ጥላ ዓልባ__________(ልብ ወለድ)

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዋናው » Tue Dec 09, 2008 3:03 am

በመደናበር የተደገመ
Last edited by ዋናው on Tue Dec 09, 2008 3:09 am, edited 1 time in total.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Tue Dec 09, 2008 3:05 am

.
.
.
አንተነህ ዮሐንስ ይዞ የመጣዉን መጠጥ ተቀበለና ተጎንጭቶለት ወደ ካትሪን መጠጥ እያየ
''ያንቺ መጠጥ ዛሬ ቀለሙ ደስ ይላል...''

''አዎ ዛሬ ትንሽ ብርዱ ውስጤ ሲገባ ይሞቀኝ ይሆን አልኩና ትንሽ ጠጠር ያለ ነገር አዘዝኩኝ ...ኮክቴል ነው ግን ያው ካምፓሪ ስላለበት ነው የቀላው''
አለች መለኪያዋን አንስታ እየተጎነጨች

''አሁን ሞቅ አደረገሽ?''
አላት ዮሐንስ ፈገግ ብሎ በትላልቅ ዓይኖቹ ዓይኖቿን እያየ
''አዎ... ''
አለች ፈጥና የዮሐንስ ድምፅ አንዳች ነገር እንዳስታወሳት ሁሉ ዓይኖቿን ጨፍና በቀስታ ፈገግ አለች: አንተነህ ፈገግታዋን ተከትሎ ትኩር ብሎ ሲያያት ለየት ያለ ስሜት አነበበባት ... ያ ዘና የሚልና ልበሙሉነቷ ዛሬ ያለም ብቻ አንድ የተለየ እንግዳ ስሜት ይነበብባታል::

''መጀመሪያ ስንተዋወቅ ያዋራናቸዉን ቃላት ታስታውሻቺዋለሽ ካትሪን?''

''አዎ... ሠዓሊ ነህ ወይ? ስልህ አይደለሁም ትምሕርቴን ስጨርስ ግን ሠዓሊ ሚለዉን ስም እይዛለው... መሰለኝ ያልከኝ ... ምነው ጠየቅከኝ?''

''ጥሩ አስታዋሽ ነሽ... አሁን ሠዓሊ ሚባለዉን ስም ለመያዝ እየታደልኩኝ ነው... ነገ ብዙ ሕልሞች ይታዩኛል ውስጤ ነግቶ በመሸ ቁጥር አዳዲስ ሥዕሎች ይወለዳሉ ለመኖር እንዴት እየጓጓው እንደሆነ አትጠይቂኝ ካትሪን... ሠሞኑን በጠዋት እየተነሳው ስዘፍን ጎረቤት ሁሉ ጉድ እያለ ነው...''
ዮሐንስም በአንተንህ ንግግር እየሳቀ ካትሪንን እያያት

'' 'እብደትና ጥበብ ማይነጣጠሉ ኮርሶች ናቸው'.... ያለው ማን ነበር ካትሪን?''
አለ::

''እኔንጃ...?''
አለች እየሳቀች
''...በነገራችን ላይ አንትነ... ከመኖር የዚህን ያህል ፍቅር እየያዘህ ለዛ ነገር እንዴት ቃልህን ሠጠህኝ?''

''መች አስፈቅደሽ አስጀመርሽኝ?''
አላት አንተነህ እየፈጠነ:
''ግን'ኮ እንደኔም ለመኖር ሚስገበገብ ያለ አይመስለኝም አንድ ነገር አስቤ ያልተሳካልኝ ጊዜ የለም ማለት ይቻላል ስለዚህ እዚች ምድር ላይ የፈለግኩትን የማግኘት ነፃነት እንዳለኝ በድንብ ስለገባኝና ስለምጠቀምበት ....''
መጠጧን ተጎንጭታ በስሜቷ ንግግሯን ጨረሰችው::
ሦስቱም ከያዙት መጠጥ ጋር ብቻ ተፋጠው መሀላቸው ፀጥታ ሆነ:: ፐቡ ውስጥ የሊዊስ ሀርምስትሮንግ ዋት ኤ ወንደርፉል ወርልድ የሚል ዜማ በቅስታ ያዜማል::

''ልክ በ23:30 ላይ ዶክተር ኤድዋርድ ይመጣል እስከዛ ድረስ ቤት መቀየር ምትፈልጉም ከሆነ ሌላ ቦታ መሄድ እንችላለን ''
አለች ካትሪን ሠዓቷን አይታ ገና መሆኑን አውቃ

''እኔ ቤቱን ወድጄዋለሁ ...ብዙ ሠዐት ስለሆነ ያለን እዚሁ እንቆይና የቤቱን ሙድ አይተን ብንቀይር አይሻልም?''
አለ ዮሐንስ

''ምናወራቸው ነገሮች ካሉ ለማውራት እዚህ ሚያመች ይመስለኛል''
አለ አንተንህም:: ይሄን ጊዜ ካትሪን ከመቀመጫዋ ተነስታ መጠጥ ልትደግም ስትል እነሱንም ጠየቀቻቸው
''ምንድነው የያዛችሁት?''
.
.
.
ይቀጥላል
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby Debzi » Sat Jan 03, 2009 2:35 am

ኧረ ዋናው!

አመቱ ሳያልቅ ጨርሰዋለሁ በለህኮ ነበር...........
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby ጣዝማዊት » Sat Jan 24, 2009 11:20 pm

:roll:
:roll:
ጣዝማዊት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 92
Joined: Sun Mar 07, 2004 6:51 pm

Postby Debzi » Tue Jan 27, 2009 4:59 pm

አይ ያንተ ነገር!! ምነው ዋናው ይህን ታሪክ አንጠልጥለኸው ተውከው? እኔማ እስካሁን መጀመርህ አይቀርም ብዬ ዘው ስል ጉድ ሰራሀኝ::
ለሁለተኛ ጊዜ ዋርካ ላይ የሚጀመር ታሪክ ላለማንበብ ቃል አስገባሀኝ::

Thank you!!
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby ማህቡብ » Tue Jan 27, 2009 5:05 pm

የተከበርክ ዋናው እኔም በመጠበቅ ላይ ነኝ
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby early_bird ! » Wed Jan 28, 2009 8:19 pm

ዋናው ጥላውን ትቶልን ሄደ ማለት ነው ? የጥላ ምስል እኮ ይከብዳል ..... :roll: ሰላም ሁን ለሁሉም !
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby ዋናው » Thu Jan 29, 2009 5:14 am

Debzi wrote:ኧረ ዋናው!

አመቱ ሳያልቅ ጨርሰዋለሁ በለህኮ ነበር...........


ደብዚቾ ሠላም የዋርካዋ አድባር.. ምን ይደረግ ብለሽ ነው ዋርካ ቃልሽን እንድትጠብቂ ሚጋብዝ ነገር ጠፋባት...
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዋናው » Thu Jan 29, 2009 5:19 am

early_bird ! wrote:ዋናው ጥላውን ትቶልን ሄደ ማለት ነው ? የጥላ ምስል እኮ ይከብዳል ..... :roll: ሰላም ሁን ለሁሉም !

በርድ :lol: :lol: መጥቼ ይሄንን ጥላ አነሳልሻለው ቆይ ሠላም ነሽ ዛሬ በስንት ጊዜዬ ዋርካ ብቅ አልኩ? ጥላ-ዓልባዬ ጠውልጋ ጓሮ ትጠብቀኛለች ብዬ ነበር አስታዋሽ አያሳጣኝ ይል ነበር ዳሞት በግ እረድልን ብለው ጎረቤቶች ሲጠሩት...
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ifa » Thu Jan 29, 2009 5:51 am

ተመስገን አልኩ ቤትህ ሞቅ ብሎ ሳየው...ስንቱ ይሆን ሽምብራ እየቕረጠመ ሱባኤ የገባው? ለሁሉም እንኩዋን ብቅ አልክ ..መኖርህ ለዋርካ ተስፋ ነው..በቀደም አንዱዋን ወዳጀ ወደ ዋርካ ጎራ እንበል ብላት "ምን ቀረኝና ..ዋናው እንደው አይመጣ " ብትለኝ አይ ዋንች እንደው ስንቱን እንዳባረርከው አውቅህ ይሆን? አልኩ ምን ይደረግ ..የስንቱ ጋጠ ወጥ ለጆሮ የሚሰቅጥጥ ጽሁፍ ሰውን ሳያስጠፋ ያንተ መጥፋት ዋርካን እዬዬ እያሰኘ ነውና..እንደው ባይመችም አቴንዳንስ ሺት ላይ እየፈረመህ ውጣ ..ቢያንስ ሰዎች ደህንነትህን አውቐው በተስፋ እንዲጠብቁ...

ከአድናቂዎች ህ አንዱዋ
Ethiopians are: " THE BLAMELESS RACE "

Homer (Greek poet of the 8th century B.C.)
ifa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 135
Joined: Mon Jul 09, 2007 6:24 am

Postby ረቂቅ 2 » Tue Mar 03, 2009 9:24 am

ሰላም ለሁሉም :)

ብዙ እርቃ ሄዳ ነበር ስቤ አምጥቻታለሁ:: ዋኒቾ ደጎስ ያለ ጽሁፍ ያቀርብልናል ብየ ባስብም አይዋ ግን እዚህ ቤት እንዲመጡ ያልፈለጉት ሰው አለ መሰል ወይ ፍንክች ብለዋል :wink: ዋንሽ ስለግዛቤር መቼ ነው ትረካውን የምትቀጥለው?

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
ረቂቅ 2
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Mon Jan 29, 2007 5:16 pm

Postby ዋናው » Tue Mar 03, 2009 11:27 am

የጎብኚን ዕይታ መቁጠር አዲሱ የዋርካ ስታይል ነው አሉ.... ቅቅቅቅ እኔም'ኮ እቺ ቤት 2መቶ ሺህ እስክትሞላ እየጠበቅኩኝ ነው........ :wink: መቼም የዋናው ሠበብ አበዛዙ....
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ማናስቦት » Tue Mar 03, 2009 2:48 pm

ዋናው wrote:የጎብኚን ዕይታ መቁጠር አዲሱ የዋርካ ስታይል ነው አሉ.... ቅቅቅቅ እኔም'ኮ እቺ ቤት 2መቶ ሺህ እስክትሞላ እየጠበቅኩኝ ነው........ :wink: መቼም የዋናው ሠበብ አበዛዙ....


እሽ ዋንሽ ይሁን
ማናስቦት
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 29
Joined: Mon Apr 23, 2007 1:34 pm

Postby መንኮራኩር » Sun Mar 08, 2009 4:42 am

:( :( :( :( :( :?: :?: :?:
Peace has to be created, in order to be maintained. It is the product of Faith, Strength, Energy, Will, Sympathy, Justice, Imagination, and the triumph of principle. It will never be achieved by passivity and quietism.

Dorothy Thompson:
መንኮራኩር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 637
Joined: Tue Mar 28, 2006 7:05 am

Postby ዋናው » Mon Apr 27, 2009 3:44 am

መጀመሪያ በስማም ብዬ አዋራዋን ልጥረጋት እስቲ...
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2799
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests