Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by Jossy1 » Wed Feb 01, 2006 8:12 am
ቀኑ ፀሀያማ ነው:: ፀሀያማ ሰኞ:: የስብሀት 'ሌቱም አይነጋልኝ' ታትሞ ለገበያ መዋሉን ስሰማ እግሬ የመራኝ ወደ 'አሸናፊ መፅሀፍት መደብር' ነበር:: አሸናፊ ግማሽ ክፍት በሆነችው የሱቁ በር አጠገብ ቁጭ ብሏል-ወጪና ወራጁን እያየ:: ለአዲስ ዘመን የሰጠው ቃለ-መጠይቅ ላይ
'አገራችን አንባቢ በዝቶ ሰዉ በብዛት መፅሀፍ እንዲገዛና እሱም በተዘዋዋሪ መኪና የመግዛት ህልሙ እንዲሳካለት' የገለፀው አይረሳኝም::
አሼ ያሰበው ተሳክቶ መኪና ገዝቶ ይሆን???? እንጃ አራት አመት ሆነኝ ካየሁት::
መፅሀፉን ገዝቼ ወደ አርቲስቲክ የሚወስደውን መንገድ ይጄ አመራሁ:: የስብሀትን መፅሀፍ ይጄ ስብሀትን ፍለጋ-ሰኞ አይደል::አሸናፊን ሳስብ ጠይም ፊቱ እየታሰበኝ; የሰኞ ቀን የስብሀት በአሸናፊ ቤት ወግ ትዝ ይለኛል:: የጠባብ ቤትዋን ግድግዳ ታከው የተጋደሙት አግዳሚዎች ወጣቶች ተቀምጠው ሸፍነዋቸዋል:: ቤቱ ግድግዳ ላይ የተሰኩት ስእሎች በስብሀት ልጅ የተሳሉ እንደሆኑ ነው የማውቀው (ነብስ ይማር):: ስብሀት ብዙ አይናገርም:: ያዳምጣል:: የወጣቶችን ስሜት ፂሙን እያሸ በጥሞና ያዳምጣል:: አጠገቡ በኮዳ ወይም በጣሳ የተቀመጠ ውሀ ነገር ይታየኛል:: ቀስ እያለ ይጎነጭላታል:: ሲጠጣት በእርጋታ; ሲናገር በእርጋታ; ሲጓዝ በእርጋታ:: እድሜው ሙሉ ያነበበው እውቀት ደክሞት በእርጋታ የሚጓዝ;የሚናገር ይመስላል::
ጠይሙ ልኡል ሰኞ ሰኞ በወጣት ሀዋርያት ተከቦ እሱ ባለበት እውቀት ሲፈስ ይውላል:: ሀዋርያት ይናገራሉ:: ልኡል ይሰማል:: አድማጭ ልኡል::.
የሚቀጥል...................
Freewill
-
Jossy1
- ኮትኳች

-
- Posts: 215
- Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
- Location: qatar
by እድላዊት » Wed Feb 01, 2006 3:34 pm
ሰላም ላንተ ጆሲ እንደው አይቼው አላልፍም ብዬ ነው አሁን ግዜ የለኝም ግን ጥሩ ሀሳብ ነው ከተቻለ የጋሽ ስብሀትን ለዛ ያላቸው ንግግሮች እናሰባስብ እና እስቲ እንጻፈው መልካም ቀን ላንተ
hany
-
እድላዊት
- ኮትኳች

-
- Posts: 283
- Joined: Sat Nov 27, 2004 12:49 pm
- Location: united states
-
by yabanje » Wed Feb 01, 2006 6:01 pm
ጆሲ ሀይ ስለ ስብሀት ክበብ እንድታወጋኝ እፈልጋለሁ
-
yabanje
- አዲስ

-
- Posts: 11
- Joined: Sat Jan 28, 2006 3:29 pm
- Location: turky
by ትምህርት » Wed Feb 01, 2006 6:13 pm
የጋሽ ስብሀትን ኢንተርቪው እንድታዳምጡ ጋብዣለሁ:: በተለይ ሰዎች ስለ ውቤ በረሀ ስለጻፈው መጽሀፍ የሚሰጡትን ሀሳብ በሚመለከት የሚሰጠውን መልስ::
:arrow: ቃለ ምልልስ
-
ትምህርት
- ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1056
- Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
- Location: somalia
by Jossy1 » Thu Feb 02, 2006 8:44 am
ትምህርት ምስጋና ይድረስህ
ስብሀት ለአዲስላይቭ የሰጠውን ቃለ-መጠይቅ ደግሜ ማድመጥን እፈልጋለሁ::
'' ከ 55 አመት በፊት ስብሀት እረኛ ነበር:: ደስተኛ ነበረ:... ፍየሎቹ ያስቸግራሉ...''
Freewill
-
Jossy1
- ኮትኳች

-
- Posts: 215
- Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
- Location: qatar
by ጃንሚዳ » Thu Feb 02, 2006 10:57 am
:lol: :lol: ይኅንን ሰውዬ የዛሬ ስንት አመት!ሀገርቤት የሄድኩኝ ጊዜ ኢንተርቪው ሲደረግ አይቻለሁኝ!
ዕጁን ልክ እንደ ውሹ ካራቴ ቲቸር እያወናጨፈ ሲያወራ;ምኑም የሚያወራው ነገር ጭብጡም ምኑዑም አይገባም::ዕንደው የሀበሻ ባህል ሆኖ ነው ዕንጂ ምኑ ነው ይሄ ድመት ፊት ሙኑ ነው የሚወደደው?ባለጌ ስለሆነ ነው?ወይንስ በጅንጅን ሆኖ ስለሚያወራ :lol: ዕኔም እንደርሱ አሁን የholy landን ጅንጅን ባገኝ አድናቂዬ ብዛቱ!!
-
ጃንሚዳ
- ኮትኳች

-
- Posts: 414
- Joined: Tue Apr 06, 2004 10:19 am
- Location: sao tome and principe
by ቦብ ማርሊ » Thu Feb 02, 2006 10:41 pm
አንተ ጃንሜዳ የተባልክ የታሪክ አተላ/ጋሽ ስብሀት ብዙ ጊዜ ይጠቀምባታል/ እባክህን አንድ የሱን መጸሀፍ አንብብና ለመወያየት ተመልሰህ ና እንጂ ዝም ብለህ ሰው አትዝለፍ.ከስተቶችህ ታርመክ ይቅርታ ጠይቅ!!!!!!!!!!!!!!!
-
ቦብ ማርሊ
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 52
- Joined: Fri Dec 09, 2005 12:37 am
- Location: DEJACH WUBE SEFER
by ሚሚlove » Fri Feb 03, 2006 7:47 am
ለወድ ዋርካ ታዳሚዎች በሙሉ እስኪ ስብሀት ካልወ ጅባ ለበላችሁ::
----ወጣትነት-----
"".....ጥሩ ነው ወጣትነት መሆን ገንዘብ ባይኖርህም ጤና ይኖርሀል መልክ ባይኖርህም አንጎል ይኖርሀል እውቀት ባይኖርህም ጉራ ይኖርሀል ደስታ ባይኖርህም ንዴት ይኖርሀል ፍቅር ባይኖርህም ተስፋ ይኖርሀል መጨነቅ ቢበዛብህ ሪቮሊወሽን ታነሳለህ መኖር ቢያስጠላህ ውይም ቢያቅትህ ራስህን ትገድላለህ ሰው ባያውቀውም ቅሉ ታሪክ ይኖርሀል ወጣት ነህ........"" ቸር ሰንብቱ
-
ሚሚlove
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 825
- Joined: Tue Sep 20, 2005 8:40 am
- Location: Ethiopia
by መርፌ ወጊ » Fri Feb 03, 2006 7:53 am
ሚሚlove wrote:ለወድ ዋርካ ታዳሚዎች በሙሉ እስኪ ስብሀት ካልወ ጅባ ለበላችሁ::
----ወጣትነት-----
"".....ጥሩ ነው ወጣትነት መሆን ገንዘብ ባይኖርህም ጤና ይኖርሀል መልክ ባይኖርህም አንጎል ይኖርሀል እውቀት ባይኖርህም ጉራ ይኖርሀል ደስታ ባይኖርህም ንዴት ይኖርሀል ፍቅር ባይኖርህም ተስፋ ይኖርሀል መጨነቅ ቢበዛብህ ሪቮሊወሽን ታነሳለህ መኖር ቢያስጠላህ ውይም ቢያቅትህ ራስህን ትገድላለህ ሰው ባያውቀውም ቅሉ ታሪክ ይኖርሀል ወጣት ነህ........"" ቸር ሰንብቱ
እንደው ስብሀትን ምን ላርገው በቃ እኮ ባጭሩ ዱቅ አርጎታል እኮ!! ሚሚላቭ እናመሰግናለን:: ይልመድብሽ
መንፈሳዊው ነኝ
-
መርፌ ወጊ
- ጀማሪ ኮትኳች

-
- Posts: 75
- Joined: Thu Feb 02, 2006 6:04 pm
by ጃንጎ » Fri Feb 03, 2006 8:30 am
መደነቅ እና መወደስ ያለበት ጸሀፊ ነው የራሱን ስታይል እየኖረ ችግራችንን በድርስቶቹ የገለጸ አሪፍ ጸሀፊ :)በመጨረሻም እድል ፊት ያሳየችው ድንቅ ጸሀፊ :!:
peace for all
-
ጃንጎ
- አዲስ

-
- Posts: 31
- Joined: Thu Jul 21, 2005 2:20 pm
- Location: ethiopia
by ጃንሚዳ » Fri Feb 03, 2006 9:42 am
ቦብ ማርሊ wrote:አንተ ጃንሜዳ የተባልክ የታሪክ አተላ/ጋሽ ስብሀት ብዙ ጊዜ ይጠቀምባታል/ እባክህን አንድ የሱን መጸሀፍ አንብብና ለመወያየት ተመልሰህ ና እንጂ ዝም ብለህ ሰው አትዝለፍ.ከስተቶችህ ታርመክ ይቅርታ ጠይቅ!!!!!!!!!!!!!!!
ያልገባኝ ቦብ የተባልከው የእንግዴ ልጅ!!በቃ ሰው ያንተን ምርጫ ካልወደደ ጠላትህ ነዉ?ማለት ነዉ? ዶማ? ወደአቶ ስብሀቱ ልመለስ አቶ ስብሀቱ!ማለት እኮ
ዱሮ ሀገር ቤት እያለሁኝ አራት ኪሎ ጫማ ሳስጠርግ ጆሊ ባር አጠገብ ቁጭ ብሎ ሳንቲም የሚቀፍል ! ሼባ ነዉ!ጋዜጣ በሌለበት ዘመን !አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ;እግረ መንገድ የተባለ ዐምድ ላይ;የራሱን ሻንጣ የያዘ ካርቶን ሰእል ለጥፎ ያቀርብ ነበር!ዕናም የዚህን ሽማግሌ ስራዎች አንብቤኣለሁኝ !!ምንም አይጥምም! ሊሞት አንድ ሀሙስ የቀረው ሽማግሌ ነው!!ወጣቱን ትዉልድ ሀሺሺ ዕንዲያጨስ የሚያበረታታ!!ይሄ ሰውዬ ዕንደዉም በሸሪያ ህግ ነው መዳኘት ያለበት!! :twisted: :twisted: ለማንኛውም ደራሲ ነዉ ማለት ባልችልም ;ጥሩ ማዘሩ ቅቅቅቅቅቅቅ የወለደችው አባባ ባለጌ ነው!!
-
ጃንሚዳ
- ኮትኳች

-
- Posts: 414
- Joined: Tue Apr 06, 2004 10:19 am
- Location: sao tome and principe
by yabanje » Fri Feb 03, 2006 3:27 pm
ትምህርት እግዚአብሂር ይባርክህ የጋሼ ስብሀት ፎቶ አስደስቶኝኣል
በተለይ ለልጅ ፍጹም :) ያለው ፍቅር ልቤን ይነካኝአል
ውስጥኣችንን ስለሚገልጽ ጥሩ ጸሀፊ ነው
-
yabanje
- አዲስ

-
- Posts: 11
- Joined: Sat Jan 28, 2006 3:29 pm
- Location: turky
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: No registered users and 4 guests