የዋናው አቁማዳ==>ሸራ ስላልወጠርኩ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

እስኪ

Postby ዋኖስ » Tue Jun 06, 2006 8:35 pm

.
.
.
.

<B><I>ቢከበር ዕለቱ
ሚስጥረ ቁጥሩ
መንፈሱን የታደሉ
-ለዕኩይ ሆ! ቢሉ
እርኩሳስን ስሜት
- ለርሱ ቢገብሩ

ላማትብን'ጂ እኔ ይሰውረኝ ብዬ
ከሤይጣኖች ሰፈር መስቀሌን አሹዬ
ለዚች ሸክላ ምድር
ላስስገበገብ ምዬ....
ይረጭ ዛሬ ደጄ
ጧፉን ይዤ በጄ
መለዐክት አማልጄ</B></I>


ከግጥም ብሥለት:- ፍሠት:-ጥንካሬ:- እንዲሁም ግልፅነት:- መልዕክት አስተላላፊነት:- ተነባቢነት አኳያ እስኪ ይመልከቱት!!ዋናው_________________________________:uote]
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Sun Jun 11, 2006 7:40 pm

ሠላም ዋኖሠ-ዳሞት

ለአንባቢነትህና ለጥልቀት ምታሬህ አመሰግናለሁ ጥበብ የሚያሳድዱህ አይኖችህ ይጉሉልህ ለዘላለሙ::
የጠየቅከው ጥያቄ ግን ትንሽ ግር ስላለልኝ ነው ማለቴ እኔን እንዳንቱታ ጠይቀህኝ ከሆነ ለግጥሙ ደረጃ .....በጓዳም ብቅ ብል ጥቆማ አልተውክልኝ እስቲ ዳግም ሹክ በልልኝማ አያ ዳሞት...... ሰሞኑን ደግሞ ትንሽ ሩጫው አፉዞኝ ከርሜ ነው ቅቅቅቅ

ከብዙ አያል ማክበር ጋር

ዋናው__________________________________::
Last edited by ዋናው on Mon Jun 12, 2006 7:39 pm, edited 1 time in total.
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun Jun 11, 2006 8:58 pm

አራት መሀዘን ጨረቃ
ከደጃፌ በርታ ከፀሐይ ብርሀን ሰርቃ
በምናብ አሳስቃ
ኩዋክብትን ዘባርቃ
ጥላ ግርዶሽ ተንኖ
ነፍሰ__ሥጋ በጥርጣሬ ሆኖ
በሞት ቅኔ ተሸፍኖ
በልዝብ ስብጥርጥር ዕይታን ተጭኖ
.
.
.
የዳንኤል ምስጦች ከታች ሲንጫጩ (ሠዓሊ ዳኔል ታዬ)
ነፍስን አሽቀንጥረው ስጋን እየነጩ
በደብዘ ፅልመታት ጨለማ እየረጩ

ያኮርፋል ብርሀን ይሰለባል ጥላ
አውታረ ዕይታ በፅልመት ሲበላ
ባለመኖር ትርጉም ሙግቱ ሲብላላ.......

እናም..... ከደጄ ያሾፈች
ቅርጿን የቀየረች
ዕይታን የሰጠች
ያቺ...አራት መሀዘን ጨረቃ
በአውታሯ መፎዜ በጣም ተሳስቃ
በጥላዬ መነጠቅ ለሹፈት ተሳልቃ
እኔም ተንሰፍርሬ___________(ተንሳፍፌ+በርሬ)
-ቀዥብሬ ሳበቃ
የዕወነታ ዓለም አድባር
-ከንቅልፉ ሲነቃ
የስብጥርጥርን ጥግ
-ወዲያ እያስጠጋ
.
.
.
ዋናው__________________________________::
[/list]
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed Jun 14, 2006 5:29 pm

.
.
.
የጀንበር ውላጅን ለዓይን እያስወጋ
ድቅድቁን ምስጢራት እንደ ኳስ እየለጋ
ያባንናል ከእሁን?
ያባንናላ ከንቅልፍ.....ዕልማለም ሳያበቃ?
?
?
?

ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Jun 19, 2006 7:03 pm

________ድንገት ልምጣ ባክሽ_______
(ስደት የሰለቸው ሠው መለዕክት)

አልቋጠርኩም ስንቄን
አልሸከፍኩም ጨርቄን
እስቲ ልምጣ እናቴ
-አትዪብኝ እጄን
ዶልዱሞ ዖና ነው
-ተሸክሞ ዕድሌን

ሳታረጂ ላይሽ ቃሌን አቀብዬ
እኔ ደከምኩልሽ በስደት በስዬ
የሰው አገር ሳቀና ሁሉ ያልፋል ብዬ
እምባም ነጥፎብኛል እያልኩ እዬዬ...

በዛሬ ጉልበቴ ነገን እየሸመትኩ
ጓዜን ለመቀርቀብ እኔ'ንድሆን አልታደልኩ
ወይ አልገረጣው ፈረንጅ ነኝ አላልኩ
አልሆነልኝም በቃ ልምጣ እናቴ
ብቀበርም እዛው ይሻላል እንደ ዕትብቴ
ውቃቤዬ ነግሮኛል እንዳልሆነ ይሄ ቤቴ
ቀርጥፌ የበላሁትን ዓመታትን ትቼ
በዕጣ-ፈንታ ሥም መሐደር አሰርቼ
ልምጣ እስቲ ባዶ እጄን
-ድንገት ተነስቼ
.
.
.
ያልፋል... እንዳትዪኝ ደክሞኛል እናቴ
በስደት መከራ ፈርሷል እኔ ኣናቴ
እዛ ሆኜ ልርዳሽ ባገር ምድር ቤቴ
እጅህ ከምን ካላልሽ አለ ጤንነቴ
እስቲ ላዝግም በቃ
ስደቴም ይብቃ
ዕድሜ ያስተምረኝ ለአገሬም ልብቃ
ቁልቁል እየታየው በሰው አገር አለቃ
ለሰው ስልጣኔ ማልጄ ስነቃ
ጉልበቴም ራደ እግሬ ሁሉ ነቃ

አንተ ብቻ ና በይኝ እባክሽን
ማየት ጓጉቼያለሁ ንፁህ ፈገግታሽን
እናቴ ደክሞኛል ሳልሞት እስቲ እቀፊኝ

ለማይሞላ ስንቅ ዓመታት ቆጥሬ
የዘር ድህነትን ለመገዝገዝ ጥሬ
ዛሬን እያጠላው ጀንበር ተበድሬ
የውሸት ፈገግታን አጉል ቀባጥሬ
...ምነው ቢቀርብኝ ባልወጣ ካገሬ
ብቸገርም እዛ ብራብም እንደዘሬ
.
.
.
በቃኝ ልምጣ እናቴ
ከርክሷል ጉበቴ
ስንቄንም ሳልሰንቅ ልገስግስ ከቤቴ

አበባም አልፈልግ ፊትሽ ያጠግበኛል
የዋህ ገፅሽን ካየሁ ይበቃኛል
.
.
.
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

ዛሬ ገና ረካሁ!

Postby ዋኖስ » Mon Jun 19, 2006 11:25 pm

:roll: ዛሬ ገና ረካሁ!

መልዕክትሕ ትየባሕ ሁሉም ነገር ሳየዉ

ዛሬ ገና ረካሁ ከላይ ባሰፈርኸው::

እንዲሕ ነው ሥንኙ! እንዲሕ ነዉ መቋጠር

ሣልሳዊ ዉሕደት በትርጉም ሲፈጠር::

የዉሥጥን ዕሳቦት ያለሕን ለእናትሕ

ቀናዒ-አንደበትን ሠላምን ሠንቀሕ

ሥትመኝ ማዬቴ በሥንኝ-ቋጠሮሕ

ለዕኔ ባትሪ ኆኗል እግዚያብሄር ይባርክሕ::

ያ ፊደል ገደፋ አንጠልጥሎ መተዉ

ሳይቋጩ መራመድ ረቂቅ ገፅታዉ

<B><I>ምርቅ-ኆኖኝ ነበር እንዳል እንዳልዉጠዉ::</I></B>

ከብዙ ብዙ አድናቆት ጋ!

ዳሞት ከዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋናው » Wed Jun 28, 2006 8:59 pm

.
.
.
የቀጠለ

በእንባ አረስርሼ የላኩት ደብዳቤ
ደረሰሽ መልዕክቱ ገብቶሻል አሳቤ?
ተቀየምሽ መሰለኝ ደነገጠ ልቤ
እናቴ ምን ላድርግ አልችል አለኝ ሆዴ

እስቲ ና! ብለሽ ጥሪኝ
እንደጨቅላነቴ ራሴን አብሽኝ
የሽኝት እምባሽን የርግማን አያርግብኝ
በቃ ይቅር በዪኝ
ልምጣና ልጡርሽ
-በሙሉ ዓይንሽ እዪኝ

ልተንፍስ አየሬን
ልርገጠው ምድሬን
ልሳም ወንድሞቼን
የፍቅር ድሕነትን
-ልጌጥ እኔነቴን

አሁንም ለምኜያለሁ
ልኬያለሁ መልዕክቴን
.
.
.
ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ሾተል » Fri Jul 07, 2006 4:11 pm

ውዱ ዋናው,

ውጫዊ እራስን በመስታዎት ያዩታል አንጎልን ግን ውስጣዊና ስውር ስለሆነ አዪም መርማሪም የለው እንዴው ፈጣሪ ይሆን እንዴው እንጂ....በርግጥ በርግጥ እኛ ሰውኛዎች ማን እንደሆንና ምን ያህል የገዘፈና እንደገለባ የቀለለ አንጎል መሸከማችንን በምንሰራው ምግባረ ገጻችን ልንመረመርና ልንታወቅ እንችላለን.....
ነገረ ቅሉ ደሞ ስነ ጽሁፍ ደግሞ እራሳችንን ይነግረናል አሉ.....ለዚህ ነው አንተም በጠለቀው የምእናብ እይታህ;ተፈጥሮ በለገሰህ የአጣጣፍ ስልትህ ስሜቴን ህመሜን ሳልነግርህ ቀድመህ ከስሜቴ ተረድተህ እኔኑ በግጥም መልክ ህመሜን ጣፍክልኝ በድንገት ልምጣ ባክሽ::
እግዚአብሄር እንደዚሁ ስሜትህንና ህልምህን አይቶ እውን ያድርግልህ::አሜን::

በርታ:: ጥሩ ጠልቆ የማየትና ያየኸውን ጭራ መሪውን ሳታስት ከሽነህ እራሳችንን እያሳየህ የመጣፍ ተሰጦ አለህ.....አንዳች እንዳታቆም::ሁሌም ጫጭር...

ከብዙ አክብሮትና ማበረታታት ጋር

ሾተል ነኝ-ከስነጽሁፉ ቀዬ
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9643
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ዋናው » Sat Jul 08, 2006 4:50 pm

አመሠግናለሁ ለ ዋኖስ እና ለ ሾተል
አንብባችሁ ለማጣጣማችሁና አጣጥማችሁ ሞራል ገንቢ ለሆነ አስተያየት ለመቸራችሁ::

ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር

ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sat Jul 08, 2006 5:11 pm

ውርጭን የቀማ አሩር
ቢወራጭ በትንፋጋሙ ምድር
ሕዝብም ቢያለከልክ ቢማረር
ተገላልጦ ዕርቃኑን በላቦት ቢነፍር

ላይበረክት በጋው
ላያሰልስ ብራው
የበረዶ አሸዋውን ላይጋርደው በዛው

ጭኖች ተገለጡ
ተጎዳና ዘምተው ዓይን ላይ ፈጠጡ
ጡቶችም ደነሱ ፈጠው እያጎጡ
ለደራሽ ስሜታት ገስግሰው እየሮጡ
ለነውር አልባ ዘመን ምስጋና እየሰጡ

በሽራፊ በጋ
ዕይታ ቢንጋጋ
የትላንቱ ቆፈን ዛሬ ላይዘነጋ
ያቃጥላል ትላንት
-ያቃጥላል ዛሬ
መሞቅና መብረድ
-አይሆን እንዳገሬ

(ጁላይ 20 06)
ለንደን

ዋናው_____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed Jul 19, 2006 7:04 pm

የእናቴ መልዕክት
.
.
.

::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ፉፊ » Sat Jul 22, 2006 1:14 pm

ህምምምምም እንደት ግሩም ሰፈር ናት
በውነት በተለይ ድንገት ልምጣ ባክሽ የሚለው ሆዴን ቦጭ ቦጭ አረገኝ ,ህልሜን በህልሜ አየሁት ላይ የመጨረቻዋን ስንኝ "በምን ይታወቃል ከህልሜ መባነኔ" የምትለው አሪፍ ናት

ዋናውዬ እጅህ ይባረክ
አድናቂህ ፉፊ
ፉፊ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 209
Joined: Tue Jan 11, 2005 12:06 pm
Location: united states

Postby ባሮ » Sat Jul 22, 2006 2:43 pm

እጅህን ለወርቅ አንባር ይበለው ድንቅ ነው እራስን መግልጽ ስሜትን በ ስነ ግጥም ቁጭ ማደርግ....

ባሮ.....
ባሮ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 87
Joined: Fri Nov 07, 2003 5:16 pm

Postby ዋናው » Sat Jul 22, 2006 8:09 pm

_____መች ጠበበ ቤቴ?_____

ወልዶ መበተንን በልጆቼ አይቼ
አሳድጌ በወግ ያቅሜን ለፍቼ
መአረግህን ሳላይ እንደዛ ጓጉቼ....
ልምጣ ወይ ማለትህ መች ሰደድኩህ ልጄ....?
አንተ ጓጓህ'ንጂ እኔ መች ፈቅጄ

ሠፊ ነው ማጀቴ
ይበቃል ሌማቴ
ረድኤት ሞልቶታል ምን ጠፋ ከቤቴ

እስቲ ና ልጄ አልሻም ጓዝህን
ፍቅርህ ነው የራበኝ የልጅነትህን
ማረፊያህ እዚህ ነው አትሽሽ ዕትብትህን
ለዚህ ለጉም ዘመን
ተጋፍተን ሳይጠበን
አዛግተን ሳይርበን

እስቲ ድረስ ልጄ
እርጥብ ነው እኔ ደጄ
ምንስ ሊሰፋኝ? አንተን አሠድጄ (ሠ-ይጠብቃል)
ለስደት ቁስልህ እስቲ ጉረስ በእጄ

ድሮም የሠው ወርቅ.......
-ነበረ ተረቱ
በፎቅ ተታላችሁ
- አገሩን ሳትለቁ
በድህነት እርግማን
-ለስደት ሳትበቁ

እስቲ ድረስ ልጄ
-ልቀበልህ ዛሬ
የነጭን ግሳንግስ
-መች ተማርኩ ከዘሬ?
አንተ ብቻ ዝለቅ
-ይበቅሀል ፍቅሬ
.
.
.
ዋናው__________________________________::
[/list]
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Jul 28, 2006 7:19 pm

ዋርካው አደመነ::

ዓመታትን በዋርካ አሰልሼ ኖሬ
በእኔነቴ ፊደል አውርቼ ከዘሬ
ዕውቀቶች ቃርሜ ቋንቋንም ተምሬ...
ስድቡን ያግድሞሽ አይቼ ፈንጥሬ
ካለኝ አካፍዬ ካጣውም ቀባጥሬ
በሠላም እየኖርኩ እየው እስከዛሬ ..........

ዛሬ ግን ዳመነ ዋርካው አጨለመ
በስድብ ምልልስ ቋንቋውም ከሠመ
ያ! ለዛ ያ! ፍቅር አጉል ተጣመመ ::

ብርት ጥፍት ብሎ ያ! ትንሽ ጭላንጭል
ለዘበተ ግድፈት ድጋሚ ቦግ ሲል
እንዴትስ ላዋራ እንዴትስ ላናግር ?
የቃላት መዶሻ ዋርካው እያፈራ
የፍቺው መላምት ጠሞ እንደከዘራ
ትውልድ ተወቃቅሶ ልዩነት ሲዘራ
በነውር ቃላት ሽልም ያም ሲያሳይ ፉከራ

ዋ! ዋርካ ግንድሽም ዘመመ
ሥርሽ ተጣመመ
አውንስ ፈራውሽ
-ውስጥሽ ጨላለመ::

(ለሠሞናቱ ዕሠጣገባዎች......)

(.......ዘ-ጥልስም)

ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests