይ ባይምሮው ግን እጅግ የላቀ ሰው ነው
መቼም እንኩዋን እሱ እኔም ሰው በስዬ ይህን አለም ለመምሰል ተጣጥሬ በሰዎች ፊት ሰው መምሰልን እሞካክራለው /እኔ ብቻ ሳልሆን የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው ከራሳችን ህሊና ይልቅ ሰው ምን ይለኛል ብለን በሌላው በጭንቀት አለም ነው የምንኖረው ጋሽ ስብሀት ግን ለምንም ግድ የሌለው ራሱን ሳያታልል የሚኖር ሰው ነው ለዛም ነው በሰዎች ዘንድ ታናሽ መስሎ የሚታየው ልልህ ወዳለው እኔ መቼም እንደጋሽ ስብሀት የምወደው ሰው የለም እስቲ ኢንተርቪውን ስማው በቃ እራሱን የሆነ ሰውነው እኮ
ትትና ላንቺ ደሞ አንድ ነገር ልበልሽ ጋሽ ስብሀት ከኢሀድግ ጋር ግንኙነት አለው ላልሽው ይህ አገር ቤትም አንዳንድ ሰዎች የሚሉት ነው ወንድሙ ባለስልጣን እንደሆኑ አውቃለው ስለጋሽ ስብሀት ግን ልል የምወደው የዘመኑን መንግስ ቢቀበል እና አብሮ ቢሰራ ዛሬ እንዲ የተጉሶቆለ ኑሮ በቀበሌ ቤት ባልኖረ እህቴ በተጨማሪም የጋሽ ስብሀት ኢንተርቪው www.ethioview.com ላይ ካላየሽው እይው

በተረፈ መንፈሳዊ ደሞ የውነት ለጋሽ ስብሀት የምትቆሮቆር ከሆነ አንድ ነገር ልበልህ ጋሽ ስብሀት በህይወት አለ በቁሙ ድንጋይ ከመካብ በቁሙ እንርዳው ያ ይሻላል ባይ ነኝ
hany
እድላዊት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 283
Joined: Sat Nov 27, 2004 12:49 pm
Location: united states

Postby እድላዊት » Wed Feb 01, 2006 3:23 pm

ትትና ስህተት ነበረ የጻፍኩት www.addislive.com
hany
እድላዊት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 283
Joined: Sat Nov 27, 2004 12:49 pm
Location: united states

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests