የዋናው አቁማዳ==>ሸራ ስላልወጠርኩ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby sarandem » Mon Mar 09, 2009 4:46 pm

ዋንሽ ከፊርማህ ሥር ያለችው ጥቅስ ሳበችኝ:: አዲስ ከቴ ልጅ እያደለህ :!: በመንገድ ስታልፍ ስታገድም በአስር ሳንቲም ሚጻፉት ጥቅሶች ተጽዕኖ እንዳለብህ ያሳብቃል: :lol: :lol:
ጥበብ እንደዚህ ጉልቤ ናት ብለህ ፊት ሰጥተካት ቀርቶ እንደዚህም እየጋለበችህ ነው :wink: ለማንኛውም ይመችህ::
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby ባቲ » Mon Mar 09, 2009 5:19 pm

ብርብር እያለ
በሩጫ ተጠምዶ
አምልጧል አራዳው
ፍቅር ጥሎ ማዶ
ግን____
የኃይሌንም ጫማ
ቢሆን ተበድሮ
ፍቅር ከቀደመ
ከአምናው ዘንድሮ
አራዳ ከነዳው
ቦታውን ቀይሮ
እትትው ከች ይላል
ቦርቅቆ ከድሮ::
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Postby ዋናው » Mon Mar 09, 2009 6:06 pm

sarandem wrote: አዲስ ከቴ ልጅ እያደለህ በመንገድ ስታልፍ ስታገድም በአስር ሳንቲም ሚጻፉት ጥቅሶች ተጽዕኖ እንዳለብህ ያሳብቃል: :lol: :lol:

ሠሩካ ጥበብ እንደቆሎ ከሚቆነጠርበት ሠፈር አይደለው የመጣዉት ምን ላድርግ ... እቺ ተፅእኖ ግን ስሞትም ሀውልቴ ድረስ ትሸኝሀለች ስላላልከኝ 10Q
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Mar 09, 2009 6:09 pm

ባቲ wrote:ብርብር እያለ
በሩጫ ተጠምዶ
አምልጧል አራዳው
ፍቅር ጥሎ ማዶ
ግን____
የኃይሌንም ጫማ
ቢሆን ተበድሮ
ፍቅር ከቀደመ
ከአምናው ዘንድሮ
አራዳ ከነዳው
ቦታውን ቀይሮ
እትትው ከች ይላል
ቦርቅቆ ከድሮ::

ባቲሻ ውድ ሠው ዌል ካም ቅጥይዋን ግጥም ውድድ ነው ያረኳት
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun Apr 19, 2009 4:03 am

እኔና ዳቦዬ

እቺህ ፅሑፍ ለመስራት ትግል ላይ ካለዉት የሀበሻ አኒሜሽን ፊልሞች የተቀነጠበች ሕሣብ ናት::
ለመተረክ እንዲያመቸኝ እንደ ድርሠት አድርጌ ነው ያቀረብኩት

እንካቹ....


የግንቦቱ ሙቀት ሌቱን እላያችን ላይ ከምንደርበው ካርቶን እና ቡቱቶ ገላግሎናል አስፓልቱ በፀሐይ ሲነፍር ስለሚዉል ማታ ሙቀቱን ለኛ ይተፋልናል: ሌሊት ላይ አንድ ሚወላከፍ ሠካራም የወረወረልኝ ሮዝማን ውስጤን አጥኖት ነፍስያዬ ደስ ብሏት አደረ ሣምባዬም ከሠለቸው ቁሩ እፎይ በማለቱ የዛሬዉን የጠዋት አየር በነፃነት እየተነፈሠ ነው:: የሡሪዬ 3 ውኃላና የፊት ኪሶች ተቀደዋል: ጥቅም ስለሌላቸው መስፋት አላስፈለገኝም:: ከጤናማዋ ኪሴ ውስጥ ያሉት ዝርዝር ሳንቲሞች በታፋዬ ሙቀት ደስ ብሏቸው እንደተኙ ሻካራ መዳፌን ሠድጄ ረበሽኳቸው::

ዳቦ ሻጯ ከጠየመው ወፍራም ላስቲክ ውስጥ ፈገግ ያለ ዳቦ ሠጠችኝ:: ሻይ በዱቤ ስጠይቃት ፊቷን ከሰከሰችብኝ: ዳቦዬን ብቻ ይዤ ወደ ላስቲክ ጎጆዬ አመራው:

ብዙም አልራበኝም ግን ሁለት ሠዓታት ብጨምር ለማዳው ረኣቤ እንዴት አደርክ ሊለኝ መምጣቱ አይቀርም:: የኔ ቂጥ የሠላቻት ጥቁር ድንጋይ ገና ስቀመጥባት ሸርተት አለች መነጫነጯ ነው እንግዲህ...

ዳቦዬን በደንብ አየዉት ትኩር ብዬ... የኑሮ ሡሴ የመሆኑ ሚስጥር እያናደደኝ...

''ምነው አፈጠጥክብኝ...''
አለኝ በሴት ድምፅ

''ምናልክ..''
አልኩት ልጎርሠው አፌ ካስጠጋዉት በኌላ መለስ አድርጌው

''አንተ አትበለኝ ሴት ነኝ:''
አለችኝ እውነትም ድምጿ ብቻ ሳይሆን ቅጥነቷ የሴት ነው ለዛዉም ዳይት ላይ እንዳለች ቀጫጫ ሴት ዓይነት

''ልበላሽ ነዋ ሌላ ለምን አፈጥብሻለው...''

''ታዲያ ሳታፈጥ ብላኛ... አንተ እጅ ያስገባኝ ሳያንሰኝ...''
ብላ አጉረመረመች
''እንዲያውም አልበላሽም በደምብ አፈጥብሻለው ምን ትሆኚ...?''
አልኳት ንድድ ብሎኝ እየጨማመቅኳት

''ባንተ አፍ ከመበላት ድርቆሽ ሆኖ በጫጩት መበላት ይሻላል...''
አለችኝ ጭብጤ እንደሻከራት እጆቼን በመጠየፍ
''አሀ ሚበላሽን ትመርጪያለሽ ማለት ነው...?''
አልኳት መጠየፏ ታውቆኝ
''ሞኞ... በዚህ ባልታጠበ አፍህ ስትሠለቅጠኝ ደስ እያለኝ ምበላ ይመስልሀል...?''
ብታበሽቀኝም ወጓ ተመችቶኛል
''በዚህ ላይ ሆድህ ውስጥ ገብቼ ብቻዬን ነው... አንድም የእሕል ዘር የለም... ቢያንስ አንድ ሌላ ዳቦ ጨምረህ ብትገዛ ምናለ... ድሮም'ኮ አበሻ...''
አለችኝ በምሬት: ንግግሯ ገርሞኝ..
''አንቺ ምንድነሽ ፈረንጅ ነሽ ማለት ነው?''

''እኔማ... ክልስ ነኝ ''

''ደግሞ የዳቦ ክልስ ምንድነው...?''
አልኳት ተገርሜ

''ግማሽ ጎኔ ከካናዳ ነው የመጣዉት''

''አልገባኝም''

''ምነው ነገር እርቃኑን ካልሄደ አይገባህም... ከካንዳ የእርዳታ ስንዴ እና ከአገራቹ የገበሬ ስንዴ ተደባልቄ ነው ዱቄት ሆኜ ተጋግሬ አንተ እጅ ላይ የጣለኝ...

''አሀ... እና በእኔ መበላትሽን አልፈለግሽም ማለት ነው?''
አልኳት ...
ከንፈሯን በሽሙጥ እያፏጨች
''... ወንድሞቼና እሕቶቼ ቀን ወጥቶላቸው ሸራተን ገብተው ከብር በተሠራ ሠዓን ላይ ቀርበው ቅቤ ተቀብተው ወዝተው ይዝናናሉ...''
ስትለኝ ከት ብዬ ሳቅኩኝ ሳቄ ግን ብዙም ሳይበረክት አቋረጠችኝ
''እስቲ አታግጥጥብኝ.... አፍህ ደግሞ ምን ይመስላል እንዲህ በቀን አንድ ዳቦ ጎርሶ ምን ሲሆን ነው እንዲህ የቆሸሸው...?''
አለችኝ ሢግራ ያጠላው ከናፍርቴን እና ጥርሶቼን በመቅፈፍ እያየች...

''ምንም ሁኙ ምንም ዛሬ ለኔ ሆድ ሲሳይ ልትሆኚ ነው የመጣሽው...''
አልኳት ጭምቅ አድርጌ በተራዬ ላበሽቃት

''ታዲያ ብላኛ... ምን የጎሳዬን ሳታማኻኝ ብላ በሚለው ዘፈን ላጅብህ ወይስ...''
ብላ አስካካችብኝ....

''ደግሞ ዝም ብዬ አልበላሽም አንገላትቼ ጠብሼሽ ነው ምብለላሽ ''
አልኳት እሷንም በተራዋ ሳቋን ለማቋረጥ ጣልቃ ገብቼባት

''እዚህ ጉሊት ከመምጣቴ በፊት የተወለድንበት መጋገሪያ ውስጥ አንድ ነገር አዋቂ የአጃ ዳቦ ነበር... ምን አለን መሠለህ ገጠር ውስጥ አሉ ወገኖቻችን ምጣድ ላይ ተጠባብሠው ነው ሚሞቱት... ለዛዉም በጪስ ታጥነው በገበሬ ሚስት መዳፍ ተጠፍጥፈው... ይሄንን ሆረር ታሪክ ያንተ ድንፋት አስታወሰኝ... ታዲያ ለምን ምጣድ አትፈልግም መቼም ቶስተር አለኝ እንዳትል ቤትህን እያየዉት ነው....''
ብላ አሻግራ የላስቲክ ድንክ ጎጆዬን ትመለከታለች...

ንግግሯ እየገረመኝ ወደአፌ አስጠጋዋት ግን ጨዋታዋ ደግሞ ተመችቶኛል ልክ ልኬን ብትነግረኝም

''አሁን አንቺን በገዛዉበት ዋጋ ድሮ 3 ዳቦ እገዛ ነበር በሠላቢ ጊዜ ተፈጥረሽ...''
አልኳት
''አሁን ነቃንባቹዋ... ዋጋችንን አራክሳቹ ባንድ ፌስታል አጭቃቹ ከናንተ ተርፎ ለውሻ ሁሉ ታስበሉን ነበር ያ ጊዜ ቀረ ሞኞ...''
አለች በኩራት ቆዳዋን እያዋደደች

''እናንተ ከካናዳ መምጣት ከጀመራቹ በኌላ ነው እኛም እንዲህ የሆንነው እዛ ተቀቅላቹ ተቀምማቹ ትመጡና ችግር ቀናሽ ሳይሆን ችግር ጠሪ ሆንችሁብን እኛም እናንተን ፍለጋ ከልመና ማጅራት እስከመምታት ደረስን''
አልኳት ሮሮዬን ስለምትስማኝ ተንፈስ እያልኩኝ

''... ለነገሩ እንጀራ ባገኝ ፈጣሪም አንቺ ላይ ባልጣለኝ...''

''አይይይይዪ.... 'ዳቦ ጥራ ቢሉት ቂጣ ይዞ መጣ...' አለ ያ የአጃ ዳቦ እሱማ አላቆማቹ አለኮ እስካሁንም በወጡ ነው ያላችሁት''
አለችኝ:: በእንጀራ ክብር የቀናች ይመስላል
''ከእንጀራ ጋርማ አትወዳደሪም አንቺ ነጫጭባ...''
አልኳት ለማናደድ

''ማ... ይሄ 3 ቀን መሶብ ውስጥ ሲያድር በንዴት ሽበቱ ሚጎፍረው...''
አለችኝ በዛ አናዳጅ ሳቋ

ከዳቦዬ ጋር ዝም ብዬ ሳወራ ቆመው የሚታዘቡኝ ባለ አንድ እግር ነዳይ
''ምነው እሕል ይዘህ መፍጠጥ... ሆድህ ከሞላ ተዘከረኝ ልጄ...''
አሉኝ ክራንች ባለያዘ ጥውልግ መዳፋቸው እየለመኑኝ: ዳቦዋ ሽማግሌዉን በመጠየፍ ታያለች የቀፈፋት ይመስላል: እሳቸዉን ዝም ብዬ ተመለከትኩና እጃቸው ላይ ዳቦዋን አስቀመጥኳት::
በዛች ሞጥማጣ ዳቦ ብዙ ምርቃት ለግሠዉኝ ከአቆማዳቸው ውስጥ ዶሏት::

በእንጀራ ስትሳለቅ የሠሟት የእንጀራ ፍርፋሪዎች እና ድርቆሾች አፈር ከድሜ ሲያበሏት ተሠማኝ::

ተፈፀመ

ዋናው

ለ2ሺህ አንድ የእኛ ፋሲካ ዕለትጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Apr 24, 2009 4:20 am

ከትኩስ ዐፈርህ መልስ

ከትኩስ ዐፈርህ ላይ
-ድምፅሕ ማዶ ይጣራል
ከቀባሪዎችህ አበቦች ልቆ ፈክቶ
-ዜማህ ትላንትን ተናግሯል
ለመኖር ተምሠሌት
-ጥላ ሆኖ ኖሯል
ጥንትም ጥላ .... ሁን ተብሎ
-በአማልክት ተተንብይዋል
.
.
.
ፍቅሬን ባንተ ዜማ
-ኖሪያለሁ አግጬ
ችግሬም ቆንጅቷል
-ባንተ ተመስጬ
ሌባ ጣቴን ሳይቀር
-በድምፅሕ አስፏጭቼ
የሕይወቴን እንክርዳድ
-ቅኔዬን አስፈትቼ
በጥቅምት አንድ አጥንት
-ለጎኔ ሸጉጬ
በመለያየት ሞትነት
-ውስጤን አስደንግጬ
ሠዎች ምን ይላሉ ብዬ
-ደግሞ ተስማምቼ
ኖሪያለሁ በዜማህ
ፍቅርን
ሕይወትን
ሞትን
ችግርን
ሁሉንም አጊጬ

ዜማህ እንደሆን ሕያው ነው
-አንተን ቀብሮ ይኖራል
ከትንፋሽህ ወጥቶ
-ነገንም ይጣራል
በሕይወት ተገጥግጦ
-እንዴትስ ይረሳል ...?
.
.
.
እስቲ ላንዲት ቀንም ቢሆን
-ልምጣና ሙት ሆኜ
አበድረኝ ቃልህን
-ላዚም ተብከንክኜ
ልጇን ላጣች ጥበብ
-በሃዘን ጨፍኜ
ድምጼም ቢጎረብጥ
-ሙሾ ይደረድራል
ከትኩስ አፈርህ መልስ
-ስንቄ ሆኖ ይቆያል ::

አውቃለው ማቾች ነን
-ሁሉም ይከተላል
ግና ምድር ቅንጣት ያልዘራ
-ስሙ እስከመቼ ይጠራል ?
ሆዱን ሞልቶ ያለፈ
-ግሳቱስ ይቆያል ...?
.
.
.
ያንተው የቃል ዘሮች ግን
-ፍቅርን እያዜሙ ሕያው ነን እያሉ
እንደነፍስሕ ሽኝት ቀን
-ትንሣሔ ሆነው ... ሌላዉን ያኖራሉ ::


ለጥላሁን ገሠሠ መታሠቢያ

ዋናው
በዕለተ ቀብሩ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዛዙ » Tue Apr 28, 2009 11:02 am

ዋናው የምትጽፋቸውን ሁሉ ተከታታይ አንባቢና የዚህን መድረክ ዕውነተኛው አላማ ከሚጠቀሙበት ምናልባትም የመጀመሪያው ሳትሆን አትቀርምና አድናቆቴና ምስጋናዬ እንደሁልጊዜው ይድረስህ::

የሀበሻ አኒሜሽን መነሻ ሀሳብ ብለህ ከላይ የጻፍከው ደሞ ከዚህ በፊት ካየኋቸው ጽሁፎችህ/ታሪኮችህ ለየት ያለ ስለሆነ በጣም ወድጄዋለሁ:: የሀበሻ አኒሜሽን እኔ ራሴ ችሎታውና አቅሙ ስለሌለኝ እንጂ ቢኖረን ብዬ የምመኘው ብዙ የአበሻ ልብወለድ ካራክተሮች አኒሜት መደረግ የሚችሉ እንዳሉ እና ቋንቋችንና ባህላችን በዚህ በጣም ሪች ነው ብዬ ስለማምን ነው::

ከአለቃ ገብረሀና ጀምሮ አባ-ቡሩ : አያ ጅቦ : ጥርሳችንን ነቅለን ጣራ ላይ ስንጥል ትወስደዋለች የምትባለው አይጥ : ከቅርብ ጊዜዎች ደግሞ የስብሀት አጋፋሪ እንደሻው ሌሎችም ለአኒሜሽን አይዲያል የሆኑ ካራክተሮች ስነ-ቃላችንንና ተረቶቻችን ሞልተውታል:: ለተረት ደሞ አበሻን ማን ብሎት!! ቀላል ምሳሌ አቡነ ተክልዬ 'ሞትና አጋፋሪ እንደሻው' የተባለው የስብሀት ትረካ ላይ ደራሲውን "ተረትህን ቶሎ ትጨርስ እንደሆን ጨርስ....እኔ በተረት ውስጥ ከመላለስ ሌላ ስራ የሌለኝ መስሎሀል? ብለው ይቆጡታል' እና ሳነበው ስብሀት ቢያስተውለውም ባያስተውለውም ቲፒካል የአኒሜትድ ፊልም ዲያሎግ ነው::

እና ከቶም ኤንድ ጄሪ ጀምረህ እነ ዳፊ ዳክ: በግስ በኒ: ስፒዲ ጎንዛሌዝ: ሲልቬስተር የፍሊንት ስቶኖቹ ፍሬድ እና ዊልማ የፈረንሳዮቹ አስተሪክስና ኦቤሊክስ የላየን ኪንጎቹ ሲምባ ቲሞን ፑምባ ዛዙ (የዋርካ ስሜ ከየት እንደመጣ አሁን ገባህ?) እረ ሰንቱ.......እነዚህን ካራክተሮች በደንብ ሳታውቅ አኒሜሽን ለመስራት እንደማታስብ እገምታለሁ:: በጣም የምወዳቸው እነዚህ ሁሉ አዲስ የተፈጠሩ ግማሾቹም ከአረብና ሌላም ተረት የተዋሱዋቸው ካራክተሮች በጣም በባህላችንና ቋንቋችን ውስጥ መሰረት ያላቸው የአበሻ ኢኩቫለንት ሊኖራቸው እንደሚችል ሳስብ ምን ያህል እምቅ ስራዎች እንዳሉ ያስተውሰኛል::

እስቲ ምን ላይ እንዳለህ በየጊዜው ግለጽልን:: ከኮምፒተር ለብቻህ መስራት እጅግ አድካሚ እንደሆነ መቼም ላነተ አልነግርህም:: የሚተባበሩህ ባለሙያዎች አግኝተሀል ከተዋንያን ጀምሮ:: ብዙ ስዎች የጥበብ እናት ቴአትር ነች ሲሉ ስምቻለሁ:: እኔ በዚህ አልስማማም:: ለኔ የጥበባት እናት አኒሜሽን ነች:: እስቲ አኒሜሽን ውስጥ የማያስፈልግ አንድ የጥበብ ዘርፍ ይጥሩልኝና አይደለችም በሚለው እስማማለሁ::

አክባሪህ
ዛዙ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 199
Joined: Sat Oct 09, 2004 12:46 pm
Location: ethiopia

Postby sarandem » Mon May 04, 2009 1:39 pm

ላልሰጠከኝ ላመስግንህ!


ሞኝነቴ ከአንተ አርቆኝ
ይጠቅማል ያልኩት ጎዳኝ
ሞልቶ ተርፎ ርካታ ራቀኝ
ጥበብ ያልኩት ከንቱ ሆነብኝ።

ላልሰጠከኝ ማመስገን ስጀምር
ሞላ የጽዋዬ ስፍር።


ትዕቢቴም አለፈ
ጉልበቴም ታጠፈ።
መካሪ ማያሻህ ጥበበኛ
ፍርድህ ቅን እውነተኛ
ሁሉን አዋቂ እረኛ።
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby ዋናው » Wed Jun 17, 2009 1:35 am

ዛዙ wrote:ዋናው የምትጽፋቸውን ሁሉ ተከታታይ አንባቢና የዚህን መድረክ ዕውነተኛው አላማ ከሚጠቀሙበት ምናልባትም የመጀመሪያው ሳትሆን አትቀርምና አድናቆቴና ምስጋናዬ እንደሁልጊዜው ይድረስህ::

የሀበሻ አኒሜሽን መነሻ ሀሳብ ብለህ ከላይ የጻፍከው ደሞ ከዚህ በፊት ካየኋቸው ጽሁፎችህ/ታሪኮችህ ለየት ያለ ስለሆነ በጣም ወድጄዋለሁ:: የሀበሻ አኒሜሽን እኔ ራሴ ችሎታውና አቅሙ ስለሌለኝ እንጂ ቢኖረን ብዬ የምመኘው ብዙ የአበሻ ልብወለድ ካራክተሮች አኒሜት መደረግ የሚችሉ እንዳሉ እና ቋንቋችንና ባህላችን በዚህ በጣም ሪች ነው ብዬ ስለማምን ነው::

ከአለቃ ገብረሀና ጀምሮ አባ-ቡሩ : አያ ጅቦ : ጥርሳችንን ነቅለን ጣራ ላይ ስንጥል ትወስደዋለች የምትባለው አይጥ : ከቅርብ ጊዜዎች ደግሞ የስብሀት አጋፋሪ እንደሻው ሌሎችም ለአኒሜሽን አይዲያል የሆኑ ካራክተሮች ስነ-ቃላችንንና ተረቶቻችን ሞልተውታል:: ለተረት ደሞ አበሻን ማን ብሎት!! ቀላል ምሳሌ አቡነ ተክልዬ 'ሞትና አጋፋሪ እንደሻው' የተባለው የስብሀት ትረካ ላይ ደራሲውን "ተረትህን ቶሎ ትጨርስ እንደሆን ጨርስ....እኔ በተረት ውስጥ ከመላለስ ሌላ ስራ የሌለኝ መስሎሀል? ብለው ይቆጡታል' እና ሳነበው ስብሀት ቢያስተውለውም ባያስተውለውም ቲፒካል የአኒሜትድ ፊልም ዲያሎግ ነው::

እና ከቶም ኤንድ ጄሪ ጀምረህ እነ ዳፊ ዳክ: በግስ በኒ: ስፒዲ ጎንዛሌዝ: ሲልቬስተር የፍሊንት ስቶኖቹ ፍሬድ እና ዊልማ የፈረንሳዮቹ አስተሪክስና ኦቤሊክስ የላየን ኪንጎቹ ሲምባ ቲሞን ፑምባ ዛዙ (የዋርካ ስሜ ከየት እንደመጣ አሁን ገባህ?) እረ ሰንቱ.......እነዚህን ካራክተሮች በደንብ ሳታውቅ አኒሜሽን ለመስራት እንደማታስብ እገምታለሁ:: በጣም የምወዳቸው እነዚህ ሁሉ አዲስ የተፈጠሩ ግማሾቹም ከአረብና ሌላም ተረት የተዋሱዋቸው ካራክተሮች በጣም በባህላችንና ቋንቋችን ውስጥ መሰረት ያላቸው የአበሻ ኢኩቫለንት ሊኖራቸው እንደሚችል ሳስብ ምን ያህል እምቅ ስራዎች እንዳሉ ያስተውሰኛል::

እስቲ ምን ላይ እንዳለህ በየጊዜው ግለጽልን:: ከኮምፒተር ለብቻህ መስራት እጅግ አድካሚ እንደሆነ መቼም ላነተ አልነግርህም:: የሚተባበሩህ ባለሙያዎች አግኝተሀል ከተዋንያን ጀምሮ:: ብዙ ስዎች የጥበብ እናት ቴአትር ነች ሲሉ ስምቻለሁ:: እኔ በዚህ አልስማማም:: ለኔ የጥበባት እናት አኒሜሽን ነች:: እስቲ አኒሜሽን ውስጥ የማያስፈልግ አንድ የጥበብ ዘርፍ ይጥሩልኝና አይደለችም በሚለው እስማማለሁ::

