ጥላ ዓልባ__________(ልብ ወለድ)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby sewnet » Sun Jun 15, 2008 11:41 pm

የዋርካ ጸሐፊያን፣
ጽሑፎቻችሁን ለማቀነባበር ይህንን ድህረ ገጽ ብትጠቀሙ ኑሯችሁን እንደሚያቃልልላችሁ አምናለሁ።
አመሰግናለሁ።

በነፃ ሙቪ ለማየት ይህንን ይጫኑ።

ሰውነት
sewnet
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 43
Joined: Mon Nov 01, 2004 7:29 am
Location: Virginia, United States

Postby ዋናዉ » Mon Jun 16, 2008 1:57 am

የተከበራችሁ የጥላ-ዓልባ ተከታታዮች ሰሞኑን ብዙ ስራ ስላለብኝ ፖስት ማድረግ አልችልምና ታገሱኝ::በሚቀጥለው ሳምንት ዳጎስ ያለ ፖስት ይዤ እቀርባለሁ
Image
ዋናዉ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Sat Mar 29, 2008 9:09 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Thu Jun 19, 2008 9:12 pm

ዋናዉ
Image

Joined: 29 Mar 2008
Posts: 1

ሞክሼዬ ለካ እዚም ጎራ ብለሀል?

ሁለት ቦታ ፅፈህ አንዱን በሙስና እንዳይቆጠርልህ አድርጌያለሁ ቅቅ :wink:

ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ድንቢጤ » Wed Jul 02, 2008 10:23 am

እረ ዋንሽ በሰላም ነው? ለማንኛውም ጥላ አልባ ከመጀመሪያው ገጽ ላይ ላጣው ስለማልፈልግ ነው እዚህ ላይ የጻፍኩት ይቅርታ
አድናቂህ
ድንቢጤ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 67
Joined: Thu Feb 02, 2006 9:52 am

Postby ዋናው » Fri Jul 11, 2008 11:18 pm

አቤት ጊዜው እንዴት ይፈረጥጣል??? እመለሣለሁ ካልኩኝ 28 ቀን ሆነኝ??.... እንቁላል ወደዶሮ ተቀይሮ የአንድ ሣምንት ጫጩት ሚሆንበት ጊዜ....

ጊዜ ሢለግም እንዲህ ነው ከውስጥ ሚያስምጥ ምናብን ሚያገላግል እፍኝ ቅስፈት'ንኳን ይነፍጋል:: ሠሞናቱን ሚያራውጥ የጥበብ ድግስ ውስጥ ሆኜ ዓይኖቼ ቢሞጨሙጩ ጠፋው::

ጊዜ ተበዳድሬም ቢሆን ፊቴን ወደጥላ-ዓልባ አዞራለሁ

እጅግ ከብዙ ብዙ መናፈቅ ጋር
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናዉ » Mon Jul 21, 2008 2:16 am

ድንቢጤ wrote:እረ ዋንሽ በሰላም ነው? ለማንኛውም ጥላ አልባ ከመጀመሪያው ገጽ ላይ ላጣው ስለማልፈልግ ነው እዚህ ላይ የጻፍኩት ይቅርታ
አድናቂህ
ድንቢጤ የጊዜ እጥረት ነው::ብቅ እላለሁ በቅርብ

ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር
Image
ዋናዉ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Sat Mar 29, 2008 9:09 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Fri Jul 25, 2008 11:50 pm

ዋናዉ

Joined: 29 Mar 2008
Posts: 2


:twisted: :twisted: :evil: :evil:
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ኦኑፈያሮ » Sat Jul 26, 2008 3:28 pm

ወንድም ዋናው ሰላም ባለህበት:-

በርግጥ አሁንም እየጠበቅንህ ነው :)
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ድንቢጤ » Sun Aug 17, 2008 12:47 am

ወንድም ዋንሽ አሁንስ በጣም ትእግስታችንን እያስጨረስከን ነ :roll:
ድንቢጤ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 67
Joined: Thu Feb 02, 2006 9:52 am

Postby ዋናው » Sun Aug 17, 2008 2:18 am

ድንቢጥዬ እንዲሁም አኑ ሠኞ እመለሣለሁ ሠሞናቱን በዛ ትያትር ምክንያት ትንሽ እየተራወጥኩኝ ስለሆነ ነው::

ከግድንግድ ይቅርታ ጋር
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Mon Aug 18, 2008 11:52 pm


.
.
.
ጥላ-ዓልባ ለረጅም ጊዜ ቆሞ ከነበረበት የተቀነጨበ


''በቃሀ ያለምንም ክፍተት ካንተ ጋር አንድ መሆንን ፈልጌ ...''

''ያንን እኔ ሳልፈልገው የቀረው ይመስልሻል ....?''

''እኔ ግን መናገር ምችለው የራሴን ፊሊንግ ብቻ ነው ዘኪ ያንተን ስሜት ማዳመጥ ብችልም በርግጠኝነት ይሄ ነው ብዬ መንገሩ ያስቸግረኛል ::

''እኔ ግን የሁልጊዜም ፀሎቴ አንቺ የኔ ሆነሽ እንድትኖሪ ብቻ ነው ''

ድጋሚ ተቃቀፉ ከዛም ተንገዳግደው ወደአልጋው ተደፉ :: በናፍቆት በመዋደድ ላብ ተጠመቁ በስሜት ተናነቁ ...

''ምን እያሰብሽ ነው ?''
አላት ዘኪ በስልኩ ውስጥ ዝምታዋ ሲረዝምበት

''ስለትላንቱ ....''

''ትላንት ምን ...?''

''ትላንትና ...........?
ዮሐንስ የእሕቱን ፊት አስተዋለና ሲጋራዉን ይዞ ወደ ውጪ ወጣላት ::
''ዘኪ ትላንትና ባይነጋ ብዬ ተመኝቼ ነበር ....''

''እሱ የኔም ምኞት ነበር .... አይ ዊሽ ከ አሁን በኌላ ግን ምንም ሚያራርቀን ሚያቃርነን ነገር ባይኖር ሠቢዬ ''

''አንድ ነገር አስቢያለሁ ....''
አለች ሠባዊት ዓይኖቿ እየተስለመለሙ

''ምን ?''

''ስትመጣ ነው ምናወራው ....''

''እሺ ምን ይዤ ልምጣ ?''

''አንተ አመዳም እሕትህን 'ኮ ሁለት ቀን ሙሉ አላየዋትም ዛሬ አንተ ቤት መሄድ እንዳለብኝ አትርሳ ቅድም ደውላ ስትሞጣመጥብኝ ነበር ምን ዓይነት ሚጥሚጣ ዘሮች እንደሆናቹ ...''
ዘካሪያስ እየሳቀ

''እንዲህ ነን ብናቃጥልም ጣፍጠን ብዙ ነገር እናጣፍጣለን''
.
.
.
''መቼም እሷስ እዛ ትሰለቺኚያለሽ ብለሽ ነው አይደል? እንዲህ ጣል ጣል ያደረግሽኝ እኔው ነኝ ሞኟ እዛው አዲሳባ ሆነን አብረን እንሂድ እኔ አስዞርሻለው ስትዪኝ መስማቴ...''

አለች ሮማን ሠባዊት ገና ገብታ ለሰላምታ ጉንጯን ስትስማት

''ባል እንኳንስ ጓደኛን አገርን እና ወላጅ እናትንም ያስረሳል ይባል የለ....''
አለ ዳኒ ቀበል አድርጎ የሚነካካዉን የቲቪ ሪሞት ጠረጴዛው ላይ ወርወር አድርጎ በሶፋው ትራስ እየተጫወተ:: በመስኮቱ የገባው የፀሐይ ጨረር ቤቱን ወገግ አድርጎታል::

''ባልና ሚስት ተቀባበላችሁብኝ ነው ሚባለው''
አለች ሠባዊት ተንፈስ ብላ ሙቀቱ ልብሷን አራቁቶ ሠውነቷ ሚያሳይ ስስ ነገር ብቻ ነው ከላይ ጣል ያደረገችው::

''...ይልቅ እንዴት ነሽ? ''

''እኔ ምን እሆነናለሁ ብለሽ ለሀኒሙን ለንደን መጥቼ ፕሮግራሜን አንቺ ቀምተሸኝ ቁጭ አልሽ'ንጂ''

''እንዴት?'''

