ለስብሀት ገ/እዝጋብሄር ሀውልት እናቁምለት!!!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby መንፈሳዊው » Wed Feb 01, 2006 5:03 pm

እዚ ጋር ሀውልት ስል ያልገባቹ ነገር አለ
ቋሚ መታወሻው ህያው የሆነ ነገር ለምሳሌ አሁን ጆሲ የከፈተው የስብሀት ክበብ አይነት ነገር ነው የምለው
እድላዊት ምን ሀሳብ አለኝ መሰለሽ አስርም አምስትም እንሁን የተወሰነ ገንዘብ አዋተን በውጭ በእገሌ አገር የሚኖሩ የስብሀት አድናቂዎች ብለን ማስታወሻና ጥቂት ፍራንክ ብንልክለት የሚል ሀሳብ አለኝ
መጽሀፍስ ቢሆን ገዝተን ለቡክ ክለቡ እንደማስታወሻ ብንልክ ምንስ ትላላቹ
እኔ የምለው ስብሀትን የጨረጨሱ ሰዎች ለምን ይጠሉታል አሁን ማን ይሙት ስብሀት ገና ለገና ትግሬ ሆነና በኢሀዲግነት ሲታማ:: ቢሆንስ እረ ----አይደለም ወያኔ አልቃይዳም ይሁን እኔ ከነጠረ አመለካከቱ ውስጠቱ እንጂ ከፖለቲካ ሌብሉ ምናለኝ
ዲጎኔ እኔን ያናደድክ መስሎህ ክፍሌ እየገባህ ነገር ትፈልጋለህአንተ ገምጭ ሽማግሌ ስለስብሀት የማናውቀውን ብታወራ አይሻልህም ንስሀ የሚገባህ አንተ ህይወትህን በሞላ ስትንዘላዘል ያቃጠልክ
ሞረቴው ምዋርተኛ ሞረድ እራስ
መንፈሳዊው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Sat Jan 21, 2006 11:50 pm

Postby Monica**** » Wed Feb 01, 2006 6:38 pm

መንፈሳዊ
በቅድሚያ ስላምታዬ ይድረስህ
አሁን ስድብን ምን አመጣው በጨዋነት ስው ማናገር ሲቻል!!
እኔ ስውዬውን አቃችዋለሁ አላልኩ.....30 ደቂቃስ ሆነ 3 ደቂቃ ምን ልዩነት ያመጣል ካላወቅኩዋችው?
ለማንኛውም ገልጃጃ አልከኝ? It takes one to know one ሲባል አልስማህ ይሆን? :wink:

Jossy1 እና ዲጎኒ ጨዋነት ለተላበስው ገለጻችሁ አመስግናለሁ!!!

ከአክብሮት ጋር
ሞኒካ
መንፈሳዊው wrote:ሞኒካ የ30 ደቂቃ ቁራጭ ፕሮግራም በማየት ስለስብሀት ልታውቂ አልጠብቅብሽም
አንችም ባጻጻፍሽ ስረዳ ገልጃጃ ነገር
ሳቶኝ አትቀሪም ሀውልት ለሞተ ሰው
ብቻ የሚመስልሽ
ጆሲና እድላዊት ከአቶ ስብሀት ጋር
ጊዜ ጊዜ አሳለፍን ብሎ አንጀባ መስራት ወቅታዊ አይደለም
ቶሎ ቶሎ በተግባር እንረባረብ
የስብሀት ክበብ ያልከው ተስማምቶኟል-----ክፈተውና እንየዋ
ሌሎች አድናቂ ነን በማለት ያካበዳቹም ቀረብ ቀረብ ማለትና የተግባር ሰው ሁኑ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

ለእድላዊትዬና ለመንፈሳዊው

Postby ዲጎኔ » Wed Feb 01, 2006 7:15 pm

ውዲቷ እድላዊት

እኔኮ ጋሼ ስብሀትን አልጠላውም ግን ከስካር ከሱሰኛነትና ከወሲብ አበረታች ነገሮች በስተቀር አዎንታዊ ተምሳሌነት ስለሌለው አሁን መታሰቢያ ሀውልት ቅብጥርስ የሚለው አልዋጥ ስላለኝ ነው::የባሰው ደግሞ ፍራንክ አዋጥተን እንላክለት የሚሉት በርጥባን ሳይቀር የሚቅምና የሚሰክርን ሰውየበለጠ toxicated ሆኖ እንዲሞት ያፋጥናል በነገራችን ላይ ድሮ የነበረኝ የደራሲ ምናብ እንደስብሀት በስካር በጫት ተቃጥሎ ማለፍ የነበረ ሲሆን ለቁም ነገሩማ ሳሙኤል ጆንስ የተባለ የእንግሊዝ ደራሲም እንደዚሁ እየሸተተ ንግስቲቱን የstink-smell ልዩነት አስተምሯል::

ለመንፈሳዊው
ስለተለመደው ስድብህ አልደነቅም ለምጄዋለሁ
አትግባብኝ ብትልም ዋርካ የጋራ ስለሆነች ኢሞራላዊ ጽሁፎች መፋለሜን ክንዴን ሳልንተራስ አላቆምም::
አረጀ ላልከኝ እድሜ ከፈጣሪ መጥገብ መታደል ቢሆንም ከያ ትውልድ በጥቂቱ መለስ ያልኩኝ ጎልማሳ ነኝ::
አክባሪያችሁ
ዲጎኔ ሞረቴው ኩራዝ አሳታሚ አጠገብ ከስብሀት ደምበኛ ግሮሰሪ ጎን
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby እድላዊት » Wed Feb 01, 2006 8:11 pm

ሰላም ዲጎን እንደምን ዋልክ ይሀውልህ በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ነገር ልልህ ወዳለው አሁን ግን ለጋሽ ስብሀት በማድላት ሳይሆን ጀነራል ነው የማወራልህ አንዳንድ ሰዎች አንተው እንደገለጽከው ለሰው መልካም ነገር ሰርተው ያልፋሉ ግን ግን ለምን መልካም የሰሩትን ብቻ ለመቁጠር ህሊናችን አይሞክርም ማለት የሰውን ባክ ግራውንድ በርብሮ ከትልቅ ቁም ነገር ውስጥ ትንሽ ጉድፍ ከምናወጣ እና የምልህ ጋሽ ስብሀት አንተ እንደምትለው ያው ለሰዎች ውጫዊ ማስመሰል ስለሌለው እንኩዋን እያለ ሳይጨናነቅ ነው የሚኖረው
መቼም እኮ በሱፍ ተኮፍሶ ውጭውን ብቻ አይተን ምርጥ ሰው ነው እንድንለው መሆን አቅቶት አይደለም አይደል እንዴ ?
መቼም እኔ እና አንተ በዚ አንጨቃጨቅም ግን አሁን ለምሳሌ በዘመናዊነትዋ የተደነቀችውን ዘሪቱን ዋውውውው ያሉኝ ብዙ አሉ ግን ኦኬ ለነሱ ወርቅ ትሆናለች እኔ ግን ምንም የሳበኝ ነገር የለም ከስዋ ዘፈን እና ዘሪቱን የወደደ ቀሽም አልልም ለዘሪቱ ፎቅ እንስራ ብትለኝ እጄን ሰበስባለው ለምን? አድናቂዋ ስላሎንኩኝ
እና ወንድም አለም መቼም ጋሽ ስብሀትን ወደዋለው ካልክ ባክ ግራውንዱን በደንብ አጥናው ጉድፉን አትይ ልልህ ነው የምፈልገው ቸር ይግጠመን ወንድም ዲጎኔ
:lol:
hany
እድላዊት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 283
Joined: Sat Nov 27, 2004 12:49 pm
Location: united states

Postby መንፈሳዊው » Thu Feb 02, 2006 2:18 am

ሞኒካ ስለግብረገብ አስተምሪኛ
ገልጃጃ ያልኩት ተሳስቼ ነው ይቅርታ
መባል የነበረብሽ መንቻኪት :D ነው----
ዲጎኔው ሞረቴው ድካሙ ኢ-ሞራል ማለት ትርጉሙን ታውቃለህ? ላንተስ ኢሞራላዊ የመሰለህ ለሌላው ሞራላዊ ቢሆንስ----ለምን ሰው ትዳፈራለህ እየዘለልክ---ስለስድቡ ሞኒካም ዲጎኔም የምሳደበው የምወደውን ሰው ነው:: ለምሳሌ እኔ ሞኒካን በፍቅር ነው የምወዳት ከሰሞኑ ምናልባት ያለችበትን አፈላልጌ ደጅ ሳልጠናት አልቀርም--እየተበሳጫቹ አታካብዱ ባልጩት እራሶች
መንፈሳዊው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Sat Jan 21, 2006 11:50 pm

Postby Monica**** » Thu Feb 02, 2006 11:09 am

መንፈሳዊ
እኔም ልክ እንዳንተ የምወደውን ነው የምስድበው!
ሞዛዛ ልብ አድርቅ :P :P :P :P :P :P :D
መንፈሳዊው wrote:
---ስለስድቡ ሞኒካም ዲጎኔም የምሳደበው የምወደውን ሰው ነው:: ለምሳሌ እኔ ሞኒካን በፍቅር ነው የምወዳት ከሰሞኑ ምናልባት ያለችበትን አፈላልጌ ደጅ ሳልጠናት አልቀርም--
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

ቀደምት ደራሲዎች

Postby እንታደስ » Thu Feb 02, 2006 4:50 pm

ስላም ወገኖች ብዙ ደራሲያን አልኮሊክ ይሆናሉ ቶሎም ወደ ተስፋ መቁረጥ ይጓዛሉ በርግጥ እንደፈለጉት ያላቸውን የሥነጽሁፍ ተስጦ በሚገባ እንዳይሰሩ ሥርዓቶችና ማእቀቦች ወደ ተስፋ መቁረጡ ይገፋፋቸዋል ብየ አስባለሁ::

እንደ ምሳሌ ብንወስድ "አቤ ግበኛ" "እውነት በለለበት ዓለም ለመኖር አልወለድም" የሚለውን መጽሐፉንና ሌሎችንም ስናነብና መጨረሻውን ስናይ ችግራቸው ይገባናል::

የአቶ ስብሀትን እንኳ አንድቀን ነው ያየኍቸው መጽሐፋቸውንም ከአንዷ በስተቀር ሌሎችን አላውቃቸውም "ሌቱም አይነጋልኝ" ታዲያ በዚህች መጽሐፍ ጀርባ ላይ የጻፉት ግጥምና ፎቷቸውን በነጠላ ጫማ ስናይ አዝማሚያው ተስፋ የመቁረጥ ነገር ይታይበታል::
ጽሁፉ እንዲህ ይላል::በከፊሉ

"እኛ ወንዶች ጢማችንን
ተላጭተን ሱፋችንን ቦርሽን
ክራቫታችንን አስረን ጫማችንን
ወልውለን ቦርሳችንን እንደ
አቅማችን አጭቀን ብቅ እንላለን::

ሴቶች ግብር ውሀ ተጣጥበው
ቀሚሳቸውን መርጠው
ፊታቸውን ተኳኩለው
ፀጉራቸውን ተበጣጥረው
ሽቷቸውን አርከፍክፈው
በካርታቸው ተንቁለው
"ቀይ ሽማግሌ ይፈልግሻል"
ሲጠብቁን ቆይተዋል::
ይላል::

ስለዚሁ ጉዳይ ቀደምት ደራሲያን ከጻፉት እነሆ::

ይድረስ ካቶ ስካር በዝና እንዴት ስንብተዋል:: እኔ ደህና ነኝ ልጆችዎስ ጠጅና ጠላ አረቄ ደህና አይደለም ወይ::
ዘወትር በናንተ ላይ ክፉ ክፉ ወሪ እየስማሁ በጣም አዝናለሁ:: ምነው ነገራችሁ ከሰው ራስ ላይ አልወርድ አለ: ዘላለም ከሰው አትጠፉ:: ስውንም ሁሉ በየግብሩና በየድግሱ ቤት ምን በላህ በል የሆድህን አውጥተህ ንገረን እያላችሁ በሰው ላይ ሁከት ታደርጋላችሁ አሉ::
ትስብእተወልድ አግዴ

እኔም ፍቺው ይህን ይመስላል ብዮ መለስሁለት አገሪቱ እንጂ መልካምነቷ ኢትዮጵያን: አትክልቶቹ ድሆቿን ይመስላሉ::አራዊቶቹ ክፉዎች ሹማምንትን ወፎቹ የውጭ አገር ስዎችን ይመስላሉ:: ስውየው ቢሆን አልተገለጸልኝም ስለሆነ እንቆቅልሹ አሁን እንደፈታሁለት እንደሆነ ያገሪቱ ስዎች በወገኖቻቸው ጨክነው የደሀውን ሥር ነቅለው ሊያጠፉ የግንዱን ሥር እየጋጡ ዛፉን ለማድረቅ መጣጣራቸው ስለዚህ የድኃው ጉዳት እጅግ ያሳዝናል::..
ታከለ ወልደሃዋርያት


ቸር እንስንብት
እንታደስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1043
Joined: Mon Jan 24, 2005 5:46 pm
Location: Europe

Postby Getsh » Thu Feb 02, 2006 11:49 pm

ብዙ ነገር አስታወሳችሁኝ : ያንዳንዶቻሁማ አብረን የነበርን ያህል ሀሳባችሁን እጋራዋለው:: ለገሀር ጉምሩክ ከስብሀት ጋር ትቅሙ ከነበረ ደግሞ ብዙ ወግና ፍልስፍና ኮምኩሟችኍል ::ባንድ ወቅት የወያኔ መሪ ነጻውን ፕረስ ጋተር ፕረስ ያለ ጊዜ በጣም ብዙ ጽሁፎች ይወጡ ነበር :: እናም ጋሽ ስብሀት ያው አዲስ ዘመን ይሁን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ላይ አላስታውስም የራሱ ወይም የሱ እንደሆን በሚታውቅ ብእር ስሙ ፍልስፍናውን ቀጥሏል :: እናም ከነጻው ፕረስ ያተረፈው ነገር ቢኖር ጥላቻ ሆነለት:: እዚህ ጋ ትትና ለማለት የፈለግሽውና ወያኔ ነው ወይ ያልሽውን ያስታውሰኛል : አንጋፎቹ ጋዜጦች ሳይቀሩ እንደጉድ ወረዱበት እንዲያውም እስከተራ ስድድብ ደርሰው እንደነበር አይረሳኝም :: አንዱን ልንገራችሁ :: ያው እንደሚታወቅው ስብሀት ጺሙን ያሳድግ ነበር እናም ጦቢያ ጋዜጣ ላይ ራሱን የጣለና ጺሙን ያሳደገ ሁሉ ፈላስፋ አይደለም ብለው አረፉት : ጋሽ ስብሀትን ባደንቀውም ወያኔን ለማስደሰት መሞከሩ ግን ለሱ ያለኝን አክብሮት ቅንሶብኛል : ለዚህም ነው አሁን እንደምሰማው ለራሱ መሆን ያቃተው : ከህዝብ ጋር ሆኖ ቢሆን ኖሮ የለገሀር አካባቢ ሰራተኛ ብቻ ብዙ ነገር ሊያደርጉለት ይችሉ ነበር:: እናም ጋሽ ስብሀት የሚያስፈልገው ሀውልት ሳይሆን ገዳም መግባት ነው:: ያውም በሱ ወሲባዊ ፍልስፍና የሚቀበለው ገዳም ካለ :: ሌላው ደግሞ በዚህ እድሜው አብሮት የኖረውን ህዝብ ይቅርታ ቢጠይቅ ሀውልት አይደለም ሌላም ይሰሩለታል :: የናንተም መውጮ አያስፈልገውም ::

Getsh ከኮልፌ
Getsh
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 64
Joined: Sat Aug 09, 2003 1:14 pm

ጌትሽ ተባረክ ወንድሜ

Postby ዲጎኔ » Fri Feb 03, 2006 4:37 am

ሰላም ለሁላችን ይሁን

ጌትሽ የኮልፌው ተባረክ ስለምስክርነቱይመችህ !

ለገሀር በየትኛው በኩል ነበር ጋሼ ስብሀት የሚያዘወትረው? የዛሬን አያድርገውና እኔም ከምጎበኘው በኮሜርስ ትይዩ ካለው ገረባው ተራ ወይስ ላጋር ሚኒ ፊት ለፊት አወዳይ ተራ? ለነገሩ ከተማውን አጥለቅልቆ ነበር::
ለማንኛውም ጫትን በእጽነት ላለመቀበል ደርግም ወያኔም ብዙ የታገሉት መንግስቱም መለስም መርቃኞች ስለነበሩና በቻርተር ከሀርጌሳና ከኪስማዩ የሚገባ የዶላር ገቢ አሳውሯቸው ነው::አንድ ፕሮፈሰር ነኝ ባይም ጫት እጽ አይደለም ብሎ ሪፖርተር ላይ ሲለቀልቅ በUN የእጽ ቢሮ UNDCP ማስረጃ አፍሯል::

ወደጋሼ ስብሀት ስንመለስ ወያኔው ሲገባ ጠጋ ጠጋ ብሎ ከህዝብ ሆድ ክፉኛ ቢወጣም ህዝባችን መሀሪ በመሆኑ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ሁሉም አድናቂዎቹ ሲረዱት አውቃለሁ::
በአዲስ ዘመን የታወቀባት የእርሱ ማጋላጫ መጣጥፍ
ለስብሀት ገ/እግዚአብሄር-አራት ኪሎ
ለአባ ሞገሴ-ሰማይ ቤት የምትለዋ ነበረች::
ያኔስ ዝም ብለን አለፍነው ግን አባ ሞገሴ ከነፊታውራሪ ጋር ተመሳጥረው ድሀ ገበሬዎቹን ያሰቃዩ ፊታውራሪ አሰጌ በስተርጅና ሰብለወንጌልን ላግባ ብለው ደም ያፈሰሱትን ያልገስጹ ንስሀ ሳይገቡ አድራሻቸው ሰማይ ቤት ሊሆን ይችላል የሚል እምነት የለኝም::
ጋሼጉዱ ካሳና እንቆጳ በዛብህና ሰብለወንጌል ግን በወንጌሉ ያመኑ ስለሚመስሉ አድራሻቸው ገነት ነው!

በተረፈ ጋሼ አቤ ጉበኛን በርቀት በ1969 የማውቀው ሲሆን ኑሮ አልሳካ ያለው እንደጋሽ ስብሀት እየቃመ እየቀመቀመና ወሲባዊ መጻህፍት እያስቃመ ሳይሆን "አልወለድም"ን በመሰሉት የፊውዳሉ ስርአት ተፋላሚ ብእሮቹ ልክ ዮፍታሄ ንጉሴ በጥላ ወጊ ባለስልጣኖች እንደተወጋው በግፍ ነበር::

የአሁኖቹ ደግሞ እነሲሳይ ንጉሱ"የቢራ ሻወር" የሚል ፈሊጥ ይዘው እንደሚቀመቅሙ ባለፈው በሬዲዮ ቃለመጠይቁ ሰምቼ ከጋሼ ስብሀት እንደተማሩት ገምቻለሁ

ፈጣሪ የወጣት ከያኒያንን አይን ከነስብሀትና ንጉሱ እይታ ሰውሮልን በነአዲስ አለማየሁ ፈለግ ይምራልን!

ዲጎኔ ሞረቴው ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ግቢ ከፉት በሉ ሜዳ ማዶ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ጃንጎ » Fri Feb 03, 2006 8:10 am

ስብሀት ግሩም ጸሀፊ ነው :) በተለይ ማህበራዊ ችግሮቻችንን በማሳየት ረገድ የተዋጣለት ነው እስቲ ወደ ትችት ከመግባታችን በፊት 5 6 7 የሚለውን ምጽህፉን እንየው በመጽሀፉ ውስጥ ያሉትንም እጫጭር ድርሰ ቶችንም እንዲሁ ከዛ ስለ ስብሀት ነንጋገር ይቻላል :wink:
peace for all
ጃንጎ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 31
Joined: Thu Jul 21, 2005 2:20 pm
Location: ethiopia

Postby ብልግና? » Fri Feb 03, 2006 2:40 pm

ሰላም ጃንጎና መሰሎቹ እንዴት ናችሁ? አንድ ያልገባኝ ነገር አለ:: ጋሽ ስብሀትን በጽሁፎቹ በመጠኑም ቢሆን አድናቂዉ ነኝ:: ግን ይሄን ያክል ሀዉልት ማሰራት ድረስ አይደለም:: እኔ ሀዉልት ሊሰራለት የሚችል ሰዉ በሙያዉ የተሻለ ደረጃ በመድረስ ለቀጣዩ ትዉልድ ሊያስተምር የሚችል ሲሆን ብቻ ይመስለኛል:: በተረፈ ግን እስኪ ጋሽ ስብሀት ቀጣዩ ትዉልድ ሀዉልቱን በማየት ወይንም ዋርካ ላይ ያለዉን የሱን የማስታዎሻ አምድ በመጎብኘት ምን የሚማር ይመስላችሁዋል:: የሱስ ተገዥ በመሆን እራስን መጣል እና ሙሉ potential'ን በወሲብ ላይ ብቻ ስላዋልው? ከፍተኛ ሀብት ፈሶበት ፈረንሳይ ሀገር ተምሮ መጥቶ በስመ ግልጽነትወሲብ ለማስተማር በሞከረ? እኔ ስለወሲብ በመነጋገር ላይ ጥሩ አመለካከት እለኝ ግን ዉጠት ያለዉ ዉይይት ሲሆን ነዉ ልክ እንደ ተድባበ ጥላሁን አይነቱን ዉይይት" በመሀልየ መሀልየ ዘካሳንችስ:: እኔ ይሄ ሰውየ ሲል የሰማሁትን ልንገራችሁ: አንድ ልጅ በጣም አድናቂህ ነኝና እባክህ ፈርምልኝ ሲለዉ ለልጁ የመለሰለት መልስ ግን እናትክን ጥራትና .... ልፈርምበት ነዉ ያለዉ:: At that time i was shocked.
ብልግና?
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 649
Joined: Fri Feb 03, 2006 6:51 am

Postby ብልግና? » Fri Feb 03, 2006 2:50 pm

ጋሽ ስብሀትን በግለሰብ ደረጃ ደስ ይለኛል: አከብረዋለሁ! public figure ግን መሆን የሚችል አይመስለኝም::

እስኪ ባንድ ወቅት ስለ ሀይማኖት ሲናገር የሰማሁትን ላካፍላችሁ:: "" እኔ ባንድ ወቅት ከኢየሱስና ከ ቼኮ ቬራ ማንን ትመጣልህ ብባል ቼን እላለሁ ምክንያቱም ቼ ለአለም ወዛደሮች የመጣ ሲሆን ኢየሱስ ግን ለእስራኤላዊያን የመጣ ነዉ"" ሲል ሰምቸዋለሁ:: እይታዉን አድንቄለታለ :D :D :D::
ብልግና?
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 649
Joined: Fri Feb 03, 2006 6:51 am

Postby ጫልቱዬ » Fri Feb 03, 2006 10:46 pm

ጋሽ ስብሀትዬ ወድሀለውውውውውውውውውውውውውውውውውው ሰውን ሳይሆን ራስህን ስትኖር ባይኔ አይቼሀለው ሌሎች ጥሩ ደራስያንን ኢትዮጽያ ብታፈራም ግን አንተ የራስህ አለም የራስህ ሙድ ስላለህ ለየትትትትትትትትት ያልክ ሰው ነህ
እዚ ያላቹ በሙሉ ግን አንድ ነገር ልላቹ ወዳለው ጋሽ ስብሀት በጣም ደስተኛ ሰው ነው ካለዘመኑ ነው የተፈጠረው እንዳአጼ ቴድሮስ
ጋሽ ስብሀት እስቲ አዳምጡት ኢንተርቪውን የሚያወራው ላይክ ሚድያ ይሰማኛል ብሎ ሳይጨናነቅ,,,, ደብሮሽ... እንኩዋን እያለ የሚመልሳቸው ሁሉ ነው የሚስበኝ አንድ ነገር ልዩነት ስላየው ነው ታዋቂ ሰዎች ኢንተርቪ ላይ የቃላት አመራረጣቸው ምናምን አንድ ወጥ ነውድምጻቸውን ኩል አርገው ተጨናንቀው ጋሽ ስብሀት ግን እራሱን ስብሀትን ሆኖ ነበር የሚናገረው
በሉ ደሞ ልሂደው ጫልቱ/እድላዊት
:lol:
this is hilinayeeeee i love all
ጫልቱዬ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Sat Jul 16, 2005 3:48 pm
Location: ethiopia

Postby Getsh » Sat Feb 04, 2006 12:56 am

ጃንጎ wrote:ስብሀት ግሩም ጸሀፊ ነው :) በተለይ ማህበራዊ ችግሮቻችንን በማሳየት ረገድ የተዋጣለት ነው እስቲ ወደ ትችት ከመግባታችን በፊት 5 6 7 የሚለውን ምጽህፉን እንየው በመጽሀፉ ውስጥ ያሉትንም እጫጭር ድርሰ ቶችንም እንዲሁ ከዛ ስለ ስብሀት ነንጋገር ይቻላል :wink:


ምንም የማይወጣላቸው ምርጥ የስብሀት ስራዎቹ መሀል ሊጠቀስ የሚገባው ይህ አንተ የጠቀስከው 5 6 7 አንዱ ነው :: ስለ አንድ ሰው ደራሲም ይሁን ከያኒ ከተነሳ ብዙ ነገሮች መዳሰስ ያለባችው ይመስለኛል : አንተ እንደምትለው ትችትም ዘለፋም አይደለም ያለውን ሀቅ መዘርዘሩ ክፋት ያለው አይመስለኝም :: ጥሩ ጥሩውን ብቻ ጫሩ ከሆነ : አውቀን ባለመናገራችን ክህደት ስለሆነ የሚሰማንን ከመናገር ፈቀቅ አንልም : ስለ ራስህ ብቻ ተናገር ካልከኝም የራሴን አንድ ብያለው : እኔ ደግሞ ፈራጅ አይደለውም : ግን ለጋሽ ስብሀት ያለኝን አድናቆት የራሱ ብእር ገና ድሮ ተመካንበት ባልንበት ሰአት ራሱ ሸራርፎታል::
ዲጎኔ እና ብልግና በደንብ አድርገው ጽፈውታልና ስላልተቀረጽው ድንጋይ ከነሱ በላይ ማለት አልችልም::

ቸር ሰንብቱ

Getsh ከኮልፌ
Getsh
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 64
Joined: Sat Aug 09, 2003 1:14 pm

Postby ብልግና? » Sat Feb 04, 2006 8:11 am

እንደኔ እንደኔ ግን ሀዉልት ከጋሽ ስብሀት ይልቅ ለወንድማቸዉ ለእዉቁ ሳይንቲስት ዶክተር ተወልደብርሀን ገ/እግዚአብሄር ቢሰራላቸዉ ሳይሻል አይቀርም:: ዶክተሩ ለሀገራችን ባበረከቱት አስተዋጾ የ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ድግሪ ሰጥቱዋቸዋል:: በተማሩበት ሙያ ህዝብን የሚጠቅም ስራ በሀገራችን በከፍተኛ ደረጃ በመስራት ላይ ናቸዉ:: እኒህን እዉቅ ሳይንቲስት ሳይ ""አይ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር"" እላለሁ:: እዚህ ጋር የተወዳጅዋ ብዙነሽ በቀለን ዘፈን ሳልረሳ ነዉ ታዲያ;

ሰዉ ከተሰማራ እንደየስሜቱ
በዋለበት ቦታ አዪከሪም ማፍራቱ...
ብልግና?
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 649
Joined: Fri Feb 03, 2006 6:51 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests