የዋናው አቁማዳ==>ሸራ ስላልወጠርኩ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዋናው » Tue Nov 17, 2009 3:37 am

ለ ሥሠረንደም
ትርንጎ
ምረቱ (ጥሩ ሃሣብ ነው)
ቲጂ
እንሰት እና
እንቅልፍ-ዓልባዋ

ምስጋናዬ ይድረሳችሁ::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed Nov 25, 2009 12:41 am

::
Last edited by ዋናው on Sat Apr 17, 2010 8:32 pm, edited 1 time in total.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sat Apr 17, 2010 8:30 pm


የሚነጋ ሌሊት እንደማይነጋ ረዝሞ
መንጊያው ሲቃረብ እጥፉን ጨልሞ
በጀምበር ሲነጠቅ አልጠበቀም ቆሞ::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun May 09, 2010 1:53 pm

ግማሽ እንስት

ስሜትሽ አስክሮኝ
-ፀጉርሽን ብዳብስ
የኔ አይደልም አልሽኝ::
ልቤ እየደለቀ
-ጡቶችን ብጨምቅ
ላስቲክ ጎረበጠኝ
ፍቅርሽን ፍለጋ
-ዓይኖችሽ ላይ ባፈጥ
ሽፋሽፍትሽ በዝቶ
-ቀልሞ ሲፈራገጥ
ጥፍርሽም ረዝሞ
-ቀንድነቱ ሲፈጥ
ፊትሽ ደቁቶብኝ
-አንዳች ሲቅለጠለጥ

ግማሽ እንስት ግማሽ ዘመን
-ማፍቀሬ
የሮጠው ስሜቴን ገታው
-ባቅፍሽም አፍሬ

(ለዘገደ-ውልቄ... ወግ)

ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

ቅቅቅቅ

Postby ዋኖስ » Sun May 09, 2010 3:18 pm

በል አይዋ! የሴት አብዮት እንዳታስነሳብን! ቅቅቅ የነሱን ነገር "ድብቅ" ነው::

ሄይ! ማዘርስ! "ኃፒይ ማዘርስ ዴይ!"
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Mon May 17, 2010 1:17 am

ትላንት
እኔን አያርገኝ ብዬ
-ዝቼብሽ ነበረ
ስሜቴ አኩርፎ
-ውስጤ እየመረረ
.
.
.
ዛሬን ግን ስታስቂኝ
-ሃዘኔም ቂሜም በረረ::

ቀንዬ ሞኝ ነኝ አይደል?
ስትነፍጊኝ አኩርፌ
-ስትሰጪኝ 'ምባበል

ይሄ ሠውኛ ፈሊጥ
-እየገባሽ ምስጢሩ
አንቺም ድር...ቅ ብለሽ
-በኛ ላይ ማምረሩ
መች ይሆን 'ሚቆመው
አጉል መቋመሩ?
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Tue May 25, 2010 1:25 pm

ደራርቦ ሲመጣ
-ቤት-ለንግዳ አለቸው
ነግቶ ሲለያዩ
-ዕርቃኑን ሸኘችው::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Re: ቅቅቅቅ

Postby ዋናው » Tue May 25, 2010 1:28 pm

ዋኖስ wrote:በል አይዋ! የሴት አብዮት እንዳታስነሳብን! ቅቅቅ የነሱን ነገር "ድብቅ" ነው::
"


አይዋ... ዘገደ-ውልቄና ጦምኔው ናቸው አብዮቱን የቀሰቀሱት እኔ አይደለሁም::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Re: ቅቅቅቅ

Postby ዋኖስ » Tue May 25, 2010 10:52 pm

አይዋ! በል አሁንም ከጋሸ ዘገደ-ዉልቄውና ከጋሸ ዉቃው ጋር እንዳታቀያይመኝ:: ቅቅቅ ተዉ ብያለሁ!

ቆይ ግን ብዙ ጠፋህ እኮ በሰላም ነው? ሰዉ አይናፍቃችሁም?

አቤት! ዘመን!

ኑርልኝ ብቻ!!

ከመልካም አክብሮት ጋ

ዳሞት ከዳሞትዋናው wrote:
ዋኖስ wrote:በል አይዋ! የሴት አብዮት እንዳታስነሳብን! ቅቅቅ የነሱን ነገር "ድብቅ" ነው::
"


አይዋ... ዘገደ-ውልቄና ጦምኔው ናቸው አብዮቱን የቀሰቀሱት እኔ አይደለሁም::
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Sat Jun 12, 2010 2:51 pm

መስካቸዉን አለምልመህ
በየማዕዘናቱ እንደባሕር አስፍተህ
ሥራህ 'ንዳይደነቅ ብረሐን ምነው አጠረህ?

አይድ ፓርክ
ሎንዶን

ዋናው
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby yammi » Mon Jun 14, 2010 8:32 am

ዋንሼ ..ድንቅ ነው ግሩም ታዝበሀል> እኔማ የግጥም ቆሌ ከሸሸኝ ወራቶች አልፈው አመታቶች እየመጡ ነው.... እስቲ ባይሆን የናንተን እያነበብኩ ልለማመጠው//// እኔ የምለው መቼ ነው በ ሰባት ዋርካ ዛፍ የታጠርከው ...ቱ ቱ ቱ ከአይን ያውጣህ ብያለሁ!
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

ያሚ

Postby ዋኖስ » Tue Jun 15, 2010 7:39 pm

ሰላም ያሚታ!

የአይዋዉ`ኮ "ግራር" እንጂ ዋርካ አይደለም:: ዋርካን ከኔ ተመልከች!: :D

ደግሞ እሱ አጠገብሽ ያለዉ ነገር እንደ ዋርካዉ አድጓል: :D

ከመልካም አክብሮት ጋ!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Wed Jun 16, 2010 12:15 am

ያሚታዬ ያንቺን ብሕር ኸከደከ ሰይጣን ብለን ማስረጨት አለብን... ወይኔ ግን መናዘዝ የጀመረ ለት....? ማነህ አንተ? ተብሎ ሲጠበጠብ ዝክዝክ ሲያደርገው .... ያኔ ነው ስንኞችሽን ማሳደድ

መሪጌታ 7 ዓመታት? የአንድ ጎረምሳ ዕድሜ...? አይደለም ሰባት ዋርካ ሰባት ዋሻስ ቢመረቅልኝ... ግራሩ ግን ተመችቶኛል
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby እአምሮ » Fri Jun 18, 2010 10:24 am

ዋናው ........በየቤቱ ያለውን የስሜት ዥዋዥዌ በጣም አድርግህ ገልጽከው :: ድንቅ ነው ወዳጄ::


ዋናው wrote:ትላንት
እኔን አያርገኝ ብዬ
-ዝቼብሽ ነበረ
ስሜቴ አኩርፎ
-ውስጤ እየመረረ
.
.
.
ዛሬን ግን ስታስቂኝ
-ሃዘኔም ቂሜም በረረ::

ቀንዬ ሞኝ ነኝ አይደል?
ስትነፍጊኝ አኩርፌ
-ስትሰጪኝ 'ምባበል

ይሄ ሠውኛ ፈሊጥ
-እየገባሽ ምስጢሩ
አንቺም ድር...ቅ ብለሽ
-በኛ ላይ ማምረሩ
መች ይሆን 'ሚቆመው
አጉል መቋመሩ?
እአምሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Mon Apr 12, 2004 12:35 pm

Postby ዋናው » Mon Jul 05, 2010 10:47 pm

ሀበሻ ሲባል.... ብለን እየተኳነን
ራስን መውቀሱ አባዜው ሳይተወን
ባንዳችን በሽታ ሁላችን እየታመምን
ባበሻነታችን እኛኑ ረግመን
እየው እንዳለን አለን ሀበሾች ተብለን::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], Google Adsense [Bot] and 12 guests