''ይሄው ያንቺን አኒሙን ቁጭ ብዬ እያየው አይደል''

''ሆ'ሆይ አሁንም እኔ ላይ ነሽ?''
አለቻት ሠባዊት በግምባሯ እያየቻት:

''...ዛሬ ዘኪ የልጅ አለማየሁ ቴውድሮስን መቃብር አስጎበኛችዋለሁ ብሎን ነበር የሱ ነገር ካልረሳው...?''
አለች ሮማን የእጅ ሠዓቷን ገልመጥ አድርጋ

''ከ15 ደቂቃ በኌላ እደርሳለሁ ብሎኛል ለምን ታዲያ ለባብሰሽ አትጠብቂዉም....?''

''አንቺስ አትዬጅም እንዴ?''

''እኔ'ንኳን እስክትመለሱ ቆንጆ እራት አዘጋጅቼ ብጠብቃቹ ይሻላል ሮሚ::''
ሮማን ቆጣ ኮስተር ብላ
''እንግዲያውስ እኔም አልሄድም''
አለች ወደባሏም እያየች::

''እሺ በቃ እሄዳለሁ ተነሽ እንለባብስ''
ሁለቱ እየተጨቃጨቁ ወደመኝታ ቤት ገብተው ትንሽ እንደቆዩ ዘካሪያስ ደረሰ:: የሙቀቱን እና የድካሙን ስሜት ፊቱን በመቋጠር ከገለጸ በኋላ የመኪናዉን ቁልፍ ጠረጴዛ ላይ ከወረወረ በኌላ
''ይሄ ከኢስት አፍሪካ ሠሞኑን የመጡት እንግዶች ይዘው ያመጡት ሙቀት መሆን አለበት እንጂ ...ለንደንን በዚህ ዌዘር አላውቃትም::''
አለ ድምፁን ከፍ አድርጎ;ዳኒን በዓይኑ ጠቀስ አደረገና ጨበጠው::

''አግኝተህ ነው ደመና ውጦኛል ብለህ ስታላዝን ከርመህ....''
አለች ሮማን ከመኝታቤቱስጥ ሆና ድምጿን ከፍ እያደረግች:: ወደ ውስጥ ዘልቆ ለመድረሱ ሠባዊትን ተሳለመና
''ያ ወፈፌ አልመጣም?''
አለ: ወደ ዳኒ እያየ

''ማን?''

''ፒካሶ....''

''አልመጣም''

''ከ20 ደቂቃ በፊት እንደሚደርስ ነግሮኝ ነበር እሱ ልጅ በቃ ቀጠሮዉን በጅምር እንደሚተዋቸው ስዕሎች እያደረገ አስቸግሮኛል አሁንማ ሴሌብሬቲ ሆኗል....''
አለና ስልኩን አነሳ ሊደውል ሲል የአዜብን የቴክስት መልዕክት ተመለከተው

''እንዳንጎዳዳ......... መለያየት ካለብን እንኳን በዚህ መልኩ መሆን የለበትም'' ይላል:: ዘካሪያስ ስሜቱን ዳኒ እንዳያነብበት እየሞከረ ወደ አንተነህ መደወል ጀመረ::

ይቀጥላል
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Tue Aug 26, 2008 10:14 pm

.
.
.

''እንዴት ነበር በቀደም ማታ ጆኒ?''
አለው አንተነህ የዮሐንስን ስሜት በሚያጭሰው የሲግራው ጪስ መሀል እየፈለገ

'' 'ምትገርም ፍጡር ናት አንቱሽ...''

''እንዴት?''

''ሚያስፈልጋትን ሁሉ የማድረግ ግዴታ እንዳለባት ራሷን ያሳመነች እንስት....''
አለ ዮሐንስ ፈገግ እያለ: ድንገት የካትሪን የአልጋ ላይ ግልቢያ ሲታወሠው የገዛ ጓደኛዉን እንደማፈር አለና
''ስታስበው ግን ላለን አጭር ዕድሜ ራሳችንን እንደሷ ምናስደስትበትን ነገር መፈለግ ያለብን አይመስልህም አንቱሽ?''

