የዋናው አቁማዳ==>ሸራ ስላልወጠርኩ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዋናው » Thu Apr 06, 2006 7:19 pm

ቅቅቅ ሰላም አብዮታችን
ኽረ አልተኛውም የሚስጨፍን ዕይታ ገጥሞኝንጂ
ለማንኛውም በዚህች አኮፋዳዬ ለሰጣችሁኝ አሰያየትና ላነበባችሁ ታዳሚዮቼ ሁል ም ስ ግ ን አድርጊያለሁ ይሄ ሰፈር ጾሙን አሏለምና

ዋናው_____________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Apr 07, 2006 2:17 pm

መልካም ንባብ
Last edited by ዋናው on Sun Apr 16, 2006 7:32 pm, edited 1 time in total.
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby አስደሳች » Sun Apr 09, 2006 1:08 pm

ዋንቾ

እቺን ሰፈር እረሳሀት መሰለኝ?
አስደሳች
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 55
Joined: Tue Nov 30, 2004 6:47 pm
Location: united states

Postby ዋናው » Sun Apr 09, 2006 6:24 pm

አንቺ አገር___________________

ትዝቶቼ አድፈው ቢሰለቻቸኝም
ባይተዋር ተብዬ ሆድም ቢብስኝም
ዛሬን ረግሜ ከፍቶ ቢያስነባኝም

ልቤ ግን እዛ ነው አንቺ አገር ምድሬ
እንዴትስ ልፋቀው ያወረሰኝን ዘሬ?

ጌጥ ሆኜ ተጊጬብሽ
ቅኔ ሆኜ ሳለፋታልሽ
.
.
.
ስትሰጂኝ ከህትብቴ
ጓዜን ብዬ ከቤቴ
ቃል ገብቼ ለመምጣቴ
ዕጣፈንታን እየነዳው ከፊቴ
ብወጣም ካንቺ ምድር
ነፍሴ ግን እዛው ቢቀር
አለቅ ብሎት ያንቺ ምድር

ቀፎ ሆንኩኝ እዚህ ሆኜ
ባንቺ ዕጣ አዝኜ
ዋ አንቺ አገር አንቺ አገር
ሕዝብሽ የጀግና ዘር
ሀሞቱ መራራ ነጩን የሚያጠቁር

ልቤ አንቺጋ ቀርቶ
ስጋዬ ተጎልቶ
አገር አገር ሲሉኝ
-አንቺን አስሸትቶ
ውስጤ ተቆጥቶ
የሀያቶቼን ጦራጦር
-ለእልህ አሰብቆ
መግረፍ የዘሬ እንደሆን
-ሲደፍረኝ ይህን አውቆ
.
.
.
እስቲ ልንገራቸው ውብት ሞገስሽን
ዕድሜ ቀጥል አየር ሞልቶሽ መድፋትችን
ገጽና ቀለምሽ ተራሮች ጋራሽን
ብራብ ዕውነት መስሎት
-ሳያይ ወንዛወንዝሽ
.
.
አለኝ እኔ ምግብ
አለኝ እኔ ፍቅር
ምድሬም ጾም አያድር
ብራብን'ኳን ባፍር

አለኝ እኔ ዝና
አለኝ እኔ ታሪክ
ለዓለም ህዝቦች ሚገርም
-ዘላለም ሚተረክ

ጌጤ ነሽ አንቺ አገር
እግሬም እዚህ ቢበር
መምጣቴ 'ንደሆን አይቀር
ስጋዬም አይውሀድ ርቆ ከሰው አፈር

ጨላልሜም አልቀር
እዚህ ጭፍግግ አገር
እመጣለሁ ነገ
ብርሀንሽ ናፍቆኛል
ንጽሁሕ አየርሽን መተንፈስ አምሮኛል
የእውነት ሳቅሽን
-ሳቅበት ብሎኛል::

እኔ መች አጣሁት ውቃቤሽ ጠርቶናል
ልቤ ሮጦብኛል
አንቺን ባወሳው ቁጥር
ሀዘን ይወረኛል::
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው__________________________________::[/list]
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Apr 10, 2006 2:08 pm

.
.
.
ህልሜን ሳላስፈታ
መላም ሳላስመታ
ጓዜንም ሳላጠብቅ
-ክሬንም ሳልፈታ
እመጣለሁ ነገ
-ሸኚዬንም ባጣ

ስላንቺ ሳወራ መሽቶም ቢነጋብኝ
ዝናሽን ስለፍፍ አድማጭም ባያምነኝ
ዕውነት በማውራቴ ደስ ደስ ሲለኝ
አወራለሁ ዛሬም እኔ ምን ቸገረኝ...

ውበትሽ ውበት ነው ልቆ የበለጠ
ታሪክሽ ዝና ነው ስንቱን ያስፈጠጠ
ልብሽን ገምግሞ ስንቱስ ፈረጠጠ?
የስንቱስ ነጭ ልብ በስጋት ተናጠ?
.
.
.
ውበትን ቢያነሱ ካንቺ ወዲያ ብዬ
ታሪክ ዝና ቢሉ ካንቺ ወዲያ ብዬ
የሰጡኝንም ስም ይቅርብኝም ብዬ
ባብድስ ምን አለበት ጨርቄን ሁሉ ጥዬ?
የካሳ ዘርነቴን ይክዱኝ 'ንድሆን ብዬ

አንቺ አገር ልደርብሽ እንደ ጋቢ
እባክሽ ልጌጥሽ አትበይኝ እምቢ
.
.
.
ዋናው________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed Apr 12, 2006 12:07 pm

________አራት ነጥብ የሌለው ሀሳብ________

እስቲ ዛሬ ድግሞ ትንሽ ልዘባርቅ ማን ምን አገባው ደግሞ በራሴ ቤት ቅቅቅቅቅ______________

''መላውን ፍጥረት እንደህያው ፍጡር ብናየው የሰው ዘር እዚያ ፍጡር ውስጥ የበቀለ ካንሠር ነው እግዜር ይቅር ይበለን እንጂ'' ብሎ ነበር ያገራችን ድንቅ ምሁር ስብሀት ገ/እግዚያብሄር
ሠውን ስናማርር ሠውን ስናወድስና ስናከብር...ሠውን ስንጠላና ስናፈቅር...ሠውን ስንገድላና ስናድን እዚህ ደርሰናል : ዕውነት ሠውን ለሁላችንም ሠዎች ህያውዊ ሆኖ ውስጣችን የሚሰርጽበት በጎ አመለካከት/ፖሰቲቭ ኢምፕሊኬሽን/ ጊዜን እንደርስበት ይሆን???
ሠው ውስጥ ምን አለ? ልቦናችን በምን ተገነባ እስቲ ትንሽ የራሳችንን ፓራዶክስ እንመርምር አላምደንም ቢሆን ልክ ማለትም ደመ ነብስ ጥቅም አለው ከሚለው ኢጎና ሱፐር ኢጎ ብለን የፍሮይድ ውስጣዊ የሠው ምህንድስና ውስጥ ጠልቀን ሳንገባ ላይ ላዩን....
እኛ ውስጥ እኩይ በሀሪ አለ አይደልንዴ? በጣም ሲገን መሠይጠን ደረጃ ይደርሳል ባለቤቱ ትሪት ሲያደርገው እኩይነቱን አዳምጦ ሲያወጣው /አዶልፊየስ/ እምደሚሉት አይነት ግን ግን ያንን ነጌቲቭ ነገር ብልጥ ከሆንን ከውስጣችን አውጥተን ወደ ፖዘቲቭ ነገሮች መተግበር እንችላለን .....ልክ ባራዳ አባባል ኸገሌ'ኮ እርጉም ተጫዋች ነው...እርጉም ሯጭ ነው...እርጉም እንትን ነው እንደምንለው ያ ማለት ውስጣችን ያለውን እኩይ መንፈስ አላምዶ ለበጎ ማዋል ነው...ለምሳሌ በምህራባዊያን አገሮች ነጻነታቸው ገደብ አልባ ስለሆነ ራሳቸውን የሚያዳምጡት ባልተለመደና ደስ በማይል ደባሪ ነገር ነው አንዳንዱ ሬፕ አድርጎ ይገላል አንዳንዱ ሰው ቆራርጦ አሰቃይቶ ይገላል.... ይሄ መንፈስ ማናችንም ውስጥ አለ... ለምሳሌአንድ ሰቅጣጭ ነገር ባህይነ ህሊናችን አስበን ወዲያው ለራሳችን ''ውይ በስምሀም ምን ሆኜ ነው?'' ብለን እናውቅ የለ እነሱ ግን ሀስበው ያደርጉታል::ለምን? እኔንጃ ወይም አያገባንም
እና ሠዋዊ ሀስተሳሰብ ምንድነው? ይሄ ጥያቄ ሁሉንም ያስቸግራል ወይስ? እኔን ብቻ ነው? በጎ ነገር ማድረግ እግዜር የሚፈቅደውን መተግበር ውስጣችን ፈረሀ እግዚያብሄር እንዲያድርብን መጸለይና መኖር ትሉኝ ይሆናል በርግጥ ይሄንን አልቃወምም ትክክል ነው:: ግን የማይሰለች ሰዋዊ መንፈስ አለ አይደል የሰው አህምሮ ምን መስራት እንደሚችል ለማወቅ ስላለንበት ትልቅ ስልጣኔ ላፍታ ማሠብ በቂ ነው ያንን የሰው ጭንቅላት ማለቴ ነበር?
ለነገሩ ተዉት መዘባረቅ ልማዴ ነው ደስ ስለሚለኝ ነው

ቸር እንሰንብት

ዋናው_________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Thu Apr 13, 2006 2:17 pm

እዛ ውስጥ ምን አለ_______________________?

ካድማስ ወዲያ ማዶ
ተራራና ሰማዩን ሁሉንም ሮጦ
አለም ዘጠኙንም ቆጥሮና ተራምዶ
ሶስቱንም አውታራት አይቶና ነካክቶ
ከዛስ ወዲይ ምን አለ?
ሳይነካ በምናብ የተሳለ
እሺ እዛም አንድ ነገር አለ
ያም አንድ ነገር ውስጡ ሌላ አለ
ከነዚያ ውስጣውስጥ
-አሁንስ ምን አለ?


ዋናው________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Apr 14, 2006 3:46 pm

አይ እቺህ ሦስት(3)_______________

''አንተ ምን ሆነህ ነው ትላንትና ስልክህን ብሞክር ብሞክር ቮይስ መሴጅ ይሄዳል''

''እኔንጃ ይሰራ ነበር ስንቴ ሞከርሽው?''

''ሦስቴ''
______________________________________
''ምን ባክህ የሰጠህኝ ዕቃ አይሰራም'ኮ ደጋግሜ ሞከርኩት ምንም...''
''እምቢ አለህ...ስንቴ ሞከርከው?''
''ሦስቴ ሞክሬው ቢሰለቸኝ ተውኩት''
_________________________________________
''ምንድነው የሰጠህኝ ካርድ ወደአገቤት አልደውል አለኮ ብሞክር ብሞክር ምንም አይቀበልም''
''እንዴት እምቢ አለሽ እስቲ ድገሚና ሞክሪው....''
''እምቢ አለኝ እያልኩህ ሦስቴ ሞከርኩትኮ....''
_________________________________________
''ይሄንን ፊልም ሦስቴ ነው ያየውት በጣም ነው የምወደው''
__________________________________________

ለምንድነው ብዙ ብዙ ነገሮች በሦስት ቁጥር የተጠመዱት ከላይ ለምሳሌ ጠቃቀስኩኝንጂ በጣም ብዙ ነገሮች በሶስት ይመሰላሉ...
ለምንድነው? የምታውቁት ነገር አለ እስቲ ጥቁሙኝ አደራ?

ሦስቱ ስላሤዎች
ሦስት ጉልቻ
ጌታን ወደ ጎለጎታ ወስደው በመስቀል ሲሰቅሉት እሱ ሦስተኛው ተሰቃይ ነበር
ጴጥሮስ የሱስን ሲክደው የሱስ ዶሮ ሳይጮው ሦስቴ ነበር ትክደኛለ ያለው(ካልተሳሳትኩኝ)
በስፖርት ዓለም ውስጥ ተወዳድረው የሚሸለሙት እስከሦስት የወጡት አሸናፊዎች ናቸው
ሁለት ጊዜ አስነጥሶንን በሦስተኛው ጉንፋን ነው ይባላል
ላንድ ነገር መንደርደሪያ ቁጥር የሚቆጠረው እስከሦስት ነው....
ብቻ ብዙ ብዙ ነገሮች ውስጥ ሦስት ትልቅ ቦታ አላት ምክኚያቱን የሚያውቅ ይኖር ይሆን እሲ ካለ ጠቁሙኝ

ቸር እንሰንብት

ዋናው________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun Apr 16, 2006 7:21 pm

ነጫጭ እንቁላልሎች
ጥቁሮች ፈልፍለው
ጥቋቁር ዶሮዎች
-ነጭ እንቁላል ጥለው
እነዛ እንቁላሎች
-በቀለም ተባዝተው
ውበትና ድምቀት
-ጊጠው ተዥጎርጉረው

እኔ ጥቁር አንተ ነጭ
-ሳይባባሉ ኖረው
ዘመናትን ኖሩ
እንደተፈቃቀሩ
አፈር እየጫሩ

ሰዉ ግን ተገርሞ በቀለም ልዩነት
ለውበት መለየቱን እያወቀው ረስቶት
አንተ ጥቁር ብሎ እርከን አበጀለት

ቢጠቁር ነጭ ላይ
ቢነጣ ጥቁር ላይ
አንዱ ያለ አንዱ
-ጎልቶ ላይተያይ

ዋናው___________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Tue Apr 18, 2006 12:19 pm

.
.
.

ነጭ በጥቁር ላይ
በጣም ስለሚታይ
ዕይታን ሲያሳድም
-በትርግርግታው ላይ
ኮርቶ መፈንጠዙ
በብርሀን ሀይል መጦዙ
ምስጢራዊ ቅኔን ማዘዙ
ያለ በለዛማ ነጭ በነጭ
-አቤት ሞማዘዙ

====(ኮንትራስት)====

ዋናው__________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Apr 21, 2006 3:36 pm

ሸፋፋ ይሉታል እግር እግሩን እያዩ
ያሰበበት ሲድርስ እነርሱ መች አዩ?
ቢንሻፈፍ ለራሱ
ቢንጋደድ ለራሱ
እንዲህ ተጥመዝምዞ
-ቀጥታ ነው ምሱ
ምን ጎደለው እሱ

(ለ ሸፋፋው ሙሁሩ ጓደኛዬ)

ዋናው______________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Tue Apr 25, 2006 4:28 pm

_________________________

የቀለም እውር ነኝ
ቀለማት ያልታየኝ
ቢጫና አረንጓዴ
-ቀይና ሰማያዊ ብለው ቢጠይቁኝ
እኔ ግን ዕወር ነኝ::

አያለሁ ጥቁሩን
አያለሁ ነጫጩን
አያለሁ ደመናን
አየዋለሁ መብረቁን....
ብርሀንና መጭለም አለመታረቁን::

እስቲ ቀለም ስጡኝ
ዓይኔን አበጭጩኝ
ብርሀኔን አቅሉት
-ሰማያዊውን አሳዩኝ ...
የቀለም እውር ነኝ::

ቡናን አጥቁሮ
-ወተትን ያነጣ
ለምን ነው ፈጣሪ
-ሰዉን ያገረጣህ
ውስጡን አጨልመህ
ላይ ላዩን ያነጣህ...?
.
.
.
ይቀጥላል::

ዋናው___________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Apr 28, 2006 3:08 pm

.
.
.
የቀለም እውር ነኝ
ነጫጩ የሰለቸኝ
ምነው ዓይኔ በርቶ ቀለማት ባየልኝ
በኑሮዬ በጭጬ በውስጤ ቀይቼ
በምድር ትዝታዬ አረንጉቼ
በሕያውነቴ ሰማያውቼ.....
ምነው ባየውት ዕኔን በቀለም በርቼ

እስቲ ቀለም ስጡኝ
ብርሀን አጎናጽፉኝ
በነዛ ዕይታችሁ
-ወስዳችሁ ጨምሩኝ
ከቡና ወተት ሌላ
-ምስል አለ በሉኝ
ድንግዝግዝ ያፎዘው
የቀለም እውር ነኝ::

ዋናው__________________________________________________
[/list]
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

ቅቅ

Postby ዋኖስ » Fri Apr 28, 2006 3:13 pm

ዋናው wrote:..
የቀለም እውር ነኝ
ነጫጩ የሰለቸኝ
ምነው ዓይኔ በርቶ ቀለማት ባየልኝ
በኑሮዬ በጭጬ በውስጤ <B><U>ቀይቼ</U></B>
በምድር ትዝታዬ <U><B>አረንጉቼ</B></U>
በሕያውነቴ <B><U>ሰማያውቼ</U></B>.....
ምነው ባየውት ዕኔን በቀለም በርቼ

እስቲ ቀለም ስጡኝ
ብርሀን አጎናጽፉኝ
በነዛ ዕይታችሁ
-ወስዳችሁ ጨምሩኝ
ከቡና ወተት ሌላ
-ምስል አለ በሉኝ
ድንግዝግዝ ያፎዘው
የቀለም እውር ነኝ::

ዋናው__________________________________________________

ኮምፒዩተሬ አልቀበል አላቸው እኒሕን ቃላት ቅቅ ጥሩ ፈጠራ ነው
[/list]
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Mon May 01, 2006 5:34 pm

ሰላም የዳሞቱ _____________ሀኖስ

ቃሉን እንደቀለም ብጥብጥ አድርጌ ቀላቀልኩና አወጫበርኩት አይደለ ...እርግጠኛ ነኝ ምን ለማለት እንደፈለኩኝ ይገባኃል:
እኔም ላመስግንህና ለአንብበህ ማድነቅህ::

ዋናው___________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests