ጥላ ዓልባ__________(ልብ ወለድ)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዋናው » Sun May 07, 2006 8:12 pm

(-ዘጠኝ-)
.
.
.
አንተነህ እቺህን ካፌ የሚወዳት ውስጧ እንደልብ ሲጋራ ማቡነን ስለሚቻል ነው:: የተም ሰፈር ቢቀጥሩት የዚህን ካፌ ስም ጠቁሞ የቱጋ እናዳለ ማጠያየቅ ነው የመጀመሪያ ስራው በቁሙ አንድ ካፌ ላቴ ሲጠጣ ብርዱም ከውስጡ መሽሹ አልፎ ቁርሱ ማለቁን የሚናገረው ሆዱም ትኝሽ ጋብ አለለት አንተነህ ለእህል እምብዛም ነው መብላት ይሰለቻል የሚል በሀሪ አለው:: 'ተፈጥሮ ያመጋገብ ድግግሞሽ ላይ አንድ የተሸወደበት ነገር አለ...ሠው እንዴት በቀን ሦስቴ ውስጡ ምግብ የተባለ አደንዛዥ ዕጽ ይከታል?' ያላል ሁሌም ታዲያ ሆዱ ትንሽ ነገር ብትፈልግም ሲራብ ወደምግብ መሮጡ የተፈጥሮው ግዱ ነውና የህለት ተግባሩ ነው::
ዛሬ በቴት ጋለሪ ለህዝብ መታየት የሚጀምረውን የታዋቂው ስፔናዊው ቬንሰንት ቫንጎግ ስራዎችን ለማየት ከዘካሪያስና ከቫኔሳ ጋር ተቀጣጥሮ ነው ቀድሞ የመጣው:: ሦስቱንም የመግቢያውን ቲኬት አባል ከሆነበት ክበብ አግኝቶዋል:: እንደዚህ ባንድ ቀን ከስልሳ የበለጠ ፓውንድ ሲያተርፍ የዚህ የሰዕል ክበብ አባልነቱን ያመሰግናል::

ዘካሪያስ ሲጋራውን እያቦነነ ፍቅረኛው ቫኔሳን ከጎኑ በክንዱ እንደሻጠ ደረሰ አንተነህ አይቷቸው ሠሀቱን ገልመጥ ሲያደርግ ዘካሪያስም የራሱን ሞባይል አውጥቶ ሰሀቱን ተመልክቶ

''አቤት ፒካሶ ደግሞ ዝምብለሽ እንደሯጭ ሠሀት ማየት ትወጂያለሽ አውን 6 ደቂቃ ነው የዘገየነው....''
አለውና ለሰላምታ ተሳለመው

''ጤና ይስጥልኝ... ቫኔሳ...''
አላት ቫኔሳንም ጉንጯን በጉንጩ እየሳመ በአማርኛ:: የተውሰውኑ የሠላምታና የምስጋና ቃሎችን ዘካሪያስ አስተምሯታል::

''ቲና...ይስቲሊ....አንተነህ..''
አለችው ተንተባትባ ፍልቅልቅ እያለች ባንድ ነገር የምሯን ስትስቅ ጉንጮቿ ፍም ይመስላሉ::
ጥቂት ሠላምታዎች ከጠፋህ...ከጠፋሽ...ጋር ተለዋውጠው አንትነህ የላቴውን ሂሳብ ዘጋና ወጡ::

ሞደር ቴት ዓለማችን ውስጥ ከታወቁት ታላላቅ ጋለሪውስጥ አንዱ ነው:: ለንደን ቅርሴ ብላ ከምትኮራባቸው አንኳር መስህቦቿ አንዱ ነው:: የታወቁ የዓለም ታላላቅ ሠዓሊዎችና ቀራጮች ምርጥ ስራዎች የሚገኝበት ጋለሪ ነው:: ወተር-ሉ በተባለ ስፍራ ላይ ከለንደን ጠመዝማዛ ተምስ ወንዝ ፊትለፊት አድርጎ የታነጸው ይህ አንጋፋ ጋለሪ በየቀኑ ብዙ ጎብኚዎች አሉት::
ከዋናው መግቢያ በር ትይዩ ቀጭኑ የዕግረኞች ድልድይ በእውቅ መሀንዲስ ተሰርቶ በብረት አምሮ ከበታቹ ድፍርሱን ተምስ ወንዝን እያሳየ ወደ ታላቁ የቅዱስ ጳውሎስ ካቴድራል ቤ/ቲያን ያሻግራል::
እዚህ ቴት ጋለሪ ውስጥ ሥራዎቻቸው ከሚገኙት ውስጥ ታላላቅ የዓለማችን ሠዐሊዎች መካከል
..ፒት ሞንድሪያን,ሳልቫዶር ዴሊ,ሄንሪ ማቲስ,ማርክ ሻጋል,ፓፕሎ ፒካሶ,ካንዲኒስኪ,ሔንሪ ሙር, ክላውድ ሞኔት,ኤድዋርድ ሞኔት, ቬንሰንት ቫንጎግና የተላያዩ ቀራጭና ሰዐሊዎች ሥራዎች ይገኙበታል:
ወደጋለሪው ገብተው የዕውቁን ቫንጎግ ሥራዎች አንተነህ በራሱ ዕይታ ምን እንደሚመስል ለነ ዘካሪያስ ያስረዳቸዋል:: ይህ ታዋቂ ሠው ኢምፕሬሽኒስት ተብለው ከሚጠሩት ሠዐሊዎች አንዱና ዋነኛው ነው የቀለሞቹ ቅቦች ከሌሎቹ ለየት የሚያደርገው በራሱ የአሳሳል ዘዬ በመጠቀም /ስፒራል/ የተጠቀለሉ ፎርሞቹን መጠቀሙ አንዱ ነው ቫንጎ በራሱ ህይወት ለየት ያለ አመለካከት ያለው ሠዐሊ ነበር ከስዐሊነቱ በፊት ቄስ የነበረ ሠው ነው:: ባንድ ወቅት አንዲት ሤት አፍቅሮ የፍቅሩን ሀይለኝነት ለመግለጽ ላፈቀራት ሤት አንድ ጆሮውን ቆርጦ ልኮላት ነበር::
ዓለማችን ላይ ውድ ስራዎች ካወጡት ስራዎች ዋነኛው የቫንጎግ ዶክተር ጋሼ የተሰኘው ስራው ነው ይህም ሰዕል በጨረታ ቀርቦ 82.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ነበር የተሸጠው:: አንተነህ ያነበበውን ለነዘካሪያስ ሲያስረዳ ባንድ ወቅት ቫንጎግ አብዶ ሆስፒታል እንደነበርና ከብደቱም በዋላ በርካታ ምርጥ ስራዎችን እስከህለተ ሞቱ እንደሰራ ነገራቸው::

ቫኔሳ ባገኘችው ትንታኔና ማብራሪያ ተመስጣ አንተነህን ታየው ነበር:: ሁሌም በአንተነህ ገደብ አልባ የጥበብ ዕውቀት ትደነቃለች::
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው_______________________________________:[/list]
Last edited by ዋናው on Wed Feb 28, 2007 4:27 pm, edited 2 times in total.
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon May 08, 2006 4:47 pm

(-አሥር-)
.
.
.
ዘካሪያስ የአንተነህን የሰዕል እውቀት ይኮራበታል ሁሌም ይጠይቀዋል:
''ፒካሶ እስቲ እዚህጋ አንድ ጥያቄ አለኝ እዚህ ስራ ውስጥ አንድ ያልተለመደ አይነት ነገር አጋጥሞኝ ነው የቀለም ቅቡ ሪያል ስቲክ/ርሀዊ/(ዕውነታዊ) ስለሆነ ነው የገረመኝ ግን ከላይ ያሉት ኩዋክብት ከመብዛታቸውም መጠቅለላቸው ትንሽ ግር ብሎኝ ነው...''
አለው ዘካሪያስ በደንዳና ሠውነቱ የልምዱን ያንገቱን ጀርባ በመዳፉ እያበሰ ሰዕሉ ላይ እንዳተኮረ

''ይኄውልህ ዘኪ ቅድም እንዳልኳቹህ ሠውየው ትንሽ ለየት ያለ የራሡ እይታ አለው ...በርግጥ ኩዋክብቶች ለኛ አይታዩንምንጂ ብዛታቸው ከዚህም ይልቃል...ግን ቫንጎግ በዚህ 'ኩዋክብታማ ምሽት' በተሰኘው ስራው ላይ........''

አንተነህ ለቫኔሳም ጭምር እያስረዳ እያለ አንድ መልኩ ግርጥት ያለ እንግሊዛዊ መጥቶ አቋረጠው:: ጨበጠው በሚማርበት ተቋም ውስጥ የቪዥዋል አርት ዲፓርትመንት አላፊ ነው አንትነህን የሚያደንቀው ሠው ነው::

''ሥራዎቹን እንዴት አየሀቸው አንተነህ...?''
አለው ሠውየው ቫኔሳን እና ዘካሪያስን በየተራ ተዋውቆ: መመለጥ የጀመረ ጸጉሩን በረጅም ነጭ ፀጉሩ ከውኃላ ወድፊቱ አምጥቶ መላጣውን ሸፍኖታል::ቅጥነቱ የገነነ ነው::የአወራሩ አኩኃንና የፊቱ የነግሮች አገላለፅ ሠዶማዊ መሆኑን ይመሰክራል

''ጥሩ ነው ሚስተር ዴቪድ ያው የቫንጎግ ሥራውችን ማየታችን ዕድለኞች ነን ማድሪድ ድረስ ከመሄድ ተርፈናል...ቅቅቅ''
አለው አንተነህ ፈገግ ብሎ::

''በነገራችን ላይ ብራውን-ስቶን የተሰኘ እውቅ ጋለሪ በተቋሙ ውስጥ ያሉትን ያንተን ሥራዎች አይቶ በመማረክ ለዕይታ ለማቅረብ ጋብዞካል...እርግጠኛ ነኝ በቂ ሥራዎች ይኖሩካል....አንተነህ''
አለው ቀጫጫው እንግሊዛዊ, ሦዶማዊው,ዴቪድ

''ዋው...ጥሩ ዜና ነው አውቀዋለሁ ብራውን-ስቶን ጋለሪን በህጋቸውም መሰረት ትንሽ ጊዜ ስለሚፈጅ በበቂ ለመዘጋጀት እችላለሁ ሚስተር ዴቪድ::''
አለው አንተነህ ኩራትና ደስታ ውስጡ እየተሰማው::
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው_________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon May 08, 2006 6:50 pm

(-አሥራ አንድ-)
.
.
.
ዘካሪያስ የሚያነበውን የታዋቂው ደራሲ ስቴቨን ኪንግ መድብልን ለምልክቱ ገፁ ስር ብጣሽ ካርድ አኑሮ ያንጫረረውን ስልኩን አነሳ የቫኔሳ የእረፍት ሰሀት ነበር:: ስልኩን ግን ቢያየው እንግዳ ቁጥር ሆንበት

''ሀሎ....'' አለ::
ሠባዊት ነበረች
''አንተ... እንዴትም የምታላምድ ሠው ነህ ምነው ደውለህ ለመድሽ ወይ? አይባልም ምነው ዘኪ...''
አለችው የወቀሳ ሰላምታዋን እያዥጎደጎደች

''ቆይ ልደውልልሽ ::''
ብሎ ስልኩን ዘጋውና በራሱ ስልክ ደወለላት::
''.....ይቅርታ ይኄውልሽ ይሄ አገር እንዲህ ቀልበ-ቢስ ያደርጋል በናትሽ ሠባዊት አትቀየሚኝ ''

''እንዴት ነህ ግን ትላንትናኮ ሮሚ ጋር ደውዬ ትዝ አልከኝ''

''አለው ምን እኔ እዛም ደውዬ አላውቅ ...አንቺ እንዴት ነሽ ለመድሽ ወደለንደን ተመለሽ?''

''አዎ ተመልሻለሁ እዚሁ ነው ያለውት ምን ያገራችሁን ብርድ አልቻልኩትም ባክህ ዘኪ''

''ምን ይደረግ ቀዝቃዛ ነው አይደል...አውሮፓ ጭጋግ ነው ባክሽ እንዴት ነው ግን ወደድሻት ብሪታኒያን...?''

''አዎ ደስ ትላለች ለንደንን ግን ገና ብዙም አላየዋትም...''

''ባራቮ አይዞሽ እኛ እናሳያለን ብዙ የሚታይ ነገር አላት...''
አለ ዘካሪያስ ፈገግ እያለ ለመፈገጉ በሞባይሉ ድምጽ እያሰማ
''ምን አንተማ ዕቃህን ተቀብለህ በዛው ላጥ አልክ'ንጂ ቅቅቅ''

''አሀይ ከምራ አውን አልጠፋም ይልቅ መች ምሳ ልጋብዝሽ?''

''ከነገ ውጪ ይመቸኛል ዘኪ::''

''ሐሙስ የቅዱሳኖች ነው ይባላል ምን ታስቢያለሽ ቅዱስነት አይማርብንም እኛ....?''

''ቅቅቅ እሺ ስንት ሰሀት?''

''2 ሰሀት ላይ ይሁን:አገር ለማየቱም ጊዜ እንዲኖረን...?''

''እንዳልክ::''
አለችው ሠባዊት::

ስልኩን እንደዘጋ ልብሱን ለባብሶ ወጣ::ዛሬ አንድ የስራ ቦታ በጋዜጣ ላይ አይቶ ስራ ለማመልከት ነው የውሎው ዓላማ:
ሠፈሩ ያለው ባቡር ብዙውን ጊዜ ይዘገያል አንዳንዴም ጉዞውን ሰርዞ የሚቀጥለውን የጉዞ ሰሀት መጠበቅ ግድ ይሆናል:: ስፍራው ሲደርስ ሰዉ እንደተለመደው እየተናደደ ነበር ::

'' አበሻ ነህ?''
አለችው አንዲት ቀይ አበሻ:: ጸጉሯ አጭር ነው

''አዎ ነኝ ጤና ይስጥልኝ....''

''አትመስልም''

''እንዴት?''
አላት ጎኗ ተቀምጦ እየሳቀ ዘኪ

''እኔንጃ የዚህ አገሮችን ሚክስ ሬስ አድርጌህ ነበር:''

''አይደለሁም የጠራው ንጹህ አበሻ ነኝ ቆንጂት...''
የደረበችውን ካቦርት መቀነት እያጠበቀች ሰረቅ አድርጋው አየችውና

''....ቆየህ እዚህ አገር?''
አለችው::

''እኔንጃ አዎ መሰለኝ...''

''ስንት አደረክ?''

''ብዙ ነው ምነው?''

''ስንት ሶስት አምስት...?''
ዘካሪያስ እየሳቀ

''ከዛም በላይ...''
አላት::

''አሥር...?''

''ከዛም በላይ....ነኝ ምነው ጥያቄሽ ያስፈራል?''

''ለምን?....''

''እኔንጃ ግዴታ የመጣውበትን ቀን ማወቅ ስትፈልጊ ቀጥለሽ የልደት ቀኔንና አድራሻዬን ሁሉ ትጠይቂኛለሽ ብዬ ነው ቅቅቅ''
ሳቀች ልጅቷ ባቡሩ ለመቅረቱ ሰሀቷን ገልመጥ አድርጋ

''ይቅርታ...እዚህ ሠፈር ብዙ ጊዜ አይካለሁ ግን አበሻ አትመስለኝም ነበር በተለይም ከነጭ ጋር ስለማይህ....እና ሳስተውልህ አበሻ ነህ በሁኔታህ ብዙ እንደቆየህ ገመትኩኝ::''
አለችው

''እንዴት የዚህን ያህል አስተዋልሽኝ ግን?''
.
.
.

ይቀጥላል

ዋናው______________________________________________________:[/list]
Last edited by ዋናው on Wed Feb 28, 2007 4:29 pm, edited 1 time in total.
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed May 10, 2006 2:37 pm

(-አሥራሁለት-)

.
.
.
''....ማለቴ ብዙ ጊዜ ስለማይህ ''

''እንዴት እኔ አላስተዋልኩሽም ግን?''

''እኔንጃ ምናልባት ባንተ ዓይን የማልገባ ሆኜ ይሆናላ ቅቅቅ''

ዘካሪያስ የልጅቷ ቀድማ መግባብት ባለበት ከተማ ለአበሻው ህዝብ እንግዳ ስለሆነበት ተገረመ

''ቆንጆ ለመሆንሽ ተጠራጥረሽ ታውቂያለሽ ?''
አላት ፈገግታው ከገፁ ሳይበርድ::

''መልከ ጥፉ ነኝ ብዬ ላንድም ቀን ኣስቤ አላውቅም''

''የዚህ ዓይነት በራስ መተማመን ውስጣቸው ያሉ ሠዎች አህምሮዋቸው ብርሁ ነው ይባላል::''

ልጅቷ ስትስቅ ፍንጭት ጥርሷ ፈገግታዋን እያጎላው የሚርገበገቡ ያይኖቿ ሽፋሽፍቶች ለዕንግዳነት ትውውቋ እያመለከቱ ...ዓይንን ብቻ ሳይሆን ቀልብም ትስብ ነበር::

''ስምህን አልነገርከኝም....?''
አለችው ::

''ዘካሪያስ......''
አላት:ወዲያው ባቡሩ ለመምጣቱ ካበሰረችው የሴትየዋ ድምጽ ቀጥሎ በራሱ ድምጽ እያማቧረቀ መጣ:: ተከታትለው ገቡ ::
''ወዴት ነሽ?''
ነገረችው መውረጃዋን የተቀመጠችበት ወንበር ላይ ያገኘችውን ጋዜጣ አጥፋ በጎሉ ፊደላት የሚታዩትን አብይ ዜና ገረፍ አድርጋ

''...እቺ ምድር ጭልምልም ብላብህ ታውቃለች ዘካሪያስ?''
አለችው ለራሷ በረጅሙ ተንፍሳ

''....እቺ ምድር ሁሌም ጨለማ ናት ምነው..?''
አላት ውስጧ መረበሹን እያስተዋለ:

''ቅቅቅቅ ድፍንፍን ያለ መጨለም ማለቴ ነው::''
ዘካሪያስ ሚቀጥለው ጣቢይ የርሱ መውረጃ መሆኑን ነግሯት ተነሳ
'' ውስጥሽን ብርሀን ማድረግ ትቺያለሽ ውጪሽ ብርሀን ነው ቆንጂት .....''
አተኩራ አየችውና ከመውረዱ በፊት
''ስሜን አልፈለከውም ...?''
አለችው::ወዲያው ወረደ በመስታወት በኩል ፈገግ ብሎ ሲያያት አስተያየቷ ዓይኑ ላይ ቀረበት ልክ ከዚ በፊት የሚያውቃት መሰለው ግን አያስታውሰውም ፍንጭቷ, ድምጿ በደንብ ከዚ በፊት የሚያውቀው ሆነበት::
__________///__________

ከመዐል ለንደን ተነስታ ወድርሷ ቤት ለመድረስ የመኪናው መጨናነቅ ስለሚሰለቻትና በተወሰኑ መካከለኛ የከተማይቱ ክልል ውስጥ ስታልፍ ለፍቃድ የምትገብረው ፓውንድ(ኮንጃክሽን ቻርጅ) ስለሚያማርራት አብዛኛውን ጊዜ የምትጠቀመው በምድር ውስጥ ለውስጥ ባቡር ነው::

ቫኔሳ ቤቷ ገብታ ለድካሟ የባኞውን ገንዳ ሞላች የኢንጆሪ መኃዛ ያለውን አረፋ አኩረፍርፋ ውስጡ ገባችና'እሠይ' አለች:: አባቷ ስለዘካሪያስ የተናገራት አህምሮዋን ብጥብጥ አድርጎታል ግን ለዘካሪያስ ፍቅር አየለላትንጂ ሌላ ነገር አላሳሰባትም:: ውስጧ እንዲህ በሀሳብ ሲጨናነቅ የወሲባዊ ስሜቷ ይመጣባታል ምናልባትም ለመርሳት ብላ ስለምትፈልገው በዕልህ ስሜት ውስጥ ስለምትገባ ይሆናል:: ዘካሪያስን አሰበችው በዚህ ቅፅበት ገላው ከፊት ለፊቷ ድቅን አለባት ፈገግታው አሽኮረመማት:: ዓይኗን ጨፈነች:
የቤቷ ደውል አቃጨለ::ከነአረፋዋ በፎጣ ተጠቅልላ ከፈተች:ዘካሪያስ ነበር ከንፈሮቹን ከትኩስ ትንፋሽ ጋር ስማው ፎጣውን ሳሎኑ ውስጥ ወለሉ ላይ ጣለችውና እርቃኗን ወደመታጠቢያ ክፍሏ ገባች ::ዘካሪያስ ከደጅ ይዞት የመጣው ብርዱ ባንዴ ከላዩ ላይ እንደጉም በኖ ሲጠፋና በስሜት ሲሟሟቅ ተሰማው::

''በጣም ደክሞኝ ገንዳ ሞልቼ ተዘፍዝፌያለሁ ትቀላቀለኛለህ?''
ብላ ጠየቀቸው
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው__________________________::
[/list]
Last edited by ዋናው on Mon May 17, 2010 2:22 am, edited 1 time in total.
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri May 12, 2006 3:55 pm

(-አሥራሦስት-)
.
.
.
የገንዳውን ውኃ በትኝሹ ቀንሳው ዘካሪያስ ልብሶቹን አውላልቆ አብሯት ገባ: ብርዱ ያኮማተረው ሠውነቱ ዘና ሲል ታወቀው

''ውሎ እንዴት ነበር ዘካር?''
አለችው: ያይኖቿ ሽፋሽፍቶች በውሀ ርሠውና በድካም ቦዝዘው ውስጧ ከተነሣሳው ሥሜት ጋር ማውራት ሚፈልግ አይነት ሳይሆን መታቀፍን የሚፈልግ ስሜት ነበራት

''ባለፈው የሄድኩበት የስራ ቃለ-መጠየቅ ነበረብኝ ግን ያንን ያህል የሚያስደስት ውሎ አልነበረም ቫኒ::''
አላት ባቷን በአረፋው አርጥቦ በመዳፉ እያበሰ

''ጥሩ ሠው አልነበረም ያጋጠመህ?''

''እኔንንጃ ብቻ ድጋሚ የሚደውሉልኝ አልመሰለኝም::''

ቫኔሳ ዓይኖቿ ተርገበገቡ የታችኛውን ከንፈሯን ጎን በጥርሶቿ እየነከሰች ወደ ጭኑ ጭኗን አስጠጋች:: ከዛም ሻምፖዎችና ሣሙናዎች ወደቁ ውኃው ተፈነጣጠቀ የቫኒ መታጠቢያ ክፍል አቃሰተች ::

__________///__________

ዛሬ ጸሀይ ወጥታ ወገግ ባይልም ብዙም ብርድ አልነበረም መሬቱም ደረቅ ነበር ንፋሱም ሩጫው እንደሰለቸው ሁሉ ፀጥ ብሏል::ዘካሪያስ ጠዋት አንተነህ የጓደኛቸው ስለሺን ለቅሶ እንዲደርሱ ቢጠይቀው ቀትር ላይ ከሠባዊት ጋር መቃጠሩን ነግሮት ለነገ አስተላልፎታል::
ኤንጅል የዘካሪያስ ሠፈር ነው እዚህ ሠፈር ከ6 ዓመት በላይ ኖሯል ባጣም ነው የሚወደው:: ስፍራው ዩኒቨርሲቲዮችና ኮሌጆች ስለሚበዙበት የተማሪ ሥፍራ ነው:: ከዋናው መንገድ ጠርዝ ላይ የተደረደሩት ካፌዎች መጠጥ ቤቶችና ክለቦች ከዕኩል ቀን ጀምረው ሁሌም እንደደመቁ ነው::
ዘካሪያስ ሠባዊትን የቀጠራት ኤንጅል ባቡር ጣቢያ በር ላይ ነበር እንግዳን ሠው ሁሌም ቲዩብ /የምድር ውስጥ ባቡር/ ጣቢያ በር ላይ መቅጠርን የተለመደ ነው:: የሎከሠው ሲጋራ ሳያልቅ ደረሰች አልገመተም ነበር

''ከሴትነትሽ ውጪ ዕንግዳም ጭምር በመሆንሽ በሰሀቱ ትደርሻለሽ ብዬ አልገመትኩም ነበር ሠባዊት''
አላት: ለመሳም ጉንጩን እያቀበላት የተቀባችው ሽቶ ከንገቷ ጠርዝ ወደአፍንጫው ገባ::

''አበሻ አገር ቢሆን ቶሎ አልደርስም ነበር ፈረንጅ አገር አይደል ያለሁት?''

ተያይዘው ምሣ ለመብላትም አገር ለመጎብኘትም ወደ መኃል ከተማ አቀኑ ያደረገችው ጅንስ ሱሪ ቅርጿን በውል ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ሠውነቷን ገረፍ አድርጎ

''ሸዋ ሁሉም እንስት ሽንቅጥቅጥ ብሎዋል ሲባል አላመንኩም ነበር አውን አንቺን ሳይ ነው ያመንኩት ....የለንደን ሤቶች'ኮ ይሄ የስንዴ እንጀራ ዙሪያቸውን እንደኮባ ዛፍ ቦርጭ በቦርጭ አድርጓቸው ....''
አላት እየሳቀ

''ሆ....ለንደን እንጀራ ትወዳላችሁ ዘኪ ''
አለችው ቀድማ እንድትገባ ወደጋበዛት አውቶብስ ገብታ ለሹፌሩ ቲኬቷን እያሳየች

''ቅቅቅ ምን ይደረግ ያገር ናፍቆት ይሆናላ ሠባዊት ደግሞኮ የሚገርምሽ የንግሊዝ እህል ልክ ንብ እንደነደፈሽ አስር ቦታ ነውየሚያሳብጥሽ::''

''ሌላ ምግብ የለም?''

''እኔንኳን እንጀራ እምብዛም ነኝ አንዳንዴ ነው ሠዉ ግን ያው ጊዜም ስለሌለው ወጥ መስራት ትንሽ ይቅላል ::''
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው___________________________________::[/list]
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sat May 13, 2006 10:19 pm

(-አሥራዐራት-)
.
.
.
ታሪካዊ ስፍራዎችን እየዞረ የሚያስጎበኘው ይህ ቢግ ባስ የተባለ የቱሪስት አውቶብስ ቪክቶሪያ ከተባለ ስፋራ ተነስቶ ዋና ዋና የቱሪስት መስህብ የሆኑትን ስፍራዎች በረዳት አስጎብኚ ማስተዋውቅ እየታገዘ ያሳያል:: ለንደን አሮጌ ነች ለንደን ታሪክ ነች,ለንደን ውብ ነች,ለንደን,ቆሻሻም ነች, ማንኛውንም ስፍራ ተጠግተው ሲያስተውሉት በመቶዎች የሚቆጠር ታሪክ አላቸው::
ዘካሪያስ የተለየዩ ስፍራዎችን ከአውቶብሱም ከወረደ በዋላ ሠባዊትን እያዞረ አስጎበኛት ለንደን አይ የተሠነ ተሽከርካሪ ባለቀለበት ታወር ላይም ወስዶ ለንደንን ከኣናቷ ጭምር ሳይቀር አሳያት ከዛም ሲጨርሱ ወርደው የወተር-ሉ ዙሪያን ትርዒት የሚያሳዩትን ትዕይንቶች አስጎበኛት::
ሠባዊት መደሰቷና መገረሟ ፊቷ ላይ የሚታየው ፈገግታና አስተያየት ይናገር ነበር::

''መቼም ቢሆን የዚህ ዓይነት ጉብኝት ጠብቄ አላውቅም ነበር ዘኪ ''
አለችው አየሩ በረድ ሲላት ያደረገችውን የቆዳ ጃኬት አዝራሮች እየቆለፈች::

''ምንም አይደለም እንግዲህ ሠባዊት ባንድ ቀን ትንሽ አስቸጋሪ ነው ገና ብዙ ያላየሽው ቦታ አለ በተለይ እንደ ግሪንዊች ያሉትን ታሪካዊ ስፍራና የብሪታኒያን ብሔራዊ ሙዚየም ሳታዪ መሔድ የለብሽም::''
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው_________________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun May 14, 2006 2:27 pm

.
.
.
የለንደን ጀምበር ካልጠለቅኩህ ብላ ያለ ሰሐቷ ወደማደሪያዋ ለማሽቆልቆሏ ሠማዩን አስኮረፈች በክረምት ወራት ብርቅ መሆኗ ገብቷት ያፈነጠቀችውን እንግዳ ብርቅርቅ ቀለም ለታዳሚው እያቁለጭለጨች ተሰናበተች:: እንዲህ ትንሽ ፀሀይ ፍንጥቅ ሲል እንግሊዛዊያኑ አገሬዎች
''ዋው በጣም ቆንጆ ቀን....አይደል...?''
ይላሉ ለሩብ ቀን 'ንኳን ሳይፈግግ እየዋለ ብርቃቸው ነውና::
ዘካሪያስና ሠባዊት ተያይዘው በእግራቸው ቀዝቅቃዛውን አየር እየቀጨሙ 'ኮቬንት ጋርደን' የተባለ ስፍራ አመሩ ጊዜው መምሸት በመጀመሩ የሰፈሩ የቱሪስት መስህብ የሆኑት ባለ ተዕይንቶች መሰናዶዋቸውን ለነግ እየሸከፉ ነበር::
የሱቪኒየር ሱቆችን አልፈው በስተግራ ወደአሉት ምግብ ቤቶች አመሩና አንድ የጣሊያን ምግብ ቤት በረንዳው ላይ ወደተደረደሩት ወምበሮች ሄደው እንድትቀመጥ ወምበሩን ስቦ ጋበዛት:: ቀስት የመሰለ አፍንጫ ያላት አስተናጋጅ የገበታ ጠርጴዛውን አስተካክላላቸው የምግብ ዝርዝር መሀደሩን አቀበለቻቸው::

''ዘኪ ትንሽ አላሞላቅከኝም...ቅቅቅ?''
አለች ሜኖውን ተቀብላ በጎሉ አይኖቿ ጭምር ፈገግ ብላ

''ግማሽ ግብዣማ የለም ሠባዊት...''
አላት ሲጋራ ለመፈቀዱ መተርኮሻውን ሲያይ ሲጋራውን አውጥቶ ለኮሰና::

ቀልቧ የፈቀደውን ፒዛ አዘዘች እሱም ለራሱ የጣሊያን ፓስታና አንድ ጠርሙስ ቀይ የወይን ጠጅ እንድታመጣላቸው ነገራት ለአሳላፊዋ::

''የዛሬው ውሎዬ አውሮፓ መኖርን እንድመኝ ውስውስ ያደረገኝ ውሎ ነው ዘኪ::''

''ለንደን ለንግድነት አሪፍ ነች ሠባዊት ለመኖር ግን አትሆንም መሬቷ ይከብዳል ::''

''ዘኪ.......?''

''አቤት?''
አላት የሲጋራውን ጢስ እያቦነነ

''አላገባህም?''

''አላገባውም ምነው ?''

''አሀይ ዝምብዬ ነው::''

''አንቺስ ?''
አላት አይኖቿን ሰብራ ወደሹካና ቢላዋ ስታይ

''ኡፍፍፍፍ.....እኔም ሲንግል ነኝ ወንድ የማይፈልግ ሲንግል ታውቃለህ?''
አለች ደረቅ ፈገግታ እየሞከረች ባንድ እንግዳ ስሜት

''አላውቅም....ምን ወንድ የማይፈልግ ስትይ እርግጠኛ ነኝ ሌዝቢያን እንዳልሆንሽ...?''

''በስምአም...ምነው አንተ?''

''ታዲያ........''

''በቃ...ማለቴ ልቤ ተሰብሯል''
አሳላፊዋ የበሰለውን ትኩስ ምግቦች አምጥታ እንደትዕዛዛቸው እፊታቸው አኖረችና
''መልካም ምግብ''
ብላ የንግድ ፈገግታዋን ቸረቻቸው::

''ሰባሪው አጋጣሚ ወይስ ወንድ?''

''ረጅም ታሪክ ነው ዘኪ ሌል ቀን ጊዜ ካለን አጫውትአለው::''

___________________///____________________


(-15-)

ስለሺ ቤት ክ10 ያለነሱ ሠዎች ለቅሶው አሰልሶ በመክረሙ, ሀዘኑም በመርፈዱ, በከበደ ስሜት ሳይሆን የሁሉም ፊት ላይ ፈገግታ እየታየ ይጨዋወታሉ ::ወንድሙን የተረዳው ስለሺ ሶፋ ላይ ሆኖ ይቀልዳል ታዳሚዎቹ የጨበጡትን የቆርቆሮ ቢራ ይዘው ሳቁን ይጋሩታል ለማስተዛዘን...ለማረሳሳት...

ስለሺ ግዴለሽ ሠው ነው ምንም ነገር ደንታ የማይሰጠው,ነገሮችን አቅልሎ የሚያይ,ግን በአህምሮው የበሰለ ሠው ነው:: በማንኛውም ነገር ላይ በሚነሳ ወግ ላይመወያየት ያስደስተዋል:: ዘካሪያስ የስለሺን በሀሪ ይወደዋል 'ወግ ያሰፋል ዕውቀት ያነባብራል' ይላል:: ከስለሺ አጠገብ የተቀመጠው ቦርጫሙ ፍቃዱ ደግሞ ፖለቲከኛ አይለኛ የኢሕአዲግ ተቃዋሚ ነው:: የሶስት አመት ወንድ ልጅ አለው:: ከዘካሪያስ ጋር አንድ ሶፋ የተጋራው ሙሴ የውንድ መልከ መልካም ነው::ሁሌም ሽቅርቅር እና ሤቶችን ማሳደድ, በስልክ እትት እያለ የተሰጠውን የነጻ አየር 3 ሺ ደቂቃ አስሯ ሴት ጋር እየደወለ ማውራት ነው ስራው:: 9 አመት ሙሉ እንግሊዝ ሲኖር ቋንቋውን እንኳን በአግባቡ መናገር ቀርቶ መረዳትም አይችልም ጓደኞቹ ሲያበሽቁት 'ሙሴ ፖሊስ ይዟት ፖሊሱ /ኢንተርፕሬተር/አስተርጓሚ ፍለጋ መንከራተት ይሰለቸውና ይለቀዋል:' ይሉታል: መኪና ያለ ፍቃድ ነው የሚነዳው::

ስለሺ በ ቶኒ ብሬይልና በኮንሰርቫቲቮች የተነሳውን እሰጣገባ በቀልድ እያዋዛ ያወራላቸዋል:: ስለሺ የኢኮኖሞክስ ትምህርቱን በኖቲንግ ሀም ዩንቨርሲት ተከታትሎ የማስትሬት ዲግሪውን ይዞዋል:: አሁን ዒዝሊንግተን በተሰኘ ኮሌጅ መምህር ነው::

ስለሺ አሁን የተረዳ ወንድሙን ተከትሎ ለቤተሰቡ ሦስተኛ ልጅ ነው:: በአዲስ አበባ ይሳተፍበት በነበር የፖለቲካ መድረክ ውስጥ ለሚከተሉት ሠዎች በሚያሳምነው ጥናትና ፅሁፎች ዕውነታነት ካገሪቱ የበላይ ገዢ አመለካከት ጋር በመፃረሩ ለእስር በቅቶ ባስገራሚ ሁኔታ ነው ከውህኔ ቤት አምልጦ ነው ስደትን የጀመረው:: ከተለያዩ አግሮች በዋላ ብሪታኒያን ሲረግጥ ብሪታኒያ በፀጋ ተቀበልቸው መንፈቅም ሳይቆይ ስለሺ አገሩ እንግሊዝ እንዲሆን የሚያበስረውን ምስራች ደረሰው::
ስለሺ እንግሊዝን ይወዳታል 'ከሰባ ምናምን በላይ አገር ለዘመናት ማስተዳደር የቻለች አገር አንድ ስለሺን ግጥም አድርጋ እናዳመሉ መያዝ አያቅታትም::'' ይላል ሁሌም እንግሊዝ ለስለሺ ነፃነቱ,ዕውቀቱ,እስትንፋሱ,ጌጡ...እንደሆነች ይሄው አስረኛ አመቱን ቆጥሮ ' ለብሪታኒያ ያንድ ዴኬድ ዕድሜ ኤክስፒሪያንስ አለኝ' ብሎ ይፎክር ጀመሯል::

''ፒካሶ....መች ነው ኢግዚብሽንሽ..?''
አለው ወደ አንተነህ ዞሮ ስለሺ

''ገና ነው 6 ሳምንት ይቀረዋል''
አለ አንተነህ የጠቀለላትን ሲጋራ በምላሱ አርጥቦ እየለጥፋት
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው____________________________________::
[/list]
Last edited by ዋናው on Mon Jul 17, 2006 12:34 pm, edited 2 times in total.
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon May 15, 2006 5:24 pm

(-16-)
.
.
.
'' በይ ደግሞ ቀድመሽ ትኬት አዘጋጂልን የፖሊሽ ሴኪውሪቲ በር ላይ አንጎማለሽ ገና ጥቁር ሲያይ ሶውሴጅ ባደለበው ደረቱ እንዳስገፈትሪን ...ፒካሶ እኛ በፉርሽካ ነው ያደግነው ነገርና እልሕ እንጂ ጉልበት የለንም::''
አለው ስለሺ ፈግግ ሲል የላይኛውን ከንፈሩ የሚገፈትረው ድዱ ብልጭ ይላል::

''ምንምችግር የለውም ስሌ እናንተ ብቻ ኑ!''
አለ አንተነህ:: የሰውነቱ መቅጠን በጓደኞቹ ዘንድ አንቺ ተብሎ እንዲጠራ አድርጎታል::

የለቅሶው ታዳሚዎች ተሰናብተው ለዛሬ ለማደር ቃል የገቡት ዘካሪያስ, ሙሴ እና አንተነህ ቀሩ:: ወዲያው የስለሺ ጓደኛ መስከረም ከስራ መጣች:: እርግዝናዋ ሆዷን ገፍቶታ በአጭር ቁመቷ ገዝፋለች::

''እንዴት ነው ዘኪ ያቺ ፈረንጅ እንዴት ነች?''
አለ ስለሺ የፍቅረኛውን ከንፈር ለሰላምታ ስሞ

''ሠላም ነች ባገሯ ም ትሆናልች ብለህ?''

''ልጅ አልፈበረከችም ቅቅቅቅ?''
አለው ወደ መስከረም እርግዝና በፈገግታ እያየ

''ገና ነች ስሌ.....ምን ይዤ ልደቅል ብለህ ነው?''

''አሃይ........መውለድ ነው'ንጂ ምን ይዤ አትበል ልጁ እንድሆን ካንተ ምንም አይፈልግ ይልቅስ ተደቃቀሉና ዘርህ ሲነጣ ምን እንደሚመስል እየው...::''

''አይ ስሌ ለሱማ ከሆነ ፒካሶ ቀለም በጥብጣ አታሳየኝም ብለህ ነው?''

''ፒካሶ ምስል ትፍጠርንጂ ነፍስ አትዘራ አንተ ደግሞ እንዲህ እየካብካት አታሳብጣትንጂ....''
አለ ወደ አንተነህ እያየ ስለሺ::

''ስሌ ትንሽ ይቆየኝ ባክህ ባስ ላይ ብጥብጥ እንደሚያደርጉን የዚህ አገር ሚክሶች ወልጄ መበጥበጥ አልፈልግም ቆይ ላስብበት::''

''ካንተ አላውቅም ብቻ እንደ ሙሴ ስትመርጥ ስትመርጥ ሱስ ሆኖብህ እንዳትቀር ቅቅቅቅ''
አለ ደግሞ ወደሙሴ እየዞረ ሙሴ የሚያወራውን ስልክ ጨርሶ ዘጋና

''ምን ላድርግ እኔ እንግሊዝ የተሰደደው ሁሉ በረሮው ብቻ ነው እንደሬዲዮ በጆሮዬ ባፍንጫዬ ሲገቡብኝ....''
አለ የሱሪውን ጠርዝ እያስተካከለ::

እንዲህ እያወጉ አመሽተው አደሩ ::

በማግስቱ ዘካሪያስ የቫኔሳ ስልክ ቀሰቀሰው

''ሀይ የኔ ፍቅር?''
እያዛጋ መለሰላት''ሀይ ቫኒ ማታ አመሸውና .....''

''ቀጠሮዋችንን እረስተከዋል አይደል?''

''ሆ! ታውቂያለሽ ርስት አድርጌዋለሁ ስንት ሰሐት ሆነ ቫኒ?''

''11 ሰኃት ከ20...እሺ የት ነው ያለኸው መጥቼ ልውሰድህ?''

''ቫኒ እንዴ እዚሁ ባደርኩበት ልብሴማ አይሆንም ኢንተርቪው'ኮ ነው ያለብኝ...''