አክባሪህ

ሠላም ዛዙ መቼም ዋርካ አንዱ ውበቷ ሲመችህ ብቻ ብቅ የምትልባት መሆኗ ነውና ዛሬ ብቅ ብዬ ለአድናቆትና መልካም ሰፊ አስተያየትህ አንድ ልል ወደድኩኝ::
በቅድሚያ ጥሩ ስም ከጥሩ ካራክተር ፒክ አድርገሀል ባትነግርኝ ይሄኛውን ዛዙ አስታውሰህ ስሙን ትወርሳልህ ብዬ አልገምትም ነበር ይልቅስ በዘመንኛው የአራዳ ቃል ዛዙ ማለት ሞዛዛ አይደል...? ሞዛዛው ብዬ ከመሰየም አዳንከኝ::
ስለአኒሜሽን እዚሁ ዋርካ ላይ ከዚህ በፊት በአንዲት ዋርካዊት ተሳታፊ ጠያቂነት ተነስቶ መጠነኛ ትንታኔ መስጠቴን አስታውሳለሁ:: አንተም ከላይ እንደገለፅከው አድካሚና የብዙ ሠው ኃይልን የሚፈልግ ነገር ነው:: ለአኒሜሽን (የድግግሞሽ ተንቀሳቃሽ ምስል) <== አማርኛው የሚሆኑ በርካታ ተረቶች አሉን ከልጅነታችን ጀምሮ ስንሰማቸው ያደግነው ተረቶች ዛሬ ''ምነው የኛዎቹም እንዲህ ቢሠሩ?'' እያልን በምኞት ለምናያቸው ዘመናዊ አኒሜሽን ፊልሞች የሚሆኑ ናቸው::
ዛዙ በየትኛውም ክ/ዓለም ያለ የኛ ማሕበረሠብ ችግር አንዱ በጋራ ያለመስራት ነው: በየስፋራው የምንገኝ አበሻዊያን ተፈላልገን ያለችንን ትንንሽ ችሎታና ዕውቀት በማገጫጨት መጠነኛ ስራ መስራት እንችላለን ግን ርዕሱ ሲነሳ የምናስበው ተነሳሽነት ለምናቀብለው የእሺታ ቃል ፅናት የለንም:: ፍላጎት እያለን ችልተኞች ነን ችሎታው እያለን ሠነፎች ነን:: ባንዴ ተነስቶ ድብልቅ ያለ የባለ 3 አውታርም ሆነ የባለ 2 አውታር አኒሜሽን መስራት ይከብድ ይሆናል: ግን ሲጀመር ቢያንስ አነስ ባለች መልኩ ከ10 እስከ 17 ደቂቃ የሚፈጅ መጠነኛ ፊልም መጀመር ይችላል:: ግን ለዚችም ቢሆን ዓለም ላይ ካሉት ጋር ሚስተካከል ስራ ለመስራት በቂ የሠው ኃይል ያስፈልጋል::
ብዙዎቻችን በየግላችን እንጥራለን በጋር መስራት ግን እንፈራለን ::
አንድ ጥሩ ምሳሌ ላንሳልህ ለምሳሌ የአማርኛን ሶ/ዌር ውሰድ በአሁን ጊዜ ድረገፅ ላይ ለመፃፍም ሆነ ለማንበብ አውርደን ምንጭናቸው ስ/ዌሮች ብንቆጥራቸው ከእጆቻችን መዳፎች እየበለጡ ነው:: በዚህም የተነሳ የተወሰነዉን ድረ-ገፅ ማንበብ ስትችል ሌላዉን ማንበብ አትችልም ማንበብ ብትችል ያንን ፊደል መገልበጥ ወይም በቀጥታ መፃፍ አትችልም ይሄ ሁሉ የሚሆነው ሁሉም በየግሉ የራሱን ስለሚሠራ ብቻ ነው እስቲ አስበው ገና ከመጀመሪያ ጀምሮ ያለዉን ፓወር/ቪዥዋል ግዕዝ በሙያው ዘርፍ ያሉ ሁሉ የዕውቀታቸዉን እየተጠበቡበት ቢያሻሽሉት/አብግሬድ ቢያደርጉት/ በአሁኑ ሠዓት ለመጠቀም ምን ያህል ቀላል ይሆን ነበር ዕድገቱም ሰፍቶ አንቀፅ እና የሆሄያት ግድፈትን የሚያርም ፈጠራ ራሱ ድሮ በተገኘ ነበር::
አኒሜሽን ላይም ያለው የዚህ ዓይነቱ ችግር ነው መቼም የአበሻ ቪዢዋል ኢፌክተር እጥረት ነው የሚል ጥርጣሬ እንደማይኖርህ ተስፋ አለኝ: ዛሬ ሆሊዉድ ውስጥ ትልቅ ኢንደስትሪ የሆነው የአኒሜሽን ፊልሞች ለሽልማት ታጭተው ሲያሸንፉ የተሳታፊያኑን ቁጥር ካስተዋልከው በጣም በርካታ ነው:: እያንዳንዱን አቀንቃኝ ካራክተር ተከፋፍሎ መስራት ደግሞ ምን ያህል የኃሳብ ጥምረት መኖር እንዳለበት አስበው ያ ማለት ደግሞ መቀራረብና አብሮ መስራት ግድ ነው...
ይሄ ሁሉ ችግር ግን አንድ ቀን እንደሚፈታ ተስፋ አለኝ ምንም ነገር እስከሚጀመር ነው የሚከብደው እኛ በወላጆቻችን መልካም አንደበት ተነግሮን በምናባችን ስጋና ደም አልብሰን አብረን ውስጣችን ያሳደግናቸው በርካታ ተረታዊ ካራክተሮች ነገ ልጆቻችን እንደነሻርክ ቴል እና እንደነማዳጋስካር እየተዝናኑ እንደሚያዩት ተስፋ አለኝ ለዚህም የ ዋናው 'ነቴን ያቅሚቲ መፍጨርጨሬን አላቆምም ::
ዛዙ በድጋሚ ስለጉብኝትህም ሆነ ስለተሳትፎህ ምስጋናዬ ይድረስህ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed Jun 17, 2009 1:47 am

ጊዜ

ባልፈለግኩህ ዘመን
-ከእቅፌ እንዳልበዛህ
አሁን ሳራውጥህ
-ነፋስ ሆነህ ጠፋህ

ዋናው
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋኖስ » Wed Jun 17, 2009 2:04 am

ለሁሉም ጊዜ አለው!

ለመጥፋትም ጊዜ

ለመልማትም ጊዜ

ለመብዛትም ጊዜ

ለማነስም ጊዜ

ለመብላትም ጊዜ

ለሥልጣንም ጊዜ
....
.....

በሆነበት ዘመን ተወልደዉ አድገዉ

ጊዜን ለሚጠብቅ ጊዜ ሸወደዉ::
ዳሞት


እንዴት ከረሙ?
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Thu Jun 18, 2009 3:03 am

አምናና ካቻምና
-እርርሪ ያለችው አላርም
ሠለቻት መሰለኝ
-ዘንድሮስ አትሰራም

(ለዘመነ-ክራንች)
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ትርንጎ* » Thu Jun 18, 2009 5:19 am

ዋንሽ እንኩዋን ደህና መጣህ!
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 709
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ዋኖስ » Fri Jun 19, 2009 3:26 pm

አምናና ታች አምና

እሪሪሪ..... ብላ ብላ `ሚሰማት ብታጣ

ዘንድሮ ለበቀል

ጊዜን አድፍጣለች ከአልጋ ሥር ተቀምጣ::


ለሊቁ!
ዋናው wrote:አምናና ካቻምና
-እርርሪ ያለችው አላርም
ሠለቻት መሰለኝ
-ዘንድሮስ አትሰራም

(ለዘመነ-ክራንች)
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Fri Aug 21, 2009 3:27 am


ማብራትና ውሃ
-አንድ ላይ ተማክረው
ላይበሩ ላይፈሱ
-ልግምትን ተምረው
ከቧንቧና ካምፖል
-አጉል ተነፋፍቀው
ሻማና ሣፋዉን
-ከጓሮ አንጓጕተው
ሠዉን ያጓጉታል
-መጡ ሲባል ሄደው

ፍቅርም ሃዘንም ሳይኖር
-ምሽቱ በሻማ ተዘከረ
ሠንበት ሳይደርስ
-በአዘቦቱ ዉሃ ተቀድቶ እንደጥንስስ ታሠረ::

ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests