የዋናው አቁማዳ==>ሸራ ስላልወጠርኩ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ያ...

Postby ዋኖስ » Mon May 01, 2006 6:36 pm

:roll: ያ ! ይገባኛል ግና ቅቅ 8ቱ የንግግር ክፍሎች ዉስጥ ልመድባቸዉ ሥጥር የአማርኛ ሶፍት-ዌሬ አልቀበልልኝ አለ ና ተቸገርኩ!! ቅቅቅቅ... እስኪ ቀጥል ምናልባት ዓዲስ አማርኛ ትፈጥር ይኆናል! ማን ያዉቃል!ቅቅ

ዋኖክሥኛ ( የአንተዉን ነው የኔዉን አይደለም)
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Mon May 01, 2006 7:06 pm

ዘጠኝ ሰሀት ሆነ
ትንሣሔውም ሆነ

ዶሮ ግን አልጮወም
-በግ ነው የባነነ
ኩስም አልሸተተ
-ሽንኩርት አልታጠነ

ጉንፋን ተጎናጽፈው
ዛሬን ነጻ ወጥተው
''እኔን የነካህ...?'' ብለው
እዚህም ሞት እዛም ሞት
-ብለው ተሰላልቀው
ጥሬም ቢያጡ ጭረው
የፋሲካን ቢላ ማለፉን አመሰግነው

ደምም አልፈሰሰ
የዛሬስ ፋሲካ
-በዳቦ ኣለፈ::
ጉንፋናማው ዓውዳመት
-እንዲህ እንደቀፈፈ

ዋናው_________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

ተብታባዉ

Postby ዋኖስ » Mon May 01, 2006 8:05 pm

:roll: ተብታባዉ የብዕር-ሰዉ ልበልሕ ይኆን!!

ምን!! ይሻለኛል እሄን ፊደል-ገደፋሕን!! እረ በፈጠረሕ ዒዲት አድርግ ቅቅቅቅ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Sun May 07, 2006 7:13 pm

እሺ ወዳጄ ዋኖስ ሰሞኑን ጸሀፊ ለመቅጠር እያሰብኩ ነውና እስቲ የተሻለ ያልገደፈ ፅሑፍ ላቀርብ እሞክራለሁ ቅቅቅ

ግን አመስግኜያለሁ::

ዋናው_________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon May 08, 2006 4:19 pm

ፊደል አንኳኩቼ
ምናብ አንጋግቼ
በምጥ የወለድኩት ሐሳቤን አምጥቼ
ኪ-ቦርድ ቀብቅቤ ሞኒተር ላይ አፍጥጬ
ጽፌ ውልደተ-ሀሳብ
አትሜ በምናብ
ደቂቃን ደቅድቄ
-ቃላትን ስሾርብ......
አጣጥሜው ዳግም
-ላንባቢዬ ሳስብ

ሰብሚት አልኩትና
ፎረም ሳይደርስ ገና
ጠፋብኝ ፅሁፌ እንደጉም ተነነና
የመረጃው መረብ
-ውጦ አስቀረውና::

አያድርስ እናንተዬ የዚህ ዓይነት ፈተና


ዋናው_______________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed May 10, 2006 1:38 pm

አንቺ የፀደይ አበባ...
የፍንጥቅ ብርሀን
-የፍቅር ጌጥ ካባ
የህይወት ምሳሌ
-የጣዝማ ወለላ

ፍቅርሽ አነፈረኝ
በቁሜ አናወዘኝ
ውስጤን እያጦዘኝ
የመታደል ህግን
-ለስሙ አስይዞኝ
ልከተልሽ ደግሞ ኮቴሽን ልመርምር
ባጣም ባገኝሽም በፍለጋ ልዙር
ዓለም'ንድሆን ጠቧል ሳላገኝሽ አልቀር
ጦስሽ አስክሮኛል አንቆኛል በፍቅር

የጨቅላ ንፍዘቴን
የድንግል ስሜቴን
ዛሬን ተናንቆብኝ ባየው ድሮነቴን

ዳግም ተጸንሼ
ለወተት አልቅሼ
በፍቅርሽ ሙጠምጢምወዲህ ተመልሼ
ዛሬን ተጃጅዬ አንቺን ስል አልቅሼ
.
.
.
ዋናው______________________________________:[/url]
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sat May 13, 2006 9:51 pm

____ሕልሜን በሕልሜ አየሁት____

ነፍሴ ተንሳፈፈች
በዕንቅልፍ እየጦዘች
በደከመ ዕይታ ብርኃን 'የሸሸች
በአልጋ ተፈናጣ ሠማያት 'የሮጠች

በሕልም ዓለም ነውልዬ
በቅኔ ድንግዝግዝ ስጋዬን እዛ ጥዬ
አየው ምስቅልቅሉን
-ይመስለኛል ብዬ
ቀለም ባልጎላበት
-ምስል ገፅ አስተውዬ

ብቻ እዛም ስር ቦዝዤ
በስጋት ፈዝዤ
አየውት ዕኔነቴን በድካም ነፍዤ

አሁንም ዝዬ በጣም ድካሜ መጣና
ድል አልባው ዕንቅልፌ ዓይኔን ጨፈነና
ዳግም ተብረክርኬ አሸላለብኩና
ስብጥርጥር ዕይታን ፈጠጥኩ ዕንደገና::
ኣለምኩ ሌላ ሕልም አሁንም ተኛውና
ሕልምን ሕልም ወልዶት
-ሳይይፈታ እንደገና
.
.
.
ዛሬስ ማን ይፍታልኝ
ማን ይጠንቁልልኝ
የንሁስ ሕልምን ሚስጥር
-ማን ይመርምርልኝ?

ዋናው____________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon May 15, 2006 4:22 pm

.
.
.
ጠዋትን ማልጄ ከሕልሜ ስባንን
ዓይኔን ሳብስ በጄ ሳየው ሕያውነቴ
ያሰለሰ ሕልም እየወረረው ውስጤን
ዓይኖቼ ደንብረው ቢያበሩት ቀኔን
ለካስ ሕልም ነበር
ይሄም መደናበር
የኔ ማግጠጥ__ ለዛሬ መደንበር

ምስል አመጣ ዓይኔ::
ዳሰሰው በድኔ:
ሸተተው አፍንጭዬ ::
-'እፎይ!' አለ ጎኔ::
ግና__ካልኖርኩበት
-የትኛው ነው የኔ?
በምን ይታወቃል
-ከሕልም መባነኔ__________________?


ዋናው___________________________________::
[/list]
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby አወዳይጫት » Mon May 15, 2006 5:19 pm

ወንድም ጽሁፍህ ይመቻል...ትቅሚያለሽ እንደ 8) አነጋገርህ እንደመረቀነ ስው ነው.
ethiopia will naver be colonised by meles
አወዳይጫት
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 7
Joined: Thu Aug 25, 2005 5:47 pm
Location: canada

Postby ዋናው » Thu May 18, 2006 4:43 pm

ቅቅቅቅ አቶ አወዳይ ሠላም
በቅድሚያ ለአድናቆትኦ አመሰግናለሁ
እኔ ግን የብህር ዙርባ ውስጤን ያመረቀነው እንጂ ከጫቱ'ንክዋን እምብዛም ነኝ::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun May 21, 2006 7:17 pm

ኃሣብና ስሜት ባንድነት ተጣምረው
ሆኖ ሲታዘበው ልብን ልብ ሊለው
የመሆንን አለመሆን
-ድርጊቱ ቢያስቆጣው
እንደሌላው ኬሬዳሽ
ብሎ ንቆ ሳይተው

ይፍልቃል ስንኙ
-ይሾረባል ቃሉ
ይወርዳል ጥበቡ
-ሀቅ ስሜት ሲሉ
በደም የሾለከን
-የአፈር ሚሥጥር ካሉ
የውላጅ እኔነት
-አርፍደውም ቢያበቅሉ
.
.
.
_________________ለዳሞት ነው እቀጥላለሁ::

ዋናው_______________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri May 26, 2006 7:01 pm

.
.
.
ብህር ያጮልቃል
አሻግሮ ማዶውን
-ወንዙን ሁሉ ይቀዝፋል

ያስቃዣል ምናቡ
ያስሮጣል በቀልቡ
ይሄዳል በትዝታ
-የክታቡን ውል ሲያስቡ
የቅኔውን ፍተሀት
-በዳንቴሉ ቃሉ...

ስሜት ማንነቱ በውስጡ ገንፍሎ
በቃላት ውዥንብር ሚስጥር ሚስጥር ብሎ
ያረገዘ ፊደል ላይወልድ እንደበቅሎ
ብቻ በምጥ ዝሎ
ቋንቋ መወለድን ባፈር አንከባሎ

ወንጌልን ላልደገምን
መልህክተን ላልቆጠርን
ላቦጊዳ ሽፍቶች ፈረንጅን ላስቀደምን...
ፎቅ ነው ሕሳብ-ቃሉ
ጠጣር ነው ፊደሉ
ቅኔ ነው ሓሳቡ...
ብለን ፉካረ-እልሁን
-በደንብ ሳናጤነው
የደም ቃሉን ህትመት
-ላደራው ሳንበቃው
.
.
.
እሱስ ውልደቱ ነው የግዴታው አሻራ
ገሳ ነው ልባሱ ዘ-ቅኔ ዋሸራ
ይፈልቃል ጅረቱ ትውልዱን እየጠራ
እድሜውን አለምልሞ ያኑሮው ባደራ::

_________________ለ ዝነኛው ገጣሚ ዳሞት/ዋኖስ

ዋናው____________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

ቅቅቅ...

Postby ዋኖስ » Sat May 27, 2006 6:07 am

:roll: እዚሕ ጋም ተጀምሯል! ቅቅ


ኧረ ! በቃ ይቅር ይሕ ቅኔ መወድሥ

ጆንያዬ ሞልቷል እኔ አልጪንም ፈረሥ::

በሽሩቡ-ኆሄ ደም-ግባት ባነቀዉ

ዘ-ቅኔ-ዋሸራሕ መድረኩን ቢሞላዉ

"ኃሴት" አሰከረኝ እዚሕ ገባሁ እሄው::

ዕንደ-ቀለም ቅቡ ሾርቦ-በፊደል

ሕብር-ሥንጥር ሚስጢር ሕያዊነት ቃል

አስዉበሕ ማቅርቡ እጂግ ይደነቃል::

=====ዳሞት========
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Tue Jun 06, 2006 7:33 pm

..........(666)...........

________ዕለተ ሤይጣን_______

ዛሬ ስድስተኛው ቀን ስድስተኛው ወር ሁለት ሺ ስድስተኛው አመትምህረት ነው:: እዚህ ለንደን ትራፋልጋር የተባለ ስፍራ እና ካምደን ታውን የተባለ ስፋር ዕለቱ ይከበራል ልክ ይህንን እኔ ስፅፍ እዛ ሤይጣን እየተወደሰ ነው: ኦመን የተሰኘ ስለሠይጣን የሚተርክ ፊልምም እዚህ ለንደን ለህዝብ መቅረብ የሚጀምረው ዛሬ ነው::
ትላንትና አንድ ጋዜጣ ላይ ያነበብኩት በዚች ቀን ከናቱ ማህፀን የወጣ ህፃን ሲያድግ እንደነማን አይነት ሰዎች ሊሆን እንደሚችል የተነበዩ...ሰዎቹ አብዛኛዎቹ ሲሪያል ኪለር የሚሏቸው ዓይነቶች ናቸው
ሠዎች ለምንድነው ውስጣቸው ያለውን እኩይ ባህሪ አስተናግደው በገደብ አልባ ነፃነት ብዙዋን የማይቀበለውን ድርጊት ለመፈፀም የሚያስደስታቸው?
ጥቁር ቀለም ለሠይጣናዊ መንፈስ መሸለሙ ያናደደን ጥቁር አፍሪካዊያን ብዙ ነን ምክኛቱም ይህ መንፈስ እኛን ዲስክሪምኔት ያደርጋል ብለን እናስባለን በርግጥ ለዛ አላማ ከተተኮረበት እነሱ እንደሚሉት ፕረጂድስ ነው:: ግን እንደ ቀለም ስነልቦናዊ ስናየው ጥቁር ቀለም ጨለማ ነው ብርሀን ሊሆን የማይችል ብርሀንን መልሶ የማያንፀባርቅ ስትሮንግ ኦፔክ ቀለም ጥቁር ነው:: ሰው ሲያገባ ነጭ ይለብሳል ሰው ሲሞት ጥቁር ይለበሳል ለምን? ይህንን ስነልቦናዊ ስሜት ማን ፈጠረው? እኔንጃ ነጭ የንፁሕነት ተምሰሌት እንደሆነ መ/ቅዱስ ውስጥ ሁሉ አለ:: አንድ ጊዜ አንድ የማውቀው ባበሻ አገላለፅ (ጠማማ) የሚባል አይነት ሁሉ ነገሩ ግራ የሆነ ሰው ''እኔ ሳገባ ሚስቴ ጥቁር ቬሎ ለብሳ ነው የምትሞሸረው እኔም እንደዛ'' ሲል ሁሉም ሠው ''ሟርተኛ!!!!'' ብሎ ጮኸበት::

ዛሬ ይህንን ቀለማዊ ወሬ ያመጣውት ዕለቱን ሊያከብሩ የሚሰማሩት ሰዎች አልባሳታቸው ጥቁር በመሆኑ ነው: እናንተስ ስለዚህ ቀን የተለየ ገጠመኝ ይኖራችሁ ይሆን? እኔንጃ....
እስቲ እኔ ስንኝ ልቋጥር
.
.
.
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Tue Jun 06, 2006 7:52 pm

.
.
.
ፈረሠኛው ሚካኤል በጦሩ እንደወጋው
ጥፍሩን አሳድጎ ሽቅብ ያቃሰተው
ጠይሙ መልከኛ በዕሳት የታቀፈው
ስሙን አሤይጢነው
በነጭ አስዶቅሰው....

ሌላ ነው በውስጤ ዕርኩስን የሳልኩት
ጥፍሩም አልሾለም ቀንድም አልሸለምኩት
ፊቱም የገረጣ ነጭ ነው የሳልኩት

ደሙንም አልጠጣ
አመድ ላይ አልተሰጣ
ኣተላም አይሻም እሱ መች ስራ አጣ...
.
.
.
ቢከበር ዕለቱ
ሚስጥረ ቁጥሩ
መንፈሱን የታደሉ
-ለዕኩይ ሆ! ቢሉ
እርኩሳስን ስሜት
- ለርሱ ቢገብሩ

ላማትብን'ጂ እኔ ይሰውረኝ ብዬ
ከሤይጣኖች ሰፈር መስቀሌን አሹዬ
ለዚች ሸክላ ምድር
ላስስገበገብ ምዬ....
ይረጭ ዛሬ ደጄ
ጧፉን ይዤ በጄ
መለዐክት አማልጄ

ዋናው_________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests