የዋናው አቁማዳ==>ሸራ ስላልወጠርኩ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዋናው » Sun Aug 06, 2006 11:19 am

ይቅርታ አንባቢያን ከላይ የጠቀስኩት ግጥም በግል ማንንም እንደማይወክል ይታወስልኝ ያለመግባባቱ ብቻ ለእኔ ስለአልተዋጠልኝ 'ንጂ
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun Aug 20, 2006 1:12 pm

______________________መስከረም ሳይጠባ_____________________

አንቺ መስከረሜ አበባሽ አብቧል
ጓሮሽ አረንጉዷል _________(አረንጓዴ ሆኗል)
ጤዛሽ አብለጭልጯል
የልጆችሽ ከበሮ ሊወርድም ተቃርቧል
እኔም ከዚህ ሆኜ ሆዴም ተምቦጫብጯል::

እዮሀሀን አዚሜ
ዕድሌን ኮንኜ
-ናፍቆት ተሸክሜ
እስቲ ላዚም ከዚህ
-አዮሃ'ን ደግሜ
.
.
.
ምነው ብቅ ባልኩኝ መስከረም ሳይጠባ
ያንን ባሕር አድርቄ ወደ አዲስ አበባ
ለ'እልል'ም ባልበቃ ሹክክ ብዬ ልግባ
አይኖቼን ባፈዘዝኩ በፀደይ አበባ
ስምቼ'ንኳን ብጠግብ የሕፃናቱን ዜማ

እቴ አበባ እቴ አበባዬ
አዬ እቴ አበባዬ

ዕድል ቆጥሬ ....ለምለም.....ብወጣ ካገር......ለምለም
እደጅ አደርኩኝ....ለምለም ኮከብ ሳልቆጥር...ለምለም
ኮኮብ ሳልቆጥር..ለምለም...ስገባ ቤቴ...ለምለም
አስቀየመችኝ..ለምለም...እደል ሕይወቴ...ለምለም
ብዬ ላዚም እስቲ መስከረም ሳይጠባ
ክንፍም ባላበቅል በርሬም ባልገባ
ላስበው ምድሬን በናፍቆት ጭብጨባ

አደዪ የብር ሙዳይ ኮለል በዪ
እቴ አበባሽ እቴ አበባዬ
.
.
.
እቺ ቀኔ ስትምል ከርማ (አዬ እታበባዬ)
ጥላኝ ሄደች በዚህ ጨለማ (አዬ እቴ አበባዬ)

ብዬ ላዚም እስቲ ሳንደርስም ለጳጉሜ
በሃሳብ ብመለስ ደጁን ተሣልሜ
ችቦውን አብርቼ ደመራውን አቁሜ
በገቢያው ኹካታ
በበጎቹ ጩኸት በቀጤማው ሽታ
አዲስ ልብስ ባጌጡት በሕጻናቱ ፌሽታ
በወረቀቱ አበባ በምኞት ሠላምታ

እስቲ ልሂድ በትዝታ
መስከረም ሳይጠባ ጸደይ ሳይበረታ
ልመለስ ደርሼ ካለኝ እዛ ቦታ

መስከረሜ አበባዬ መስከረሜ
ዛሬስ ሆንሽብኝ እመሜ
በትዝታ ነጎድኩ ቀረሁኝ ዘምሜ
ለፀደይቱ ውልደት ቢጫን እንዳቀለምሽ
ምነው ለእኔ ክንፍ ማብቀሉን ተሳነሽ
ለሌላ አይደለ መጥቼ እንዳደንቅሽ
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun Aug 27, 2006 9:25 pm

.
.
.
መስከረሜ

ያኔ ነው በሠኔ ሠላሣ የማለፍና መውድደቅ ምስራችና መርዶ ሆዳችን እንደራደ የተማርንበትን ሠርተፍኬቱን ሆዳችን ውስጥ ወሽቀን ዓመቱን ሙሉ ለተዛዛትን ሁሉ ፀብ ያለሽ በዳቦ ..ብለን የምንፋጠጥ በነበረበት ጊዜ ....ውስጣችን የልጅነት እልሁ ቢታይም መጨካከኑ የዘርም የእጣም ስላይደለ ለመከረሙ ለመተያየት በመሳለም እንሰነባበት ነበር :: ታዲያ ወራቱን በጭቃ እና በዝናብ እንቆይና የቡሄንም የቅዱስ ዮሐንሱንም ችቦ ማግደን መስከረምን ስንቀበል ...ምድር ትበራለች ላዲስ ተስፋ በፀደይ የብርሀኖች ፈርጥ ትሞላለች : ወትሮም ብራዋ ምድር ዕጥፉን ትበራለች ::
ደብተር ይለበዳል ''መስከረም ሲጠባ ወደ አዲስ አበባ ...እልል ብዬ ልግባ '' ተብሎ ገጠርም ለክረምት የገባው ሁሉ መስከረሜን መጣው ይላታል ...ቀጥራ ቀርታ አታውቅምና ...ያለ ጉንጉን አበባ መቀበሏን አቋርጣው አታውቅምና ...ሕፃናቱ በቀለም የመልካም ምኞት ምስል በነጭ ወረቀት ላይ ይስላሉ ያገሬውን ''ሴሌብሪቲዎች '' ማስታወሻ ነውና :
ውርጩ የሚጋረፈውን ነሐሴና ጳጉሜ ወደውኃላ እያሸሸች መስከረም ብቅ ስትል ፍጡራን ሁሉ ይፈግጋሉ ከብርሐን በላይ ምን አለ ?

ይስቃል ምድርሽ
ይስቃል ፍጡርሽ
መስከረሜ ብሎ ሲፈኩ አበቦችሽ

ፍቅር ነው ምድሬ
ውበት ነው ፍጡሬ
ዛሬ ሳስታውሰው ርቄ ካገሬ
በስደት 'ም ልክፍት ብስቅ ቀባጥሬ
አንቺ መስከረሜ አስታወስኩሽ ዛሬ
እየተሽከረከርኩኝ በማያልቀው እግሬ
ምድር ላትሰፋኝ ላይ ታቹን ዞሬ

ዛሬን ባላደንቅሽ በአበባሽ ጠንግሬ
ዕመጣለሁ ከርሞን ዕድል ዕጣዬን ጭሬ
የሁለት ሺ 'ን ዕድሜሽ
-ላከብር ባገሬ ::
.
Last edited by ዋናው on Wed Sep 17, 2008 3:09 pm, edited 5 times in total.
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby yammi » Tue Aug 29, 2006 1:05 am

በጨገገው ክረምት
የቀረበው ሰማይ
እንባውን ሲቋጥር
ምህረቱን ሲያሳይ
ዙፋኑን ሲያስረክብ
ለመስከረም ጸሀይ
ወንዞቿ ሲጠሩ
ምድር ስታሽቃብጥ
በአበቦች አጊጣ
እዮሀን ስታቀልጥ
ችቦው ሲንቦገቦግ
ሲቀልጥ ያገሬ ወግ
ዘንድሮስ አልደርስም
አታጣድፈኝ እግሬ
ከከርሞ ልጫወት
ይያዝልኝ ፍሬ

28/8/2006
yammi
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 441
Joined: Fri Jul 28, 2006 11:02 pm

Postby ዋናው » Wed Aug 30, 2006 10:02 pm

ያሚዬ ማለፊያ ስንኝ ገመድሽልኝማ'

እንኳን ወደ ቤቴ በሰላም መጣሽ::
ይልመድብሽ
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

በትዝታ ፈረስ...

Postby ዘማች » Fri Sep 01, 2006 10:29 am

በትዝታ ፈረስ

በትዝታ ፈረስ ነጎድን ተጓዝን
ዋናው እየመራን ከሸገር ከተምን::
ባርማዶ ተሻግረን ተፈረንጅ ቀበሌ
የጠፋው ቆሌያችን ተመለሰ ዛሬ::

ክረምት አልፎ አደይ ስታብብ
ትዝታ በሽበሼ በእምባ መታጠብ::
እንሂድ እንሂድ አገር ቤት እንግባ
ሆያ ሆዬ ልንል መስከረም ሲጠባ
የሶላቶው ናይት ለራሱም አልረባ::

ዘማች


ዋናው wrote:.
.
.
____________________________መስከረሜ______________________________


ያኔ ነው በሠኔ ሠላሳ የማለፍና መውድደቅ ምስራችና መርዶ ሆዳችን እንደራደ ሠርተፍኬቱን ሆዳችን ውስጥ ወሽቀን አመቱን ሙሉ ለተዛዛትን ሁሉ ፀብ ያለሽ በዳቦ ..ብለን የምንፋጠጥ በነበረበት ጊዜ ....ውስጣችን የልጅነት እልሁ ቢታይም መጨካከኑ የዘርም የእጣም ስላይደለ ለመከረሙ ለመተያየት በመሳለም እንሰነባበት ነበር:: ታዲያ ወራቱን በጭቃ እና በዝናብ እንቆይና የቡሄንም የቅዱስ ዮሐንሱንም ችቦ ማግደን መከረምን ስንቀበል ...ምድር ትበራለች ላዲስ ተስፋ በፀደይ የብርሀኖች ፈርጥ ትሞላለች: ወትሮም ብራው ምድር ዕጥፉን ትበራለች::
ደብተር ይለበዳል ''መስከረም ሲጠባ ወደድ አዲስ አበባ...እልል ብዬ ልግባ'' ተብሎ ገጠርም ለክረምት የገባው ሁሉ መከረሜን መጣው ይላታል...ቀጥራ ቀርታ አታውቅምና...ያለ ጉንጉን አበባ መቀበሏን አቋርጣው አታውቅምና...ሕፃናቱ በቀለም የመልካም ምኞት ምስል በነጭ ወረቀት ላይ ይስላሉ ያገሬውን ''ሴሌብሪቲዎች'' ማስታወሻ ነውና:
ውርጩ የሚጋረፈውን ነሐሴና ጳጉሜ ወደውሀላ እያሸሸች መስከረም ብቅ ስትል ፍጡራን ሁሉ ይፈግጋሉ ከብርሐን በላይ ምን አለ?

ይስቃል ምድርሽ
ይስቃል ፍጡርሽ
መከረሜ ብሎ ሲፈኩ አበቦችሽ

ፍቅር ነው ምድሬ
ውበት ነው ፍጡሬ
ዛሬ ሳስታውሰው ርቄ ካገሬ
በስደት'ም ልክፍት ብስቅ ቀባጥሬ
አንቺ መስከረሜ አስታወስኩሽ ዛሬ
እየተሽከረከርኩኝ በማያልቀው እግሬ
ምድር ላትሰፋኝ ላይ ታቹን ዞሬ

ዛሬን ባላደንቅሽ በአበባሽ ጠንግሬ
ዕመጣለሁ ከርሞን ዕድል ዕጣዬን ጭሬ
የሁለት ሺ'ን ዕድሜሽ
-ላከብር ባገሬ::
.
.
.
ዘማች
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 88
Joined: Wed Aug 18, 2004 7:02 pm
Location: ethiopia

Postby ዋናው » Fri Sep 01, 2006 7:32 pm

.
.
.
አንቺ የአደይ አበባ
የቀለማት ትሕፍሰት
-የወራት ወለባ
የክረምታት ፈርጥ
-የምኞት ዘገባ
ቀለምሽ ሳይቦዝዝ
-እንዴት ሆኜ ልግባ....?

መሀዛሽ ሳይጠፋ
ቅጠልሽ ሳይረግፍ
-ውበትሽ ሳይጠፋ
ልምጣ እስቲ በርሬ
በናፍቆት ሳልጠፋ
.
.
.
ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Tue Sep 05, 2006 8:08 pm

.
.
.
ደጅሽም ይታጠን
-ችቦ እሳቱ ይብራ
ጓሮሽ ሲረኖጉድ______(አረንጓዴ ሲሆን)
-አበባሽ ንብ ይጥራ
ይድመቁ ቀናትሽ
-በልጆች ጭፈራ
ልብስና ፊታቸው
-እንደ ፀደይሽ ሲያበራ

አንቺ መስከረሜ
ዛሬስ ሆንሽኝ እመሜ
የጨቅላ ቡረቃዬን
-በትትዝታ አስታምሜ
በፅልመታት ሠፈር
-ፈዝዤ ቆዝሜ

እስቲ አስጨብጭቢ ለእኔም
በከበሮ ውዳሴሽ ሕዝብሽ ሁሉ ሲያዜም
እግሬ አንክሶልሽ ሮጬ ባልመጣም
ባገሬ ትዝታ ከዚሁ ሆኜ ላዚም
.
.
.

ዋናው_________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sat Sep 09, 2006 12:12 am

.
.
.

መስከረሜ
የዕጣ-ፈንታ ሆኖ
-ሣላይሽ መክረሜ
በረገፈ ቅጠል ሥር....(የኦቶም ወቅት)
-እዚህ መቆዘሜ
የአንጀት ናፍቆታቴን
-እራሤ አስታምሜ
እዮሀ እያልኩኝ
-ለራሤ አዚሜልበል ለመልካም ምኞት ስል
-ቃል ካለኝ ገጥሜ
::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Sep 11, 2006 10:57 pm

::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Sep 11, 2006 10:58 pm

::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Sep 15, 2006 11:29 pm

አንቺ የመስቀል ወፍ

ወራትን ቆጣጥረሽ
ጭራን ለውበት መዝዘሽ
በዓደይ መኃል ፉጨትን አዚመሽ
እንዲያው ብቅ ስትይ
-ለምለሙን ሾላልከሽ

ምነው ታዲያ
-ሁሉም ጋር ደራርሰሽ
ለሱሴ እንኳን ቢሆን
-እኔ ዘንድ አቃተ_______________ሽ??

ዋናው__________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Sep 25, 2006 12:15 am

ጥቁር ሙሉ ጨረቃ

የሚስጥራት ዓለም ዘውዶች በድቅድቁ ፅልመታት ፍንጥቅጣቂ የከበዱ ጨለማዎች የመዳፈን ውበቱን ይዞዋል:: ዕይታ ምንድነው? የእይታ ምልከታስ....? የእነኚህን መልስ-ጭንቁ ጥያቄዎችን ሚስጥር ያረገዙ የዳመና ቋጥኞች ከላይ ተንጠልጥሎዋል :: ብረሐን ፈርቷል ግን ምስል አለ ግኡዙም ትንፋሹም .....

መከሰት ምንድነው ለምን እንደማሠብ ቀላል አልሆነም? ፍጡርና ሕያው ቃል ናቸው ከስያሜያቸው ጀርባ ስላለው ሁሉ ዳግም ከተመለስንባቸው ወይ ቃል ወይንም ሃሳብ ይሆናሉ:: እኛነታችን እና ነገ ትላንትናና ዛሬ እያለን የምንለፋበት ሕይወት ጠዋት ላይ ለመረሳት ካኮበኮበው ሕልማችን ሀሳብ ብቻ ቢሆንስ...? ልክ ይሄንን ፅሑፍ ስታነቡ ''ዋናው'' እንዲ ቢፅፍ ብላችሁ በጥርጣሬ እንደምታነቡት.....

ወዴት ወዴት ሃሰብኩኝ ሠዎች'ዬ እስቲ ወደዝምታዬ...

ዋናው_______________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Sep 25, 2006 4:07 pm

በአረብ አገር ተሠደው ለተንንገላወቱት እሕቶቻችን


ለአብሮው ኑሮው ፍቅር
-ከስራቸው አድጌ
ኑሮን በአቋራጭ
-መቅደሙን ፈልጌ
የእንባን ዘለላ በጉንጬ አድርጌ
ወጣው ከማጀቴ
ከደመቀው ቤቴ
ዕጣ-ፈንታን ብዬ
-ላየው እኔነቴን
.
.
.
ጓዝም አላበዛው
ደህና ጫማ አልገዛው (ጫማው-ማምለጫ)
ማዳም ማዳም ብዬ
-ለአመታት ተገዛው

የታል ያ መብቴ
ሀያቴ ያወረሡኝ እንቢ ባይነቴ
ማን ወሰደው ወኔዬን
-የዘር እኔነቴ

ጤፍን ላልወቃበት
ዕጥፍ ላልጎርስበት
እንደአጋሰስ ተንቄ
-ጌጤም ላይደምቅበት
ዘር እንዳጣ አውሬ
-ስነዳ እንደከብት

ባይጠግብም________ሆዴ
ቢያቄምም _________ሆዴ
ቢቃጠልም አንጀትና __ሆዴ
ምነው በተመለስኩኝ
-አንክሼም በዳዴ

ስዳድ
ስደት
ሰደድ
ብዬ ተብከንክዬ
-የማዳምን ቁጣ ጆሮ ዳባ ብዬ
አንድ ሁለት እያልኩኝ
-መዳፌን አክስዬ

ዛሬም አልነጋልኝ
የኔ ብዬ የሾምኩት
-ቀኔ መች በራልኝ?
ያ- የናፈቅኩት
-እዛ ሆኜ የታየኝ
.
.
አለፉ ዓመታት
ነጎዱ የባከኑ ወራት
እጄም ዶለዶመ
-ነፍሤም ስልችት አላት::

ምን ተይዞ ጉዞ
ያለጓዝ ቢታሰብ ባህር ተጠማዞ
የእንባን ሽኝት ለለውጥ አስተክዞ
እድሜ ባነባብር ዕድል ዕጣዬ ፈዞ

ዳግም ዕሳት መጣ
የዘንድሮስ ጣጣ
በማዳም ቁጣ ስማረር
በባዶ ሻንጣዬ ሳፍር
የባ__________ሠበት መጣ
በስቃይ ሕይወት ነፍሴን ሁሉ ላጣ

የባሩድ በረዶ
ከሠው ደጅም ወርዶ
አልሸሸው ነገር
-እዚህም እዛም ነዶ
የፍም ንፋስ ክፉ ዘመን ወልዶ
አንጋጥጬ አልለምን
-ጪሡ ጋርዶት ሄዶ
አልሻገር በእግሬ
-ምድሬ እዚያ ማዶ................
.
.
.
(ቤሩት ለተሠቃዩት ዜጎቻችን)

ይቀጥላል

ዋናው___________________________________:[/u]
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

ወደፊት በሉለት ይለይለት

Postby noor » Wed Sep 27, 2006 11:26 pm

በቅድሚያ ከፍ ያለውን የዋርካን ሰንደቃላማ አንስቸ የዋርካን ማአረግ በክብር ብሸልምህ የሚቃወመኝ ያለ ይመስለኛል ስለዚህ እና ተመችቶኛል ይመች እያልኩኝ በዚች አባባል እየደገፍኩህ አብሪክ እያጀብኩህ እጎዛለሁ ወደፊት በሉለት ይለይለት ጎበዝ አንድላይ በሉእንጂ ከአድናቂዎች አንዱ በርታታታታታታታታታታ...............
noor
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Mon Sep 27, 2004 7:15 pm
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests