የዋናው አቁማዳ==>ሸራ ስላልወጠርኩ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዋናው » Fri Aug 21, 2009 4:15 am

በጀርባ ተንጋለን
-ኳክብት የቆጠርነው
ጨረቃን እየሞቅን
-እርቃን የተኛነው
አሸዋን ደልድለን
-መደብ ያበጀነው
ተጃጅለን ሳይሆን
-ስሜት አስክሮን ነው::

መሃበሉ ሲፎክር
-ጨለማዉም ሲበረታ
ስካራችን ቅኔ ሆኖ
-በድቅድቁ መች ተፈታ?
.
.
.
አንቺ እኔ ውስጥ...
-እኔ አንቺ ውስጥ ተኝቼ
ሕልሜን ስትሰርቂኝ
-ቅዠትሽን አይቼ
ባንኜ ተነሳው
-በ ጎሕ ብረሐን በርቼ

ራስምታት ሆኖ አጭር ትዝታችን
-አጭር ስካራችን
በፍቅር ሀንግ ኦቨር
-ዳግም ተሳከርን::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sat Aug 29, 2009 2:53 pmየቅርቡን ሳታዪው ማዶ ስታገጪ
ይሄኛውም ማዶ ሄዶ ድጋሚ እንዳትፈጪ

(ስታነቢው ለሚገባሽ)
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Thu Sep 24, 2009 2:30 pm

ዕምባው ነጥፎበት
-ፈገግ ቢል ከፊታቸው
ፈገግ አሉ እነሡም
-የሳቀ መስሏቸው
መቅደድ በቻለና
-ውስጡን ባሳያቸው
ፈግግታውና ዕንባው
-አብረው መጉረፋቸው
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Nov 13, 2009 1:55 pm

ቢያባብሉ የማይባበል ቀን
ከዕለታት ውስጥ አንዱን ቢሰጠን
ከነበረን ፅናት ውስጥ ነጠቀን
የመቻቻልን ካብ አስሠበረን
.
.
.
ምናልባት የመፎረሽን ተራ
በዙር ካልተቀበልን::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Nov 13, 2009 2:06 pm

መጣው... አንዴ ይላል
-ለመሄድ ተነስቶ
መሄድ እና መምጣት
-ትርጉሙ ተምታቶ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋኖስ » Fri Nov 13, 2009 3:22 pm

ቅቅቅቅቅ አይዋ! አንድ ነገር አስታወስከኝ:: አንድ እብድ ነበር ከተወለድኩበት ቀዬ:: ቅቅቅ ... እዚያ ሰፈር አንድ ባለ ጸጋም ነበር:: እና አንድ ቀን ያ በለ ጸጋ ከደረቱ ተንጠራርቶ አድማስ ባሻገሩን እያየ ሲሄድ እብዱ ከኍላ ይከተል ነበር:: ባለ ጸጋው ሳያይ ልክ እንደ ኳስ መሬት የወደቀችን መቶ ብር በካልች ከልቿት ሲያልፍ እብዱ ከኋላው ያችን መቶ ብር አነሳና ሄይ! ምን ሰማይ ሰማይ ታያለህ ነገሩ ሁሉ እኮ መሬት ነው ያለዉ አለና ባለ ጸጋዉ አፍንጫ ላይ ያቺን መቶ ብር ለጠፈበት:: ቅቅቅ እናም ሎንዶኖች ሰማይ ሰማይ እያዩ አስቸገሩህ አይደል? ቅቅቅቅ ተዋቸው ቀን የሰጠዉ ባለ ስልጣን, ከችግር ላይ ያልተነሳ ባለ ጸጋ, የደረሰች ኮረዳ አንድ ናቸዉ አሻግረዉ እንጂ ዙሪያቸዉን ማየት አይችሉም:: ቅቅቅ


ዋናው wrote:

የቅርቡን ሳታዪው ማዶ ስታገጪ
ይሄኛውም ማዶ ሄዶ ድጋሚ እንዳትፈጪ

(ስታነቢው ለሚገባሽ)
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Fri Nov 13, 2009 8:39 pm

ስደትና ሆድ


ገና ሃገር ለመልቀቅ ሻንጣዬን ሳነግት እናቴ
''አይ መከራህ አሁን የሆድህን ነገር እንዴት እንዴት ልታደርገው ነው ...?''

ብላኝ ነበር ሆዳም ሆኘ አይደልም ይቅልቅስ ወስፋታም ቢጤ ነኝ ብቻ የተወጠወጠን ወጥ እንኳን ማሞቅ የማይሆንኝ ዓይነት ነበርኩኝ ማዕድቤት ምገባው ምናልባት የበላዉበትን ለማንሳት ብቻ ነው ብል ይቀለኛል አንዳንዴም ለናቴ እንጨት ፈልጬ ላደርስላት እሱንም ቢሆን እናቴ ሰሪ ቤት ያስሳለቸዉን ስለታም መፍለጪያ የምፈልጥበትን የንጨት ትራስ ጉቶ እየሳትኩኝ ከድንጋይ ሳላትም መፍለጫው ባንዴ ችርችፍ ብሎ መዶሻ ሲመስል
''ልጄ ተዎው ''
ትለኛለች ወጪው ቢሰለቻት
አሁን ፈረንጅ አገር ነው ያለዉት እግሬ እዚህ እንደረገጠ ይሄንን የኪናትኪ የሞተ ዶሮ ስጠቀጥቅ ልክ እንደዶሮ በጊዜ መስፈር ጀምሬ ነበር የቀረኝ ነገር ቢኖር ክንፌን እያራገፍኩኝ መሬት መጫር ነበር ይሄንንም ቢሆን የምበላቸው ዶሮዎች እንደማያደርጉት አውቃለው :: ዶሮውን መብላት ቢሰለቸኝ የአልጄሪያ ክባብ ቤት ደምበኛ ሆንኩኝ የሚሽከረከር ጥቅጥቅ ስጋ እንደባሕርዛፍ ቅርፊት እየገሸለጡ ካልበሰሉ ሽንኩርቶች ጋር ይሰጡኛል እሱን ማስገባት ቀጠልኩኝ :;
አንድ ቀን በቲቪ የሆነ ፕሮግራም ላይ የምበላዉን ክባብ ከምን እንደሚሠራ አሳየኝ የዛን ቀን የበላዉትን ብቻ መፀዳጃ ቤት ሄጄ ፋክስ አደረግኩት (አስመለስኩት )'ና ሁለተኛ ብዬ ማልኩኝ :: ከዛ እንደምንም ብዬ ምግብ ማብሰል እንዳለብኝ ወሰንኩኝ :: የመጀመሪያ ቀን ሜኑዬ እንቁላል ቅቅል ነበር ምንም ዓይነት ሙያ የማይጠይቅ ቀስ እየተባለ ይለመዳል አልኩኝ እንቁላል ቅቅሌን እየበላው ...
በማግስቱ ፓስታ ለመስራት ሞከርኩኝ ከቀላሉ መጀመር ስላለብኝ ሃሳቡ እስኪመጣልኝ ፓስታዉን ውሃ ውስጥ ከትቼ ጣድኩት ለሶስ የሚሆን ሽንኩርት ስከትፍ አነባው '

'ገና ስንትና ስንት መርዶ ይጠብቀኛል ካሁን እንባዬን ጨረስኩት 'ኮ ''
ብዬ ተውኩት በተጨናበሱ ዓይኖቼ የጣድኩትን ፓስታ ሳየው ቀበቶ ሆኗል ውሃው ከፈላ በኌላ እንደሆነ ፓስታው መግባት ያለበት መረጃው አልነበረኝም እሱን በሹካ ላለያየው ብሞክር የማይሆን ሆነብኝ ስለራበኝ ያንኑ የፓስታ ድሬድ በካቻፕ በልቼ ዋልኩኝ ::
እዚህ እንጊልዝ ውስጥ ምግብ የለም እንዴት የራሳችሁ የሆነ ባሕላዊ ምግብ የላችሁም ሲባሉ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በፊት ነበረን ብለው ማይገናኝ ነገር ያወራሉ አሁን እስቲ ምግብ አይማረክ አይደመሰስ
አንድ የሚኮሩበት ምግብ ቁርስ ነው ቤከን እና ሶሴጅ ከቢንስ ጋር ... በምላጭ የተተገሸለጠ የዓሳማ ስብ ... ቦሎቄና እንደላጲስ የደነደነ ጥቅልል ስጋ ገና ሲያዩት ሲያስጠላ በዚህ ላይ አብሮ ሚቀርበው እንቁላል አይበስልም ቢጫው አስኳል እንዳለ ሆኖ ነጩ ብቻ በመጠኑ ግግር ይላል እነሱ ግን እንዴት አድርገው ጥርግ አድርገው እንደሚበሉት በሱ ላይ ኢንግሊሽ ቲ ይደረግሙበታል ... ሕልም ሕልም የሚል ቀዝቃዛ የወተት ሻይ ...

ድሮ ሃገሬ ሆኜ የተሰደዱት ሁሉ ሹሮና በርበሬ ላኩ እያሉ ሲጨቀጭቁ እስቅ ነበር ለካስ ወደው አይደለም እዚህ የቆርቆሮ ምግብ ቢሰላቸው ነው። የታሸገ ሕይወት

እዚህ ኑሮ እንደት እንደሚኖር በታሸጉ ፖስታዎች ሕግጋት ይጀመራል ከዛ የታሸገ ብር... የታሸገገ ምግብ... የታሸገ ዕዳ... የታሸገ ተስፋ.... የታሸገ መርዶ... ብቻ ብዙ ነው አሁን አሁንማ የፍቅር ጉድኝነት በታሸገ መስኮት መሆን ከጀመረ ከራረመ መነካካት የለም በምናብ እየተሳሳሉ ብቻ ንፈቅኩሽ ናፈቅኩህ መባባል ካላስቻለ በዛው እንደተሻሸጉ አዲዮስ መባባልና ደግሞ ሌላ ተመሳሳይ መፈለግ .... ወደ ምግቤ ልመለስ

ዛሬ የስንቱን እንስት ደጅ ጠንቼ ሽንኩርት ማቁላላት ተምሪያለው የመጨናበሱም ጉዳይ የውሃ ዋና መነፅር አድርጎ ከመክተፍ ተገላግያለሁ። ቢያንስ ከለር አልባ እና ጣዕም አልባ ሹሮ አፈላለው ለእንግዳ ባይሆንም ለራሴ ይጣፍጠኛል

‘’ሹሮ ሞላ ብለሽ ውሃ ስትዶዪ

ውሃ ሞላ ብለሽ ሹሮ ስትዶዪ

ያው ድስቱም ሞላልሽ ምኑን ታማስዪ...

እያልኩኝ በቅኔ እያጣጣምኩኝ እበለዋለሁ፡ ወይም መጥፎ ወጥ በጥሩ እንጀራ ይበላል በሚለው ተረት እየተፅናናው የግዢ እንጀራዬን አሞጋግሳለሁ። ስለንጀራ ሳነሳ የሃበሻ የንግድ ቤቶች የማትረፍ ካኩሌሽናቸው እንዴት እንደሚባዛ አንድዬ ይወቀው ለነገሩ ምርጫ የላቸዉም ብለው ነው። የ ፪፭ ፒ አንድ ኪሎ ዱቄት ስንት እንጀራ እንደሚወጣው ባልሞክረዉም ተነግሮኛል ታዲያ እነሱ የሚሸጡልን እንጀራ አንዳንዴ ወደትሪ ስገለብጠው እንደእፉዬ ገላ አየር ላይ ሁሉ ይንሳፈፋል ገና ከመንጣቱ ጋርና ከሸንቃጣነቱ ጋር ሳየው እንደማያጠግበኝ ይታወቀኛል ‘’የማያጠግብ እንጀራ...’’ ብዬ እንዳልተርት ምጣዳቸው አይታይ ለነገሩ የሃበሻ ሬስቶራንቶች ሄዶ ከሚበሉት ይሻላል እዛስ አለመሄድ ይሻላል። በዚያ ሰላቢ ነጫጭባ እንጀራ ላይ በወዛች ሚጢጢ ጣባ ላይ በፊሊት ዕቃ ክዳን ማትሞላ ስጋ ያደርጉባትና በሚጥሚጣና በአዋዜ አጅበው ያቀርባሉ እንኳን ለወንድ ለወስፋታም እንስት አይበቃም... (ለነገሩ ዘንድሮ በሆድ ነገር ወንድና ሴት ማለት ይከብዳል..)

አንድ ቀን አንዲት ያገሬን ዕንስት በስልክ ስንጠዛጠዝ ለካ ሳላስበው ባለሙያ ነኝ ብዬ ዋሽቼ ኖሯል

‘’ቤት ነይ ‘’

ስላት ግብዣዬን ተናግሬ ሳልጨርስ

‘’...ሆ ዛሬ ሙያህን ልናየው ነዋ’’

አለችኝ ... ሙያሽ... የሚለዉን የነደረጀ ዘፈን ለራሴ እየዘፈንኩኝ ምንተፍረቴን አዎ አልኩኝ ምን ትወጂያለሽ ብላት

‘’ዶሮወጥ’’

አለችኝ አሁን ማን ይሙት የዘንድሮ ወንድ ቀርቶ ሴቱስ ዶሮ ይችላል በሆዴ እንደዶሮ ይረዱሽ አልኩና እንደማልችል ነገርኳት

‘’ደስ ያለህን...’’

ስትለኝ ትንሽ መለስ አለልኝ

ፍሪጅ የከረመ ስጋን ዲፍሮስት ማድረግ እንዴት እንደሚሰለቸኝ ላዩ ላይ ማፈስበት ሙቅ ውሃ እኔ ሦስቴ ሻወር እወስድበታለሁ። በቅዝቃዜ ጠርሙስ ከሆነ በድን ሥጋ ጋር መክተፊያ ላይ ስታገል ስልኬ ጭርርር! አለች

‘’በር ላይ ነኝ!’’

አሁን እስቲ ቀጠሮ ላይ ፈርንጅ ነሽ እንድላት ነው ከውካዋ! ብዬ ከፈትኩላት ለነገሩ እሷ ምን አደረገች ከውካዋው የለንደን ባቡር

ቤት ገብታ ውሸታምነቴን እና የሙያ ችግር እንዳለብኝ ስነግራት ከትከት ብላ ሳቀችብኝ ለካስ ከርሷ እኔ እሻላለሁ እሷ ወጥ ውስጥ ስኳር ምትጨምር ዓይነት ሙያ ቢስ ናት።

እናቴ ይሄ ሁሉ ታይቷት ነበር የሆዴ ነገር ቀድሞዉን ያሳሰባት ሦስት ጉልቻ አይደለም ዘጠኝ ጉልቻ ቢጎልቱ ማይሞላበት ምድር... ምግብ ሞልቶ ሙያ ችግር የሆነበት ዘመን..

አንድ ጊዜ ምስር ወጥ አምሮኝ አንዲት ጓደኛዬን

‘’ስለምስር ወጥ አሰራር አስረጂኝ’

ብላት ሙልቅቅ ብላ

‘’እኔ ሃገሬ ምስር ምበላው ሰውቤት ስሄድ ብቻ ነበር እኛ ቤት እሱና ሹሮ ገብተው አያውቁም’

አለችኝ በሷ ቤት የኑሮ መሠረቷን ከፍ ከፍ ማድረጓ ነው አሁን ማን ይሙት ምስር የድሕነት ማሕረግ መሆኑ ነው፧ እናም እያማረኝ መስራት ስላልቻልኩኝ ምስር ወጥ ሳይሆን የምስር ሳምቡሳ አረቦች ቤት ሄጄ በላው።ቀሪዉን ለማንበብ ሌባ ጣትዎን እና ዓይንዎን ልዋስና ይከተሉኝ እቺን ጠንቆል ያድርጉ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby yammi » Fri Nov 13, 2009 9:33 pm

:lol: :lol: :lol: ዋንሼ እንደምንም ብዬ ሰሞኑን ዶሮ ቢጤ ሰራርቼ ምሳ ልጋብዝህ አስቤ ነበር ተውኩት በቃ.........እያላመጥክ(መቼም አልበላም አትልም )...
""አይ ሞያ ዶሮ ተሰርቶ ተሙቷዋል"" ስትለኝ ታየኝ :lol: :lol:
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby sarandem » Sun Nov 15, 2009 8:32 am

ውይ ስደትና ሆድ ምትለዋን መጣጥፍ በጣም ነበር የተመቸችኝ:: ድጋሞ ላነባት ስመጣ ምን እንደሰወራት እግዜሩ ይወቅ::
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby ትርንጎ* » Sun Nov 15, 2009 2:30 pm

:lol: የስንቱን ቁስል ነካካኸው...ኧረ እኛም (ሴቶቹ) "እጅ ያስቆረጥማል" እያልን ስንቱን ጉድ ውጠናል...መቼም መውደድ እብደት አይደል:: የአሜሪካው ጤፍ...ቂቂቂቂ...በቀደም አንድ ጉዋደኛዬ በስልክ ማዘዝ እንደምችል ሲነግረኝ ነበር እኮ! አይ ዋንሽ :D ...ገበሬውም አሜሪካ ተሰድዋል...እኮ!
Code: Select all
እዚህ ኑሮ እንደት እንደሚኖር በታሸጉ ፖስታዎች ሕግጋት ይጀመራል ከዛ የታሸገ ብር ... የታሸገገ ምግብ ... የታሸገ ዕዳ ... የታሸገ ተስፋ .... የታሸገ መርዶ ... ብቻ ብዙ ነው አሁን አሁንማ የፍቅር ጉድኝነት በታሸገ መስኮት መሆን ከጀመረ ከራረመ መነካካት የለም በምናብ እየተሳሳሉ ብቻ ንፈቅኩሽ ናፈቅኩህ መባባል ካላስቻለ በዛው እንደተሻሸጉ አዲዮስ መባባልና ደግሞ ሌላ ተመሳሳይ መፈለግ .... ወደ ምግቤ ልመለስ


ድንቅ እይታ!!! ድንቅ አገላለፅ!!!

ያሚታ ቆንጆ እጅ ነስቻለሁ::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 716
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ምረቱ » Sun Nov 15, 2009 7:56 pm

ሰላም ዋናው

ንባብ ነገር ሲደብረኝ ወደ ዋርካ መሄድ ይቀናኝ ነበር...ይኼን ፌስ ቡክ የሚሉት ነገር መጠቀም ሳልጀምር በፊት... ዋርካ እኮ ብታዘናጋም የልብ ታደርሳለች ...ከበየአይነቱ ሀሳብ; ከበየአይነቱ ሰው; ከበየአይነቱ ፍላጎት ... ከበየአይነቱ ቀልድ ሀገራዊና ባህላዊ ለዛውም ሳይሟጠጥ ታንበሻብሻለች:: ፌስ ቡክ በደረቁ ( በ lol እና በ yup ብቻ) የገጹ ተገዢ ሊያደርገኝ እየሞከረ ነው...እንድ ቀን ጥርቅም የማረገው ይመስለኛል...

እስቲ ዛሬ ዋርካ ላይ ሀንግ አውት ላርግ ብየ ወደ ስነ-ጽሁፍ ሰመጣ ...ዓይኔ ኮሮጆህ ላይ ማረፍ...ከዛ ስክሮል ሳደርግ "ስደት እና ኑሮን' አገኘሁ...

እዚህ ኑሮ እንደት እንደሚኖር በታሸጉ ፖስታዎች ሕግጋት ይጀመራል ከዛ የታሸገ ብር... የታሸገገ ምግብ... የታሸገ ዕዳ... የታሸገ ተስፋ.... የታሸገ መርዶ... ብቻ ብዙ ነው አሁን አሁንማ የፍቅር ጉድኝነት በታሸገ መስኮት መሆን ከጀመረ ከራረመ መነካካት የለም በምናብ እየተሳሳሉ ብቻ ንፈቅኩሽ ናፈቅኩህ መባባል ካላስቻለ በዛው እንደተሻሸጉ አዲዮስ መባባልና ደግሞ ሌላ ተመሳሳይ መፈለግ ....


ግሩም ትዝብት ነው ...ምን ሀሳብ መጣብኝ ...ይቺን ራሱአን ለዮዮ እህት እና ወንድሞች በሚገባ መልኩ አርጌ ፌስ ቡክ ላይ መለጠፍ...እንዴት ትላለህ? በነካ እጂህ ብትሞክራትማ እንዴት ጥሩ ነበር ...

ምረቱ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby Tጂ » Mon Nov 16, 2009 3:20 am

ትርንጎ እንደጻፈችው
ድንቅ እይታ !!! ድንቅ አገላለፅ !!!

ትክክል!!
ግን ስንት ጉዋደኞቼን አስታወስከኝ
“Love is like the wind, you can't see it but you can feel it."
Tጂ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 301
Joined: Sat Aug 11, 2007 3:59 am

Postby እንሰት » Mon Nov 16, 2009 6:28 am

ዋናው wrote:መጣው... አንዴ ይላል
-ለመሄድ ተነስቶ
መሄድ እና መምጣት
-ትርጉሙ ተምታቶ


ሸጋ ቅኔ እንዲሁ ሳስባት የአማርኛ የመስተዋት ምስል ትመስለኛለች:: ይቺን አሁን ምን ብለን ነው ቃል በቃል የምንተረጉማት?
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby sleepless girl » Tue Nov 17, 2009 12:29 am

ዋናው wrote:በጀርባ ተንጋለን
-ኳክብት የቆጠርነው
ጨረቃን እየሞቅን
-እርቃን የተኛነው
አሸዋን ደልድለን
-መደብ ያበጀነው
ተጃጅለን ሳይሆን
-ስሜት አስክሮን ነው::

መሃበሉ ሲፎክር
-ጨለማዉም ሲበረታ
ስካራችን ቅኔ ሆኖ
-በድቅድቁ መች ተፈታ?
.
.
.
አንቺ እኔ ውስጥ...
-እኔ አንቺ ውስጥ ተኝቼ
ሕልሜን ስትሰርቂኝ
-ቅዠትሽን አይቼ
ባንኜ ተነሳው
-በ ጎሕ ብረሐን በርቼ

ራስምታት ሆኖ አጭር ትዝታችን
-አጭር ስካራችን
በፍቅር ሀንግ ኦቨር
-ዳግም ተሳከርን::


ዋንሽ..........ይህችኛዋ በጣም ትመቻለች!!! ደጋግሜ ነው ያነብኳት ከምር....... :wink:
Nothing is impossible!!
sleepless girl
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1510
Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
Location: near u!

Postby ዋናው » Tue Nov 17, 2009 3:33 am

yammi wrote::lol: :lol: :lol: ዋንሼ እንደምንም ብዬ ሰሞኑን ዶሮ ቢጤ ሰራርቼ ምሳ ልጋብዝህ አስቤ ነበር ተውኩት በቃ.........እያላመጥክ(መቼም አልበላም አትልም )...
""አይ ሞያ ዶሮ ተሰርቶ ተሙቷዋል"" ስትለኝ ታየኝ :lol: :lol:

ያሚታዬ... ግዴለም ብቻ አንቺ ስሪው ባይሆን ለወደፊትም የሚሆን ህግ እናወታ ይሆናል ዶሮ ወጥ ሲሰራ 12ቱ ብልቶች የሚቆጠሩ እና የማይቆጠሩበት ብለን በሁለት እንከፍለዋለን :: :lol: :lol: :lol:
አሁንስ 1ኛዬን እንደ ደጉሸት ቬጂ ልሁን መሠለኝ ....
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests