ጥላ ዓልባ__________(ልብ ወለድ)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዋናው » Thu Sep 18, 2008 4:04 am

.
.
.

የጉንጮቹ አጥንቶች እንደ ክርኑ እጥፋት ሾሎዋሉ ከናፍርቱ ትኵስ ትንፋሽ ሲያስወጡ ስለከረሙ ቀልተዋሉ የከሳ ፊቱ ላይ የጎደጎዱ ዓይኖቸ ስሜታቸው ደስ አይልም:

''አሁን እንዴት ነህ?''
አለው አንተነህ ጠረጴዛው ላይ የተከመሩትን መድኃኒት ፓኬቶች አገላብጦ እያነበበ

''ደህና ነኝ ፒካሶ?''
አለ ሙሴ በሳሳ ድምፅ

''ለምን እኔ ቤት አንሄድም ሙሴ ቢያንስ አንድ ሁለት ሳምንት እዛ ቆይ በሽታህን ሚያባብሰው ብቻህን ቤት ዘግተህ መዋልህ መሆኑን አትርሳ''

''እዚህ ይሻለኛል''
መልሶቹ አጫጭር ናቸው

''ለምን ?''

''ብቻዬን መሆን እፈልጋለው ፒካሶ..... ብቻዬን ሆኜ ራሴን መርገም እፍለጋለው''

''ግዴለም እዛ እንሂድና ሙሴን አብረን እንረግመዋለን''
አለ አንተነህ የሙሴን ቁጣ በቀልድ ለመቀየር እየሞከረ : ሙሴ እንደማፌዝ ዓይነት ፈገግታ እየሞከረ
''ይልቅ ውለታ ዋልልኝ አንዲት እሕት ነች የቀረችኝ ብር እየፈለገች ነው ትልክልኛለህ?''

''እንሂድና አብረን እንልካለን ተነስ''
ሙሴ ጀርባዉን እየሠጠው

''ፒካሶ እኔ አልወጣም አልኩህ'ኮ''

''ሙሴ!!!!!''
በቁጣ ተጣራ አንተነህ:: ቆሞ እየትንጎራደደ
''....ምንድነው እንደዚህ መሆን ወንድ ልጅ አይደለህ እንዴ?''

''አይደለሁም''

''አንድ ነገር ልንገርህ ማንም ሚሆነዉን ነው የሆንከው ዕድሜያቸው ጨቅላ የሆኑ ስንት መከራ አይተው እዚህ ለንደን የደረሱ ያገራችን ወጣቶች አሉ ተመልከታቸው ስለምንም ነገር ደንታ የላቸዉም እቺ ዓለም ድንገት እንደቁና ብትደፋብን እንኳን አይገርማቸዉም ምክኒያቱም ብዙ መከራ አይተው ነው እዚህ የደረሱት ለዛዉም በዕድሜ ያንተ ታናሽ ታናሽ ሚሆኑ... እነሱ የገባቻቸው ሕይወት እንዴት ላንተ እንቆቅልሽ ትሆንብሀለች...?''
አንተነህ እየተንጎራደደ ያወራል

''ሁሉም የራሱን ሕይወት ነው መኖር ሚችለው'' ፒካሶ
''
አለ ሙሴ ቅርፍፍ ባለ አንደበቱ

''ያንተ ሕይወት የተለየ ነው?..... ነው?... ተስፋ መቁረጥ በዚህ መልኩ አይደለም ይህ አንተ ያየኸው ኤክስፕሪያንስ ብዙ ምትማርበት ቢሆን እንጂ እንዲህ እየተጸጸትክ ምትብከነከንበት አይደለም.... ያ?''
ሙሴ ሶፋው ላይ ሆኖ በቀጫጫ መዳፎቹ ፊቱን አጥሮታል የእጆቹ ደምስሮች ተጠማዘው እስከ ክንዱ ተሰማምረዋሉ::

''...እሺ ለእኔ ርስፔክት የለህም?''
ሲለው ሙሴ ድንገት ቆም አለና

''ፒካሶ... ስለማከብርህ'ኮ ነው እውነተኛ ስሜቴን ምነገርህ''
አለው

''ግን ምጠይቅህን እሺ አትለኝም''
አለው በቁጣ አንተነህ

''እሺ ግን አንድ ቀን ብቻ ነው ማድረው አንተ ጋር''
አለና ሙሴ ፈገግ አለ ፈገግታው ግን ድንገት ብልጭ ብላ ወዲያው ደመና ውስጥ እንደምትወረወር ፀሐይ ነች::
ያንተነህ ስልክ ተንጫረረች

''የት ነው ያልኸው አሁኑኑ ድረስ''
የተርበተበተ የጠዳፈ የሴት ድምፅ ነው
.
.
.
ይቀጥላል


ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Thu Sep 18, 2008 4:06 am


በስሕተት የተደገመ[/i]
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby early_bird ! » Wed Sep 24, 2008 4:59 am

መጨረሻ ለይ አቺያት ነው የሳብኮት :lol: :lol: ከ ፍሮንት ፔጅ ለይ ስትጠፋ ደስ አይለኝም ባለቤት አልባ ትመስላለችና 8) :lol: :lol:
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby ዋናው » Thu Oct 02, 2008 9:33 pm

መጣው ለማለት ነው::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ድንቢጤ » Fri Oct 03, 2008 2:38 pm

መምጣት እንደዚህ ከሆነስ ባትመጣ ይሻል ነበር :roll:
ድንቢጤ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 67
Joined: Thu Feb 02, 2006 9:52 am

Postby ዋናው » Thu Oct 09, 2008 11:21 pm

.
.
.
አንተነህ ካትሪን የጠራችው ቦታ ሲደርስ ስሜቱ እሷ የቸኮለችበትን ለማወቅ መጓጓት ሳይሆን ኣባብሎ ሊወስደው የነበረዉን የሙሴ የፊት ገፅታ ላይ ነበር። '' ተመልሼ መጥቼ አወስድሃለው'' ሲለው ሙሴ ግን የአሕቱን ኣድራሻ በኣደራ ብቻ ኣቀበለው።
''አቺን ቀን የግላችን ለማድረግት በጣም መሮጥ ኣለብን''
ኣለች ካትሪን ረጋ ያለ ፈገግታዋን በተቀመጠችበት አየቸረችው
''ከጊዜ ጋር አልህ የገባች ፍጡር ኣንቺን ኣየው፣ ጊዜ ነፍስ ቢኖራት ጥምድ ምታረግሽ ይመስለኛል"
ኣላት ኣንተነህ ከሠላምታው ቀጥሎ ኣጠገቧ አየተቀመጠ፤የመቀመጫውን መደገፊያ ጥቁር ፀጉሯ ሸፍኖታል።ብዙም ሳይቆዩ ፓት መጣ፤ ወደ ፐቡ ያቺ ፈገግታው ቀድማው ገባች።ቁም ነገራቸዉን ለሶስት ሆነው አትየተሳሳቁ ሲያወሩ ነገ ሌሊት ላሰቡት ከባድ ውጥን ሚያወሩ ሳይሆን አንዲሁ መለኪያ ለማጋጨት ብቻ የተጠራሩ ነው ሚመስሉት።

ኣንተነህ ተልይቷቸው ወደቤቱ ሲገባ ኣንድ ማያውቀፍ ፍረሓት ወረረው። ውስጡን ኣዳምጦ ይበልጥ መፍራትም ፈለገ፥ ግን ደግሞቤቱ ሲገባ ሚጠብቀዉን የኤልሣን ውብ ፈገግታ በኣይነ ሕሊናው አየሳለ ውስጡን በመቆጣጠር ስሜቱን ለፍቅር ኣዘጋጅቶ ቤቱ ደረሠ።
.
.
.
ዘካሪያስ ሠባዊት እቅፍ ውስጥ ሆኖ ፀጥ ብሏል እሷም ፀጥ ብላ እሱ ወደሚያይበት ታያለች:: ጡቶቿ መሀል ራሱን ደግፋ እጆቿን ድረቱ ላይ እየዳበሰች አገጯን መላጣው ላይ ተክላ ተክዛለች:: የዛሬው ሌሊት ምንኛ አጭር መሆኑ ገና ሳትጀምረው በመስጋት ነገን ታስባለች: እሱም ብዙ ሃሣቦቹን በርሷ የፍቅር ጥላ ውስጥ ተጠልሎ የመዋደዱን ፀጋ እያሞገሰ ውስጡን ያዳምጣል:: ተኳርፈው የቆዩበት ወደ እናት ምድሩ የመመለስን ጉትጎታ ዛሬ ፍፁም የነርሱ ብቻ በሆነው ዛሬ ላያነሱ ተማምለዋል: ዛሬን ብቻ ነውም አብረው ሚያድሩት:: ነገ ከሁሉም ጋር ተሰባሰበው እራት ይወጣሉ ከነገ ወዲያ ደግሞ እቺን ጭፍግግ ምድር ሊያያት የመጡ በቅቷቸው ይመለሳሉ: ተብትባ ያስቀረቻቸዉም እዚሁ ይቆያሉ::

''እስቲ ፀልይ....''
አለች ሠባዊት ትንፋሿን ደጋግማ ባንገቱ ዙሪያ በግለት እየተነፈሰች ቆይታ...

''ምን ብዬ...ሠቢ?''

''ፈጣሪ ቢያንስ እቺ ሌሊት ቶሎ እንዳትነጋ...''

''ስንት ድምፃዊያን በዜማ ሲለምኗት ስንት ባለቅኔ በችሎታቸው ሲዘርፉላት.... ያልሰማች አንድ ባተሌ ቢጠይቃት እሺ ትላለች ብለሽ ነው?''

''አንተ ግን ምንም አይመስልህም አይደል?''

''ምኑ ሠቢዬ''

''መለያየታችን...''

''እንደዛ ዓይነት ስሜት ነው ምታነብቢኝ ግን?''
ከዛም ተጋግለው እሷም ትንሸራተትና እሱም ይዞርና ሙቀታቸው ይጨሳል..... ፍቅር መሀላቸው ይምቦገቦጋል.... ከበረከቱ የስሜታት ንሑስ ድምጾች በኌላ ካባራ ስሜት ውስጥ ሆነው እቺን ዓለም ከካደች አልጋቸው ስር በትኩስ ላባቸው እየሳቁ

''ዛሬን ሞተን ነገን በድን ብንሆንም'ኮ አንጠጋገብም....''
ይላታል ዘካሪያስ: ታፍርና አንሶላዋ ውስጥ ትሰጥማለች::
.
.
.ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Thu Oct 16, 2008 2:52 am


.
.
.
ስለሺና ዘካሪያስ ሳይተያዩ ለመቆየታቸው ሚያስታውቅ ስሜት ውስጥ ሆነው ያወራሉ : ሠባዊት ሮማን ኤልሣቤት ሆነው ዛሬ ስላደከማቸው ሾፒንግ ያወራሉ ዳንኤል ወደኢትዮጵያ የደወለው ስልክ ጫጫታው እንዳይሻማበት ከምግብ ቤቱ በራፍ ላይ ነው
ኤልሣ ደጋግማ ሠዓቷን ትመለከታለች በዚህ ሠዓት የዮሐንስን እና የአንተነህን የት ቦታ መሆን እና ምን እየሠሩ እንደሆነ ምታውቀው እርሷ ብቻ ናት ከፊል ስሜቷ ካለችበት ግርግር ውስጥ እንዳልሆነ ያወቀባት ግን የለም ::

''የማን ምርጫ ነው ግን ይሄ ቤት እስቲ ሸዋ ገብተው እንጀራ ሊቀበላቸው በእንጀራ ትሸኟቹዋላችሁ ...?''
አለ ስለሺ የአገጩን ፂም ወደታች እየላገ የምግብ ቤቷ አስተናጋጅ ብቅ ብላ የጠርሙስ ቆርኪ ፍንቅላ እየከፈተች ተመልሳ ትሰወራለች :: ቤት ውስጥ ብዙም ባይሆን መጠነኛ ተስተናጋጅ አለ :: ከነርሱ ፈንጠር ብሎ ካለው ወንበር ላይ ቋንቋቸዉና የግንባራቸው አግድም መስመሮች ከሠሜናዊ ኢትዮጵያ መሆናቸው ሚታወቅ በቋንቋቸው ክርክር ይዘዋሉ ::

''ሮሚ ናት ይሄን ቤት ተመችቶኛል እዚህ ካልመጣን ብላ ያመጣችን ''
አለች ሠባዊት አሻግራ የዘካሪያስን ዓይኖች እየፈለገች

''አውቃ ነው ስለሺ ከዘኪ ጋር የሆነ ትዝታ ስላላቸው ነው እዚ ያመጣችን....''
አለች ሮማ እየሣቀች: ዘካሪያስ እየደጋገመ ወደ አንተነህ ስልኩን ይሞክራል: የአንተነህ ስልክ ግን ጠፍቷል::

''ጆኒ ስለዛሬ ማታ ያወራሽ ነገር እርግጠኛ ነሽ የለም?''
ይላታል ለሠባዊት ዮሐንስጋር'ም ደውሎ ይሞክርና

''እየነገርኩህ ዘኪዬ.... እንግዲህ ትነዘንዘኛለች ብሎ ይሆናላ... ለነገሩ'ኮ እሱ ከሠው ጋር ለመቀላቀል ዓይነጥላ አለበት አይደል?''

ዘካሪያስ ቀጫጫዉን የቢራ ጠርሙስ አንስቶ ወደ አፉ ሠደደና
''የሁለቱም አንድ ላይ መጥፋት ገርሞኛል....''
አላት: ኤልሣቤት ቀስ ብላ የዘካሪያስን ስሜት ተከታተለችና
''አሁን መድረስ ነበረባቸው ...''
አለች ሠዓቷን ገልመጥ አድርጋ
የቀረበዉን እንጀራ እያጣቀሱ እየጎረሱ ከሳቅ ከጨዋታ ጋር ገበታው ደማመቀ::
.
.
.
አንተነህ አሁን ያለው የግል ኤግዚብሽኑስጥ ነው ታላቁ የብሪታኒያ ጋለሪ ቴት ውስጥ ነው:: ባለው የጥበብ ክሕሎት ያስደመመው ሕዝቡ አንተነህ ሊያይ የፈለገበትን ምናብ ሊያጮልቅለት ሞክሯል በእርግጥ ከውስጡ ታግሎ ሚወጣው አያል ፈጠራው መጀመሪያ ገፅ ለብሶ ራሱ ሲያየው ልክ ወላጅ እናት አምጣ ልጇን ከነደሙ እንደምትስም ሁሉ እሱም መጀመሪያ ይቦርቃል: ከራሱ ጋር ሆኖ እያወራ ስለጥበብ ብሎ ያዜማል እነደግና በድጋሚ ለተመልካች አቀብሎ በፈለገው መልኩ ሲያዩለት ብሎም ሲያደንቁት ደስታ ይነባበራል:
ይህ የአንተንህ ምናልባትም መጠን ኖሮት ቢለካ የመጨረሻ ደስታው ነው: ከዚህ በኌላ ያለው ሁሉ ትርፍ ነበር አንድ ነገር ለማግኘት አንዱን ነገር መክፈል እቺህ ቁማርተኛ ዓለም የያዛት ሡስ ነው ሲላት ነበር ዛሬ ቀን ከኤልሣቤት ዕቅፍ ውስጥ ሲወጣ
''ሃሣብህን መቀየር አትችልም?''
አለችው ኤልሣ መልካም እንዲመኝላት ጠይቋት ወደዚህ ሲመጣ
''አልችልም''
መልሱ ውስጥ አንዳች የተለየ ዜማ ነበረው
''ፈራው''
ፍቅር ያጌጠ ገፅታዋ ውስጥ የቆነጀ ሀዘን ይታይባታል::
''ፈሪ ሚስት እንዲኖረኝ አልፈልግም''
ዝም አለች ከዛም ደረቱ ላይ ተነጠፈች አንገቱ ስር ተሸጎጠች
የዮሐንስ ዓይኖች በበኩላቸው ከዚህ በላይ መቅላትና መፍጠጥ አይችሉም እንጂ የተለየ ስሜት ይታይባቸዋል: ከሩብ ሠዓት በፊት ልቡ ምን ያህል ይመታ እንደነበር መልሶ ሲያስታውስ ድጋሚ ይደነግጣል: ከሄንሪ ሙር ክፍል ሲወጡ 11:45 ነበር::
አንተነህ ለሣምንት ያህል ዓይኑ ውስጥ የነበረው የፍራንሲስ ቤከን ስዕል ነበር:: 12:00 ሠዓት ላይ ከጊቢው ከዮሐንስ ጋር ተያይዘው ወጡ በሚለኒየም ድልድይ የተምስን ወንዝ ተሻግረው ወደታላቁ ቅዱስ ጳውሎስ ካቴድራል አመሩ: የአንተንህም የዮሐንስም ስልኮች እንደተዘጉ ነው::
.
.
.
የስንብት እራቱ ተገባዶ ቢራዎችና ሌሎች አልክሆሎች መቀዳት ጀምረዋሉ ስለሺ ይቀልዳል ዳንኤል በስለሺ ወሬ እንደተደሰተ ሁሉ ቢራዉን እየደጋገመ ምሽቱ እንዳስደሰተው በፈገግታው ያስታውቃል: ሮማን ከሠባዊት ጋር እየተተራረበች ከወንድሟ ጋር እየተለካከፍች ስሜቷን ዘና አድርጋለች:: ኤልሣ ግን ትክዝ ብላለች ደጋግማ ስልኳን ታያለች ምናልባት ጫጫታው የአንተንህን ጥሪ ያላሰማት መስሏት አሁንም አሁንም ስልኳን ትቃናለች::

የዘካሪያስ የሞባይል ስልክ ቢራና ውስኪ ከተደረደረበት ጠረጴዛ መሀል ሆኖ መብራቱን እያንቦገቦገ ጠርጴዛዉን ያነዝራል::
አነሳው

''ምን?.....''
ጩኸቱ ሁሉንም አስደነገጠ

''የት....?''
ስሜቱን አፍጥጠው ሚያዩ በጥያቄ አጣደፉት:: ዘካሪያስ ስልኩን ዘግቶ ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ቀብሮ በሃዘን ተደፋ::
.
.
.

ይቀጥላል
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Oct 24, 2008 2:36 am

.
.

.

ዘካሪያስ ዙሪያዉን የከበቡት በጥያቄ የፈጠጡ ጥንድ ጥንድ ዓይኖችን የውስጡ ሀዘን እንባ ባረጠበ ዓይኖቹ እያየ ሊፋጠጣቸው ፈራ: የሠማው አስደንጋጭ መርዶ ግን ልቡን ሠበረው:: ብረሐን ባልበረከተባት በዚች ምድር ያለጥላ እንደቁም ሕልም በሚወዣበሩበት እዚች አገር በርካታ ዓመታት የአብሮ ቆይታቸውን ጊዚያት ሲያስታውስ ሀዘነ:: የያዝኩትን ቋጥሬ ከተበጠበጥኩበት ዐፈር እመለሣለሁ ብሎ ነገ ዛሬ የሚል ጓደኛው ሕይወቱን ሊቀይርባት የተዋሳት ምድር ነፍሱን ነጥቃ በድኑን ስታቀብለው.... ዘካሪያስ ሀዘነ:: ዘር ሳይተካ ያባቱንም የርሱንም ስም ስጋ አልብሶ ለነገ ሳያቀብል ትንፋሹ ሲቋረጥ ....ሀዘነ:: ስለሺ በበኩሉ መርዶውን ሲሰማ ምሳር አንገቱን የቀላው ያህል ራሱን ሊስት ምንም አልቀረዉም::

በስደት ላይ 'ሚፈስ እንባ ከሠማይ ይድረስ ከምድር ይግባ ሁሌም እንቆቅልሽ ነው::

ከሠዓታት በፊት

ሙሤ ሚፈልጋትን ሤት ለማጥመድ ሲያስብ እንደሚዘንጠው ሁሉ ዝንጥ ብሏል:: ሰሞናቱን ጉንጩን የወረረዉን ፂሙን ሙልጭ አድርጎ ተላጨ: እንደወተት የፀዳ ነጭ ሸሚዙን አጥልቆ ራሱን በመስታወት አስተዋለው:: ወደድሮው ትዝታዎቹ መሄድ አልፈለገም ሚፈልገዉን ነገር ሁሉ ለማድረግ ሚፈነቅላቸው ድንጋዮች ግን ትዝ አሉት:: ከእንስት ጭን ስር ያለ ዓለም ሙሴን ሲያሰግድ ሙሴን ብዙ ብዙ ነገር ሲያስደርግ ኖሯል:: ግን የጠዋት ጅምበር መስኮቱን እስክታንኳኳ ድረስ ብቻ ነበር:: ቀን ሲረፍድ ራሱን መፈለጉ ግድ ይሆንበትና ወደ ሙሴ ጥልቅ ባሕር ውስጥ ሲገባ የፍራቻ ይሁን ይስንፍና ድጋሚ ሚረሳበትን ቀን መጠንሰስ ያስባል::
የራሱን ፊት አስተዋለው ከስቷል እጅግ በጣም ከስቷል:: ፈገግታዉን ሊፈልግ አስቦ ከናፍርቱን በግድ የአግድም ሲዘረጥጥ አሁን ድረስ መኖሩ አስጠላው:: እናቱን አሰበ... አባቱን አሰበ.... ወንድሙን አሰበ....ይልቅ የ3ቱም ፈገግታ ከዛሬ ጨለማ አውጥቶ ብርሐን ሲያጎናፅፈው ተሠማው እናም ናፈቃቸው መናፈቅ ብቻም አይደለም ማየትን ጓጓ::
ወንድሙ እጁን ስላሳጠረበት ከማኩረፍ ይልቅ የናፍቆት እያየው ሲጠብቀው አስተዋለ::
ቤቱስጥ ተንጎራደደ የቀዳውን አልክሆል ወደአፉ ሲሰደው ከእሕል የተነፋፈቀ ሆዱ ተቃጠለ:: ጓደኙቹ ትዝ አሉት የአንተነህ ጠንካራ ስሜት የዛሬ ዓላማዉን ብዙ ጊዜ ሲፋለም ቆይቷል:: በርግጥም ተሸንፎለት ነበር: የሠዓታት ለውጦች ናቸው::
ለእሕቱ የፃፈዉን ደብዳቤ ድጋሚ አነበበው እንባው ሸሚዙ ላይ እስኪንጠባጠብ አነባ:: ዓይኖቹን እንዳበሠ አንዳች ማያውቀው ኃይል ድንገት ውስጡ ተሞልቶ ፈንጠር ብሎ ቆመ:እናም ከትከት ብሎ ሳቀ:: ወደ ብረንዳው ሚያስወጣዉን የቤቱን በር ከፈተው ለንደን በምሽቱ ሕይወቷ እንደደመቀ ሁሉ ድምጿን ከፍ አድርጋ ትጮኻለች: ብርቱካን ቀለም ያላቸው ብረሐን ሚተፉት መብራቶቿ ጩኸቷን አድምቀውላታል:: ጥቁሩ ሠማይ በለንደን ድምቀት ተሸንፎ ኩርፊያዉን ተነጥቋል: ኳክብት 'ሚያስተውላቸው 'ሚፈልጉ ይመስል ለዕይታ ርቀው ይጣቀሳሉ ሠማያት ስር ተደብቀው አየሁ አላየሁ እንደሚጫወቱ.... ሙሤ እነኚህን ትዕይንት ሲያይ መኖር አጓጓው:: የለንደን መብራቶች ሚምቦገቦጉት የርሱን ነፍስ ሊታገዱ ሁሉ መሠለው::
ግን ከመለአከ-ሞት ጋር ወሣኝ ቀጠሮ ነበረውና በረንዳው ላይ በተለየ ስሜት ውስጥ ሆኖ ቆመ::ውስጡን ለዘመቻ በል! ሚለው ዓይነት ሙዚቃ ተሠማው ሳቁን ቀጠለ:: የሚኖርበት ፎቅ ስር ያለዉን ስፍራ ቁልቁል ቃኘው:: ከተደረደሩት መኪኖች ስር አልፎ አልፎ ሠዎች ሲተላለፉ ይታያል: ርቀታቸው የነፍሳት ያህል አሳንሷቸዋል:: ከ17ኛ ፎቅ......
ሤት እቅፍ ውስጥ ያለም መሠለው: ከነዘካሪያስ ጋር እየተቀላለደ ሚስቅም ይመስለዋል.... ለበቀል ያጨችው የመጀመሪያ ፍቅረኛው ምትስቅበትም ይመስለዋል: ከዛም የነኤልሣቤት እንባ... ይታየዋል::
ሕይወቱ ውስጥ የመሸጉ እነኚህ ክስተታት ከትንፋሹ ጋር ቅፅበት ሆነው ተቋረጡ::
.
.
.
ይቀጥላል

Last edited by ዋናው on Wed Dec 02, 2009 2:22 am, edited 2 times in total.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Oct 31, 2008 3:05 am

የፃፍኩት ሲያንስብኝ ነገ ዳጎስ አድርጌው እለጥፋለው ብዬ ነው.......
ለአስተያየት መስጫ አስተያየቶቻችሁ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Thu Nov 20, 2008 3:45 pm

::
Last edited by ዋናው on Wed Dec 02, 2009 2:24 am, edited 1 time in total.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ደጉ የት ገባ » Fri Nov 21, 2008 12:54 am

ዋናው wrote:የፃፍኩት ሲያንስብኝ ነገ ዳጎስ አድርጌው እለጥፋለው ብዬ ነው.......
ለአስተያየት መስጫ አስተያየቶቻችሁ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ::


ወንድሜ ዋናው በለንደንኛ ነገ ማለት አንድ ወር ግድም መሆኑ ነውን ???

በዛ ላይ ዛሬ እንኳ ምናምንቴ አገኘሁ ብዬ አይኔን አሞጥሙጬ ከች ስል እንደ ጓድ ሊቀ መንበር ዛሬንም በፉከራ አለፍከን:: ተው ጡር አለው

በል እጅህን ይፈታልን ዘንድ እጠልያለሁ
ደጉ የት ገባ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 548
Joined: Wed Feb 22, 2006 4:02 am
Location: usa

Postby ዋናው » Fri Nov 21, 2008 5:36 am

.
.
.
ከሁለት ቀናት በኌላ

አንተነህ የጓደኛው ሀዘን ልቡን እንደሰበረው ካትሪን ጋር ደረሰ የዛሬዋን ቀጠሮ ማሸጋገር ቢችል ደስ ባለው ግን ትላንትና ለዛሬ ሲያስተላልፈው ካትሪን ውስጥ የነበረው እርግጠኛነት አንተንህን አስፈራው: ምክኒያት ሚደረድሩላት ዓይነት እንስት እንዳልሆነች ያውቃል
እቺ ዓለም ግን ላንዱ ስትሠጥ ለምን ካንዱ ትወስዳለች? ብሎ ከራሱ ጋር ተሟገተ ዛሬ ቀትር ላይ የሙሤን አስክሬን ከበው ያወሩ የነበሩት የኃይማኖት ሠዎች ውስጥ ደጋግማ የተነሳችው ቃል ትዝ ብሎት ፈገግ አስባለው ከፈጣሪ ትዕዛዝ ውጪ ሚሆን አንዳችም ነገር የለም... ምትለዋ
''እኔን የፈጠረኝ ፈጣሪ ግን ራስህን ከፎቅ ፈጥፍጥ ብሎ ሚጨክን ፈጣሪ አይደለም'' እያለ ከራሱ ጋር ሲያወራ ድንገት ፈገግ ሲል የቀረበላትን ሠላጣ ከነጭሽንኩርት ዳቦ ጋር እያጣጣመች ምትጎርሰው ካትሪን ድንገት አይታው ከሃዘኑ መለስ ሚልበትን ቅፅበት እንዳገኘች ደስ ተሰኝታ

''ምነው?''
አለችው: አንተንህ ፈገግ አለና ሹካዉን ወደምግቡ ሠደደ
''... የጓደኛህ ሀዘን እና የድላችን ቀን ባንድ ቀን በመሆኑ አዝናለው አንትነ...''
ጥቁር በጥቁር ለብሳ ጥቆር ዘንፋላ ፀጕሯን ጀርባዋ ላይ ለቀዋለች የዓይኖቿ ሽፋሽፍት ደጋግሞ የዓይኖቿን መገለጥ ጮክ ብለው እንዲናገሩ ተዕዛዝ የተሰጣቸው ይመስላል

''ምን አዲስ ነገር አለ ብለሽ ነው ካትሪን ... እዚጋ ሲጎድል እዚጋር ይሞላል አንዱ ሲያለቅስ አንዱ ያዜማል... ዛሬ በነኚህ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ውስጥ ጣልቃ ስለገባ ነው እንጂ...''

''ቆይ ግን በጣም እንደምትቀርበው ነግረህኝ ነበር አይደል?''

''አዎ''

''ታዲያ እንድዴት ልትቀይረው አልቻልክም ማለቴ እንደዚህ ዓይነት ሴንሴቲቨ ስሜት ያላቸዉን ሠዎች መቀየር በጣም ቀላል ነው ሠው ሊጎዱ ያሰብትን ሠዎች መቀየር እንጂ ሚከብደው....''
አለች ካትሪን የወይን ብርጭቆዋን አንስታ እየተጎነጨች
''ካትሪን አንድ ነገር ከታየሽ መጥፎ ነው... ግራ ቢገባሽ ይሻላል ሙሴ ግን ያ ነገር ከታየው ቆየ ''
ካትሪን ስለ ሙሤ ሃዘን መካፈል የመፈለግ ስሜት ያህል ትንሽ አዋራችውና ወደራሳቸው ጉዳይ ገባች

'' ስዕሉ የት እንዳለ ለማወቅ አልጎተጉትህም የትም የማስቀመጥ መብት አለቹ.... ግን ለሁላችንም ዓላማና ደሕንነት ሲባል አስተማማኝ ቦታ መቀመጥ ይኖርበታል''

''ያን ሁሉ ነገር የቻልን ይሄን እንደማያቅተን ትጠራጠሪያለሽ የሚል እምነት የለኝም የነገርሽኝ መንገር ስላለብሽ እንደሆነ አውቃለሁ ግን አይዞሽ አትስጊ :''
አሳላፊው የተበሉበትን የሠላጣ ሠዓኖች አንስቶ ትኩስ ምግብ የያዙትን ሠዓኖች ከፊታቸው አኖረና ሄደ:: የምግቡ ሽታ ብንን ከሚሉ ትንንሽ ትኩስ ጪሶች ጋር ስፍራዉን አወደው

''እስካሁን ስንጀመር ከተስማማነው ውጪ የተቀየረ ነገር የለም ለጆን ሚደርሰውም ክፍያ ዶክተር ኤድዋርድ ያነሳዉን ጥያቄ አሳምኜዋለሁ''
አንተነህ የቀረበለትን ትኩስ ስቴክ በሹካ እየገዘገዘ
''ካትሪን አልዋሽሽም በጣም ስጓጓለት የነበረው ቀን ብሩን 'ምንካፈልበት ቀን ሳይሆን ስራዉን ጨርሰን ምንገላገልበት ቀን ነበር ''
ፈገግ ብላ ተነፈሰችና
''እንደዚህ ዓይነት ነገር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ስገባ እኔም እንደዚህ ዓይነት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር''
አለችው::
''... በዚህ አጋጣሚ ሊቨርፑል ሚገኘው ቴት ጋለሪ ለሚቀጥለው ሠመር ስራዎችህን ሊያሳዩ መፈለጋቸዉን ሚናገር ደብዳቤ እንደደረሳቸው ዛሬ ዶክተር ኤደዋርድ ነገረኝ ''

''በጣም ደስ የሚል ዜና ነው ግን እምቢ የማለት መብት ካለኝ ርፊውዝ ባደርገው ደስ ይለኛል ''
አለ አንተነህ ድንገት ፊቱ ቅይርይር እያለ

''ለምን?''
እሱን አገር በጣም ነው ምጠላው ከውስጤ በፍፁም ልረሳው ማልችል ጠባሳ አኑረውብኛል ካትሪን''

ካትሪን እንደመደንገጥ ብላ ምግቡ እንደበቃት ሁሉ ከናፍርቷን በገበታው ሶፍት ጠራርጋ
''አንተ ላይ?''

''አዎ ካትሪን....''
አላት ማይፈልገው ትዝታ ውስጥ እየገባ

''ምን አረጉህ?''

''የሊቨርፑል ሕዝብ ለዚህ ቀለም ክፉ ጥላቻ አለው''
አላት የእጁን ቆዳ ቆንጥጦ እያሳያት አቆነጣጠጡ እነሱን በአካል አግኝቶ ሚመዠልግ ነው ሚመስለው

''አሃ''
አለች ካትሪን እንደገባት ሁሉ

''...እዚህ አገር እንደመጣው እዛ ተመድቤ ነበር ምኖረው የዕድል ሆኖ የምኖርበት መንደር ውስጥ ጥቁር ሚባል አልነበረም ታዲያ ድንገት የወጣው እንደሆን አረጋዊያኑ ምራቃቸዉን ሲተፉብኝ ሕፃናቱ ጎ ሆም! እያሉ ሲጯጯሁብኝ ለመንግስት አቤት ብዬ ሠፈር ቀየርኩኝ ... ግን የተሻለ አልነበረም አንድ ቀን ቢራ አምሮኝ ፐብ ስገባ ቀጥቅጠው ቀጥቅጠው ለቀቁኝ''
አላትና የሸሚዙን እጄታ ሰብስቦ ክንዱ ላይ ያለውን ጠባሳ አስያት
''... ሚገርምሽ ፖሊሶቹም ጥፋተኛ እኔ እንደሆንኩኝ ፈርደው አስረው አሳደሩኝ..... በሣምንቱ አገሩን ለቅቄ መጣው''
አላት በምሬት በሹካው ሠዓኑን እየቀበቀበ

''ታዲያ'ኮ መበቀል ምትችለው ሊቨርፑልን ባለመርገጥ ሳይሆን ያ የናቁት ሠው ምን ዓይነት በሣል አሕምሮ እንዳለው በማሳየት ነው... አውቃለው ሠሜናዊ እንግሊዛዊያን በጥንት አስተሳሰብ ውስጥ ሆነው መኖርን ነው ሚፈልጉት ''
የካትሪን ስልክ ድንገት ሲጮኽ አንስስታ ተነስታ እያዋራች ፈጥና ከአንተነህ ራቀች ::
አንተነህ አንድ የሆነ ስሜት ውስጡ እንደነገረው ሁሉ ድንግጥ አለ... ከዛ ራሱን ታዘበና ቢራዉን ተጎነጨ:: ካትሪን ስልኩን አዋርታ ስትጨርስ ተመለሰችና ወይኗን ተጎንጭታ ወደመፀዳጃ ቤት መሄድ እንድደምትፈልግ ነግራው ሄደች: አንተነህ እግሯን ጠብቆ ስልኳን ከቦርሳዋ አውጥቶ ለመጨረሻ የደወለላትን ካየ በኌላ ቦታው መለሰው:: አንድ እሱ እንዲሰማ ያልተፈለገ ነገር እንዳለ ጠረጠረ::
.
.
.
ይቀጥላል


Last edited by ዋናው on Sun May 16, 2010 11:23 pm, edited 1 time in total.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Tue Nov 25, 2008 4:27 am

.
.
.
የአዲሳባ እንግዶች የጉዙ ቀናቸዉን በሙሴ ሀዘን ምክኒያት ለጥቂት ቀናት አስረዝመውታል:: ሙሴን ሮማን እና ባሏ ዳንኤል የሠባዊትን ያህል ባያውቁትም አሳዝኗቸዋል: ሌላው ቢቀር በአገር ልጅነቱ ባይተዋር ሆኖ ሕልሙን እውን ሳያደርግ እስትንፋሱ መቋረጡ ልባቸዉን ነክቷቸዋል::
ሠባዊት የሙሴን ሞት ስትሰማ ለሙሴ ብላ ዓይኖቿ እስኪያብጡ ብታነባም የነገን የፍቅረኛዋን ዘካሪያስ ቀን አስባ ፈራች: ሳትስማማበት የቋጨችውን ጉትጎታ አሁን ድጋሚ አነሳችው...

''ዘኪዬ... ይህ አገር 'ሚተማመኑበት አገር አይደለም ትክክለኛ ዓላምህ ግን ምንድነው?''
አለችው በእምባ ዥረት ያበጡ ዓይኖቿ ቀልተው

''ሠቢዬ... በራሳችን የቅርብ ሠው ስለመጣንጂ ይሄ ዓይነቱ ዜና'ኮ ድሮም የነበረ ነው:''
አላት አጠገቧ ሄዶ ከተቀመጠችበት ሶፋ ላይ እያቀፋት
''ምክኒያቱ ምንድነው?''

''ምክኒያቱን ብዘረዝርልሽ አያልቅም ሠቢ ከአገር የወጣ ሁሉ በሠላም ይመለሳል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው የትም ቢሆኑ ማይቀረው ሞት እዚህም መኖሩን አትርሺ... ለምን ራስን ማጥፋት ለሚለው ጥያቄሽ ግን ምክኒያቱ ብዙ ነው:: ብዙ ታውቂያለሽ? ''
አላት ዓይኖቹን ወደግድግዳው ተክሎ

''ታዲያ አንተስ ከነኚህ ብዙ ምትላቸው ምክኒያት ውስጥ ነፃ መሆንህን በምን አውቃለሁ....?''
አለች ለቅሶ በሚመስል ዜማ
''ሠቢ..... ካ..ሞን!''

''እንደምወድህ ታውቃለህ አይደል...? ''
ንፍርቅ ብላ እቅፉ ውስጥ ገባች ትኩስ ትንፋሿ ደረቱን ተሰማው ጥብቅ አድርጋ ስትይዘው መውደዷ የጥሪ ያህል ውስጡ አቃጨለበት... ስለፍቅር ሚያዜም አንዳች ዜማ ጆሮው ላይ ሚያዜም መሰለው

''ቫኔሣን ትወዳታለህ አይደል...?''
ሠባዊት ደረቱ ስር ሆና ለቅሶና ጥያቄዋን ቀጠለች

''ይሄንን ጥያቄ ስንቴ ልመልስልሽ?''

''ታዲያ ከኔ ጋር ለመኖር ያልፍቀደከው ለምንድነው?''

''እኔ አልፈቀድኩም አልኩሽ...?''
ቁጣም ማባበልም በሚመስል ፀጉሯን እያሻሻት ጥያቄዋዎቿን በጥያቄ ይመልስላታል: ሠባዊት ትኩስ እምባዎቿን እያፈሰሰች ከዘካሪያስ ሠውነት መለየት ባለመፈለግ ተለጥፋለች: ደጋግማ በዘካሪያስ ፍቅር የመውደቋን ምስጢር ስታስበው ሁሌም ለራሷ እንቆቅልሽ ይሆንባታል አንድ ፍፁም ልትደብቀውና ልትክደው ማትችለው ነገ ግን መቼም ቢሆን ዘካሪያስ የርሷ ብቻ እንዲሆን መመኘታን ማቆም ያለመፈለጓ ነው::

''... ሠቢዬ ትንሽ ጊዜ ስጪኝ ሁሉም ነገር ይስተካከላል... አንቺ ከምትፈልጊው በላይ እኔ ካንቺ ጋር አብሮ የመኖሩን ጉዳይ እፈልገዋለሁ... ልጄ ትንሽ ካደገች ምትዪኝን ሁሉ አደርጋለሁ''

ሠባዊት ቃል የመስጠቱ ጉዳይ ቢያስደስታትም በሁለቱ አብረው የመኖር ሕልም ውስጥ ከቫኔሳ ጋር ያፈሯት ፍሬ ምክኒያት መሆኗ አስከፋትና.... ደግሞ ጨቅላዋ ሕፃን ፊቷ ድቅን ስትልባት ራሷ በደለኝነት ተሰማት:

''ይቅርታ በእናትና ልጅ ፍቅር ጣልቃ እንኳን መግባት መቼም ቢሆን አልፈልግም ዘኪ...''
አለች ቀና ብላ በውብ ድፍርስ ዓይኖቿ ስሜቱን እያስተዋለች::
''እንደዛ ዓይነት ስሜት እንዲሰማሽ ፈልጌ አይደለም ይሄንን ያልኩሽ ሠቢ....''
አላት ዘካሪያስም በበኩሉ ስሜቷን አስተውሉ ምን እንዳሰበች ገብቶት
''ሠቢ... የመቆየቴ ምክኒያቴ ማኪ መሆኗን እስከዛሬም ያልነገርኩሽ አሁን የተሰማሽን ስሜት ፈርቼ ነው... አልዋሽሽም ማኪን በጣም ነው ምወዳት ያ ማለት ግን ላንቺ ካለኝ ፍቅር ጋር ምንም ሚያገናኘው ነገር የለም: ከእናቷ ጋር ምንም ዓይነት የቀረ እንጥፍጣፊ የፍቅር ግኑኝነት እንደሌለኝ ነግሬሻለሁ ካስፈለገም በማኪ ስም እምልልሻለሁ...''

''እንዳምንህ ልትምልልኝ አያስፈልግም ''

እየተቃቀፉ እየተሳሳሙና እየተላፉ ቆዩ:: ፍቅር በየትኛዉም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ራሱ 'ሚፈልገዉን ጥንዶቹን የማዘዝ መብት አለው: ስለስሙ ብለው የተጎዱና ሕሤትን ያገኙም ይገዙለታል::

''በነገራችን ላይ ዘኪዬ... አዲሳባ ገዛሕኝ እየዛተ ጥርሱን ነክሶ ነው ሚጠብቅሽ ብለው ነገሩኝ...''
አለችው ነገሩ ዜና ቢሆንም ጥቂት ሚያፌዙበት ነገር በማግኘቷ ፈገግ እያለች::

''ምን ሊያደርግ?''

''ያው የንብረት ይገባኛል ጥያቄዉን አንስቶ ነዋ ''

''ተጠንቀቂ ሊጎዳሽ ይችላል ሕግ ያወጣኛል ብለሽ ምትኮሪበት አገር አይደለም ምትህጂው ሠቢ....''
አላት ይሄንን ዜና ስትነግረው ግን አንድ ደስ የማይል ስሜት ተሠማው ምን እንደሆነ ግን በውል አላወቀዉም
.
.
.
ይቀጥላል
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Nov 28, 2008 3:54 am

::
Last edited by ዋናው on Sun May 16, 2010 11:28 pm, edited 1 time in total.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sat Dec 06, 2008 1:23 am

.
.
.
ዮሐንስ አንተነህ ቤት ሲደርስ ቀኑ ረፋፍዶ ነበር:: አንተነህ የሙዚቃዉን ድምፅ ጮክ አድርጎ ስቲል ፐልስ የተሠኙ የሬጌ ስልት አቀንቃኞች የሚያዜሙትን ኢሞሽናል ፕሪዝነርየሚለዉን ዜማ አብሮ ያዜማል::
''ዛሬ ኤልሢ የለችም እንዴ?''
አለው ፀጉሩን ሚያፍተለትለዉን አንተነህን በትከሻው ተሳልሞ:
''የለችም ባክህ ቤቱ በጣም ዶኩኮኛል...''
አለው ዜማዉን እያዜመ
''የት ሄደች?''
''እሕትህ ጋር ''
ዮሐንስ ሲጋራዉን አቀጣጥሎ አንዴ ሲምገውና ሲያቦነው ቤቱ በጭስ ተሞላ:
''... ዛሬ ደስተኛ ትመስላልህ?''
አለው በጪሱ መሀል የአንተነህን ፈገግታ የተሞላበት የሚያዜም ፊት እያየ
''ሁሌም ደስተኛ ለመሆን እንደጣርኩኝ ነው... ብቻ አንዳንዴ አይሳካልኝም እንጂ''
አለ አንተነህ ፈገግታው ከፊቱ ሳይጠፋ
''ምን ተገኘ?''
''ለመደሰት ሁሌም አንድ ነገር መገኘት የለበትም... አንዳንዴ እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ ደስ ይልሀል.... ታዲያ ምክኒያቱን ለማወቅ መጣር የለብህም ያንን ደስታ ዝም ብለህ እየተደሰትከው ለማሳለፍ መሞከር ነው:''
ዮሐንስ በአንተነህ ንግግር ተገርሞ
''አንቱሽ... እኔ በበኩሌ ምንም ሳላገኝ ደስ ብሎኝ አያውቅም ካለኝም ጤነኛ አይደለሁም''
አለው:
''ጆኒ.... ይሄውልህ ለዚህ'ኮ ነው ደስታ ቶሎ ምታልቅብን... ሁሌም ምንሸምትበት ነገር እንፈልግላታለን... በርግጥ የሁላችንም የደስታ ምንጭ እንደየራሳችን ይለያል ግን ውስጥህን ደስ እንዲልህ ምታዘጋጀው ራስህ ነህ:''
ዮሐንስ ጓደኛው አንተነህ በዚህ መልኩ ያለዉን ሃሣብ ማንሸራሸር ከጀመረ እንደማያቆም ስላወቅ
''በል አሁን ያንተን ደስታ ምንጭ ምርመራው ይቆየን እና ወጥተን ምሳ እንብላ ..... ጠይቆኛል''
አለ ሆዱን ገልጦ እየዳበሠ

''አዎ እንውጣ እኔም መርዝ የሆነ ቡና አምሮኛል... ኤልሲ ነበረች በሆነ ነገር እየመታች ምታጠጣኝ ''

....................................................*****.....................................................

''ዛሬ ምን ታይቶህ እንጀራ አማረህ?''
አለው አንተነህ የበሉበትን ሂሣብ ከፍለው ሊወጡ ሲል: ይሄን ጊዜ
''የተከበሩ ክቡር አርቲስት ፒካሶ''
የሚል የሴት ድምፅ ሁለቱንም አስዞራቸው
''አንቺ........ አለሽ?''
አለ አንተነህ ደመናዉን ሚያባርር የአዜብን ስርጉድ ፈገግታ እያየ
''አለው እኔማ ምን እሆናለሁ...''
አለችና በየተራ ጉንጫቸዉን ሳመቻቸው
''ስለሙሤ..... ሃዘን ከሌላ ሠው በመስማቴ ተቀይሜያቹ ላላናግራቹ ወስኜ ነበር ለማንኛዉም ሌላ ጊዜ እንወቃቀሳለን''
አለች ጥርሳቸው ላይ የሰኩትን ስንጥር አይታ ሊሄዱ እንደሆነ ገብቷት...
''አዚቲ... እኛ በነበርንበት ስሜት ውስጥ ሆነሽ ማን ለቅሶ ይድረስ ብለሽ ማሰቡ ይከብዳል''
አላት አንተንህ
''አዪ... ምነው ቢያንስ ለኤልሲ እንድታስታውሰኝ ብትነግራት... ምንም ላደርግ አይደለም ግን ቢያንስ መስማት ነበረብኝ ብዬ እንጂ... ለነገሩ ከጓደኛችሁ ጋት ብትወግኑ አየገርመኝም...''
አለች ፊቷ እንደመከፋትም ማሾፍ እንደፈለገም እየሆነ
''እኛን እዚ ውስጥ ምን አገባን ብለሽ... ለነገሩ'ኮ አንቺም ጠፋሽ''
አለ ዮሐንስም ፀጥ ላለማለት በሚፈልግ ስሜት ሆኖ እያያት
''እሱስ አዎ ልክ ነህ ጆን... እናንተ ምን አገባችሁ ''
አለች አዜብ አንዳች ተተለየ ስሜት የሚታይበት የ'ውሸት ሳቅ በትንሹ እየሞከረች:
''ኤግዚብሽኔ ላይ ስላየውሽ ደስ ብሎኛል አዚቲ... የዛን ቀን ሳላመሰግንሽ ሄድሽብኝ''
አላት አንተነህ
''አንተም አክብረህ ስለጠራህኝ አመሰግናለሁ አንተን በማወቄ ብቻ ሳይሆን በአግርልጅነቴ ጭምር ነው የኮራዉት... ማለቂያው ላይ ሚዘጋጀዉን ፓርቲ በሙሤ ሞት ምክኒያት መሰረዝህን ሠማው::''

''አሀ ዝምብለን ነዋ ጠፋሽ ምንለው ስለሁሉ ነገር ምታውቂ ከሆነማ አልጠፋሽም ''

''ሁላችሁም የጠፋው የመስላችኌላ እንዳልጠፋ ሆኜ ከጉርፓቹ እንደተዋወቅኩኝ ማውቀው እኔ ብቻ ነኝ:''
አለች በረጅሙ ተንፍሳ: አንተነህ የሞባይል ስልኩን ሠዓት አየና
''በሌላ ጊዜ አብረን ቡና ለመጠጪያ 'ሚሆን ጊዜ ካለሽ ብንገናኝ ደስ ይለኛል''

ተሰናብተዋት ከሐበሻው ምግብ ቤት ሲወጡ አንተህም ዮሐንስም ውስጥ ስለአዜብ ሚብላላ ነገር ነበር ግን ሁለቱም ሊናገሩትና ስለርሷ መወያየቱን አልፈለጉትም::
ፒከድሊ የተሠኘ ስፍራ ደርሰው ወደ አንድ ቄንጠኛ ፐብ ውስጥ ሲገቡ ካትሪን መደገፊያዋ ላይ ያኖረችው ባለ ፈር ግራጫ ካፖርት ዙሪያዋን አቅፏት መለኪያዋን ይዛለች::
ከውጪ ገና ከአመሻሹ 5 ሠዓት እንኳን ሳይሆን ፈጥና የገባችው ደብዛዛ ጅንበር ጨለማ ውስጥ ሠምጣ ሙት ሆናለች : ውርጩ ጆሮን እያቃጠለ ጣትን እየጠዘጠዘ እግርን ያደነዝዛል:: ፐቡ ውስጥ ወቅታቸው ደርሶ ተሰቅለው በመብራታቸው ደስ ያላቸው ሚመስሉት የገና መብራቶች ከባልኮሊው አናት ጥግ ሆነው ቀለማቸዉን እየቀያየሩ ይሳሳቃሉ::
ዮሐንስ እና አንተነህ ሲገቡ መጠጣቸውን ይዘው የቆዘሙ ጥቂት የቤቱ ታዳሚያን ዓይኖቻቸዉን ወረወሩ::
.
.
.
ይቀጥላል
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests

cron