''ስለስጋህ ስታስብ የነፍስህን ማረፊያ ደግሞ ማሰብ አለብሃ... በእርግጥ እንደእኔ ዓይነቱ ከፈጣሪው የራቀ ሠው ይሄንን ባያስብም ግን አንድ ምትፈራው ኃይል ይከለክልሀል ጆኒ አስተዳደጋችንም ሊሆን ይችላል ''

''አምላክ በአምሳሉ ፈጥሮን ሠው መሆናችንን አክብረን ራሳችንን መንከባከቡን ማይፈልገው ይመስልሀል?''

''ይሄንን መመለስ ሚከብደኝ ይመስለኛል ጆኒ.... አንተ ምሳሌ ብለህ የጀመርካትን ካትሪን ዓይነት ስጋዊና ስሜታዊ ፍላጎትን ማርካትና ፈጣሪ ሚፈቅድልንን ሠው የመሆናችን ክብር ሚለያይ ይመስለኛል:''

''በል አታስፈራራኝ ካትሪን ሚጋልባት ጋላቢ ጉልበትን ስትሻ እኔ ውስጥ ያስገኘላት ሴይጣን ይሁን ፈጣሪ ማጣራበት ድፍረቱ የለኝም ሠው ሆኜ ተሸንፌያለሁና ያቺን ቀን ስጋዬን አንሳፍፌባታለሁ::''
አለ ዮሐንስ እየሳቀ ድፍርስ ዓይኖቹን በሁለት የሌባ ጣቶቹ ጀርባ እያበሰ::
ካምደን ገና ከረፋዱ ግርግሩ ነግሷል: የበጋው ወቅት ሕዝቡን ሁሉ ጨርቅ አስጥሎ ግልፅልፅ ኮረዶች ባታቸዉን እንደ ፀሐይዋ እያበሩ በፎቅ ጫማቸው ላይ ተንጠላጥለዋሉ: ከናፍርት... ቅንድብና አፍንጫቸው ላይ ያንቆጠቆጡት የብር ጌጣጌጥ ለግርግሩ መድመቅ አስተዋፅዖ አድርጓል:: ውሻ እንዳየች የድመት ፀጉር ሽቅብ የቆመ የወንዶቹ ፀጉር እዛም እዚም ይታያል:: አንተነህ ሠፈሩስጥ ሚያውቃቸዉን እና ድሮ ከሡሱ ሳይላቀቅ ያቺን ቅጠል አብረው ሚጠቀልሉትን ካምደኖች በዓይኑ ሠላም እያለ ሚቀርበዉንም በአግሬው ቋንቋ እየተሳለመ ወንዙ ጫፍ ካለው መቀመጫ ወንበር መደገፊያ ላይ ቁጢጥ ብሎ እግሩን መቀመጫው ላይ አነባብሯል: ዮሐንስ ወንበሩ ላይ ደልደል ብሎ ተቀምጧል::

''ዛሬ በጠዋት የቀጠርከኝ ስለካትሪን ወሲብ ልታወራኝ ነው እንዴ?''
አለ ዮሐንስ የሞባይሉን ሠዓት እያየ ቀኑ ግማሽ ሊሆን ደቂቃዎች ቀርተዉታል::

''እስቲ ንገረኝ በናትህ.... አልጋ ላይ እንዴት ናት?''

''ምን ልንገርህ ልትስለው ነው? ቅቅቅቅ''

''ሚታይን ነገር ከመሣል ማይታይን ነገር መሳል እንደምወድ ታውቃለህ አይደል?''
አለ አንተንህ ቀበል አድርጎ
''...ይልቅ አታረሳሳኝ እንዴት ናት?''

''ቦ! ቦ! ቦ!ቦ! ፈረስ ናት አንቱሽ በጠዋቱ ከስቼ ነው የተለያየነው''
ዮሐንስ ዓይኑኖቹን ሠብሮ በራሱ አባባል ሳቀ::

''ታስታውቃለች''

''መቼም በኔና ባንተ ይቅር ብለህ እንደምታስምለኝ ተስፋ አለኝ..... አንተ ሳትሞክራት ቀርተህ ነው አሁን?''

''ኖ!''
አለ አንተነህ ድምፁን ከፍ አድርጎ:

''ሌባ....?''

''ጆኒ ... እኔ አንድ ሠው ከወደድኩኝ ለ ስሜት ብዬ እንደማልቀብጥ ድሮም ታውቀኛለህ::''
ዮሐንስ ፈገግ አለና
''ያው ብዙ ጊዜ አብራቹ ስለምትጠጡ አትምርህም ብዬ ነዋ''

''ኤልሢን እንደምወዳት ስለምታውቅ በዚህ መልኩ አትደፍረኝም በተረፈ በጣም በግልፅ እንቀራረባለን''

አንተነህ ሠሞኑን ሚጠራባቸው ትላልቅ ቢሮዎች ሳቢያ አለባብሱን በመጠኑ ቀየር አድርጓል: ቢያንስ ቀለም የነካው ልብስ ላለመልበስ መጠንቀቅ ጀምሯል:: በዚህም ላይ ከቤቱ ሲወጣ ኤልሣቤት ይሄን ቀይር ይሄንን ልበስ እያለች በመጠኑ ትጨቀጭቀዋለች: ሠላማዊ ጉትጎታ.....

ከጥቂት ዝምታዎች በኌላ አንተነህ
''ለኤግዚብሽናችን መዝጊያ ከባድ ኦፕረሽን አለብን: እስከዛው ብዙ ታክቲኮችን ማሰብ አለብን ያሰብኳቸዉን አንዳንድ ሃሳቦች እስቲ ላማክርህ ብዬ ነው በጠዋቱ የጠራዉህ ዛሬ ከሠዓት የአዲሳባዎቹን እንግዶች የልጅ አለማየሁን መቃብር ለማስጎብኘት ቀጠሮ ይዘናል: ካትሪን 8 ሠው ሚይዝ መኪና ትልክልናለች::''
አለ የንግግሩን ዜማ ወደ ቁምነገር እየቀየረ: ዮሐንስ በዝምታ ሲሰማው አንተነህ ፈገግ አለና
''መቼም ጆኒም አለ ስላት ነው መኪና ያዘዘችልኝ''
አለው::


ይቀጥላል
.
.
.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby early_bird ! » Mon Sep 15, 2008 3:58 pm

:roll: :roll: :roll: :roll:
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby ዋናው » Tue Sep 16, 2008 2:17 am

.
.
.

ዘካሪያስ የዛሬን ቅዳሜ ሲያስባት ሠንብቶ ነበር የእጁን ጣት ተንጠራርታ ይዛ በጨቅላ እግሮቿ ድክ ድክ ማለት የጀመርችዉን ማክዳን ይዞ ሽር ሽር ሚልበት ቀን ነው:: ከጠዋቱ 10:00 ሠዓት ሲል መኪናዉን ይዞ ወደ ቫኔሣ ቤት መንገዱን አቀና መኪና ውስጥ ከፊለፊቱ ያንጠለጠለው የልጁ ፎቶግራፍ ከመኪናው ንቅናቄ ጋር እየተንዠወዠወ ይታየዋል: ልክ መኖር እንደሚያጓጓ ስሜት አየውህ አላየውህ .... ገዝቶ ያዘጋጀላትን ስጦታ ይዞ የበሩን መጥሪያ አንቃጨለ:: የቀኑ ፀሐይ ከንፋስ ጋር ልፊያ የያዘች ይመስላል እሷም እንደንፋሱ ቅዥቅዥ ትላለች አንዴ እየገባች አንዴ ብልጭ እያለች
''ልጅህን ለመውሰድ ስትመጣማ ሚቅድምህ የለም....''
አለችው ቫኔሣ ለሠላምታ አንድ ጉንጯን ተንጠራርታ እያቀበለችው የእግሮቿ ጣቶች መሀል የተሰነቀሩት ነጭ ጥጦች አኪያሄዷን ቀይሮታል ጥፍሮቿን እያቀለመች ነበር:

''እዚህ ቤት መምጣት ሲኖርብኝ ያረፈድኩበት ጊዜ ትዝ አይለኝም ቫኒ...''
አላት

''ስቀልድ ነው''
አለችው ዞራ ፈገግ እያለች የፀጉሯ ለቀኑ መዘጋጀትና አኩዋኗ ቤት የመዋል ዕቅዱ እንደሌላት ታስታውቃለች

''አንቺም ለመውጣት የተጣደፍሽ ይመስላል ቫኒ....?''

''ልክ ነህ ዘካር በጋው ካማኪጋር ቤት ስላፋ ሊያልፍብኝ ሆነ...''

ይሄኔ ማክዳ እየሮጠች መጥታ አባቷን ሽቅብ ማየት ጀመረች: ዘካሪያስ ዘውትር ምታመጣው እድገት ሁሌም እንዳዲስ ይገርመዋል:: ሲያቅፋት እጆቿን ባንገቱ ዙሪያ አኑራ አፍጥጣ ታየዋለች ደጋግሞ ሲስማት ቀና ብላ በፈገግታ ታየውና እናቷን ትመለከታለች

''ምነው ማኪ... ዳዲ አትዪውም እንዴ? ዳዲ በይ ዳዲ...!''
ማክዳ ቀበል አድርጋ
''ዳዲ...''
አለች ጣቶቿን እየቀሰረች ዘካሪያስ ደጋግሞ ሳማትና ያመጣላትን ስጦታ ሠጣት ለደቂቃዎች ከተበረከተላት መጫወቺያ ጋር ሆና አባቷንም እናቷንም እረሳች::

''ቫኒ...?''
አላት ዘካሪያስ ከመስታወቱ ጋር የተፋጠጠ ፊቷን በመስታወቱ እየፈለገ

''... እኔማ ምሳ በልተን እንለያያለን ብዬ ነበር''

''ይሄንን ፕሮግራም አልነገርከኝም ዘካር የማውቀው ማኪን ይዘሀት ሄድ ከሷ ጋር ብቻ እንደምትዉል ነው''
አለችው እሷም በመስታወቱ ውስጥ እያየችው

''አዎ....ግን?''

''ዘካር እንኳን አሁን ተራርቀን ድሮም ያለፕሮግራም ምሳም ሆነ እራት ተገባብዘን አናውቅም''
አለች ቫኔሣ

''ልክ ነሽ ምትችዪ ከሆነ ነው እንጂ...''

''ይቅርታ ዛሬ የራሴ ፕሮግራም አለኝ ለምሳ ግብዣው ግን አመሰግናለው በእኔ ፋንታ ማኪን ጋብዝልኝ''
አለችዉና ዓይኖቹን ቀስ ብላ ተመለከተች:

''ዘካር....''

''አቤት''
አላት ቀረብ ብሎ ወደ ጀርባዋ እጁን እየሰደደ

''ጠንካራ ሠው ነህ?''

''እንዴት ቫኒ?''
ዞረችና መኳኳሏን ገታ አድርጋ
''... እኔ ምናልባት ያንተን ያህል ጠንካራ ላልሆን እችላለው ወይም ውስጥህን ስለምትደብቀኝ እኔ ካንተ የተሻልኩኝ ጠንካራ ልሆን እችላለው ካንተ ጋር ምሳ ወይም እራት የመብላቱና የመቀራረቡ ስሜት ውስጤ ሲኖር ልቤ ሌላ ሊያስብ ይችላል... እኔና አንተ ደግሞ በዚህ መልኩ ምንተሳሰብ ሰዎች መሆናችን ከቀረ ቆየ አንድ ነገር ብቻ ነው ሚያቀራርበን.... እሷም ማኪ ናት:''
ትንሽ ተንፈስ አለና
'' ማኪ..... እዚች ምድር ላይ ሠዉን ያቀራርባሉ ተብለው ከተከሰቱት ነገር በላይ ታቀራርባለች::''
አላት:: ዘካሪያስ ቫኔሣን ቀረብ ብሎ ሲመለከታት ዓይኖቿ ስር የድካም ወይም የሕመም ስሜት አስተዋለ

''ቫኒ ምነው? ሠሞኑን አሞሽ ነበር?''

''አዎ ትንሽ አመም አድርጎኝ ነበር''
አለች የሚሸሹ የዘካሪያስ ዓይኖችን በዓይኖቿ እየተከተለች

''ለምን አልነገርሽኝም?''
አላት በጨዋታ ወደ ተጠመደችው ልጁ እያመራ: አልመለሰችለትም ቫኔሣ...

''...ሠው እንደሚያስፈልግሽ አውቃለሁ''
ቫኔሣ አቀርቅራ ስሜቷን ለመደበቅ ሞከርችና ድንገት ክፍት ብላ ሢጋራዋን ከልብስ ሣጥኑ አናት ላይ ይዛ ወደ ውጪ ፈጥና ወጣች::
በአዲሱ መጫወቻ ጥግብ ያለችው ማክዳ ድክ ድክ እያለች ወደ አባቷ አመራችና እጇን ዘረጋጅለት: እናቷን ተከትላ ውጪ መውጣት እንደፈለገች ገባው::

ዘካሪያስ ከቫኔሣ ተለይቶ ማክዳን ከ1 ቀን ጓዟ ጋር ይዞ በመኪናው ሲሄድ የቴዲ አፍሮን ዘፈን እየሰማ ነበር: ሆዱ ይረበሽ ጀመር በመኪናው መቀመጫ ቀበቶ ታስራ አንገቷን በጫወታ ወደምትወዘውዘው ማክዳ ይመለክታል እሷን ይዞ ወደ አገሩ እንዳይገባ እሷ የእንግሊዝም ናት ትቷት አይገባ የአጥንቱ ፍላጭ ናት....
''ኸረ እንዴት...? ኸረ እንዴት....''
እያለ ሲያዜም ከያኒው እንደተቃኘው ውስጡ እያነባ በጣቱ ሲያጨበጭብ ማክዳ እየሳቀች ትንንሽ መዳፎቿን ትጠፈጥፍለታለች የፈጠጡ የፊት ጥርሶቿ ሳቅ ስትጨምርባቸው ልቡ የሸፈተ የአባቷን ስሜት ወደደስታ ትቀይረዋለች::''

.
.
.
ይቀጥላልLast edited by ዋናው on Mon Sep 22, 2008 1:24 am, edited 2 times in total.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Thu Sep 18, 2008 3:14 am

ሮማን ማምሻዉን እጇ የገባችዉን ማክዳን ስታጫውት አመሸች ''ዳዲ'' የሚል ሚጣፍጥ ድምጿን ስትሰማ ደጋግማ እየሳመቻት እናቷን አስታወሰች ባለፈው ለናቷ ይህንን የምስራች ልትናገር ስትል ዘካሪያስ ከልክሏት ነበር አሁን ግን ደውላ መናገር ፈለገች ደግሞ የሠባዊትን እና የወንድሟ ዘካሪያስን ግንኙነት እናቷ መስማታቸዉን ስታስብ በዘካሪያስ ታዝንበት ይሆን? ብላ ታስብና ታመነታለች: ከነጭ መውለዱን ምን ዓይነት ስሜት እንደሚፈጥርባቸዉም እያሰላች ግራ ይገባታል... ግን ዜናዉን መናገር ፈልጋለች እናቷ ሃያት የመሆናቸውን ብስራት በርሷ አፍ መነገሩን በጣም ፈልጋለች:: ይሄን ሃሣቧን ሚያውቁት ባሏ ዳኒ እና ሠባዊት የማክዳን ፎቶ ወስዳ እዛው አዲሳባ ስትሄድ ስለሁሉ ነገር አስረድታ ብታበስር መልካም እንደሆነ ነግረዋታል::
የስልክ መደወያ ካርዷን በሣንቲም ፈቅፍቃ ቁጥሮቹን አስገብታ ከሰኮንዶች በኌላ
''ሀሎ እማዬ...''
አለች ማክዳ ሮማን እቅፍ ውስጥ እንዳለች በራሷ ዓለም ውስጥ ሆና በራሷ ቋንቋ ታወራለች.... ትጮኻለች ትስቃለች....

''የማንን ድምፅ ምትሰሚ ይመስልሻል?''
የናትዬውን መልስ እየሰማች ወደ ማክዳ ዞራ ትስማታለች ዘካሪያስ ሠባዊትና ዳኒ ሣሎን ሆነው የሞቀ ጨዋታ ይዘዋሉ ከፊታቸው ያለው ጠረጴዛ ባዶና ግማሽ የሆኑ አረንጓዴ የቢራ ጠርሙሶች በዝተዋል

''እንኳን ደስ አለሽ ዘኪ ሤት ልጅ ወልዶዋል''
እናትዬው እልልታቸዉን ሲያቀልጡት ሮማን በምታወራበት ስልክ ውስጥ ይሠማል እሷም በስሜት ጮክ ብላ ስታወራ ዘካሪያስ ፈጥኖ ደረሰ

''ከማን ጋር ነው...?''
አላት እጇን የዘረጋችለትን ማክዳን በፈገግታ እያቀፋት

''ቆይ አናግሪው...''
አለችና ስልኩን ለዘካሪያስ ሰጥታ ማክዳን ይዛ ከመኝታቤቱ ወጣች::የዓይኖቿን መንቀዥቀዥ ያስተዋሉ ዳኒ እና ሠባዊት አንድ ነገር እንዳረገች ገባቸው ሁለቱም በፊታቸው ገፅ ጠየቋት

''አፈረጥኩት''
አለች ማክዳን ወለሉ ላይ አኑራት

''ምኑን?''
አለች ሠባዊት
''ለማዘር ነገርሻቸው አይደል?''
አላት ዳኒ ገብቶት በመቸኮሏ ለሁለት ተቀባብለው ሲወቅሷት ዘካሪያስ እንደተናደደ ገባ: ፊቱ ላይ ግራ የተጋባ ስሜት ይነበብበታል

''አታድርጊ ያልኩሽን ነገር ሁሉ እያደረግሽ ይሄው ከልጅነትሽ ጀምሮ እስካሁን አለሽ.... ለምን ሮሜ?''

''መናገር ስላለብኝ''

''እኔ ደግሞ መንገር ስላልፈለግኩኝ ነበር እስካሁን የቆየዉት''
አላት ዘካሪያስ በንዴት እያያት

''ካንተ መናገር ያለመፈለግ ምክንያት የእኔ ምክንያት ይበልጣል ዘኪ''
አለች ሮማን ፊቷን ቅርዝዝ አድርጋ ማክዳ እየሮጠች ቢራዎች ወደተሸከመው ጠርጴዛ ስትሄድ ሠባዊት አቀፈቻት እሷ ግን ጠርሙሶችን ካልነካው ብላ ከእቅፏ ውስጥ ትፈራገጣለች

''ዘኪ የወሰንኩት ማታ አገርህ አሁን መግባት እንደማትፈልግ ስትነግረኝ ነው እማዬ ከመቼዉም በላይ ዓይኖችህን ማየት ትፈልጋለች እንግዲያውስ ንገረኝ ካልከኝ ልንገርህ... ጤንነቷ አሳሳቢ ድረጃ ላይ እየሆነ ነው
''አንድ ነገር ሳልሆን የልጄን ዓይን ልይ'' እያለች ማልቀስ ከጀመረች ቆይታለች::''
ዘካሪያስ ሚሠማው ሁሉ ቅዠት እንደሆነበት አንገቱን እየነቀነቀ ዓይኖቹን አፍጥጧል

''እናም ዓይኖችህን ማየት ባትታደል የምስራችህን እንኳን ትስማ ብዬ ደውልኩላት.... ካንተ ጋር እመለሳለሁ ብዬ ባዶ እጄን ስገባ ሃዘኗን ማየት ስለከበደኝ ቢያንስ በዚህ ዜና ፈገግታዋን ፈለኩት.... አሁንስ ገባህ?''
አለችው ሮማን ፊቷ በእንባ ርሷል ጉንጮቿ ፈመዋሉ: ሠባዊትም የዓይኖቿን ሽፋሽፍት ያረጠበዉን ትኵስ የንባ ዘለላዎች በሌባ ጣቷ ጀርባ ትቀበላለች::
ዘካሪያስ ግራ ተጋባ ልጁ ስሩ ሆና እንደልማዷ እጇን ዘረጋችለት
.
.
.
ይቀጥላል
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests