ሰላም ውድ አንባቢያኖች ሆይ እነሆ ቃል በገባውበት መሰረት አዲስ ልብ ወለድ ይዤ ቀርቤያለሁ::እንደተለመደው ሁሉ ሙያዊና ሀሳባዊ አስተያይቶቻችሁ ይጠቅመኛልና አደራ__ብትችሉ ውድ ወንድሜ ዋኖስ በከፈተልኝ የአስተያየት መድረክ ላይ አስተያየቶቻችሁን ታሰፍሩልኝ ዘንድ እለምናለሁ::
ታዲያ ኮፒራይቱ በሣይበር ኢቲዮጲያ አላፊነት ቢሆንም አደራ በመተማመን ይሁን
ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር
_______________________///______________________
(-1-)
ለንደን
ጭጋጉ ካሁን አሁን ወርዶ የሰው ራስ ሊነካ የደረሰ ይመስል ከብዷል:: ህዝቡ እጣው ነውና ኑሮውና ህይወቱ ነውና ፊቱን በጭጋጉ ላይ ከማቀጨም በቀር ምርጫ አልነበረውም ሰሀቱ ለመጨለም ባይደርስም ያቺ የማትበረክት የክረምት ጀንበር ግን የከበደውን ደመና ሸሽታ በምን አገባኝ ስሜት ወደማደሪያዋ አዘቅዝቃለች
ለንደን አኩርፋለች መዝነብ የሚፈልግ ሚመስለው አየርም ኩርፊያዋን ሊያባብስ ሁሉ እየተለዋወጠ ያናድዳታል ይሄኔ ህዝቧ በየፐቡ/መጠጥ ቤት/ ውስጥ እየተከተተ ፓይንት/ድራፍት/ ይጨብጣል ሲጋራ ያቦናል
ዘካሪያስ ሁለቱን ሲጋራ አከታትሎ እየማገ ሲተክዝ ያመጣውን ስቴላ የፓይንት ቢራ ሲጨርስ አልታወቀውም:: ያደረገውን ወፍራም የጃኬት ኮሌታ ወደጆሮግንዱ እየሳበ አንገቱን ወደደረቱ እየቀበረ ከደጅ ይዞት የመጣውን ብርድ ቀጭሞታል አህምሮው ግን ያንሰላስላል ከዛም ፊቱን አንዴ ኮስተር አንዴ ፈገግ እያደረግ ብቻውን እንደሚያወራ ሁሉ ያጉተመትማል ግን ቃሎቹ አይሰሙም::
ሰሀቱን ሲመለከት 5 ሰሀት ከ23 ሆኖዋል ጸሀይዋ ከጠለቀች ትንሽ ቆየች ዘካሪያስ ደንዳና ሠ[/list]ነት ሰፊ ትከሻው ሁሌም ያልከፋውና ያልተቸገረ ያስመስለዋል:: ጠይምና ሁሌም የራስ ጸጉሩን እየላጨው መላጣ ነው:: አጠገቡ የነበረ አንድ አገጩ ሹል እንግሊዛዊ ምናልባት ፑል መጫወት ይፈልግ እንድሆን ጠየቀው አጫዋች በመፈለጉ ዘካሪያስ ጓደኛው የምትመጣበትን ሰሀት አሰላና አንድ ጌም ቢጭወት እንደሚችል ነግሮት ሲጋራውን አጠፋና የፑሎቹን ድንጋይ የሚጠነቁልበትን ዱላ መምረጥ ጀመረ::
ፑሉን እየተጫወተ ሳለ ቫኔሳ መጥታ ፍልቅልቅ ያለ ደማቅ ሰላምታ ሰጥታው የፑሉን ጠርጴዛ አስደግፋ ከናፍርቱን ለመናፈቋ ጎርሳውና አጣጥማው መጠጧን ለመቅዳት ወደ ባርቴንደሮቹ አመራች:: ቨኔሳ ጂንጀር ጸጉር ያላት ረጅም አቋሟ ያማረ ወጣት ናት የፊቷ አወራረድና የቋንቋዋ ቃና ከደቡባዊ ብሪታኒያ መሆኗን ይናገራል ቅልጥፍናዋ ከንግሊዛዊነቷ ቢሆንም ስትናገርና ነገሮችን ስታስረዳ ርጋታዋ ይስባል
''የሰጠህኝን መጸሀፍ አልጨረስኩትም የኔ ፍቅር ዛሬ ላመጣልህ ቃል ገብቼ ነበር ይቅርታ በስልክ እንደማልችል መንገር ነበረብኝ::'' አለችው ሲጋራዋን እየለኮሰች የላይኛው ከንፈሯ ስስ ሆኖ የታችኛው ትንሽ ስጋ ከብዶት ጠልጠል ያለ ነው
''ምንም አይደለም ቫኒ ለባለቤቱ ካምስት ቀን በኅላ እንደምመልስለት ልነገረው እችላለሁ ''
አላት የዱላውን ጫፍ በመሞረጃ ጠመኔ እየሞረደ የባለጋራው አይን ሲቁለጨለጭ አስተዋወቀው ቫኔሳን:: ቫኔሳ ደክሟት ስለመዋሏ በግጽታዋ ያስታውቃል
''በጣም ደስ የሚል ዜና አለኝ ዛሬ የኔ ፍቅር''
አለችው የዘካሪያስን አይኖች ቀርዝዛ በፍቅር እያየች ስትናገር እንግሊዘኛዋ ለጆሮ ደስ ይላል ከድምጿ መረዋነት ጋር
''ምን ተገኘ ቫኒ....?''
አላት ተራው ደርሶ ፑሉን እያነጣጠረ
.
.
.
ይቀጥላል
ዋናው_________________________________________________::[/list]