''እና ታዲያ ባንድ ሰሀት ተኩል ውስጥ ቤትህ ሄደህ ልብስ ቀይረህ ትደርሳለህ....''
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው______________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Thu May 18, 2006 5:10 pm

(-17-)
.
.
.
ስደት ርግማን ነው ይላል ዘካሪያስ ከሕትብቱ ርቆ ከቀዬው ተፈናቅሎ ብራ ሰማዩን ጥሎ ጫግግ ምድር መጥቶ መደናበሩ አንዳንዴ ግርም እያለው: የሚገርመው አገር ቤት ያሉት ወንድሜ ውጪ ነው እህቴ ውጪ ናት ብለው ስደትን እንደሹመት መከበሪያ ሲያደርጉት እነኚያ ባለውጪዎች የሚኖሩትን መከራ የማወቅ አቅም አለማግኘታቸው ነው:: ለምን? ይሁልግዜም ይሁሉም ጥያቄ ነው: ግልፅነት የለም ለዛም ነው ብዙ ችግሮች እየጎሉ የሚመጡት::

አንተነህ ዛሬ ዘካሪያስ የሚያስተዋውቀውን ያገር ቤት እንዳይቱን ፍላጎት ለማርካት ለንደን ውስጥ ስላሉት በርካታ ሙዚየሞች እያስበ ነበር ዘካሪያስ የሰጠው የቤት ስራ ነበርና::

ዘካሪያስ ሠባዊትን ይዞ ወደርሱ ቤት ሲደርስ ሁለት ሰዓት ሞልቶ ነበር ከቀኑ አንተነህ የመሳያ መሰናዶዎቹን እያጣጠፈ
''እንኳን ደህን መጣሽ ''
ብሎ ስሞ ተቀበላት
''ሠባዊት ፒካሶ ይባላል የለንደን እርጉም ሰዐሊ ነው ትንሽ ግን ቀዠብ ያደርገዋል ......''
እያለ በቀልድ አስተዋወቀ ዘካሪያስ

''አትስሚው ስሜ አንተነህ ነው ሰዎች ፒካሶ ይሉኛል ጤነኛ ነኝ ቅዥቢዎች ግን እኔን ቅዥቢ ይሉኛል ::''
አላት እንድትቀመጥ እየጋበዛት

''ሆ ሆ ፒካሶ ተነሺንጂ ርቧታል ፒዛ መብላት ትፈልጋለች አንቺ ቤት ደግሞ እህል የለ...::''

''እሺ መጣው ቴን ሚኒት ሠባዊት::''
አላት ፈገግ ብሎ ወደመኝታ ክፍሉ እያመራ ሰባዊት እርሷን በንግዳ ስሜት ነቅንቃ እሺታዋን ገለፀችና ቤቱስጥ ያሉትን ስዕሎች እየቃኘች ፊቷን ግራ በመጋባት ስሜት ወደዘካሪያስ ዞራ

''...ይቅርታ ዘኪ ይሄንን ልጅ በዝና የማውቀው ይመስለኛል ባንድ ወቅት ቢ.ቢ.ሲ ላይ ቀርቦ የነበር ሰዐሊ ነው አይደል?''
አለችው
''አዎ....የዛሬ ሶስት አራት አመት አካባቢ ጠይቀውት ነበር ታውቂዋለሽ...?''

''አዎ በሚገብ እንዲያውም የስራ ባልደረባዬ በሱ ህይወት ዙሪያ ላይ ሰፊ ዘገባ አቅርቦ ነበር::''

''ይቅርታ ግን ታውቂያለሽ በድንብ አልትዋወቅንም ምን እንድምትሰሪ አልነገርሽኝም .......''

''እኔ ጋዜጠኛ ነኝ ዘኪ ግን ትርፍ ስራዬ ነው ዋና ስራዬ ከእህትህ ሮሚ ጋር ነው አብሬ የምሰራው ጋዜጠኝነት ውስጤ ስላለ......''
አለችው ፈጥና
''በጣም ደስ ይላል .....
.
.
.[/list]
ዋናው_______________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Sun May 21, 2006 8:19 pm

.
.
.
''....አትመሲይም ግን ''
አላት ዘካሪያስ እየቃኛት

''እንዴት...?''

''እኔንጃ በቃ ... ምን ዓይነት ጋዜጠኛ ነሽ ማለቴ የሬዲዮ የቲቪ ወይስ የጋዜጣ...?''

''በእንጊሊዘኛ ቋንቅ የሚታተም አንድ የግል ጋዜጣ አለ: እዛ ላይ አንዳንድ አርቲክሎች እሰራለሁ''

አንተነሕ እናዳመሉ ግዴለሽ አለባበሱን ለብሶ ቁልፉን ይዞ ለመጨረሱ እያንቃጨለላቸው ብቅ አለ:ዘካሪያስ ወዲያው ሠባዊት እንደምታውቀው ነገረው: ተያይዘው ወጡ ፒዛ ሀት ገቡና አሰልቺውን የፒዛ ጥበቃ በባጥ የቆጡ ወሬ እየጠበቁ ቆዩና ምግቡ ሲመጣ የቀረበውን ቂጣ የየፍላጎታቸውን ተቋድሰው በሉ:: ከካምደን ታውን ኮተታሞች የሰፈሩ ሰዎች ጀምሮ የነርሱ ዕቃዎች የሚሸጡበትን ሱቆች ጉብኝታቸውን ጀመሩ ሠባዊትም በቦርሳዋ የያዘችውን ካሜራ አውጥታ አነገተችና አይኗ የሳበውን ሁሉ ታነሳ ጀመር ...በባለ ፎቁ የለንደን አውቶብስ ተሰቅለው የከተማይቱን ያላየቻቸውን ታሪካዊ ስፍራ ጎበኘች ከዛም በአንተነህ ምርጫ የብርቲሽ ሙዚየም ገብተው ሲመሽ ወጡ::

ሠባዊት ጉብኙቱ አልቆ ሲሸናኙ አንተነህን ለቃለ መጠይቅ ፍቃደኛነቱን ጠየቀችው አንተነህ ደስተኛ ነበር::

''ለንደን መጥቼ ያልጠበቅኳቸው ሰዎች ናቸው አዝናንተው የተቀበሉኝ::''
አለች ሠባዊት ለዘካሪያስ ቀና ብላ በተምቦገቦጉ ዓይኖቿ እየቃነችው

''እኛ አዲሳባ ስንመጣ የምናውቀው ሁሉ ሞቶና ካገር ወጥቶ ስላለቀ የሚቀበለን እንዳናጣ'ኮ ነው::''
አላት በፈገግታዋ ላይ የሳቅ ልዝብ ድምፅ እየፈጠረ

''ዛሬ ግን ባመሽ ደስ ይለኛል በዚሁ ስሜት እንዲሁ እንዳማረብን ሰው እንደቀናብን ምሽቱን ደግሞ......''
አለ አንተነህ::

''እኔ ደስተኛ ነኝ እንዲያውም የለንደን ክለቦች ምን እንደሚመስሉ ሠባዊት ብታይ አይከፋም::''

ሠባዊት የመጣችበት ምድር ቤተሰባዊ ይሉንታ ውስጧ እንዳለ ነበረና ለመግደርደርና ለመቃወም ፈልጋ ነበር ፈገግታዋ ውስጥ ግን መፈለጓ ይንፀባረቅ ነበር::
ተያይዘው ወደምሽቱ ለመንደርደር ወደ አንድ የንግሊዝ መጠጥ ቤት ሲያመሩ ሠባዊት አለባበሷን አይታ

''የወጣውት አለባበስ ለክለብ አይሆንም::''
አለች ራሷን ቁልቁል እየቃኘች

''ግዴለም ለክለብ በሚሆን አለባበስ ደግሞ ከመሄድሽ በፊት አንዴ እንወጣለን::''
አላት ዘካሪያስ

''... ቅቅቅ ሤት ልጅ ሳትዘንጥ ስትቀር ለኔ በጣም በራሷ የምትተማመን ትመስለኛለች...ይህንን ስል የምትዘንጥ ሴት በራሷ አትተማመንም ማለቴ አይደለም...ደግሞ ይህ አባባል የዛሬው ያንቺን አለባበስ አይጨምርም ለለንደን በጣም ዘንጠሻል አንቺ ''
አለ አንተነህ::

''እንዴት...?''
ጠየቀች ሠባዊት ባባባሉ ተገርማ

''...ምን እዚህ አገር ያቺ በጋቸውንኳን ስትመጣ በብር ከምናምን ቀሚስ ነው የሚዘንጡት አብዛኛው እንግሊዛዊ ላለባበሱ ግዴለሁም ለዚህም ነው ሰዉ አገር ቤት ሲገባ ያዲሳባ ሰው ዘናጭ የሚሆንበት...''

ሠባዊት ተግደርድራ የቀረበላትን ሲምርኖፍ አይስ ተጎንጭታ ልቧ ሲመታባት ተገርማ አዳመጠችው:: ምን ሆኜ ብላ ራሷን አዳመጠች ደግሞ አንድ ነገር አሰበች ለምን ዘካሪያስ የዚህን ያህል ሊንከባከባት ቻለ? ባንድ ነገር እርግጠኛ ነበረች ዘካሪያስ ሁለመናው እሷ ውስጧ የሳለችው አይነት ወንድ ነው....ያንን ወንድ ትፈልገው አትፈልገው አታውቅም::
በኃሳብ ጭልጥ ብላ ሄደች ስጋዋን ለንደን ጥላ ነብሷ ሸፈተ: ገዛህኝን ባዓይነህሊናዋ አስታውሳ ፊቷን ኩምጥጥ አደረገች ስትወለድ አብሯት የነበረውን ፆታዊ ፍቅር ቀምቶ ባዶዋን ያስቀራት .....
ገዛህኝ ማነው?
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Thu May 25, 2006 8:56 pm

(አስራ ሥምንት)
.
.
.
ጠራራው ያዲሳባ ፀሀይ አናትን ይበሳል ፊትን ይለበልባል ሠባዊት ከትላን ጀምራ ከጓደኛዋ ሮማን ጋር ጠብ እርግፍ እያለች መሰናዶውን አከናውና ዛሬ ፍቅረኛዋ ገዝሽን በድንገተኛ ግብዣ ልደቱን አብስራው ደስታውን የምታገንበት ቀን ነው ምግብና መጠጦቹን በወጉ አስተካክላ የሷን ውበትም ፏ! ለማድረግ ፀጉር ቤት ባሰለቸ ወረፋ ካየሩ መሞቅ ጋር ጨራርሳ ወደቤቷ ስትሔድ ነበር አጋጣሚው የተከሰተው:: ሠባዊት ከብሔራዊ ቲያትር ወደ አምባሳደር ታክሲ ለመያዝ ፀሐዩን እየሸሸች ተቻኩላ ስትራመድ እነኚያ ለውበትና ለእውነት ብቻ የተፈጠሩ የሚመስሉት አይኖቿ ድንገት ገዝሽን አዩ:: ካንዲት የጠይም ቆንጆ ጋር እየተሳሳቁ ኢቲዮጲያ ሆቴል በረንዳ ላይ ተቀምጠዋሉ ከፊታቸው ያለው ጠርጴዛ የተጠናቀቀውን የምሳ ግብዣ ባዶ እቃዎች ይዟል:: ገዛህኝ የቆንጆይቱን መዳፍ በመዳፎቹ ከትቶ እያበሰ በፍቅር ያያታል እርሷም ዓይኖቿን በሽኩርምሚት ትሰብራለች... ከዛም በልዝቡ የጆቿን ጣቶች ይስምና የሆነ ቃል ሲነግራት ትፍለቀለቃለች::

ሠባዊ ከጥቂት ደቂቃዎች በሗላ ነበር ልደቱን የደገሰችለት ቦታ ድረስ ሞባይሉ ላይ ደውላ በድንገትኛ ጠርታው ሰርፕራይዝ ልታደርገው ያስውበችው...ግን አሁን ድንዝዝ አለች...ፈራች...ደነገጠች...ተብረከረከች...

''ሠባዊት!!!''

የዘካሪያስ ጥሪ ከመጥፎ ያዲሳባ ትዝታዋ አብርሮ ወደ ለንደን መሸታ ቤት አመጣት::

''...የት ሕእድሽ...ምነው ቦታውን አልወደድሽውም ሌላ ቦታ እንቀይር?''
ቀጠለ አንተነህ የፊቷን መለዋወጥ አስተውሎ

''ኖ! በጣም ተስማምቶኛል ድንገት አንድ ነገር አስታውሼ ነው አንዳንዴ እንዲህ ያደርገኛል::''
አለች እየተደናበረች ሁለቱን ጋባዦቿ እያየች ውበቷ ግን አውንም ብልጭ!! እንዳለ ነበር::
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው__________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Wed May 31, 2006 7:28 pm

.
.
.
አንተነህ ከፊቱ አረፋውን እንደ ባርኔጣ ከላዩ ያኖረ የጊነስ ፓይንት ቢራውን ትጎንጭቶ አፉን እያበሰ

''ምነው ሠባዊት አዲሳባ ሄድሽንዴ እኛን እዚህ ትተሽ?''
አላት::
ሠባዊት በመሽኮርመም መጠጧን እየተጎነጨች በጎሉ ዓይኖቿ ለይቅርታ መልከት አድረገችና አንገቷን ሰበረች::
መጠጥ ቤቱ ሁካታው እይደመቀ ቦታ እየጠበበ መጣ የንግሊዝ መሸታ ቤቶች እንደ መኖሪያ ቤቶቻቸው የጠበቡ አይደሉም ስፋታቸው ደስ ይላል:: እንግሊዛዊያን ለመጠጥ ልዩ ፍቅር አላቸው በተለይ አርብ ምሽትን በጣም ይወዷታል በስራ የደከመ አህምሮን በቢራዎች ጎርፍ አጥበው በስካር አንፍዘው ለበናጋው ራስምታት የቆርቆሮ ቢራን ቤታቸው ሆነው ይፈወሱበትና ለሀንጎቨር ብለው ያሰልሱበትና በዛው ስፖርት እያዩ የምደገፍም ካለ እየደገፉ ይቀጥላሉ:: ለንደ ባንድ ወቅት ብዙ መጠጥ ከሚጠጣባት የአውሮፓ ከተሞች አንደኛነቷን እየመራች ነበር በተለይ ከሌሎች አውሮፓዊያን ህንስቶች ግራ ሲነፃጸሩ የለንደን ሴቶች አጫሽና መጠጥ የሚወዱ ናቸው::
በምሳ ሰሀት አንድ ፓይንት ጧ! አድርገው ወደቢሮ ሁሉ የሚገቡ አሉ::

''ሠባዊት እንግዴ የንግሊዝ ፐብ ጫጫታ ነው ቻዪው ዛሬ የትም ብንሄድ ግርግር ነው ማለቴ የሚጨንቅሽ ከሆነ ብዬ ነው....''
አላት ዘካሪያስ በንግዳ ስሜት ወደእድምተኞቹ አይኖቿን ስታቅበዘብዝ አይቷት

''በጣም ደስ ይላል ዘኪ ገርሞኝኮ ነው ባድ ጊዜ በቱ ጢም አለ ...ለነገሩ ፐብ ሲባል ሞቅ ሲል ነው ደስ የሚለው::''

''አዎ .....ግርግሩ ራሱ ብዙ ሳትጠጪ ያሰክራል በዛውም ራስሽን ሳትጎጂም ለቢራው ፔኒም ሳትከስሪ....''
አላት አንተነህ ጥቅልል ሲጋራውን እያቦነነ

''ምንድነው የምታጨሰው አንተነህ?''
አለቸው ቅድም ጀምሮ ሲጠቀልል ትኩር ብላ እያየችው ግራ አጋብቷት ነበር

''ይሄ ሲጋራ ነው አይዞሽ ቅቅቅ ምን ማሪዋና መስሎሽ ነው?''

''ከዚህ በፊት አይቼ አላውቅም ተጠቅልሎ የሚጨስ ...''

''ያው ነው ይሄም ሲጋራ ነው ልዩነቱ ይሔኛው ፍሬሹ ትንባሆ ለብቻው ታሽጎ እንገዛውና በሲዝለር/መጠቅለያ ወረቀት ጠቅልለን እናጨሰዋለን::''
አላትና እያሳያት አስረዳት ጪሱን ጭምር ጉም አስመስሎት

''አንዳንዴ ያቺንም ነገር ይስባል ሠባዊ እኔንም ያስለመደኝ እሱ ነው አሁን'ንኳን ዶክተሬ ከልክሎኝ ቆየሁ እኔ እሱ ግን ይነፈዋል ብር ስለማይበቃው ነው ይሔንን ርካሽ ትንባዎ እየጠቀለለ የምታዪው...''
አላት ዘካሪያስ የራሱን ሲጋራ እያቦነነ ፈገግ ብሎ በማብሸቅ ወደ አንተነህ እያየው

''ኸረ ......ውይ እሱስ ምን ያረግላችዋል ቢቀርባችሁስ?''

''ቅቅቅ ሕልሞች እንሸምትበታለን ሠባዊት እዚህ አገር ቶኒ ብሌየር ሳይቀር ያጨሳል ሽመታው ላይ ወንጀል ነውንጂ የማያጨስ የለም ....ለኔ ይስማማኛል በዚህ ላይ ደግሞ ተተናኩሎኝ አያውቅም ''

''ሱስ አይዛችሁም?''

''ሡስ የሚባል ነገር የለም ሠባዊት ሡስ ማለት መኖር መፈለግ ነፍስን ለማስደሰት መሯሯጥ ነው ይሄ ደግሞ በጎነት ነው የሠው ልጅ ኖሮ ይሞታል ....አባትና እናትሽ ሰው እንደሚሞት እያወቁ አንቺ ወለዱሽ ለምን? መኖር ስለሚያጓጓ......''

''አልገባኝም:''
አለች ሠባዊት የአግርሞት አንተነህን ትኩር ብላ ርያስተዋለች:

''ወይ ጉድ አንቺ ትላንትና መጥተሽ አልገባኝም ትያለሽንዴ ይሄው እኔ ስንትናስንት አመት ሙሉ አብሬው ስኖር ይሄው አንተነህ ሳይገባኝ አለ አይደልንዴ
?''

አንዲቷ እንግዳና ሁለቱ ለንደነሮች/ለንደናዊ አበሾች በንግዳና ተቀባይ ስሜት ውለው አመሹ ከመጠጡም እየደጋገሙ እያሰለሱ እያከታተሉ ጠጡ ብቅል ነውና ሲጠነሰስ የነበረን ቃሉን እሁን ሊያደርግ አናት ላይ ወጣ ሞቅታዎች ፈገግታ ሳቅ ጨዋታ እንዲሁም የአህምሮ ነፃነት ምሽቱን በአሳዳሚዎቹና በታዳሚይቱ ድምቀቱን አሳየ::

''ይሄ እስካሁን ያሳላፍነው የለንደን የመጀመሪያው የምሽቱ ክፍል ነው ከዚህ በዋላ ወደክለብ እናመራለን ::
አላት ዘካሪያስ መላጣውን ወደውሀላው በመዳፉ እያበሰ አይኖቹ ለመደፍረስ ያሰቡ ይመስላሉ:: ሠባዊት ሰሀቷን ተመልክታ
''አልመሸም?''
አለች: በፍርሀት እሷም የደጋገመችው ሞቅ አድርጓታል::

''ም...ነው ከቤተሰቦችሽ ጋር ነው'ንዴ የመጣሽው?''
አላት ዘካሪያስ እየሳቀ
ሠባዊት ለመግደረደር ሳይሆን የማንነት ልምዷስለሆነ ነበር::

''ማለቴ ትራንስፖርት ላላገኝ እችላለሁ ብዬ ነው ያገራችሁ ባቡር እኩለሌሊት ላይ እንደሚያቆም ተነግሮኛል::

''ከመሸም እኛ እናሳድራለን ሠባዊት በዛውም ቤታችንን እናሳይንጂ ....አይዞሽ ራስሽን ነፃ አድርጊ ማለቴ እየደበረሽ እንድታመሺ አልገፋፋሽም ...ግን ጥሩ ጊዜ አሳልፈሽ ብትሄጂ እኔም የሮሚን አደራ መወጣቴን ፍልጌው ነው በደብዳቤዋ ደጋግማ ነው ያስጠነቀቀችኝ''
.
.
.
ይቀጥላል
(ትንሽ ሰነባብቼ ብቅ በማለቴ ይቅርታ)

ዋናው__________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Tue Jun 06, 2006 7:08 pm

(-19-)
.
.
.
ሠባዊት የተውሶ አየሩን ከውጪዋ ቀዝቅዛው ውስጧ ግን በንግዳ ስሜትና በልዝብ ሞቅታ ተጋግላ የተፈጥሮ ፀዳል ያዳመቀላትን ውበታዊ ፈገግታዋን እንደለንደን ቡርቱካናማ መብራት አጉልታው አሳዳሚዎቻን አስደሰተች ታዳሚ ሲደሰትኮ አሳዳሚ ከተደሳቹ ታዳሚ ይበልጥ ይደሰታል::
ሌስተር ስኴር የተሰኘ ስፍራ አመሩና ከለንደን በርካታ የምሽት ክበቦች አንዱ'ስጥ ገብተው ተዝናኑ የስፍራው ስሜት የሙዚቃው ዜማና የህዝቡ ነፃነት ኮርድዳ አለሟን ከቀጨችበት አዲሳባ መዲና ፍፁም የተለየ ነበር::

ለሷ የተለየባት እዚህ ማንም ለማንም ግዴለሁም ያሻውን ያደርጋል ስሜቱን ያለገደብ ያስተናግዳል .....አልፎ አልፎ ከራሳቸው ፆታ ጋር ስሜትን አደባባይ የሚያሳዩ ሶዶማዊያኖችም ነበሩ

''...ሠባዊት እንግዴ አውሮፓ መሴይጠንና መሰልጠን አንድ ላይ ነው...::''
አላት አንተነህ እንደመብረቅ ብልጭታ ከሚብለጨለጨው ብርሀን ስር የሠባዊትን ስሜት እያየና ከነጎድጋድ የሙዚቃው ድምፅ ጋር እየተፎካከረ

ሠሀቱ ንጋት የኔ ነው ብላ የምትቆጣበት ሆነና ምሽቱ ሲያልቅ አንተነህ ሰክሮ ነበር ግን ቢሰክርም ለዛ ነበረው የርሱ ሱስ ራሱን አዝናንቶ የሚያስደስተውንጂ እንደሌላው ሱሱ ሱስን አይወልድም....ሴት አያምረውም ፀብ አይሸተውም ብቻ ጨዋታው ይደምቃል ፍልስፍናው ይባስኑ እየዘነበ ይመጣል ::የለንደን ሰው ለመጠጥና ለምሽት ክበብ ፕሮግራም ኖሮት ከቤቱ ሲወጣ ማንም መኪና የሚጠቀም የለም ሁሉም አውቶብስ ነው የሚጠቀመው እንደቀኑ ሁሉ ማታም በቂ አውቶቡሶች 24 ሰሀት ነው የሚሰሩት ብቻ ትኩስ ስካሩን ታቅፎ የሚመጣ ሰካርማ አውቶብስ ውስጥ ያመሉን ሁሉ እየፎከረ ይበጠብጣልንጂ ...አንዱ ያንዱን ትከሻ ተደጋግፎ መተኛት የተለመደ ነው::

ዶሮም ባይኖር ወፎች ለመንጋቱ ሲያስካኩ አንተነህ ጥቅልል ሲጋራውን እየማገ ደስ በሚል ፈገግታው ተሰናብቷቸው ተለየ:: ዘካሪያስና ሠባዊት ተያይዘው ውደ ኤንጅል የዘካሪያስ መኖሪያ አመሩ ሞቅታዋ ጉንጯን አቅልቶት ነበር ወደዘካሪያስ ቤት ብቻዋን መሔዷ ትንሽ ግራ ገብቷታል ስሜቷን በቅጡ ልታውቀው አልቻለችም ለራሷ ብቻ ፈገግ ትላለች

''ሠላም ነው?''
ይላታል ትንሽዬ ንፋስ ያለው የግርምት ሳቋን እያየ

''ሠላም ነው ዘኪ በጣም ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍኩኝ::''
አለችው አይኑን ለማየት በፈራ ስሜት ራሷን ደፍታ
.
.
.
ይቀጥላል

ዋናው____________________________________::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ቡናማ » Wed Jun 07, 2006 7:44 pm

ሰላም ዋናው

ያላስፈላጊ መዘባረቅ እንዳላደርግ ከብዙ መጠንቀቅ ጋር ነው ጥቂት ልል እዚህ የገባሁት::ፅሁፍህን ወድጄዋለሁ- በተለይም ቢያንስ በምትኖርበት አለም ስላለው ነባራዊ ህይወት ለሌሎች ርቀውና ሳያውቁት ላሉ የሚያስተምረው ነገር ስለሚበዛ::ጥቂት ብታደርገው የምለው ነገር ቢኖር የድርሰትህ ቃናና የትረካህ ፍሰት ያላሰናካይ መስረቅረቁን እንዲያበዛ atleast ንድፉን ከትየባ በፊት ብታዘጋጀው የሚል ነው::ዘባረቅሁ?
በነገራችን ላይ የአንተነህን የስዕል ኤግዚቢሽን መከፈቻ ስነ ስርአት ዘገባህን ለማንበብ ጓጉቻለሁ::አንድ ጊዜ ታዴ(ታደሰ መስፍን) አሜሪካን ሀገር ጥቂት ቆይታ አድርጎ አገር ቤት ሲመለስ ለስዕል ትርኢቱ የጋበዛቸው ሀበሾች ለዚያን ዕለት የበላቸው ጅብ የመሸኛ ግብዣው የመብልና መጠጥ የቀለጠ ግብዣ ላይ እንደጮኸ ምናምን የተናገረውን አልረሳም::የለንደን ሀበሾችስ ከላይ ሲዛዛቱ እንዳነበብኩት ስዕል ማየትና ማድነቅ መውደድም ያውቁ ይሆን???

ይኸው ነው
በወዳጅነት እንቀጥል
ቡናማ
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

Postby ቡናማ » Thu Jun 08, 2006 1:19 pm

...ግን ከላይ የፃፍኩልህ ላይ "ከሰላቢ ቤት ጉብኝት እንደተመለሰ ቡዳ" ሁኘብህ ይሆን???
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests